"ከዚህ በኋላ በምንም ዓይነት ሁኔታ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በአካባቢ የሚመደብበት ሁኔታ አይኖርም።" ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)
33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ "ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም!" በሚል ጭብት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ተካሒዷል። በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፥ በትምህርት ዘርፍ ላይ ያሉ አመራሮች የትምህርት ሥራን ከፖለቲካ መለየት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
"ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የመላው ኢትዮጵያውያን እንጂ የተቋቋሙበት መንደር አይደሉም" ብለዋል ሚኒስትሩ። "ከዚህ በኋላ በምንም ዓይነት ሁኔታ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በአካባቢ የሚመደብበት ሁኔታ እንደማይኖር" ገልፀዋል።
"የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ምደባ በውድድር እና በብቃት ላይ ብቻ የተመሠረተ እንዲሆን ይሠራል" ብለዋል።
@Ethiopian_Digital_Library

በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት ሥራ ያቆሙ መምህራን በዝውውር በሌሎች አካባቢዎች እንዲሠሩ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መመርያ አስተላለፈ፡፡
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
በፔሩ ሊማ በተካሄደው የአለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 1ኛ ከአለም 2ኛ በመሆን አጠናቃለች:: ኢትዮጵያ 6 ወርቅ 2 ብር እና 2 ነሀስ በድምሩ 10 ሜዳሊያ አግኝታለች::
Peru | Lima 24 | World Athletics U20 Championship
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
Peru | Lima 24 | World Athletics U20 Championship
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
በመንግስት በኩል የሚደረግለት የተማሪዎች ምደባ አለመኖሩን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ 2017 የትምህርት ዘመን አቅምና ብቃትን ብቻ መሰረት ያደረገ የተማሪዎች ቅበላ እንደሚያደርግ አስታውቋል። በትምህርት ዘመኑ ለዩኒቨርሲቲው በመንግስት በኩል የሚደረግለት የተማሪዎች ምደባ አለመኖሩንም ነው ያስታወቀው።
ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎችን በራሱ መመዘኛ ብቻ የሚቀበል ይሆናል ተብሏል። በሀገራዊ ፈተናው 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ማምጣት አንዱ መስፈርት ይሁን እንጂ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አቅምና ብቃትን ብቻ መሰረት ያደረገ ቅበላ ለማድረግ ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና እንደሚሰጥ ነው የዩኒቨርሲቲው ተ/ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ያስታወቁት።
አሰራሩ በመንግስት ወጪ የሚሸፈን የትምህርት እድል (ስኮላርሺፕ) እና በግል ወጪን በመሸፈን የተማሪዎችን ስብጥር በጠበቀ መልኩ ማስተናገድ እንዲቻል ተደርጎ የተቀረፀ ነው። ዩኒቨርሲቲው አፍሪካዊ የሆነ ስመጥር ዩኒቨርሲቲ ለመሆን እየሰራ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም፣ በተለይ ለጎረቤት ሀገራትና በኢትዮጵያ ተጠልለው ለሚገኙ ስደተኞች ቅድሚያ በመስጠትም ተማሪዎችን እንደሚቀበል ተጠባባቂ ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።
ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ከሀገራት ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያግዛል ብለዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ነፃነትን መሬት ላይ በማውረድ፣ ፍትሃዊ እና ብዝኀነትን በማስተናገድ ብቃትና አቅምን መሰረት በማድረግ በየዓመቱ እስከ 5 ሺህ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን ለመቀበል ይሰራል ብለዋል።

Scholarship for Ethiopian Students
Bachelor, Master and Doctoral study programmes
Czech Republic
https://mzv.gov.cz/addisababa/en/development_cooperation_and_humanitarian/scholarships/index.html#:~:text=For%20the%20academic%20year%202021%2F2022%2C%20the%20Czech%20Republic%20will,are%20very%20popular%20among%20students.&text=2)%20in%20follow%2Dup%20Master,programmes%20or%20Doctoral%20study%20programmes.

የቲክቶክ ጊፍት በአሜሪካ የሀበሾችን ትዳር አፈረሰ
ስማቸው ያልተጠቀሰ ሀበሻ ባለትዳሮች ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ሀገር ነው። በጋራ የሚጠቀሙበት የካፒታል ዋን የባንክ አካውንት አላቸው ከሰባት ወር በኋላ ባል ወደ ባንክ በአጋጣሚ ሲሄድ እሱ የማያውቀው 50ሺ ዶላር ወጪ መሆኑን ይመለከታል ይላል ፋስት መረጃ ከታዲያስ አዲስ የሰማው ዘገባ፣ ከዛ የባንኩን ኃላፊዎች ሲያናግር 50ሺ ዶላሩ ለቲክቶክ አፕሊኬሽን ወጪ እንደሆነ ይነገረዋል።
ባል ወደ ቤት በመግባት ባለቤቱን ሲጠይቅ "ስራ ስለሌለኝ ለመደበሪያ ብዬ ነው ቲክቶክ ስጠቀም ለጊፍት ያወጣውት" የሚል ምላሽ ከሚስቱ ያገኛል፣ ባል እሺ በማለት ነገሩን ተቀብሎ ከቆይታ በኋላ 50ሺ ዶላሩ ለአንድ ወንድ ቲክቶከር ብቻ ወጪ እንደሆነ ይደርስበታል።
ጉዳዩ ወደ ፀብ ተቀይሮ በመሃል ሽማግሌ ገብቶ ትዳሩ መቀጠል ሳይችል በፍቺ ተጠናቋል። የጊፍተር ትዳር ተበተነ። #ዳጉ_ጆርናል

መምህራን ሞያቸውን ትተው በግብርና ሥራ መሰማራታቸውን ተናገሩ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ስለማይከፈላቸው አንዳንድ መምህራን የተማሩባቸውና ሲያገለግሉበት የነበረውን ሞያ ትተው በግብርና ሥራ መሰማራታቸውን ተናገሩ:: በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ውስጥ በሚገኙ 21 ወረዳዎች ተቀጥረው በማገልገል ላይ የነበሩ የመንግሥት ሠራተኞች የወር ደሞዛቸው ለረዥም ጊዜ በመቁረጡ ለኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ ችግሮች መጋለጣቸውን አስረድተዋል። #VOA

የስራ እና ተግባር ትምህርቶች ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መሰጠት ሊጀምር ነው
ከቀጣዩ ዓመት የትምህርት ዘመን ጀምሮ ለ11ኛ ክፍል ተማሪዎች፤ የስራ እና ተግባር የሙያ ትምህርቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ መሰጠት ሊጀምር ነው። ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለሚሰጡ ትምህርቶች የሚሆኑ “ሞጁሎች” በቀጣይነት እንደሚዘጋጁም ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እንዲሰጥ የታቀደው የስራ እና ተግባር ትምህርት፤ ከ2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ የጀመረው የትምህርት እና ስልጠና ፖሊሲን መሰረት ያደረገ ነው። ፖሊሲው የስራ እና ተግባር ትምህርቶች፤ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ከእድሜያቸው ጋር በተመጣጠነ መልኩ እንዲሰጡ ማዕቀፎችን አስቀምጧል።
ፖሊሲውን ተንተርሶ የተዘጋጀው ስርዓተ ትምህርት፤ የስራ እና የተግባር ትምህርት ለ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሰጠው አንድ የትምህርት አይነት እንደሆነ አመልክቷል። የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በበኩላቸው፤ ከ40 የሙያ እና ተግባር ትምህርቶች ውስጥ አንዱን መርጠው እንዲማሩ እንደሚደረግ በስርዓተ ትምህርቱ ማዕቀፍ ላይ ተካትቷል።
በ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ለ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሰጡት የስራ እና ተግባር ትምህርቶች ብዛት 12 ብቻ መሆናቸውን በትምህርት ሚኒስቴር የስራ እና ተግባር የስርዓተ ትምህርት ባለሙያ አቶ ግርማ ደምሴ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሰባት የስራ እና የተግባር ትምህርቶችን የሚያማርጡ ሲሆን ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ አምስት ትምህርቶች በተመሳሳይ መልኩ ቀርበውላቸዋል። #ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር

የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የሚሰጥበት ቀን እና ሰዓት
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
መንግሥት ባሻሻለው አዲሱ የኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ መሠረት ከመስከረም ጀምሮ ለአራት ዓመታት በየአራት ወሩ በኤሌክትሪክ ታሪፍ ላይ ጭማሪ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
በሰዓት አራት አምፖል የሚጠቀም ቤተሰብ የሚከፍለው ክፍያ ከ24 ብር ወደ 41 ብር ከፍ ተደርጓል።
በማሻሻያው መሠረት የመኖሪያ ቤት ኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚዎች በአራት ዓመታት ውስጥ ከ256 እስከ 477 በመቶ የሚደርስ የታሪፍ ክፍያ ጭማሪ ይጠብቃቸዋል።
ማሻሻያው፣ የመኖሪያ ቤቶችንና ንግድ ድርጅቶችን እንዲኹም የአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን የፍጆታ ክፍያ የሚመለከት ነው።
ጭማሪው የኑሮ ውድነትን እንዳያባብስ፣ ከዜሮ እስከ 200 ኪሎ ዋት የኃይል ፍጆታ ለሚጠቀሙ ደንበኞች ድጎማ የተደረገ ሲኾን፣ ለአብነትም ከዜሮ እስከ 50 ኪሎ ዋት የሚጠቀሙ ደንበኞች በሚከፍሉት ታሪፍ ላይ 75 በመቶውን መንግሥት እንደሚደጉም ተገልጧል። #wazema

ደመወዝ
ኢትዮጵያውያን ቅጥር ሰራተኞች ግብር የማይከፍሉበት መነሻ ደመወዝ፣ ከስራ ለሚገኝ ገቢ የሚከፍሉት ግብር ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሲወዳደር ምን ይመስላል ? የነፍስ ወከፍ ገቢያችንስ?
✍️ግብር የማይከፈልበት መነሻ ደመወዝ በጣም ዝቅተኛ የሆነባት
✍️በዝቅተኛ ደመወዝ ላይ ከፍተኛ ግብር የሚጣልባት
✍️የግብር ቅንፉ በጣም ጠባብ የሆነባት
✍️ትልቅ ግብር የሚከፈልበት የደመወዝ ጠገግ ዝቅተኛ የሆነባት
✍️እጅግ ከፍተኛ የገቢ ግብር ተመን ያለባት
✍️የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ (GDP/capita/ PPP) ከጎረቤት ሀገራት ዝቅተኛዋ ኢትዮጵያ እንደሆነች ያውቃሉ።
====================
👉ኢትዮጵያ ውስጥ (1 ዶላር በ100 ብር) ተሰልቶ ከ6 ዶላር (600 ብር) በታች የሚከፈለው ሰራተኛ ከግብር ነጻ ነው። ከ109 ዶላር (በብር 10,900) በላይ የሚያገኝ ሰራተኛ ከፍተኛውን ጣራ 35% ግብር ይቀረጣል። የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ (በተመጣጣኝ የመግዛት አቅም) በዶላር 2803 ( በብር 280,300) ።
👉ኡጋንዳ ውስጥ እስከ 63 ዶላር (በብር 6300) የሚከፈለው ሰራተኛ ከግብር ነጻ ነው። ከ2684 ዶላር (በብር 268,400) በላይ የሚያገኝ ሰራተኛ ከፍተኛውን የግብር ጣራ 30% ይቀረጣል። የኡጋንዳ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ (በተመጣጣኝ የመግዛት አቅም) 3098 (በብር 309,800)
👉ኬንያ ውስጥ 186 ዶላር (በብር 18,600) የሚከፈለው ሰራተኛ ከግብር ነጻ ነው። ከ1613 ዶላር (በብር 161,300)በላይ የሚያገኝ ሰራተኛ ከፍተኛውን የግብር ጣራ 32.5 % ይቀረጣል። የኬንያ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ (በተመጣጣኝ የመግዛት አቅም) በዶላር 5700 (በብር 570,000)
👉ታንዛንያ ውስጥ ከ99 ዶላር (በብር 9900) በታች የሚከፈለው ሰራተኛ ከግብር ነጻ ነው። ከ368 ዶላር (በብር 36,800) በላይ የሚያገኝ ሰራተኛ ከፍተኛውን የግብር ጣራ 30% ይቀረጣል። የታንዛንያ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ (በተመጣጣኝ የመግዛት አቅም) በዶላር 3581( በብር 358,100)
👉ግብጽ ውስጥ 828 ዶላር በብር (82,800) ድረስ ደሞዝ የሚከፈለው ሰራተኛ ከግብር ነጻ ነው። 24,752 ዶላር (በብር 2,475,200) በላይ የሚያገኝ ሰራተኛ ከፍተኛውን የግብር ጣራ 27.5% ይቀረጣል። የግብጽ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ (በተመጣጣኝ የመግዛት አቅም) 16,961 (1, 696,100 በብር)
👉ጅቡቲ ውስጥ እስከ 189 ዶላር (በብር 18,900) ድረስ የሚከፈለው ሰራተኛ ከግብር 11,236 ዶላር (በብር 112,3600) በላይ የሚያገኝ ሰራተኛ ከፍተኛውን የግብር ጣራ 45% ግብር ይቀረጣል። የጅቡቲ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ (በተመጣጣኝ የመግዛት አቅም) በዶላር 6493 ( በብር 649,300)
Mushe Semu

የሰራተኞች_የኑሮ_ውድነት_ጫና_መደጎሚያ_የደመወዝ_ማሻሻያ.pdf
14.9 MB
#New
የደመወዝ ጭማሪው ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ለውሳኔ ቀረበ
በቅርቡ ትግበራው የተጀመረውን የአገራችን የተሟላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ተከትሎ የመንግስት ሰራተኞች በተለይም ዝቅተኛ የደመወዝ ተከፋይ ሰራተኞች በኑሮ ውድነት እንዳይጎዱ እና ሊደርስ የሚችለውን የኑሮ ጫና በመጠኑም ቢሆን ለመቋቋም እንዲችሉ ከመንግስት በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት የሰራተኞች የኑሮ ውድነት ጫና መደጎሚያ የደመወዝ ማሻሻያ ጥናት ተካሂዷል፡፡
ይህ የሠራተኞች የኑሮ ውድነት ጫና መደጎሚያ ደመወዝ ማሻሻያ ጥናት በገንዘብ ሚኒስቴር እና በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በጋራ ተካሄዶ ለማክሮ ኦኮኖሚ ኮሚቴ ቀርቦ ታይቷል።
ለደመወዝ ጭማሪው የሚያስፈልገው ተጨማሪ የወጪ በጀት ከነመጠባበቂያው ብር 91,439,368,014 /ዘጠና አንድ ቢሊዮን አራት መቶ ሰላሣ ዘጠኝ ሚሊዮን ሦስት መቶ ስድሳ ስምንት ሺህ ከአሥራ አራት ብር/ ሲሆን የደመወዝ ማሻሻያ የተደረገላቸው አካላት ዝርዝር ተለይቶ ቀርቧል።
የደመወዝ ጭማሪው ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ለውሳኔ የቀረበ ሲሆን ዝርዝር ትግበራውን የገንዘብ ሚኒስቴር እና የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በጋራ የሚያስፈጽሙት ይሆናል፡፡
ስለዚህ በሁለቱ መ/ቤቶች ተጠንቶና ተደግፎ የቀረበው እና በማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ የታየው የደመወዝ ጭማሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ ቀርቧል፡፡ #newsalaryethiopia2024