Ethiopian Digital Library
70.8K subscribers
971 photos
63 videos
753 files
591 links
በዚህ ቻናል ስለ
👉ትምህርት፣
👉ሥራ እና
👉ማህበራዊ ጉዳይ
መረጃ ያገኛሉ!

Contact: @ethiodlbot
Download Telegram
የግል ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በትምህርት ሚንስቴር ላይ ቅሬታ አቅርበዋል

Exit Exam በተመለከተ የግል ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ትምህርት ሚኒስቴር በደል እያደረሰ ነው።

1ኛ ፈተናውን እኩል ተፈትነን የነሱን ውጤት በነገታው ከለቀቀ በኋላ የግሎችን ከ15 ቀን በኋላ ነው የለቀቀው።

2ኛ የመንግስት ከ90 ፐርሰንት በላይ ሲያልፉ የግሎች ከ90 በላይ እንዲወድቁ ተደርጓል።

3ኛ 37.92 እና የመሳሰሉ ነጥብ ያላቸው ውጤቶችን አይተናል ። እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ነጥብ ያላቸው መቶ ጥያቄዎች ተፈትን 37.92 የምል እርማት በምን ተሰልቶ እንደመጣ እንዲገለፅልንና የAI ስህተት ካለ እንዲነገረን እንፈልጋለን።

ፈተናውን በአንድ አይነት የAI ሲስተም ከተፈተንን እንዴት የመንግስት ዩንቨርስቲን ብቻ ውጤት በነገታው ሊያሳይ ቻለ። የእኛ የግሎች ውጤት የዘገየበት ምክንያት ለግሎች ትኩረት በመነፈጉ ምክንያት ነው ወይስ የሲስተም ችግር ነበር?

በጣም ተዘጋጅተን ፈተናውን የተፈተንን ሰዎች በዚህ ትኩረት ሳይሰጠው በተፈተነው ፈተና ምክንያት ሞራላችን እንዲነካ እና ተስፋ እንድንቆርጥ ተደርገናል። ውጤታችን እንደገና ሊታይልንና የተፈተነው ጥያቄ ከነመልሱ ይፋ ሊደረግልን ይገባል።

በጉዳዩ ላይ ትምህርት ሚንስቴር ተጠይቆ እስካሁን ማብራሪያ አልሰጠም።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የኢንተርኔት አገልግሎት ተለቋል

በአማራ ክልል ባህርዳር፣ ወልዲያ፣ደብረብርሃን፣ደሴ፣ፍኖተሰላም፣ደብረማርቆስ፣ደጀን እና በሌሎች አካባቢዎች የኢንተርኔት አገልግሎት ተለቋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
በሚቀጥሉት ጥቂት አመታት ውስጥ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሙሉበሙሉ በኦላይን(online) እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

ስለሆነም የኮምፒውተር አጠቃቀም ክህሎትን ማሳደግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ነገ ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ይጀመራል

ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ዛሬ ዩኒቨርሲቲዎች አጠቃላይ ገለፃ እየሰጡ ነው ፡፡

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና ከነገ ሐምሌ 9/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ተፈታኞች ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ የገቡ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት በፈተናው ዲሲፕሊን ዙሪያ አጠቃላይ ገለፃ እየተደረገላቸው ነው፡፡
መልካም ፈተና !

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም መጠናቀቁ በጣም ደስ ይላል::

ግን ፈተናው እንዴት ነበር?
Anonymous Poll
24%
ቀላል
42%
መካከለኛ
35%
ከባድ
ለ62 ሺህ መምህራን ስልጠና

በክረምት የሚሰጠው የመምህራን ስልጠና ከ12ኛ ክፍል ፈተና በኋላ ይጀመራል::

በክረምት 62 ሺህ መምህራንን በሚያስተምሩት ትምህርትና የማስተማር ሥነ ዘዴ ዙሪያ ሥልጠና ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስትር አስታውቋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
ያልተመገበ መምህር ክፍል ግባ ቢባልም ሊገባ አይችልም ” - የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር

በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የሚገኙ መምህራን ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው፣ በዚህም ቤተሰብ ማስተዳደር እንዳልቻሉ ገለጹ።

መምህራኑ፣ “የ3 ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም። ታዲያ ቤተሰብስ እንዴት እናስተዳድር? ” ሲሉ በአንክሮ ጠይቀዋል።

ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው የሚመለከታቸውን አካላት እንደጠየቁ፣ ሆኖም መፍትሄ እንደሌለ፣ በዚህም ችግር ላይ እንደሆኑ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበርም ቅሬታው አግባብ መሆኑን ገልጾ፣ “ እንደውም እስከ ርዕሰ መስተዳደሩ ቢሮ ድረስ ጋውናቸውን ለብሰው ሂደው በክልሉ ልዩ ኃይል ነው የተመለሱት ” ብሏል።

የማኀበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አበበ በሰጡት ቃል፣ “ ቅሬታቸው የቆዬ ነው። የ3 ወራት ደመወዝ ተባለ እንጂ ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ የትምህርት ማሻሻያ፣ የደረጃ እድገት የማይሰጥበት አካባቢ አለ ” ብለዋል።

“ አሁን ላይ ደግሞ ደመወዝ ይቆረጣል። ለድርጅት ተብሎ ሁሉ ደመወዝ የሚቆረጥበት አካባቢ አለ ” ሲሉ ተናግረዋል።

መምህራኑ የ3 ወራት ደመወዝ እንደተቆረጠባቸው፣ በዚህም የክልሉ መምህራን ማኀበር፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር  ጥረት እንዳደረጉ የገለጹት አቶ ሽመልስ፣ “ ታች ያለው አመራር የላይኛውን የሚሰማ አይደለም ” ብለዋል።

“ መምህራን ግን ለከፋ የመልካም አስተዳደር ችግር እየተጋለጡ ናቸው፤ እዚያ አካባቢም (ሰመራ) በጣም የከፋ ችግር ነው ያለው ” ሲሉ አክለዋል።

ታዲያ ማኀበሩ ለቅሬታው ምን ምላሽ አገኘ ? በሰጡት ምላሽ፣ “ ቀደም ብለን ለርዕሰ መስተዳደሩ አቶ አወል አርባ ደብዳቤ ፅፈንላቸዋል። እሳቸውም ለታችኛው መዋቅር ችግሮቹ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ብለው በደብዳቤ አሳውቀዋል ” ብለዋል።

ሆኖም ከታች ያሉት አመራሮች ጉልበተኛ እንደሆኑ ነው አቶ ሽመልስ ያስረዱት።

“ አንድ መምህር ደመወዙ እየተቆረጠበት፣ ጉልበቱ ሌላ ጋ ከሆነ፣ ያልተመገበ መምህር ክፍል ውስጥ ግባ ቢባልም ሊገባ አይችልም። በጉልበት ቢገባ እንኳ ያስተምራል ወይ ? የሚለው ሌላ ጥያቄ ነው ” ብለዋል።

ይህ ድርጊት መማር ማስተማሩ ላይ በቀጣይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያስከትል ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው ገልጸው፣ “ ምስቅልቅሉ የወጣ አሰራር ነው ያለው ” ሲሉ ወቅሰዋል።

“ የታችኛው አመራር ለትምህርት የማያስብ፣ ለጊዜው ለፓለቲካ ተቆጥሮ የማሰጠውን አጀንዳ ብቻ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ፣ መደማመጥ የሌለበት፣ ለትውልድ የማያስብ አመራር እያየሁ ነው ” ነው ያሉት።

Credit: tikvahethiopia

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
ተማሪዎቼ እንዳያዩኝ ተደብቄ ነው የምገባው

የኑሮ ውድነት እና የቤት ኪራይ ጫና ከአቅማቸው በላይ የሆነባቸው የመቀለ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በሚያስተምሩበት ተቋም ውስጥ ለተማሪዎቻቸው በተዘጋጁ የማደሪያ ክፍሎች ውስጥ መኖር ግድ ሆኖባቸዋል።

ነገር ግን ይህ ሁኔታ ከባድ ሥነ ልቦናዊ ጫና በእነሱ ላይ ብቻ ሳይሆን በተማሪዎቻቸው ላይ ጭምር እያሳደረ ነው።

ቢቢሲ መምህራኖቹን አነጋግሮ ከሰራው ዘገባ
1.‘ተማሪዎቼ እንዳያዩኝ ተደብቄ ነው የምገባው’ ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት የሆኑት አንደኛው መምህር ለሰባት ዓመታት ያህል በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በመምህርነት አገልግለዋል።

2.“ሁሌም ሥራ ውዬ ወደ ቤቴ ስመለስ ኪሴ ባዶ ስለሆነ ልጆቼ እጅ እጄን ሲያዩ እሳቀቃለሁ። ልጆቼ ያዩትን ነገር እንዳይጠይቁኝ ስለምሳቀቅ ወደ ውጭ ይዣቸው አልወጣም።
በዚህም ማኅበራዊ ግንኙነታቸው እየተዳከመ መምጣቱን ስለምረዳ፤ ሥነ ልቦናችን በከፍተኛ ሁኔታ እየተጎዳ ነው።”

በአገሪቱ የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ የተሻለ ነው ባይባልም ቀደም ባሉት ዓመታት ከቀን ወደ ቀን ለመሻገር ግን ከብዷቸው እንደማያውቅ የሚናገሩት መምህሩ፣ ከትግራይ ጦርነት በኋላ ግን ሁሉም ነገር በአስከፊ ሁኔታ መቀየሩን ይናገራሉ።

አንድ ዓመት ተኩል ለሚጠጋ ጊዜ የቤተሰባቸውን መሠረታዊ ነገሮች የሚሸፍንላቸው ወርሃዊ ደሞዝ በመቆሙ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቆይተዋል።

“በጦርነቱ ወቅት በየቀኑ በረሃብ የሚሞቱ ብዙ ሰዎች ነበሩ። እንደ ዕድል ሆኖ በረሃብ ካልሞቱት ግን ደግሞ ሆዳቸውን ሞልተው ለማደር ካልታደሉት የመንግሥት ሠራተኞች መካከል አንዱ ሆኜ ነው አሳለፍኩት።”

የጦርነቱን ወቅት የቤተሰባቸውን ቀዳዳ ለመሸፈን በየቀኑ ከዚህም ከዚያም እየተበደሩ መቆየታቸውን የሚናገሩት የመቀለ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ፤ ሰላም ከወረደ በኋላ “ደመወዝ መከፈል ሲጀምር የተወሰነ ምሳ እና እራት በልቼ የምውልበት ዕድል አግኝቼ ነበር” ይላሉ።

ነገር ግን የሚያገኙት ወርሃዊ ደሞዝ እና እና የገበያው ሁኔታ ያልተመጣጠነ እየሆነ፣ እንዲሁም ከዕለት ዕለት እየባሰበት የሄደው የዋጋ ንረት ኑሯቸው ላይ ከፍተኛ ጫና እያስከተለ መጣ።

“ደሞዛችን ላይ የታየ ምንም ለውጥ አልነበረም። ስለዚህ ኑሮን መምራት፣ ልጆቼን ማስተማር፣ ልብስ መቀየር እና በልቶ ማደር ከባድ ሆኖ ተቸገርን።”

ደሞዛቸው አስር ሺህ ብር የማይሞላው እኚህ መምህር የቤትI ኪራይ ቢያንስ 5,000 ብር ከፍለው በቀረው ውሃ እና ኤሌክትሪክ፣ ምግብ እና የልጆችን ትምህርት ወጪን መሸፈን ፈተና ሆኖባቸዋል።

“ከዚች ደሞዝ ላይ አሁን ባለው ገበያ እህል ተገዝቶ ለዕለት አስቤዛ የሚሆን ነገር ማትረፍ አይቻልም። ህመም ካጋጠመም መታከሚያ አይኖርም። ልጆችም የመማር ዕድላቸው እየጨለመ እየሄደ ነው” ሲሊ ያማርራሉ።

እንግዲህ ይህ ሁኔታ ነው መምህሩን እና ሌሎች ባልደረቦቻቸውን ተማሪዎቻቸው በሚኖሩበት የዩኒቨርሲቲው ዶርም ውስጥ መጠለያ እንዲሰጣቸው እንዲጠይቁ ያስገደዳቸው። በዚህም በርካታ መምህራን በተማሪዎች ማደሪያ ዶርም ለመኖር ተገደዋል።
#ቢቢሲ
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ለመፈተን ከተመዘገቡት 701 ሺህ 749 ተማሪዎች ውስጥ 684 ሺህ 372 ተማሪዎች መፈተናቸውን ነው ትምህርት ሚኒስቴር የገለጸው፡፡ 

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መጠናቀቁን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ 701 ሺህ 749 ተማሪዎች ተመዝግበው 684 ሺህ 372 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ይህም ከተመዘገቡት ውስጥ 97.5 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች ፈተናውን ያልወሰዱ ተማሪዎች 17 ሺህ 377 መሆናቸውን የጠቀሱት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፣ 9 ሺህ 152 ተማሪዎች በአማራ ክልል ካለው የጸጥታ ችግር ጋር በተገናኘ ትምህርት ዘግይተው በመጀመራቸው ሳይፈተኑ ቀርተዋል ብለዋል።

29 ሺህ 718 ተማሪዎች ፈተናውን እንደ አዲስ በተጀመረው በይነመረብ (በኦላይን) መፈተናቸውን እና ቀሪዎቹ በወረቀት መፈተናቸውን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ ፈተናው በሰላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጻኦ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
154 ተፈታኞ ፈተና እንዲያቋርጡ
ተደረገ

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ በነበረበት ወቅት የተወሰኑ ተፈታኞች የፈተና አስተዳደር መመሪያ ድንጋጌ ጥሰቶች መፈፀማቸውን በትምህርት ሚኒስትሩ ተገልጿል።

ጥሰቶቹ በአይነትና በመጠን ቢለያዩም በሁሉም ክልሎች ባሉ የፈተና ማዕከላት መፈፀማቸውን ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

ተፈታኞች የሞባይል ስልክ፣ ላይተር፣ አደንዛዥ ዕፅ፣ ካናቢስ፣ የሞባይል ቻርጀር፣ ጥይት፣ ፍላሽ ዲስክ፣ ሲጋራ፣ ክብሪት፣ ጫት እንዲሁም ለሌላ ሰው ለመፈተን ሲሞክሩ በፍተሻ ወቅት መያዛቸውን ጠቁመዋል፡፡

በቡድን ሆኖ ለመጮህ መሞከርና ኃይማኖታዊ ስርዓቶችን እናደርጋለን በሚል ምክንያት የመረበሽ ሁኔታም ማጋጠሙን አንስተዋል።

በአጠቃላይ 354 የሞባይል ስልክ በፍተሻ መያዙን የገለፁት ሚኒስትሩ፤ 154 ተፈታኞ ፈተና እንዲያቋርጡ የተደረገ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ውጤታቸው ይሰረዛል ብለዋል።

12 ተማሪዎች የሌላ ተፈታኝ የግል ንብረት በመስረቅ ወይም በማበላሻት ሪፖርት እንደቀረበባቸውም ተገልጿል።

የተከለከሉ ነገሮችን በግቢ ውስጥ ወይም በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ይዘው ወይም ሲጠቀሙ የተገኙ ተፈታኞችም በቀረበባቸው ሪፖርት መሠረት በከፍል ወይም ሙሉ በሙሉ ውጤታቸው እንደሚሰረዝ ሚኒስትሩ ገልፀዋል::

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና

👉 44 ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከል ከገቡ በኃላ ወልደዋል፡፡

👉በተለያዩ የመፈተኛ ማዕከላት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ሕመም አጋጥሟቸው እንደነበረ ተሰምቷል። የአንድ ተፈታኝ ተማሪ ህይወትም በህመም ማለፉ ታውቋል።

👉በመፈተኛ ማዕከላት እያሉ አንድ ተፈታኝ የወባ ህመም፣ አንድ ተፈታኝ የመንፈስ ጭንቀት ህመም፣ ሁለት ተፈታኞች የአይን ህመም እና አንድ ተፈታኝ የትርፍ አንጀት ህመም አጋጥሟቸው እንደነበር ተገልጿል። በየማዕከላቱ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

👉ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ከምፓስ ዳንኤል ኃይለማሪያም ፈይሳ የተባለ የግል ተፈታኝ ባደረበት የልብ ህመም ምክንያት ወደ ህክምና ተቋም ተወስዶ በመታከም ላይ እያለ ህይወቱ ማለፉን ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አንስተዋል።

@Ethiopian_Digital_Library 
@Ethiopian_Digital_Library
የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

ተማሪዎች ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መለያ ቁጥርና ስም በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ፡፡

https://aa6.ministry.et/#/result

Or

@emacs_ministry_result_qmt_bot

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና

👉የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45

👉በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ፈተና የወሰዱ 85,046 ተማሪዎች

👉94.3% ያህሉ 50% እና በላይ ማምጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቀል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
ከ10 ስራዎች 9ኙ የዲጂታል ክህሎቶችን ይፈልጋሉ

እንደ ዓለም ባንክ ትንበያ በ2030 እ.አ.አ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ከ230 ሚሊዮን በላይ የዲጂታል ሥራዎች ይፈጠራሉ ተብሎ ይጠበቃል። እነዚህ የሥራ ዕድሎች በፍጥነት በማደግ ላይ ባለው የዲጂታል ኢኮኖሚ አማካኝነት የሚፈጠሩ ናቸው።

እነዚህን እድሎች በአግባቡ ለመጠቀም መካከለኛ እንዲሁም የላቀ የዲጂታል ክህሎት መኖር ግድ ይላል። በተጨማሪም መሰረታዊ የፋይናንስ እና የዲጂታል እውቀት በእጅጉ ያስፈልጋል።

አሁን ላይ በአህጉሪቱ ከፍተኛ የዲጂታል ክህሎት ክፍተት ከመኖሩም በተጨማሪ በጾታ መካከል ያለው ልዩነት ሰፊ ነው። የቴክኖሎጂ ልምምድ አናሳ መሆን በተለይ ደግሞ በፐብሊክ ሴክተሩ ያለው ደካማ የዲጂታል ክህሎት በፍጥነት ከሚጓዘው የቴክኖሎጂ እድገት ጋር የማይጣጣም ነው።

የአሁን ላይ ባለው የዲጂታል እድገት የሥራው ዓለም በፍጥነት እየተቀየረ መጥቷል። በዚህም በሚቀጥሉት 10 ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ10 ስራዎች 9ኙ የሚሆኑት የዲጂታል ክህሎቶችን እንደሚፈልጉ ይገመታል።

ለዚህ ደግሞ የትምህርት ሥርዓቱን ማሻሻል፤ በምን፣ እንዴት፣ እና በማን የሚሉ ጥያቄዎችን የሚመልስ ግልጽ የፖሊሲ ሥርዓት ያስፈልጋል። በተጨማሪም ህጻናት በትምህርት ቤታቸው እንዲህ አይነቱን ክህሎት እንዲያገኙ ማስቻልና ልዩ ልዩ ንቅናቄዎችን መፍጠር አስፈላጊ ነው። #DigitalSkill
Credit: Tikvaheth

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
በክረምት የሚሰጠው ልዩ የመምህራንና ትምህርት አመራሮች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ጊዜ

ትምህርት ሚኒስቴር በክረምት ልዩ የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ ።

ለስልጠና አፈጻጸም የተዘጋጀ መምሪያ በቀን ሰኔ 19 / 2016 ዓ.ም በቁጥር 10/242/217/16 በተጻፈ ደብዳቤ ለሁሉም ለአሰልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎች መላኩ ይታወቃል ። በዚህ መሰረት

1. ሁሉም ሰልጣኝ መምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች ሐምሌ 22 / 2016 ዓ.ም እስከ ቀኑ 6:00 ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ይገባሉ ።

2. የትምህርት ቤት አመራረሮች ነሐሴ 4 / 2016 ዓ.ም እንዲሁም መምህራን ነሐሴ 16 / 2016 ዓ.ም ስልጠና አጠናቀው ከዩኒቨርሲቲዎች ይወጣሉ ።

ስለሆነም ሁሉም ክልል / ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ከላይ በተጠቀሰው መረሃ ግብር መሰረት ለሰልጣኝ መምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች ጥሪ እንዲደረግ እና በየትምህርት መዋቅሩ ቅድመ ስልጠና ኦረንቴሽን እንድትሰጡ እያሳሰብን አሰልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎችም ሐምሌ 22 / 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8 ፡ 00 ጀምሮ በየዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጠው የስልጠና ኦረንቴሽን ዝግጅት እንዲደረግ በጥብቅ እናሳስባለን::

ትምህርት ሚኒስቴር

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
በአዲሱ የትምህርት ዘመን አዲስ የቀን ዋጋ ተመን ይፋ ይደረጋል

ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በቀን ተተምኖ የሚመደበው ሂሳብ ማሻሻያ ከ2017 ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስራዎች እያጠናቀቅሁኝ ነው አለ፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማር አንድ ተማሪ በቀን ለምግብ የሚታሰብለት ዋጋ 22 ብር ነው፡፡

በዚህ ዋጋ ቁርስ፣ ምሳውና እራቱን መመገብ ይቻል ተብሎ ተተምኖለታል፡፡

አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ግን ይህ 22 ብር አንዳንድ አካባቢዎች የአንድ ሲኒ ሻይን ሂሳብን እንኳን መሸፈን አይችልም፡፡

በዚህም ምክንያት በተለያዩ ጊዜያት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ጨምሮ ዋጋ ማስተካከያ ሊደረግ ይገባል፡፡ጊዜውን ያማከለ ትመና አይደለም የሚል ተቃውሞ ሲነሳ ይደመጣል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አሁን ያለው የኑሮ ሁኔታ እና ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚመደበው የቀን ዋጋ ተመን አይመጣጠንም ይላሉ፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ጥናት እየተደረገ ነው ያሉ ሲሆን እስከ ነሃሴ ድረስ ስራዎች ተጠናቀው በአዲሱ የትምህርት ዘመን አዲስ የቀን ዋጋ ተመን ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
እስከ ህዳር ጥናቱ ይጠናቀቃል

የዩኒቨርስቲ መምህራን ኑሮ ከብዷቸው ደሞዝ አንሷቸው በተጓዳኝ የጉልበት ስራ እየሰሩ መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት ሲናገሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለዩኒቨርሲቲ መምህራን የሚከፈለው ደመወዝ አነስተኛ ነው ይህንን ችግር ለመፍታት ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር እየተነጋገርን ነው፡፡

ከኮሚሽኑ ጋር በመሆን ጥናቶች እየተደረጉ ነው ያሉ ሲሆን እስከ ህዳር ድረስ ጥናቱ ይጠናቀቃል ያኔ አዲስ ነገር ሊኖር ይገባል ብለዋል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
በመጽሀፍት ላይ የተጣለው የተጨማሪ እሴት ግብር  
                   

ኢትዮጵያ እጅግ ዝቅተኛ የመጽሀፍት ህትመት እንዲሁም ዝቅተኛ የማንበብ ባህል ካላቸው ሀገራት ተርታ እንደምትሰለፍ ይታወቃል።

አንድ መጽሐፍ ታትሞ 10 ሺህ ኮፒ ለገበያ ከቀረበ "ተቸበቸበ" በሚባልበት፣ ደራሲያን ከጊዜ ወደ ጊዜ አንባቢ በማጣት አዳዲስ ሥራዎችን ለገበያ ለማቅረብ በሚፈሩበት፣ በወረቀት ዋጋ ንረት ምክንያት የመጽሀፍት ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ በጨመረበት ጊዜ ላይ በሆንንበት በእዚህ ወቅት መጽሀፎች ላይ የተጨማሪ እሴት ግብር መጣል የመጽሀፍ ዘርፉን ከድጡ ወደ ማጡ እንደሚያደርገው ሳይታለም የተፈታ ነው።

አብዛኞቹ ደራሲያን በመጽሀፍ አከፋፋዮች አሊያም በሌሎች ግለሰቦች እርዳታ መጽሀፍ የሚያሳትሙበት ሀገር እንደሆነ ከእዚህ ቀደም ሁለት መጽሀፎችን ስላሳተምሁ፣ ብዙ ደራሲያን ጓደኞች ያሉኝ በመሆኑ በቅርበት የማውቀው እውነታ ነው። አብዛኛው ደራሲ ከእጅ ወደ አፍ የሚኖርበት ሀገር መሆኑን መጽሀፍ ጽፈው በማሳተም ብቻ ኑሮአቸውን የሚገፉ ደራሲያንን ህይወት መመልከቱ ብቻ በቂ ነው።

በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ግብር አዋጅ ውስጥ ከትምህርት መርጃ መጽሀፍት እና ከቅዱሳን መጽሀፍት በቀር ሌሎች መጽሀፍት ከግብር ነጻ የሆኑ አቅርቦት ውስጥ አልተካተቱም።

ስለሆነም መንግስት ከዘርፉ ከሚያገኘው ጥቅም ይልቅ የንባብ ባህሉ ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን በመረዳት ለወደፊት የሚወጣ መመሪያ የመጽሀፍ ህትመትና ስርጭት ዘርፉን ከተጨማሪ እሴት ግብር ነጻ እንደሚያደርግ ከፍተኛ እምነት አለኝ። #Ferenka

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሃላፊዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በሙስናና በሃብት ምዝበራ ተጠርጥረው ነው። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ታምራት ታገሰ (ዶ/ር) ይገኙበታል።

ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ ለአንድ የዩኒቨርስቲው የፋይናንስ ቡድን መሪ የ790 ቀን አበል እንዲሁም ለሌላኛው የፋይናንስ የቡድን መሪ ደግሞ በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ የ1,469 ቀን (1,056,854 ብር) አበል እንደተከፈላቸው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሰነድ ማስረጃዎችን፣ጥቆማዎችን እና መመሪያዎችን በማጣቀስ ምርመራ አድርጎ ውጤቱን ይፋ አድርጓል።

ሌላም የዩኒቨርስቲው ፋይናንስ ሳያውቅ 1.4 ቢሊዮን ብር ለኦክስጅን ማምረቻ በሚል በህገወጥ መንገድ መንቀሳቀሱን እና ፍቃድ የሌለው የኮንስትራክሽን ድርጅት ግንባታውን እንዲሰራ ያለ ጨረታ እንደተሰጠው በምርመራ ውጤቱ ተገልጿል። በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተመሳሳይ ምርመራ ቢደረግ ከዚህም በላይ የሙስና ወንጀል እንደሚገኝ እሙን ነው:: #FBC

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
ኦሎምፒክ - 2 ቀናት ብቻ ቀርተዋል

ተወዳጁ የኦሎምፒክ ውድድር በፈረንጆቹ 1896 ላይ በግሪክ የተጀመረ ሲሆን
የዘንድሮው ውድድር በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።

ውድድሩ የፊታችን አርብ በይፋ የሚከፈት ሲሆን ከ206 ሀገራት የተውጣጡ ከ10 ሺህ 500 በላይ አትሌቶች እንደሚወዳደሩ ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል።

እስካሁን በተካሄዱት የኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ አሜሪካ 2 ሺህ 629 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ በታሪክ ስኬታማዋ ሀገር ነች።

ከአሜሪካ በመቀጠል ሶቭየት ህብረት፣ ጀርመን እና ብሪታንያ ብዙ ሜዳሊያዎችን ካገኙ ሀገራት መካከል ተጠቅሰዋል።

ከአፍሪካ ኬንያ በ113 ሜዳሊያዎች በአንደኝነት ስትቀመጥ ደቡብ አፍሪካ በ89 እንዲሁም ኢትዮጵያ ደግሞ በ58 ሜዳሊያዎች በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። #Alain

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library