ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ ይሆናል
የሰው ልጅ ሊሰቀል አልፎ ይሰጣል
ሁልጊዜ ከእኛ ጋር ስለማይኖር እሱ
ሽቶውን ቀባችው አፍሳ በራሱ
በቀያፋ ግቢ ሁሉም ተሰብሰበው
ሊገድሉት መከሩ በተንኮል አስይዘው
ፍቅሩን እያሳየ ፈውስን በሰጣቸው
ሞቱን ተመኙለት ቅናት አውሯቸው
አይ ሰው ሰው ከንቱ
ፈጣሪውን አሳልፎ ለሞት መስጠቱ
በፍቅር አቅርቦ ሁሉን እየሰጠው
በሠላሳ ዲናር አሳልፎ ሸጠው
እኔ እሆንን ይላል ደግሞም አያፍር
ምነው ባይወለድ ይሻለው ነበር
አይ ሰው ሰው ከንቱ
ፈጣሪውን አሳልፎ ለሞት መስጠቱ
እባክህ ይሁዳ ጉንጩን አትሳመው
የልብህን ይዘህ በአፍ አትሸንግለው
እሱ እኮ ነግሮሃል አንተ እንደምትሰጠው
ያኔ በወጭቱ እጅህን ስትከተው
አይ ሰው ሰው ከንቱ
ፈጣሪውን አሳልፎ ለሞት መስጠቱ
የዓለም ብርሃን ቆሞ ከፊት
በችቦ መጡ ጌታን ሊይዙት
እልፍ ሠራዊት እንደሌለው
በትህትና እጁን ሰጣቸው
አይ ሰው ሰው ከንቱ
ፈጣሪውን አሳልፎ ለሞት መስጠቱ
ጴጥሮስ መልሰው ሰይፍህን ከአፎቱ
ግድ ነውና ሊፈጸም ትንቢቱ
እስከ ቀራኒዮ መከራው ይዘልቃል
ስለ ፍቅር ብሎ ህይወቱን ይሰጣል
አይ ሰው ሰው ከንቱ
ፈጣሪውን አሳልፎ ለሞት መስጠቱ
አላውቀውም ብሎ ሦስት ጊዜ ቢክደው
ዶሮውም ጮኸና ቃሉን አስታወሰው
ተፀፅቶ ወጣ ተንሰቅስቆ ሊያለቅስ
የንስኃን እምባ በጉንጮቹ ሊያፈስ
አይ ሰው ሰው ከንቱ
ፈጣሪውን አሳልፎ ለሞት መስጠቱ
የሰው ልጅ ሊሰቀል አልፎ ይሰጣል
ሁልጊዜ ከእኛ ጋር ስለማይኖር እሱ
ሽቶውን ቀባችው አፍሳ በራሱ
በቀያፋ ግቢ ሁሉም ተሰብሰበው
ሊገድሉት መከሩ በተንኮል አስይዘው
ፍቅሩን እያሳየ ፈውስን በሰጣቸው
ሞቱን ተመኙለት ቅናት አውሯቸው
አይ ሰው ሰው ከንቱ
ፈጣሪውን አሳልፎ ለሞት መስጠቱ
በፍቅር አቅርቦ ሁሉን እየሰጠው
በሠላሳ ዲናር አሳልፎ ሸጠው
እኔ እሆንን ይላል ደግሞም አያፍር
ምነው ባይወለድ ይሻለው ነበር
አይ ሰው ሰው ከንቱ
ፈጣሪውን አሳልፎ ለሞት መስጠቱ
እባክህ ይሁዳ ጉንጩን አትሳመው
የልብህን ይዘህ በአፍ አትሸንግለው
እሱ እኮ ነግሮሃል አንተ እንደምትሰጠው
ያኔ በወጭቱ እጅህን ስትከተው
አይ ሰው ሰው ከንቱ
ፈጣሪውን አሳልፎ ለሞት መስጠቱ
የዓለም ብርሃን ቆሞ ከፊት
በችቦ መጡ ጌታን ሊይዙት
እልፍ ሠራዊት እንደሌለው
በትህትና እጁን ሰጣቸው
አይ ሰው ሰው ከንቱ
ፈጣሪውን አሳልፎ ለሞት መስጠቱ
ጴጥሮስ መልሰው ሰይፍህን ከአፎቱ
ግድ ነውና ሊፈጸም ትንቢቱ
እስከ ቀራኒዮ መከራው ይዘልቃል
ስለ ፍቅር ብሎ ህይወቱን ይሰጣል
አይ ሰው ሰው ከንቱ
ፈጣሪውን አሳልፎ ለሞት መስጠቱ
አላውቀውም ብሎ ሦስት ጊዜ ቢክደው
ዶሮውም ጮኸና ቃሉን አስታወሰው
ተፀፅቶ ወጣ ተንሰቅስቆ ሊያለቅስ
የንስኃን እምባ በጉንጮቹ ሊያፈስ
አይ ሰው ሰው ከንቱ
ፈጣሪውን አሳልፎ ለሞት መስጠቱ
#በእንተ_ጸሎት_ሐሙስ
"ተራሮችን በኃይሉ የሚያስታጥቃቸው ለማገልገል ማበሻ ጨርቅ ታጠቀ፡፡ የባሕርን ውኃ እንደ አቁማዳ የሚሰበስበው በቀላያትም መዝገቦች የሚሾማቸው ርሱ ከወዳጁ ከአልዓዛር ቤት የውኃ ማድጋ አንሥቶ እግሮችን ለማጠብ ያገለግልባት ዘንድ ወደ ኩስኩስት አፈሰሰ፡፡ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በሚታጠቡበት ገንዘብ የናስ ኩስኩስት ሠርቶ በደብተራ ኦሪት ደጃፍ እንዲያኖራት ሙሴን ያዘዘው ውኃውን በኩስኩስት ሞልቶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ዠመረ፡፡ የተረከዞቻቸውንም እድፍ በታጠቀው ማበሻ ጨርቅ አሸ፡፡" (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)
"በወገቡ የታጠቀውን ማድረቂያ አይተው መላእክት አደነቁ፤ ስሙ ከፀሓይና ከጨረቃ በፊት የነበረ ርሱ አገልጋይ ኾነ፤ ሕያው ጌታን ሱራፌል ያመሰግኑታል፤ ቦታውን ግን አያውቁም፤ ሱራፌልን የፈጠረ ርሱ በራት ጊዜ ወገቡን ዘርፍ ባለው ዝናር ታጠቀ፤ እንዳያቃጥል በመፍራት የማይታይ እሳት ለሐዋርያት አገልጋይ ኾኖ አብነት ይኾናቸው ዘንድ የትሕትና ሥራን የሚሠራበትን ውሃ በኩስኩስት ቀዳ የደቀ መዛሙርቱን አለቃ ጴጥሮስንም እግሩን ሊያጥበው ጠራው"
(ሃይማኖተ አበው ዘያዕቆብ ዘሥሩግ)
@yemezmurgetemoche

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ጥያቄና መልስ 1. መርገመ በለስ ተብላ የተሰየመችው እለት ምን ትባላለች? 2. በዕለተ ማግሰኞ አይሁዶች ለጌታ የጠየቁት ጥያቄ ምን ነበር? 3. ለታላቅ ለንስሓ ዶሮ የቀሰቀሰችው ሐዋሪያ ማን ይባላል? 4. ጌታችን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተናገራቸው ዐቢይ ቃላት ምን ምን ነበሩ? 5.የትኛው ዕለት…
የጥያቄዎቹ መልስ
1. ዕለተ ሰኑይ/ ሰኞ/
2.ከምድራዊያን ነገስታት፣ አሌዊያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራትነ ማድረግ፣ ገበያ መፍታት በማን ስልጣን ታደርጋለህ?
3.ሐዋሪያው ቅዲስ ጴጥሮስ
4."ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ"
" እውነት አውነት እልሀለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ"
"የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው"
እመቤታችንን" አንቺ ሴት ሆይ እነሆ ልጅሽ"
ደቀ መዝሙሩን" እናትህ እነኋት"
" አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ"
" ተጠማሁ"
"ተፈፀመ"
5. ዕለተ ረቡ
6.ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ በአልባሲጥሮስ ብልቃጥ የሞላ ሽቱ ይዛ በመሄድ በጠጉሩ / በራሱ/ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ነው።
7."የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነው? ከሰማይ ወይስ ከምድር?
8. አላዶር፣ ሳዶር፣ ሮዳስ፣ ዳናት፣ አዴራ።
9.ሐዋሪያው ቅዱስ ዮሐንስ ነው። ምክንያቱም ጌታ ከተሰቀለበት ቀን ጀምሮ ስላልሳቀ ነው።
10. ሐዋሪያው ቅዱስ ዮሐንስ ነው።

#ፀሎተ_ሐሙስ
ዛሬ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ 12ቱ ሐዋሪያት ጋር ለመጨረሻ ጊዜ እራት የቀረበበት ቀን ነው።

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🎵 #መዝሙር
🔴 አዲስ የንስሓ ዝማሬ " ቀራንዮ " ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ @EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs
For any suggestion or question 👇 http://t.me/KIDAN_MEHRET_ENATEbot
For more join 👇
@EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs
Bot configuration by:- @gutaitagu16

✞ ቀራኒዮ አየሁት ✞
@yemezmurgetemoche
ቀራኒዮ አየሁት
ቀራንዮ አየሁት ቀራንዮ አየሁት
የተጠማሁት ጌታን አገኘሁት
እረፍት ሆኖልኛል ሸክሜን ተሸክሞ
ሕይወቱን በሰጠኝ የኔን ሕይወት ታሞ
ቁስሉ ፈውሶኝ ጌታዬ
ንጹህ ደሙ ነው ዋጋዬ
የኔ አይደለሁም የራሴ
ለዋጀኝ አለኝ ውዳሴ
ልብሴ ነው ለኔ እርቃኑ
ደስታን የሰጠኝ ማዳኑ
የኔን መሰደድ ተሰዶ
በክብር አስጌጠኝ ተዋርዶ
የተቀበለው መከራ
የኔን ጨለማ አበራ
እንባየን ገድቦት ደሙ
በልቤ ሞልቷል ሰላሙ
ፍቅር ያደከመው ኃይለኛ
ይጠብቀኛል ሳይተኛ
ቀድሞ እየወጣ በሰልፌ
ዛሬም አለሁኝ አትርፌ
በምድረ በዳ መንጭቶ
ውሃ ሆነልኝ ተጠምቶ
ስፍራ አዘጋጄ በሰማይ
ጩኸቴን ጨኸ መስቀል ላይ
ሰርጓጉት ሸለቆ ሞልቷል
አጥፊውም ሳይነካኝ አልፏል
ቀራንዮ ላይ ብቃቴን
አግኝቸዋለሁ ንጋቴን
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ቀራንዮ አየሁት ቀራንዮ አየሁት
የተጠማሁት ጌታን አገኘሁት
እረፍት ሆኖልኛል ሸክሜን ተሸክሞ
ሕይወቱን በሰጠኝ የኔን ሕይወት ታሞ
ቁስሉ ፈውሶኝ ጌታዬ
ንጹህ ደሙ ነው ዋጋዬ
የኔ አይደለሁም የራሴ
ለዋጀኝ አለኝ ውዳሴ
ልብሴ ነው ለኔ እርቃኑ
ደስታን የሰጠኝ ማዳኑ
የኔን መሰደድ ተሰዶ
በክብር አስጌጠኝ ተዋርዶ
የተቀበለው መከራ
የኔን ጨለማ አበራ
እንባየን ገድቦት ደሙ
በልቤ ሞልቷል ሰላሙ
ፍቅር ያደከመው ኃይለኛ
ይጠብቀኛል ሳይተኛ
ቀድሞ እየወጣ በሰልፌ
ዛሬም አለሁኝ አትርፌ
በምድረ በዳ መንጭቶ
ውሃ ሆነልኝ ተጠምቶ
ስፍራ አዘጋጄ በሰማይ
ጩኸቴን ጨኸ መስቀል ላይ
ሰርጓጉት ሸለቆ ሞልቷል
አጥፊውም ሳይነካኝ አልፏል
ቀራንዮ ላይ ብቃቴን
አግኝቸዋለሁ ንጋቴን
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
እስኪ ንገረኝ ! ሕፃናት ቤት እንሥራ ብለው የሚጫወቱት ጨዋታና እኛ በዚህ ዓለም የሚያማምሩ ቤቶችን ስንሠራ ልዩነታችን ምንድን ነው? ሕፃናት እራት እናሰናዳ ብለው በሚጫወቱት ጨዋታና እኛ በምናዘጋጀው ጣፋጭ ማዕድ ልዩነቱ ምንድን ነው? ምንም ምን ልዩነት የለውም፡፡ እንዲያውም እኛ እንደዚህ በማድረጋችን በእኛ ላይ የሚያመጣው ከፍ ያለ ቅጣት (ኵነኔ) አለው፤ [የሕፃናቱ ግን የለውም፡፡] ይህን የምናደርገው ነገር ፍጹም የጎስቋላነት ተግባር እንደ ኾነ ያልተገነዘብነው እንደ ኾነም ይህ ምንም አያስደንቅም፡፡ ገና እስከ አሁን ድረስ ዐዋቂ ሰዎች አልኾንንምና፡፡ ያን ጊዜ ግን ዐዋቂዎች ስንኾን ግን [ረብ ጥቅም የለውም እንጂ] አሁን የምናደርገው ተግባር ኹሉ የሕፃን ሥራ እንደ ኾነ እናውቃለንና፡፡
ሕፃናት እያለን ስናደርጋቸው የነበሩት ተግባራት ዐዋቂዎች ስንኾን እንንቃቸዋለንና፡፡ ሕፃናት እያለን ግን እነዚህን ልናገኛቸው ብለን አስበን የምንጨነቅባቸው የነበሩ ናቸው፡፡ ሕፃናት ኾነን ገልና ሸክላ ስንሰበስብና ካብ ስንከምር ረጃጅም አጥሮችን ከሚሠሩ ሰዎች እንደማንተናነስ አድርገን እናስብ ነበር፡፡ ነገር ግን እነዚያ ያቆምናቸው የድንጋይ ክምሮች ወዲያውና እዚያው ፈራርሰው የሚወድቁ ነበሩ፤ ጸንተው ቢቆሙም እንኳን የሚሰጡን ረብ አልነበረም፡፡ አሁንም እኛ በዚህ ዓለም የምንሠራቸው የሚያማምሩ ቤቶች ያው እንደ እነዚህ የሕፃንነታችን ጊዜ ካቦች ናቸው፡፡ አሁን የምንሠራቸው ቤቶች ሀገሩ በሰማይ የኾነውን ሰው ተቀብለው ማኖር የሚቻላቸው አይደሉምና፤ እነርሱ ተቀብለው ማኖር አለመቻላቸው ብቻም ሳይኾን በላይ በሰማይ ሀገሩ የኾነ ሰውም በእነዚህ ቤቶች መኖርን የሚሻ አይደለምና፡፡ ሕፃናት የከመሩአቸው ካቦች እኛ በእግራችን ነካ ብናደርጋቸው የሚፈራርሱ ናቸው፡፡ ልክ እንደዚሁ በመንፈስ ልዑል የኾነ ሰውም እነዚህን እኛ የምንደነቅባቸው ቤቶች የሚመለከታቸው እንደዚህ ነው፡፡ ሕፃናቱ ቤት ብለው የከመሩአቸው ካቦች በእግራችን ነካ ብናደርግባቸውና ብናፈርስባቸው ስቅስቅ ብለው ሲያለቅሱ ተመልክተን [የማያስለቅስ ያስለቅሳቸዋል ብለን] እኛ እንደምንስቅ ኹሉ፥ እነዚህ በመንፈስ ልዑላን የኾኑ ሰዎችም እኛ በእነዚህ ቤቶች መፍረስ ስንተክዝ ተመልክተው [በማያሳያዝን ያዝናሉ በማያስተክዝም ይተክዛሉ ብለው] ይስቃሉ፡፡ እንዲያውም መሳቅ ብቻም ሳይኾን ያለቅሳሉ፡፡ ምክንያቱም፡-
[አንደኛ] ርኅሩኀን ናቸው፤
[ኹለተኛ ደግሞ] እኛ ከእነዚህ ቤቶች ጋር ይህን ያህል በመጣበቃችን ምክንያት የሚመጣብን ጉዳት ብዙ የብዙም ብዙ እንደ ኾነ ያውቃሉና ያለቅሳሉ፡፡
ስለዚህ ዐዋቂዎች እንኹን፡፡ እስከ መቼ ድረስ ነው በምድር ላይ የምንንፏቀቀው? እስከ መቼ ድረስ ነው በድንጋዮችና በምድራዊ መኖሪያ ቤቶች ራሳችንን የምናስታብየው? እስከ መቼ ድረስ ነው ዕቃ ዕቃ የምንጫወተው?
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ ድርሳን 23:10)

#ሚያዝያ_25
#ቅድስት_ሣራ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሚያዝያ ሃያ አምስት በዚች ቀን ቅድስት ሣራ ከሁለቱ ልጆቿ ጋራ በሰማዕትነት አረፈች፡፡ ይቺም ቅድስት ከአንጾኪያ አገር ናት እርስዋም ከዲዮቅልጥያኖስ መኳንንት ለአንዱ ስሙ ስቅራጥስ ለሚባል ሚስቱ ናት እርሱም በፊት ክርስቲያን ነበረ በኋላ ንጉሡን በመፍራት ካደ እርስዋ ግን በክርስትናዋ ጸንታ ኖረች።
ባልዋ ስቅራጥስም እኔ የክርስቲያንን ሃይማኖት እወዳለሁ የንጉሡን ሥቃይ ከመፍራት በቀር ክርስቶስን በልቤ አልካድኩትም ይላት ነበር። እንደዚህም ስትኖር ሁለት ልጆችንም ወለደች በአንጾኪያም አገር የክርስትና ጥምቀትን ልታስጠምቃቸው አልተቻላትም። አብያተ ክርስቲያናት ተዘግተዋልና ጠፍተዋልምና ሰውን ወዳድ ክርስቶስን ብዙ ስለመውደዷ ልጆቿን ታስጠምቃቸው ዘንድ ታላቅ ተጋድሎ አደረገች ወደ እስክንድርያ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጴጥሮስ ልትሔድ ወዳ አሽከሮቿን አስከትላ ሁለቱን ልጆቿን ይዛ በመርከብ ተሳፈረች።
የክብር ባለቤት ጌታችንም የሃይማኖቷን ልዕልና ለመጪው ትውልድ ሊገልጥ ወዶ ያቺ መርከብ ለመሥጠም እስከምትደርስ በባሕር መካከል ጥቅል ነፋስን አስነሣ። ይቺ ቅድስትም ልጆቿ ሳይጠመቁ እንዳይሞቱ ፈራች ተነሥታም ጸለየች ከዚያም ምላጭ አንሥታ ጡቷን የቀኙን በጣች ከደሟም ወስዳ ፊታቸውን በመስቀል ምልክት ቀባች በደረታቸውና በጀርባቸውም ላይ እንዲሁ አደረገች በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በባሕሩ ውስጥ አጠመቀቻቸው ያን ጊዜም ታላቅ ጸጥታ ሆነ።
ወደ እስክንድርያ አገርም በደረሰች ጊዜ ከሀገር ልጆች ጋራ ያጠምቃቸው ዘንድ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጴጥሮስ ልጆቿን አቀረበች በዚያን ጊዜም ከሀገር ልጆች አጠመቀ። ወደልጆቿም ደርሶ ሊአጠምቃቸው ወሰዳቸው ያን ጊዜ ውኃው ረጋ እነርሱን ትቶ ከአገር ልጆች አጠመቀ ውኃውም ተፈትቶ ወረደ ደግሞ ሊአጠምቃቸው ወደ ልጆቿ ተመለሰ አሁንም እንደቀድሞው ውኃው ረጋ እንዲሁም ሦስት ጊዜ አደረገ ውኃውም ይረጋል አደነቀ። እናታቸውንም አቅርቦ ጠየቃት እርሷም ፈርታ ተንቀጠቀጠች ከእርሷም የሆነውን በባሕር መካከል ዐውሎ ነፋስ እንደተነሣባት ጡቷን በጥታ ደሟን እንደ ቀባቻቸውና በባሕር ውስጥ እንዳጠመቀቻቸው ነገረችው ስለ አደረገችውም ድፍረት በፊቱ ሰግዳ ይቅር ይላት ዘንድ ለመነችው።
አባ ጴጥሮስም ሴትዮ አትፍሪ ሃይማኖትሽ ፍጹም ነው አንቺ በባሕር ውስጥ በአጠመቅሻቸው ጊዜ በመለኮታዊት እጁ ያጠመቃቸው ባለቤቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና አይዞሽ አላት።ማጥመቁንም በፈጸመ ጊዜ ሥጋውን ደሙን አቀበላቸው ይቺም ቅድስት ወደ አንጾኪያ ቤቷ ተመለሰች።
ባሏም በአያት ጊዜ ይህን በማድረጓ ተቆጥቶ ወደ ንጉሡ ሒዶ ከሰሳት ያደረገችውንም ነገረው። ንጉሡም ወደርሱ ያቀርቧት ዘንድ አዘዘ ስትቀርብም ወደ እስክንድርያ ለምን ሔድሽ ከክርስቲያን ወገኖች ጋራ ልታመነዝሪ ነውን አላት። እርሷም እንዲህ ብላ መለሰችለት ክርስቲያኖች አያመነዝሩም እንደናንተ የረከሰ ጣዖትን አያመልኩም ከእንግዲህ ደግሞ ከእኔ ቃልን አትሰማም የወደድከውን አድርግ ሁለተኛም በእስክንድርያ ካንቺ የሆነውን ንገሪኝ ብሎ ጠየቃት ምንም ምን አልመለሰችለትም ።
ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም እጆቿን የኋሊት አሥረው ሁለቱንም ልጆቿን በሆድዋ ላይ አድርገው ሦስቱንም በእሳት ያቃጥሉአቸው ዘንድ አዘዘ። ፊቷንም ወደ ምሥራቅ መልሳ ወደ ክብር ባለቤት ጌታችን ጸለየች ከዚያም ከልጆቿ ጋራ አቃጠሉዋት የድልና የሕይወት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ለዘላለም ይማረን አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሚያዝያ)

#የፍቅር_ ቀን#
❤❤❤❤❤
እኔ የማከብረው ሁሌ ምዘክረው
አለኝ የፍቅር ቀን አለኝ የማረሳው
ልቤን አሸንፎት በእንባ የማወሳው
የኔ ውድ አፍቃሪ በቀጠሮው ሰአት በቀጠሮው ቦታ
ሳያረፍድ ተገኝቶ በዛች በከፍታ
በደሙ ቀለበት ገብቶልኝ ቃልኪዳን
በእውነተኛ ፍቅር ለእውነተኛ መዳን
ልሙትልሽ ብሎ በፅኑ መሀላ
መውደዱን ገልጦልኝ እንድኖር በተድላ
በዛች በለተ አርብ በፍቅር ቀናችን
ፍቅሩን ገልጦልኛል
ቀይ አበባ ሳይሆን ቀይ ደም ሰቶኛል
ስለዚህ ያቺ ናት እርሷ ናት
የኛ ቀን የኔና የውዴ
ለአለም የታየበት በርሱ መወደዴ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ክብርና ምስጋና ይግባው በእለተ አርብ ለተሰቀለው
⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅
❤❤❤❤❤
እኔ የማከብረው ሁሌ ምዘክረው
አለኝ የፍቅር ቀን አለኝ የማረሳው
ልቤን አሸንፎት በእንባ የማወሳው
የኔ ውድ አፍቃሪ በቀጠሮው ሰአት በቀጠሮው ቦታ
ሳያረፍድ ተገኝቶ በዛች በከፍታ
በደሙ ቀለበት ገብቶልኝ ቃልኪዳን
በእውነተኛ ፍቅር ለእውነተኛ መዳን
ልሙትልሽ ብሎ በፅኑ መሀላ
መውደዱን ገልጦልኝ እንድኖር በተድላ
በዛች በለተ አርብ በፍቅር ቀናችን
ፍቅሩን ገልጦልኛል
ቀይ አበባ ሳይሆን ቀይ ደም ሰቶኛል
ስለዚህ ያቺ ናት እርሷ ናት
የኛ ቀን የኔና የውዴ
ለአለም የታየበት በርሱ መወደዴ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ክብርና ምስጋና ይግባው በእለተ አርብ ለተሰቀለው
⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅
ነገ ሰግዳችሁ አረፍ በምትሉበት ሰዓት ይህንን ያንብቡ👇
#አንድ_አምላክ_በሚሆን_በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ ስም አሜን
የመድኃኔዓለምን የሕማሙን የሞቱን ነገር መናገር እንጀምራለን፡፡ 13ቱ ሕማማተ መስቀል እነማን ናቸው ቢሉ ተዓሥሮ ድኅሪት (የፊጥኝ መታሰር)፣ ወዲቀ ዲበ ምድር (በመሬት ላይ መውደቅ)፣ ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በአይሁድ እግር መረገጡ)፣ ተስሕቦ በማዕከለ ዓምድ (ታንቆ መጎተት)፣ ተጸፍዖ መልታሕት (ፊትን መጥፊ መመታት)፣ ተኰርዖ ርእስ (የራስ መገመስ)፣ አክሊለ ሦክ (የእሾህ አክሊል)፣ ተዐርቆተ ልብስ (ርቃን መቆም)፣ ተቀሥፎ ዘባን (ጀርባን መገረፍ)፣ ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)፣ ተቀንዎ በቅንዋት (በችንካር መቸንከር)፣ ተሰቅሎ በዕፅ (መሰቀል) እና ሰሪበ ሐሞት (ሐሞት መጠጣት) ናቸው፡፡
13ቱ ሕማማተ መስቀል የሚባሉት እነዚህ ናቸው፡፡ ምነውሳ ወሪቀ ምራቅ፣ ጽርፈተ አይሁድና ርግዘተ ገቦ ከእነዚህ ውስጥ የማይቆጠሩ? ቢሉ እነዚህ ሦስቱ ከንዑሳን የሚቆጠሩ ናቸው እንጂ ከ13ቱ ገብተው አይቆጠሩም፡፡ ስለምን አይቆጠሩም? ቢሉ ወሪቀ ምራቅ የምራቅ መተፋት ነው፡፡ አይሁድም ጌታችንን ርኩስ ምራቃቸውን ተፍተውበታል ነገር ግን ሰውን ቢተፉበት ይጸየፈዋል እንጂ ምራቅ ሕማም ሆኖ አይገድልም፡፡ ስድብም ያናድዳል ያስቆጣል እንጂ ሕማም ሆኖ አይገድልምና ጽርፈተ አይሁድ አይቆጠርም፡፡ ርግዘተ ገቦ ማለት የጌታችን ጎኑ በጦር መወጋቱ ነው፡፡ ሰውን ከሞተ በኋላ ቢወጉት ሕማሙ አይሰማውምና ርግዘተ ገቦ አይቆጠርም፡፡
13ቱን ሕማማት እንዴት ነው የተፈጸሙ ቢሉ ክፉዎች አይሁድ መድኃኔዓለምን ሊይዙት የጦር መሣሪያቸውን ሰብስበው የታጠቁ 300 ጭፍራዎችን አስከትለው ወደ ጌቴሴማኒ በመጡ ጊዜ ‹‹ማንን ትፈለጋላችሁ?›› ቢላቸው ‹‹የናዝሬቱን ኢየሱስን እንፈልጋለን›› ሲሉት ‹‹እኔ ነኝ›› ቢላቸው ከአንደበቱ የወጣውን መለኮታዊ ቃል ብቻ መቋቋም አቅቷቸው መሬት ላይ ወድቀው ተዘርረዋል፡፡ ይህም ክስተት ለሦስት ጊዜ ያህል በተደጋጋሚ ተከስቷል፡፡ ዮሐ 18፡1-14፡፡ የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ መሆኑንና የትዕግሥቱን ብዛት አይተን እናደንቅ ዘንድ ከመጻሕፍት ጠቅሰን እንነግራችኋለን፡፡ አይሁድ ጌታችን አብርሃም ሳይወለድ በፊት እርሱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን አምላክ መሆኑን ቢነግራቸው ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፡፡ እሱ ግን ጊዜው ገና ነበርና ተሰውሮአቸው በመካከላቸው አልፎ ሲሄድ በፍጹም አላዩትም ነበር፡፡ በቅዱስ ወንጌል ላይ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- ‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። አይሁድም:- ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ኢየሱስም:- እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ፡፡›› ዮሐ 8፡56-59፡፡ የጌታችን ሞቱ በፍጹም ፈቃዱ ባይሆን ኖሮ በጌቴሴማኒ ሊይዙት የመጡት ክፉዎች አይሁድን እንደመጀመሪያው ሁሉ በተሠወራቸው ነበር አሊያም ከአንደበቱ በሚወጣው አምላካዊ ቃሉ ብቻ በፊቱ እንዳይቆሙ አድርጎ ባጠፋቸው ነበር፡፡ ጌታችን ግን ወደዚህች ምድር የመጣበትን ዓላማ ይፈጽም ዘንድ እንዲገድሉት በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ቢሰጣቸው ያን ሁሉ እጅግ አሠቃቂ መከራ አደረሱበትና ለመስቀል ሞት አበቁት፡፡
ወዮ ለዚህ ለመድኃኒዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል! ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደሌባ ተያዘ፤ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድኃኔዓለም እርሱ ሊፈረድበት በፍርድ አደባባይ ቆመ፤ በእስራት ያሉትን የሚፈታ እርሱ በብረት ችንካር ተቸነከረ፤ ሰማይን በከዋክብት ምድርም በአበባ ያስጌጠ እርሱ ግን የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፋ፤ ዓለሙን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብ እርሱ ተጠማሁ አለ፡፡ ወዮ የመድኃኔዓለም የማዳኑ ምሥጢር ምንኛ ድንቅ ነው!!! ይህንን ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
የሕማማቱን ነገር ወደመፈጸም እንመለስ፡፡ ጌታችን 300 የታጠቀ ሠራዊት አስከትለው ሊይዙት የመጡትን አይሁድን በፊቱ ሦስት ጊዜ በጣላቸው ሰዓት በመጀመሪያው በልባቸው ጥሎ ገሃነመ እሳትን አሳይቷቸዋል፤ በሁለተኛው በጀርባቸው ጥሎ መንግሥተ ሰማያትን አሳይቷቸዋል፡፡ በሦስተኛው ደግሞ ፈረስ በቅሎዎቻቸውን ከላይ አይሁድን ከሥር አድርጎ ፊታቸውን ከኋላ ኋላቸውን ከፊት፣ ቀኛቸውን ግራ ግራቸውን ቀኝ አድርጎ በማሳየት ሁሉን ማድረግ የሚችል የባሕርይ አምላክ መሆኑን በተግባር አሳይቷቸዋል፡፡
እነርሱ ግን አንድ ጊዜ ሰይጣን በልባቸው አድሯልና ወደ ህሊናቸው መመለስ አልቻሉም፡፡ እነርሱም ‹‹እኛ ታዘን ነውና የመጣነው እባክህ ጌታ ሆይ! በፈቃድህ ተያዝልን›› ብለው ለመኑት፡፡ ሁሉ በእጁ የተያዘ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያንጊዜ ራሱን አሳለፎ ሰጣቸው፡፡
1ኛ. #ተዓሥሮ_ድኅሪት፡- አይሁድም ከዚህ በኋላ የጌታችንን መጋፊያና መጋፊያው እስኪጋጠም ድረስ የፊጥኝ ረግጠው ካሠሩት በኋላ አፍንጫውን 25 ጊዜ ቢመቱት ደሙ በመሬት ላይ እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ አሥረውም ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፈ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ዮሐ 18፡12፡፡ ይህም ለአርአያ እና ለቤዛነት ነው፡፡ ቤዛነቱ አዳምንና ሔዋንን አጋንንት ገሃነመ እሳት አውርደው በእሳት ሰንሰለት የፊጥኝና የግርግሪት አሥረው ሲያሠቃዩአቸው ነበርና እነርሱንና የሰውን ልጅ በሙሉ ለማዳን ነው፡፡ አርአያነቱ በእኔ ምክንያት ያስሯችኋል ነገር ግን በፍቅሬ ታስራችሁ ኑሩ፣ መከራን ተቀበሉት እንጂ አተሰቀቁ ሲል ነው፡፡
2ኛ. #ወዲቀ_ዲበ_ምድር፡- ክፉዎች አይሁድ ጌታችንን ካሠሩት በኋላ ከጌቴሴማኒ እስከ ሐና ቤት ድረስ 65 ጊዜ በምድር ላይ ጥለውታል፡፡ የራስ ጠጉሩንም እየያዙ እያንጠለጠሉ 25 ጊዜ እያነሡ ጥለውታል፡፡
3ኛ. #ተከይዶ_በእግረ_አይሁድ፡- አይሁድ አሥረው እየጎተቱ ሲወስዱት የፊተኞቹ ሲስቡት የኋለኞቹ ይለቁታል ያንጊዜም በልቡ ሲወድቅ ከኋላ ያሉት ፈረሳቸውን በቅሏቸውን በላዩ ይነዱበታል፡፡ የኋለኞቹ ሲስቡት የፊተኞቹ ይለቁታል በጀርባው ይወድቃል፡፡ ቀድመውት የሄዱትም ‹‹…ወዴት ሄደ? አመለጠን?...›› እያሉ በመዘበት ተመልሰው በልቡ ላይ ይሄዱበታል፡፡ እንዲህ እያደረጉ 65 ጊዜ ከመሬት ጋር አጋጭተውታል፡፡ ሳውልም በዚያ ጊዜ ከእነርሱ ጋር ነበርና ጌታችን ‹‹መመለስህ ላይቀር ለምን ትረግጠኛለህ?›› ቢለው ትንቢት ተናገረብኝ ብሎ ሳውል 440 ጊዜ አስገረፈው፡፡ ዳግመኛም በጅንፎ በትር 62 ጊዜ መቱት፤ በአለንጋ 62 ጊዜ ገረፉት፤ አፉንና አፍንጫውን ደሙ እስኪወርድ ድረስ 40 ጊዜ መቱተ፤ የእጆቹ ጣቶች እስኪደቁ ድረስ 42 ጊዜ መቱት፡፡
4ኛ. #ተስሕቦ_በማዕከለ_ዓምድ፡- ይኽም ጉሮሮን ታንቆ እንደውሻ መጎተት ማለት ነው፡፡ ጌታችንን አይሁድ ጉሮሮውን በብረት ሰንሰለት አጥብቀው አሥረው ደም እስኪነስረው ዐይኑ ሊፈርጥ እስኪደርስ ድረስ 27 ጊዜ በጡጫ መቱት፡፡ በሁለት ታላላቅ ግንዶች መሐል አግብተው አንገቱን የታሠረበት ከግንዶቹ ጋር በማሠር የፊተኞቹ ሲስቡት የኋለኞቹ ይለቁታል በፊቱ ያለው ግንድ ልቡን ደረቱን ፊቱን ይመታዋል፤ የኋለኞቹ ሲስቡት የፊተኞቹ ይለቁታል የኋላው ግንድ ወገቡን ራሱን ይመታዋል፡፡ እንዲህ እያደረጉ 62 ጊዜ ከግንዱ ጋር አጋጩት፡፡

5ኛ. #ተጸፍዖ_መልታሕት፡- ሊቀ ካህናቱ ሐና ወደ ቀያፋ በላከው ጊዜ ቀያፋም ‹‹‹አምላክ ነኝ ከሰማይ ወርጃለሁ› የምትል አንተ ነህን?...›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ጌታችንም ‹‹አምላነቴን እኔ ብቻ የምናገረው አይደለም አንተም ደግሞ ራስህ ተናገርኽ እንጂ›› አለው፡፡ ማቴ 27፡11፡፡ ቀያፋም ሎሌዎቹን ‹‹ተቀምጣችሁ አታሰድቡኝ›› ብሎ በመቆጣት ልብሱን ቀደደ፡፡ እነርሱም ይህን ጊዜ ጌታችንን ፊቱን በጥፊ መቱት፡፡ ዮሐ 18፡22፡፡ እጃቸውን ቢደክማቸው ድንጋይ ጨብጠው አጥንቱ እስኪደቅ ድረስ በድንጋይ ጥፊ 120 ጊዜ ፊቱን ጸፉት፡፡
6ኛ. #ተኰርዖ_ርእስ፡- አይሁድ ጌታችንን ‹‹ኃላፊያቱን መጻኢያቱን አውቃለሁ ትላለህ…›› እያሉ በመዘበት ፊቱን እየመቱ ራሱን እየገመሱ ‹‹የመታህ ማነው?›› ይሉት ነበር፡፡ ማቴ 26፡67፣ ሉቃ 22፡63፡፡ ዳግመኛም አክሊለ ሦኩን ለማድረግ እንዲያመቻቸው የራስ ፀጉሩን 25 ጊዜ ነጩት፡፡
7ኛ. #አክሊለ_ሦክ፡- እነሆ ክፉዎች አይሁድ ሰይጣን በልባቸው ነግሦ ክፋትን ብቻ እንዲያስቡ አድርጓቸዋልና ስቁረት ያለበት እንደ ወረንጦና እንደ ወስፌ እንደ መርፌም ያለ 300 እሾህ ያለው ስረወጽ አድርገው የብረት አክሊል ሠርተው ከፍላት አግብተው በጉጠት አንሥተው ‹‹ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ነህ ዘውድ ይገባሃል› ብለው ያ ሁሉ እስኪገባ ድረስ በራሱ ላይ መቱበት፡፡ ለአክሊለ ሦኩም 73 ስቁረት ነበረው፡፡ ዳግመኛም እራሳቸው እንደ መሮ፣ ወርዳቸው እንደ ሞረድ 4 ማዕዘን አሠርተው ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸውን እንደ ወስፌ እንደ መርፌ አድርገው 73 ችንካር ሠርተው በዚያ በአክሊሉ 73 ስቁረት አግብተው ያ ሁሉ እስኪገባ ድረስ በራሱ ላይ ቢመቱበት ሥጋ ለሥጋ ገብቶ በአንገቱ ወርዶ መሐል ልቡን ወጋው፡፡ አክሊሉንም እንዳሸከሙት ጲላጦስ እንዲመረምረው ከቤት ወደ አደባባይ 3 ጊዜ አመላለሱት፡፡ በ4ኛው ከአደባባይ አኑረው ‹‹ንጉሥ ሆይ!...›› እያሉ ርኩስ ምራቃቸውን እየተፉበት ተዘባበቱበት፡፡ እየሰገዱ ሲነሡ በፊቱ ተፍተውበት ይነሣሉ፡፡ ጀርባውንም በዘንግ ይመቱት ነበር፡፡
8ኛ. #ተዐርቆተ_ልብስ፡- አይሁድ ‹‹ስቃዩን አበዛነው አሁን ደግሞ አፍሮ ደንግጦ ይሞታል›› ብለው በሰው ሁሉ መካከል ራቁቱን አቁመውታል፡፡
9ኛ. #ተቀሥፎ_ዘባን፡- አይሁድ ጲላጦስን ‹‹…ኃይለኛ በደለኛ ሰው ይዘናል ጉባኤ ሥራልን›› አሉት፡፡ ጲላጦስም በጠዋት ጉባኤ ሠራላቸው፡፡ ክፉዎች አይሁድም ጌታችንን ‹‹በቃሉ ሐሰት በሰውነቱ ክፋት የለበትምና ጲላጦስ ይህን ተመራምሮ በነፃ ቢለቀውና ባይፈርድነበት ሀዘናችን ይበዛል በኋላ እንዳይቆጨን›› ብለው አስቀድመው 305 ጊዜ በሽመል ደበደቡት፡፡ በባሕርይ አምላክነቱ ቻለው እንጂ አንዱ ብቻ በገደለው ነበር፡፡
እያዳፉም ወስደው ጲላጦስ ፊት ካቆሙት በኋላ ‹‹ኃይለኛ በደለኛ ነውና ስቀለው›› አሉት፡፡ ጲላጦስም ‹‹በምን በደሉ ልስቀለው? በደሉን ንገሩኝ?›. አላቸው፡፡ አይሁድም ‹‹ሰንበትን ሻረ፣ የሰሎሞንን ቤተ መቅደስ አፈርሱት በ3ኛ ቀን እሠራዋለሁ አለ፣ ራሱን አምላክ አደረገ›› የሚሉ ሦስት ክሶችን አቀረቡ፡፡ ዮሐ 9፡16፣ 13፡29፣ 18፡30፣ ኩፋ 34፡13፣ ሉቃ 23፡1-10፣ ማር 15፡3፣ 19፡10፡፡ የአይሁድን ክፋት ማሸነፍ የማይሆንለት ሆኖ ነው እንጂ ጲላጦስ ጌታችንን ለማዳን ብዙ ለፍቶ ነበር፡፡ በሕጋቸው መሠረት የሚሰቀል አይገረፍም፣ የሚገረፍም አይሰቀልም ነበርና ጲላጦስ ‹‹ገርፋችሁ ልቀቁት›› አላቸው፡፡ አይሁድንም ዳግመኛ ‹‹ሕጋችሁ ስንት ይገረፍ ትላለች?›› ቢላቸው እነርሱም ‹‹…41 ይገረፍ ይላል ነገር ግን ለእርሱ አይበቃውም›› አሉት፡፡ ጲላጦስም ‹‹ለእርሱ ስትሉ ሕጋችሁን ትተላለፋላችሁን? በሉ እንደሕጋችሁ ብቻ ገርፋችሁ ልቀቁት፣ ከቁጥር አብልጣችሁ ብትገርፉት ግን ከደሙ ንጹሕ ነኝ›› ብሎ በፊታቸው ታጠበ፡፡ አይሁድም ‹‹ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን›› በማለት በራሳቸው ላይ ርግማን ስላወጁ ዛሬም ድረስ ወንድ ቢወልዱ ልጁ ደም ጨብጦ ይወለዳል፣ ሴት ቢወልዱ ልጅቱ ያለድንግልና ትወለዳለች፡፡
ርጉማን አይሁድ ጌታችንን ከጲላጦስ ተረክበው ከወሰዱት በኋላ አዝማሪ አስመጥተው ጌታችንን እያሰደቡት 80 ጊዜ ፂሙን ነጭተውታል፡፡ መከራውን ሲያጸኑበት አድረዋልና ደሙ እንደ ውሃ ጎርፍ ፈሷል፣ ሥጋው እየተላጠ መሬት ላይ ወድቋል፡፡ ክፉዎች አይሁድ ‹‹አሠቃቂ ግርፋትን ሲገረፍ ያየነው እንደሆነ ልባችን ሊራራ ይችላል›› ብለው ሰንጠረዥ ገበጣ ሠርተው ሲጫወቱ አንዱ ተነሥቶ 50 እና 60 ድረስ ይገርፍና ሲደክመው ‹‹ቆጠራችሁን?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡ ሌሎቹም ‹‹አልቆጠርንም›› ሲሉት ከድካሙ የተነሣ ‹‹እኔው ልግረፍ እንደገና እኔው ልቁጠር›› ብሎ ትቶት ሲቀመጥ ሌላኛው ይነሣና እንደመጀመሪያው ገራፊ ሁሉ በተራው እንደገና አንድ ብሎ ጀምሮ 50 እና 60 ይገርፈዋል፡፡ ሁሉም እንዲህ እያሳሳቱ የራሳቸውን ሕግ እየተላለፉ አይሁድ ጌታችንን ሥጋው አልቆ አጥንቱ እንደበረዶ ነጭ ሆኖ እስኪታይ ድረስ 6666 ጊዜ ጽኑ ግርፋትን ገረፉት፡፡ በእነዚህ ሁሉ ግርፋቱ ወቅት 366 ጊዜ ሥጋው ተቆርሶ መሬት ላይ ወድቋል፡፡ ሥጋው እየተቆረሰ ከምድር የወደቀው 76 ነው፡፡ ያበጠውና የበለዘው ግን የሚቆጠር አይደለም፡፡ ስፍር ቁጥርም የለውም፡፡
10ኛ. #ፀዊረ_መስቀል፡- ጌታችንን አይሁድ የዕንጨት መስቀል አሸክመው ከሊቶስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ እያዳፉ ሲወስዱት 136 ጊዜ በምድር ላይ ጥለውታል፡፡ ከኋላ ያሉት ‹‹ፍጠን›› እያሉ ገፍትረው ይጥሉታል፣ ከፊት ያሉት ደግሞ ‹‹ምን ያስቸኩልሃል?›› እያሉ መልሰው ገፍትረው ይጥሉታል፡፡ እንዲህ እያደረጉ መስቀል አሸክመው እያዳፉ ቀራንዮ አድርሰውታል፡፡
11ኛ. #ተቀንዎ_በቅንዋት፡- ቀራንዮ ካደረሱት በኋላ አይሁድ ቁመታቸው ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸው እንደ ወስፌ እንደ መርፌ ያሉ፣ ወርዳቸው እንደሞረድ የሆኑ፣ 4 ማዕዘን የሆኑ ራሳቸው እንደ መሮ ያሉ 5 ታላላቅ ችንካሮችን ሠርተው ሳዶር በሚባለው ችንካር ቀኝ እጁን፣ በአላዶር ግራ እጁን፣ በዳናት ሁለት እግሮቹን፣ በአዴራ መሐል ልቡንና በሮዳስ ደረቱን ቸንክረው የአዳም ራስ ቅል ባለበት ቀራኒዮ አደባባይ ላይ ሰቅለውታል፡፡
12ኛ. #ተሰቅሎ_በዕፅ፡- መስቀሉን በሥሩ ተክለው ጊዜ ቀትር ሲሆን ጌታችንን ቢሰቅሉት ሥጋው በግርፋት አልቆ ነበርና የጎኑ አጥንት ተተረተረ፡፡ አይሁድም ‹‹የጎኑ አጥንት ስንት ነው? እስኪ ቁጠሩት…›› እያሉ ተዘባበቱበት፡፡ ይኽም በነቢዩ ቅዱስ ዳዊት ‹‹አጥንቶቼ ሁሉ ተቆጠሩ›› (መዝ 21፡17) ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ ጌታችን ከምድር ከፍ ከሰማይ ዝቅ ብሎ በ7 ክንድ ከስንዝር መስቀል ላይ በጊዜ ቀትር ተሰቅሎ 7ቱን መስተፃርራን አስታረቃቸው፡፡ እነዚህም 7 መስተፃርራን እግዚአብሔርና ሰው፣ ሰውና መላእክት፣ ነፍሥና ሥጋ፣ ሰማይና ምድር፣ ሕዝብና አሕዛብ ናቸው፡፡ በቀራንዮ አደባባይ ላይ በገበያ ቀን በተሰቀለም ጊዜ አይሁድ ሲያልፉ ሲያገድሙ ‹‹…ከወንበዴዎች ጋር የተሰቀለው ያ ‹አምላክ ነኝ ከሰማይ ወርጃለሁ› ብሎ ይናገር የነበረው አይደለምን? ታዲያ ምነው ተሰቀለ!?…›› ብለው ስቀው አንገታቸውን ነቅንቀው ያልፋሉ፡፡ ቅዱስ ዳዊት ‹‹እኔም በእነርሱ ዘንድ ለነውር ሆንኩ፣ ባዩኝ ጊዜ ራሳቸውን ነቀነቁ›› ብሎ ትንቢት እንደተናገረ፡፡ መዝ 108፡25፡፡ ነገር ግን ‹‹የጌታችን ርቃን አናሳይም›› ብለው ፀሐይ ጨለመች፣ ጨረቃም ደም ሆነች፣ ከዋክብትም ረገፉ፡፡