(ኢኮባ ነሐሴ 16 ቀን 2015 ኣ.ም)፡- ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በመንግስት የተሾሙት ም/ዋና ዳይሬክተሮች ከተቋሙ አመራሮች ጋር ትውውቅ አካሄዱ
ኢ/ር ደረጀ አረጋኸኝ የግንባታዎች ቁጥጥር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር፤ ዶ/ር ሙአዝ በድሩ የምዝገባና ሰርተፍኬሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ሆነው በመንግስት በቅርቡ ተሾመዋል፡፡
አመራሮቹ ነሐሴ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ከተቋሙ አመራሮች ጋር የትውውቅ ፕሮግራም አካሂደዋል፡፡ የባለስልጣን ተቋሙ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዓላማዎች እና ተግባራት እንዲሁም የተቋሙ የመካከለኛ ዘመን ስትራተጅክ ዕቅድ
ላይም ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
በተጨማሪም የ2015 ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2016 በጀት ኣመት ዕቅድ ላይም ማብራሪያ ቀርቧል፡፡ የትውውቅ ፕሮግራም እና ማብራሪያውን ተከትሎ አመራሮቹ ተቋሙ እስካሁን ያስመዘገባቸውን ስኬታማ ውጤቶች በላቀ ሁኔታ አጠናክሮ ለማስቀጠል፤ የነበሩ ክፍተቶችንም ለማረም ከተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች ጋር በትጋት እና በቁርጠኝነት ርብርብ እንደሚደረግ መናገራቸውን ከዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት የተገኘ መረጃ አመላክቷል፡፡
የኢኮባ ህዝብግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ ፡- https://www.facebook.com/oficialpageofECA/
ቴሌግራም፡- https://t.me/Ethiopiaconstructionaouthority
ዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/channel/UCUJNzKAbrJzNV9w3rJwc4tg
Ethiopian construction authority
ዌብሳይት፡- www.eca.gov.et

(ኢኮባ ነሐሴ 16 ቀን 2015 ኣ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን( ኢኮባ) አመራሮችና ሰራተኞች ነሐሴ 17 ቀን 2015 ዓ.ም የዛፍ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሂደዋል፡፡
በየካ ክ/ከተማ ሚሊኒየም ፓርክ ላይ በተካሄደው ፕሮግራም ላይ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች 1500( አንድ ሺህ አምስት መቶ የዛፍ ችግኞችን ተክለዋል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ ባስተላላፉት መልዕክት የዕለቱ ክንውን በሀገር አቀፍ ደረጃ "ነገን ዛሬ እንትከል"በሚል መርህ ኢትዮጵያን በአረንጓዴ እፅዋት የማልበስ ታላቅ ሀገራዊ ተልዕኮ አካል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በምስራቁ እና በምዕራቡ ዓለም በሚገኙ ሀገሮች ላይ የተከሰቱት ሰሞነኛ የተፈጥሮ አደጋዎችን በዋቤነት የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ ዋነኛው መንስዔው ከአየር ንብረት መዛባት ጋር የተያያዘ መሆኑንም አውስተዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ ያለው የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻም በኣለም ደረጃ ስጋት እየሆነ የመጣውን የአየር ንብረት መዛባትና ይህንኑ ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ የአደጋ ስጋቶችን በማስወገድ ረገድ የኢትዮጵያን ሚና ከፍ የሚያደርገው እንደሆነም ኢ/ር መስፍን ነገዎ ገልፀዋል፡፡
በተቋም ደረጃ ለአምስተኛ ጊዜ በመርሃ ግብሩ ተሳትፎ መደረጉን አውስተው ይህን ቅዱስ አላማ ባህል በማድረግ ለትውልድ ማሸጋገር ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ መንግስት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን( ኢኮባ) ም/ዋና ዳይሬክተሮች አድርጎ በቅርቡ የሾማቸው አመራሮች ከሰራተኛው ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡
ኢ/ር ደረጀ አረጋኸኝ በኢኮባ የግንባታዎች ቁጥጥር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር፤ ዶ/ር ሙአዝ በድሩ በኢኮባ የምዝገባና ሰርተፍኬሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር በመሆን መሾ ማቸው ይታወቃል፡፡

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.