ኢትዮጵያ ታበጽዕ እደዊሃ ሐበ እግዚአብሔር
933 subscribers
4.42K photos
116 videos
530 files
66 links
✝️✝️
ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ÷ይህ ስለ ኦርቶዶክሳዊት ሀይማኖትና አስተምህሮ ሀሳብ የምንለዋወጥበት ቤት ነው።
✍️በዚህ ቻናል👉 ወረብ፣ሀይማኖታዊ መፃሀፍቶች÷ ዜማ÷ ቅዳሴ ÷ መዝሙሮች ÷ መንፈሳዊ ፎቶግራፍና ሌሎችም የተለያዩ የምትፈልጉትን መረጃ በጠየቁበት ፍጥነት እናደርሳለን።
ሀሳብ፣አስተያየት እንዲሁም ጥያቄዎች ካሉበት ያናግሩን
👉👉👉 @Ethiopia_Orthodox_tewahdo_bot
Download Telegram
አልተለወጠምና“ በማለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞቱና ከትንሣኤው አስቀድሞ በውኃ ላይ እንደተራመደ ሁሉ፣ በለበሰው ሥጋ ወደ ሰማይ ማረግም እንደሚቻለው አስረድቷል ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈወርቅ፣ ክፍል ፲፫ ምዕ ፥፹፯፡፲፪-፲፫/። ቅዱስ ሉቃስም “እያዩት ከፍ ከፍ አለ” ማለቱ በእርግጥ ዕርገቱ በአካል እንደነበር ያስረግጥልናል፤ ምክንያቱም ሰው መለኮትን መመልከት አይችልምና ።

ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ስለ ጌታችን ዕርገት “በደብረ ዘይት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሲመገብ እጁን በደቀ መዛሙርቱ ላይ አኖረ፤ እያንዳንዳቸውንም ባረካቸው ከዚያም የእሳት ደመና ተቀበለው፤ ከእነርሱም ሰወረው፤ በጨርቅ የጠቀለሉት ይህ ሥጋ በኪሩቤል ክንፎች ተጋረደ፤ በጒልበት ያቀፉት ይህ ሥጋ በእሳት ሠረገላ ተቀመጠ፤ በዚህ ዓለም የተራበና የተጠማ ይህ ሥጋ እህል መብላት፤ ወይን መጠጥን ውሃም መጠጣት ወደ ማይሻበት ወደ አርያም ከፍታ ወጣ፤ በሊቀ ካህናቱ አገልጋዮችና በጲላጦስ አደባባይ ራቁቱን የቆመ ይህ ሥጋ በምስጋና መብረቅ ተሸፈነ፤ በእሳት ደመናም ተጋረደ፤ ጉንጮቹን በጥፊ የተመታ ይህ ሥጋ ከፍ ከፍ አለ" ብሏል።

ቅዱስ ማርቆስ የጌታችንን ዕርገት በገለጸበት አንቀጽ “ጌታችን ኢየሱስም ከተነጋገራቸዉ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፥ በአባቱም በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፡፡” (ማር. ፲፮፡፲፱) ብሏል፡፡ “ወደ ሰማይ” የሚለው ቃል ወደ ሰማየ ሰማያት ማለት ነው :: ይህም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በሚሠራበት ወቅት በጸለየው ጸሎት ውስጥ እግዚአብሔርን “በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ!” (፩ኛ ነገ. ፰፡፪፯) ብሎ በጸለየው ይታወቃል። “ዐረገ” የሚለውም ( መላእክት አሳረጉት አላለም በራሱ ኃይል ሥልጣንና ማረጉን ያሳያል፡፡ ከጌታችን በቀር በራሱ ኃይል ያረገ የለም፡፡ ሌሎች ቅዱሳን፡ ለምሳሌ ኤልያስ እና ሄኖክም ቢሆኑ እግዚአብሔር ዐሳረጋቸው እንጂ በራሳቸው ስልጣን ዐላረጉም ።

ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ይህንን "የእግዚአብሔር ልጅ ግን ያለ መሰላል በሚንቦገቦግ የደመና ተን (ጉም) ዐረገ፤ መለኮቱ ይተጋለታልና ወደ አየራትም ነጥቆታልና፤ ነገደ መናብርት ሊያሳርጉት አልመጡም ርሱ ራሱ በመለኮቱ ኀይል አብን ተካክሎ በቀኝ በኩል ተቀመጠባቸው” ሲል ገልጾታል። ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግም ስለ ዕርገት በተናገረበት አንቀጽ ''በራሱ ሥልጣን ተነሣ፤ ርሱን ያስነሣው ማንም አይደለም፤ በሚያርግም ጊዜ ማንም ርሱን ያሳረገ አይደለም፤ ኤልያስን አስመልክቶ ዕርገቱ በጌታ አማካይነት የኾነ ነውና እንዲያርግ ያደረገው ጌታ ነው፤ ከዚኽም የተነሣ በሠረገላ እና በእሳት ፈረስ የከበረ ሥነ ሥርዐት ተደረገለት (፪ኛ ነገ ፳፥፲፩)፤ ምክንያቱም ወደ ዐረገበት ቦታ በራሱ ማረግ አይቻለውምና፤ የጌታችን ግን እንደተጻፈው ተለየ፤ ወደ ላይ ለመነሣት ምንም ዐይነት መንኲራኲር አላስፈለገውም፤ በአንድ ቦታ በተወሰነ ጊዜ የሚቀመጡት ሰው በአጋዥ መውጣት ያስፈልገዋል፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ ብቻ ነውና፤ የእግዚአብሔር ልጅ ግን ራሱ እግዚአብሔር ነውና መንኰራኵር አያስፈልገውም” በማለት የእርሱ ዕርገት በራሱ ስልጣን መሆኑን አብራርቶታል። በአብ ቀኝ ተቀመጠ።

ጌታችን በዕርገቱ በአብ ቀኝ ተቀመጠ” መባሉ ለእግዚኣብሔር ግራና ቀኝ ታችና ላይ ኖሮት ሳይሆን ወደ ቀደመ ክብሩ መመለሱን በስልጣን እኩል መሆናቸዉን የሚያስረዳ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ ፪፡፯ "ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰዉም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ዝቅ አደረገ። እንደ ሰዉም ሆኖ ራሱን አዋረደ” የሚለዉ ቃል ጌታችን በሥጋዌው ራሱን በፈቃዱ ዝቅ አደረገ እንጅ በክብር ከአብ ከመንፈስቅዱስ እንደማይለይ ያስረዳናል፡፡ በቤተክርስቲያን ኣስተምህሮ መሰረት በአብ ቀኝ ተቀመጠ ማለት በሥልጣን አንድ መሆንን ያሳያል፡፡ ስለዚህም ነቢዩ ዳንኤል በትንቢቱ በሌሊትም ራእይ አየሁ፤ እነሆም የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ፤ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘለዓለም ግዛት ነው፣ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።” (ዳን. ፯፡፲፫-፲፬) ሲል ተናግሯል። ስለዚህ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ቀኝ ተቀመጠ ስንል በክብር በልዕልና ከአብ ጋር እኩል ነው ማለታችን ነው። ይህም ከተዋሕዶ በፊት ደካማ፣ በደለኛ እና ውርደት ይስማማው የነበረው የእኛ ሥጋ ከተዋሕዶ በኋላ ጸጋን የሚያድል፣ እውነተኛ ፍርድን የሚያደርግ፣ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል ሥልጣን ያለው እውነተኛ ፈራጅ አምላክ እንደሆነ ለመግለጽ ነው እንጂ በመለኮቱስ ከአብ ሥልጣን ዝቅ ያለበት የዐይን ጥቅሻ ያህል ጊዜ እንኳ የለም። “ቀኝ” የሚለው ቃል ኃይልን ቅድስናን ወይም ክብርን የሚያመለክት ነው ። ኃይልን ከመግለፅ አኳያ ነቢየ እግዚኣብሔር ክቡር ዳዊት "የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች” (መዝ. ፩፲፯፡፲፭) ሲል ተናግሯል፡፡ ክብርም ከመግለጽ አኳያ
"ጻድቃንን በቀኙ ያቆማቸዋል" (ማቴ. ፳፭፡፴) እንላለን። ስለዚህም "የእግዚአብሔር ቀኝ ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ፣ ጽድቅ ፣ ክብር ማለት ነው። ይህም በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ ያህልም ያህልም የሚከተሉትን ማየት ይቻላል፡፡

ጌታ ጌታዬን፡ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው። (መዝ. ፻፱፡፻) ከእንግዲህ ወዲህ የሰውን ልጅ በኀይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይ ደመናም ሲመጣ ታዩታላችሁ አለው። (ማቴ ፳፮፥፳፬)

እነሆ፥ ሰማይ ተከፍቶ የሰው ልጅም በእግዚኣብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ። (ሐዋ ፯፡ ፶፮)

ኀጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ፣ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፡፡ (ዕብ ፩፡፫)

በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ (ዕብ ፰፡፩)

እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና፡፡ (ዕብ ፲፪፡፱) የጻድቃንን ዕርገት ያስገነዝብ ዘንድ ዐረገ።

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤው በተስፋ ለምንጠብቀው ትንሣኤያችን አርአያ እንደሆነው ዕርገቱም ለዕርገተ ነፍሳችን፣ መንግሥተ ሰማያትን ለመውረሳችን አርአያ ምሣሌ ነው። እግዚአብሔር ወልድ የጻድቃንን ዕርገት ያስገነዝብ ዘንድ ዐረገ። ከእኛ የተዋሐደዉን ሥጋ በዕርገቱ ከአባቱ ቀኝ በእግዚአብሔርነቱ አስቀመጠው። እንግዲህ በዕርገቱ የእኛን ሥጋ ከመላዕክት ሁሉ በላይ አክብሮ በሰማያት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስተካክሎ ካስቀመጠውማ እንደምን እኛን መንግሥተ ሰማያትን አያወርሰንም ሊባል ይችላል? (፩ተሰ. ፳፡፲፯) ክርስቲያኖች በሰማያት ስፍራ ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረን እንደምንቀመጥ የጌታችን ዕርገት ያረጋግጥልናል። የጌታችን ዕርገት ዓይነ ልቡናችንን እሱ ወደ አለባት መንግስተ ሰማያት ይመራል። ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ሲያስረዳ እንዲህ ሲል ይላል፡፡ "ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ በአለበት በላይ ያለውን ሹ፡፡ የላይኛውን አስቡ ፤ በምድር ያለውንም አይደለም። እናንተ ፈጽማችሁ ሞታችኋልና፤ ሕይወታችሁም ከክርስቶስ ጋራ በእግዚአብሔር ዘንድ የተሰወረች ናትና። ሕይወታችሁ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ ያንጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በፍጹም ክብር
ትገለጣላችሁ።" (ቆላ. ፫፡፩-፬) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዕርገቱ የተስፋ ቃል ኪዳን ሰጥቶ ነበር። ለምሳሌ “እኔ ብሄድ ይሻላችኋል፤ እኔ ካልሄድሁ ጰራቅሊጦስ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ከሄድሁ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ፡፡” (ዮሐ. ፲፮፡፲) ብሏል፡፡ እርሱ በአካል ስለሚለያቸው የሐዘን ሰሜት እንዳይሰማቸው የሚያጽናና መንፈስ እንደሚልክላቸው ከሞቱ አስቀድሞ አብ በስሜየሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል”(ዮሐ ፲፬፥፮) ብሎ ነግሯቸዋል። ከምድራዊ አስተሳሰብና ከስጋ መንፈስ እንዲላቀቁ እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ እናንተ ግን ኃይልን ከላይ እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ" ሉቃ ፳፬፥፵፱ ብሏቸዋል፡፡ ይህንን ተስፋ በማመን ጌታችን ሲያርግ ወደ ሰማይ ትኩር ብለዉ ይመለከቱ የነበሩት ደቀ መዛሙርት በሃምሳኛዉ ቀን መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸዋል። እኛም ዕርገቱን እያሰብን ዓይናችንን ወደ ሰማይ እናነሳለን። የራሳችንንም ዕርገት ተስፋ እያደረግን ልባችንን ወደ ሰማያዊዉ ህይወት ከፍ ከፍ እናደርጋለን። በክብር ያረገ አምላክ ከትንሣኤ ሙታን በኋላ ያለውን ዕርገታችንን የክብር ያድርግልን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

የእግዚአብሔር አብ ጸጋ የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት የቅድስተ ቅዱሳን የንጽሕተ ንጹሐን እመቤታችን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱስ ዕጸ መስቀሉ የቅዱስ በዓሉ የታላላቆቹ ቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት የቅዱሳኑ ሁሉ በረከት ረድኤት ጸሎት ምልጃ አይለየን፤
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር !!!


👇👇👇 👇👇👇
@ethiopia_orthodox_tewahdo
@ethiopia_orthodox_tewahdo
@ethiopia_orthodox_tewahdo
👆👆👆ይቀላቀሉ እና ያጋሩ👆👆👆
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
ሥርዓተ ነግሥ:-
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክዐ ሥላሴ፦
ሰላም ለጒርኤክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ: ብኡላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ: እመትትኃየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ: ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ስጋየ ጌሠ: ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
ኢይጽሕቅ ዘይመክሮ ወኢየኀሥሥ ዘይመክሮ: አልቦቱ ጥንት ወኢተፍጻሜት: ኢየኀልቅ መንግሥቱ ወአልቦ ዘይክል መዊዓ ኀይሉ: ወአልቦ ኁልቊ ለሠራዊተ መላእክት እለ ይትለአክዎ: አንተ ውእቱ አቡሃ ለጥበብ: ገባሬ ኲሉ ፍጥረት ወገባሪሃ ለሕግ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ነግሥ
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳሕል: እንበለ ባህቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
አመ ይነፍህ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክዐ ሚካኤል፦
ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ: ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ፀሃፈ: ሶበ እጼውእ ስመከ ከሢትየ አፈ: ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ: ለረዲኦትየ ነዓ ሠፊሐከ ክንፈ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ዓቢተነ በመድኃኒትከ: ጸግወነ ንጸውዕ ስመከ: ኖላዊነ ኄር ትጉሕ ዘኢትነውም ሰላመከ ሀበነ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
ሀበነ ሰላመከ ንጸውዕ ስመከ/፪/
ዘኢትነውም ትጉሕ "ኖላዊነ ኄር"/፪//፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክዐ ሚካኤል፦
ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተኃበለ: በእንተ ስጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበኃለ: ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ: ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ: በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ/፪/
"በብሂለ ኦሆ"/፪/ ፍጡነ አስምአኒ ቃለ/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
አመ ይነፍሕ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክዐ ሚካኤል፦
ሰላም ዕብል ለአስናኒከ ዘመንፈስ: ዘኢይረክቦን ጥረስ: ሚካኤል ረዳኢ ለእለ ውስተ ባሕር ወየብስ: እስመ ረሰይከ ካህነ ምሥዋኡ ክርስቶስ: መፍትው ሊተ ትተንብል ቀሲስ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ ምስሌሁ: ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ: ዮም ሰማያዊ በምድር አስተርአየ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ/፪/
ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ ስዕንኩ/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለእስትንፋስከ ቁሱላነ ነፍስ ለአጥዕዮ: ዘይነፍሕ ፄና አንህዮ: ሚካኤል ነዓ ኲናተከ በተረስዮ: ለገቢር ከመ ቀዳሚ ለአርዌ አመፃ ደርብዮ: እስመ ኢኃደገ እንከ ዘትካት እከዮ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
ወከሢቶ ረከበ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ: ወእከስተ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን: ወእፈውስ ሎሙ ለቁሱላነ ልብ: ወእሰምዮ ለባሕራን ኅሩየ: ዝኬ ዘተነግረ በመዋዕለ ትካት: ለ፳ኤል ኅብስተ መና ዘአውረደ በገዳም: ወርእየቱ ከመ ተቅጻ ወከመ አያያተ መዓር ጥዑም ፈድፋደ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
"ወከሢቶ ረከበ"/፪/ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ/፪/
ወእስብክ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን ወእስምዮ ለባሕራን ኅሩየ/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክዐ ሚካኤል፦
ሰላም ለአጻብኢከ መጽሐፈ እለ ለክዑ: ዕጒለ አባግዕ እምኖሎት በጊዜ ተመልዑ: ሚካኤል አንተ ለንጉሠ ነገሥት ካህነ ምሥዋኡ: አሣዕነ መድኃኒት ለእገርየ አጻብኢከ ይቅጽዑ: ከመ በፍናውየ የኀዝ ለሰላም ቅብዑ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
ቅዱሳት አጻብኢከ ለጽሒፈ መጽሐፍ እለ ተቀንያ: ወብጹዓት አዕይንቲከ ምስጢረ መለኮት ዘርእያ: ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
ምስጢረ መለኮት ዘርእያ አዕይንቲከ/፪/
ሚካኤል መልአክ መልአክ ወሐዋርያ ሚካኤል መልአክ/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክዐ ሚካኤል፦
አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክዕከ ኲሉ: ለለአሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ: ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ: ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኃ ሰማያት ዘላዕሉ: ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል: ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ: አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዓቢይ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
መልአከ ሰላምነ/፬/
ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል በእንቲአነ/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አንገርጋሪ
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ: ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ: ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ: ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አመላለስ
ወሪዶ እመስቀሉ/፪/
እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ/፬/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ/፪/
ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
እስመ ለዓለም፦
ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ: አዓርግ ሰማየ አቡየ ወአቡክሙ: ኀበ አምላኪየ ወአምላክክሙ: ዘንተ ይቤሎሙ ዓርገ ውስተ ሰማያት: ካዕበ ይመጽእ በዘዚአሁ ስብሐት: ሠርጎሙ ለሐዋርያት ብርሃኖሙ ለእለ ውስተ ጽልመት: መድኃኔ ነገሥት ክብሮሙ ለመላእክት ኖላዊሆሙ።

ዓዲ እስመ ለዓለም-
እምድኅረ ተንሥአ እሙታን ዓርገ ውስተ ሰማያት በስብሐት አምላከ ምሕረት: ወተቀብልዎ አዕላፋ አዕላፋት: ወሚካኤል ሊቀ መላእክት በንፍሐተ ቀርን እምኀበ እግዚአብሔር: ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር።


🇪🇹👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCmahlet👈                 
👉@EOTCmahlet👈
👉@EOTCmahlet👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹
        
🌼🌹🌹🌼🌹🌹🌹🌹🌼🌹🌼🌹🌼🌻🌼🌻🌹
እንኳን ለታላቁ ክቡር ልዑል አባታችን የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።
የሊቀ መላዕክቱ አባታችን በረከቱም ከኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አሜን።
🌼🌻🌻🌻🌹🌻🌹🌻🌼🌼🌹🌹🌹
መልካም በዓል
👇👇👇 👇👇👇
@ethiopia_orthodox_tewahdo
@ethiopia_orthodox_tewahdo
@ethiopia_orthodox_tewahdo
👆👆👆 ይቀላቀሉ እና ያጋሩ👆👆👆