"ኡማ ቲቪ " Tv
42.8K subscribers
28.5K photos
1.07K videos
13 files
4.82K links
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV38o3WF-YJ6jh
Download Telegram
ሳዑዲ (መካ መዲና) ይህን ሰሞን ሙቀት እየጨመረ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው ... እናም ሀጅ ሚመጡ ሰዎች ስለ አየር ሁኔታ ኢንፎርሜሽን ቢኖራቸው እና ስለ አለባበሳቸው ቢያስቡበት እና ቢዘጋጁበት መልካም ነው (እንዲሁም ቀደም ብለው ነፍስየን ዝግጁ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል) ፤ ሀጅ ሲቀርብ ደግሞ ሙቀት ከፍ ይላል ተብሎ ይጠበቃል ....
ግንቦት 13፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 13፣ 1445 ዓ.ሂ.
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአል-ረህማን እንግዶችን መዲነቱል ሙነወራ ይዞ ገባ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መዲና |

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሳፈሩት የ1445 ዓ.ሒ የመጀመሪያዎቹ የአል-ረህማን እንግዶች መዲነቱል ሙነወራ ገቡ።

ሐጃጆቹ መዲና አይሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፣
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ምክትል ሰብሳቢና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሸይኽ አብዱልሃሚድ አሕመድ እና የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ሸይኽ ዛኪር ኢብራሂም አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ መዲነቱል ሙነወራ የገቡት የአል-ረህማን እንግዶች 263 ሲኾኑ፣ ከእነዚህ ውስጥ 55 ያህል ሴቶች መሆናቸውን የአቀባበል አሥተባባሪው አቶ አብዲ ሲራጅ ተናግረዋል።

መዲነቱል ረሱል (ሶ.ዐ.ወ.) የገቡት ሐጃጆች በቆይታቸው ማድረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄ እና ስለ ጤናቸው ጉዳይ አስፈላጊ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

የ1445 ዓ.ሂ. የአል-ረህማን እንግዶች በመዲና በሚያደርጉት የሁለት ቀናት ቆይታ መስጂድ ቂብለተይንን፣ ኡሑድ ተራራን፣ በዚሁ ስፍራ ሸሂድ የሆኑትን የነሐምዛን ቀብር ይዘይራሉ።

በመጨረሻም በመስጂደል ነበዊ የሚገኘውን ረውዳ በቡድን ኾነው ከዘየሩ በኋላ፣ ወደ መካ እንደሚጓዙ ከመስተንግዶ ኮሚቴው ለማወቅ ተችሏል።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ዘንድሮ ሀጅ ለምትሄዱ!!
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያደረገው የተሳታፊ ልይታ የክልሉን ህዝበ ሙስሊም ያገለለ መሆኑ ተገለፀ!


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በፃፈው ደብዳቤ  ለሀገራዊ ምክክር በሚደረገዉ ሂደት የመጀመሪያ ዙር የምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ ስዎች ተለይተዉ ወደ ስራ እንደገቡ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በተሳታፊ ልይታ ወቅት ክልላችን አብዛኛው ህዝብ ሙስሊም መሆኑ እየታወቀ ሙስሊሙን ያገለለ እና የክልሉን እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትን ከግምት ውስጥ ባላስገባ መልኩ ምልመላ መካሂዱን አንስቷል።

ስለሆነም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ከጠቅላይ ም/ቤቱ የምንፈልገው ችግሩ ተወግዶ አሰራሩ ተሻሽሎ ከፍተኛ ምክር ቤቱ የሚሳተፉ ሰዎችን መልምሎ እንዲያቀርብና ሙስሊሙን የሚያሳትፍ ምክክር እንዲሆን በእናንተ በኩል ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሺን ጥያቄያችን እንዲቀርብልን እየጠየቅን አሰራሩ ሳይሻሻል ባለበት የክልላችን ሙስሊሙን ባገለለ መልኩ የሚቀጥል ከሆነ ለሀገራዊ ምክክሩ እዉቅና የማንስጥ መሆናችንንም ጭምር እንድታሳውቁልን በአክብሮት እንጠይቃለን ሲል ለጠቅላይ ምክር ቤቱ በፃፈው ደብዳቤ ላይ ገልጿል።
ሶስቱ ሀገራት ማለትም አየርላንድ፣ ኖርዌይ እና ስፔን ለፍልስጤም የግዛት እውቅና መስጠታችንን በይፋ አስታወቁ
...
ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሞን ሃሪስ በዳብሊን እየሰጡት ባለው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሶስቱ የአውሮፓ ሀገራት ለፍልስጤም እውቅና ለመስጠት ያደረጉትን ታሪካዊ ውሳኔ ይፋ አድርገዋል።

ሃሪስ በተጨማሪም ከሌሎች ሀገራት መሪዎች እና አቻዎቻቸው ጋር በዚህ ጉዳይ መነጋጋገራቸውን ጠቅሰው "በሚቀጥሉት ሳምንታት ተጨማሪ ሀገራት ተመሳሳይ ውሳኔ ላይ እንደሚደርሱ እርግጠኛ ነኝ" ብለዋል። ይህ ውሳኔ ለፍልስጤም ታሪካዊ ስኬት ተደርጎ እየተገለጸ ይገኛል።
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf
"ኡማ ቲቪ " Tv
Photo
«አንድነታችን ለሰላማችን በሚል መሪ ቃል በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኮምቦልቻ ከተማ ሀገር አቀፍ የአብሮነት የወንድማማችነት እና የሰላም ኮንፈረስ ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ!

ግንቦት 14/2016፣አዲስአበባ)
...
በፌዴራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነት የአንድነትና የሰላም መድረክ ከዚህ በፊት በባሌ በአዲስ አበባ እና በጂማ ከተማ በተለያዬ ቅርስና ቀለም የተደረገ ሲሆን ለአራተኛ ግዜ በአማራ ከልል በኮምቦልቻ ከተማ የሚካሄደዉ ዝግጅት የክልሉን ተጨባጭ ባገናዘበና ወቅቱን በዋጀ ዝግጅት በሰደቃ በዱአ እንዲሁም በዓሊሞች፣ በሙህራንና በወጣቶች በፓናል ውይይት የታጀበ ታሪካዊ ዝግጅት እንደሚሆን የፌደራል እና የአማራ ክልል መጅሊስ በዛሬው ዕለት በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
...
ከዚህ ቀደም በተደረጉ ዝግጅቶች የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን አብሮነት ከማስቀጠልና በተለያዬ ወቅት የላሉ ግንኙነቶችን በማጠናከር ፍፁም ወንድማማችነትን ያመጡና በጋራ የመስራት ውጤትን በተጨባጭ ያሳዩ እንደነበሩ አይዘነጋም። እንዲህ አይነት መድረኮች ከሀይማኖታዊና ማህበራዊ ፋይዳ በተጨማሪ ሀገራዊ ጥቅማቸው የነላ በመሆኑ የተገኙ ውጤቶችን ለማስጠበቅ የቀሩ ጉድለቶችን ለመሙላት አጋዥ ሁነው አግኝተናቸዋል።
...
በታሪክ አጋጣሚ ሀገራችን ኢትዮጵያ ብዝሐ ሐይማኖት እና ብዝሐ ብሔሮች በአንድ ላይ ተሰባሰበው የሚኖሩባት የጋራ ቤታችን መሆኗ ሁላችንም የሚያኮራ እና በባለቤትነት ስሜት የምንኖረው ፀጋችን ነው። በሀገር ግንባታ ሂደት የተለያ ብሄሮችና እምነቶች በመደጋገፍ የጋራ ጠላት በገጠማቸዉ ጊዜ አብረዉ በመቆም በጋራ ደማቸዉን አፍስሰዋል አጥንታቸዉን ከስከሰዉ የተሊያዩ እምነቶች በሰላምና በችግር ጊዜ አብረዉ በመቆም ለሀገር መጽናት ዉድ ዋጋ ከፍለዉ የጋ የሆነችን ሀገራችንን አስረከበዉናል፡፡

"እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም የዚህ ታሪክ ወራሽ በመሆናችን አባቶቻችን በከፈሉት ዋጋና ባስረከቡን ሁ ልጆቻቸዉ ኩራት ይሰማናል። ስለሆነም ዋጋ የተከፈለላት ሀገራችን መጭው ትውልድ ይህንን እሴት እንዲያስቀ ለማድረግ እንዲህ አይነቱ ሀገራዊ ዝግጅት ከየትኛውም ጫፍ ያለን በተቋሙ ጥላ ስር በማሰባሰብ የሀገር ፍቅር መዝ የሆነውን ሰላምና አንድነት እንሰብክበታለን።"
...
ዝግጅቱ ቅዳሜ ግንቦት 17/2016 እንግዶችን በመቀበልና ጥሪ በተደረገላቸው እንግዶች በፓናል ውይ የሚጀምር ሲሆን እሁድ ግንቦት 18 ቀን 2016 ህዝባዊ መድረኩ በድምቀት ይካሄዳል። በዝግጅቱ የፈዴራል መጣ ፕሬዝዳንት ከብር ዶክተር ሀጂ እብራሂም ቱፋና ስራ አስፈጻሚዎቻቸው፤ ኡለማዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊ አዲስ አበባ እና ድሬደዋ ከተማ መስተዳድርን ጨምሮ የሁሉም የክልል መጅሊስ ፕሬዝዳንቶች: ከተለያዩ የሃይ ተቋማት መሪዎች፥ ዱአቶች ኡስታዞች ሙህራኖች፤ ተፅእኖ ፈጣሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ህዝቦች ይሳተፉበታል ተብሏል። በተጨማሪም በዝግጅቱ ለአዲስ ፕሮጀከት በተጠየቁ ቦታዎች የመሰረት ድንጋይ እንደሚጣል ተገልጿል።
...
"ሙስሊም መስለው ተመሳስለው ኒቃብ ለብሰው እየገቡ ስለሆነ ላይብረሪ ለመግባት ኒቃብ ማውለቅ አለባችሁ"የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሰፈረ ሰላም ካምፖስ የላይብረሪ ሀላፊ


በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሰፈር ሰላም ካምፖስ ላይብረሪ ሀላፊ በሆነቸው አልማዝ ተስፋዬ በዛሬው ዕለት በተፃፈ ደብዳቤ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ኒቃባቸውን ካላወለቁ ላይብረሪ እንዳይገቡ መከልከሉ ተገለፀ።

በደብዳቤው ላይ እንደተገለፀው ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብ በመልበሳቸው ለመለየት እና ሌሎች የሙስሊም እምነት ተከታይ በመምሰል ወደላይብረሪው እየገቡ ስለሆነ ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብ ካላወለቁ ላይብረሪ እንዳይገቡ መከልከሉን ለሀሩን ሚድያ ገልፀዋል።

ተማሪዎቹ እንደገለፁት ከሆነ ከዚህ በፊትም በቃል ደረጃ ለመከልከል የላይብረሪው ሀላፊዎች መሞከራቸውን እና ሙስሊም ተማሪዎችን ሆን ብለው ከትምህርት ገበታ ለማፈናቀል የተደረገ ሴራ መሆኑን በማንሳት የሚመለከተው የመንግስት አካል አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf