#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ፖሊስ አንድን ወጣት አግተው 10 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።
አጋችና ታጋች የአንድ ወር ጓደኛሞች እንደነበሩም አሳውቋል።
የእገታ ወንጀል የተፈፀመበት ወጣት ልዑል መብራቱ ይባላል፡፡
ወጣቱ #በማህበራዊ_መገናኛ_አውታር (ማህበራዊ ሚዲያ) አማካኝነት ባንቴ ይድረስን የተባለውን ግለሰብ ይተዋወቃል፡፡
ትውውቃቸው አንድ ወር ከሞላ በኋላ ባንቴ ይድረስ የተባለው ወንጀል ፈፃሚ የወንድሜ ጓደኛ ቤት ላሳይህ በማለት ወጣቱን ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ/ም ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቁሊቲ መንደር 4 አካባቢ ይዞት ከሄደ በኋላ ከግብረ አበሩ ልዑል ጫላ ጋር በመሆን ያግቱታል፡፡
ወንጀል ፈፃሚዎች እጅግ ዘግናኝ ፊልሞችን እና ፎቶግራፎችን ለወላጆቹ በመላክ 10 ሚሊዩን ብር ካልተከፈላቸው ወጣቱን እንደሚገድሉት የማስፈራሪያ መልእክት ይልካሉ፡፡
የእገታ ወንጀል እንደተፈፀመ ሪፖርት የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ጋር ባደረጉት ክትትል ወንጀሉን በተፈፀመ በአራተኛው ቀን ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ወጣቱን ከእገታው ነፃ እንዳወጣው አሳውቋል።
ሁለቱ ግለሰቦች ወንጀሉን ለመፈፀም በ5ሺ ብር ቤት መከራየታቸውንና የታጋቹ ወጣት ወላጅ አባት ውጭ ሀገር ይኖራሉ በሚል መረጃ ወንጀሉን መፈፀማቸውን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።
ፖሊስ ፤ በልዩ ልዩ ምክንያት
በተለይ ሙሉ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች የተከራዮችን ማንነትና ለምን እንደተከራዩ ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስቧል። ይህን ሳያደርጉ በሚፈጠር ችግር የህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስጠንቅቋል።
መረጃው ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘ ነው።
ፎቶ፦ አዲስ አበባ ፖሊስ
@tikvahethiopia @ethiofreetech

👍1
✅ለፊልም አፍቃሪያን ከላይ የምታዩት አዲሱ አማርኛ ፊልም ነው። #የሱፍ_አበባ የተሰኘው
✅ ማወረድ ላልቻላችሁ ይጠቅማችኋል እዩት አሪፍ ፊልም ነው።
#share @ethiofreetech
✅ ማወረድ ላልቻላችሁ ይጠቅማችኋል እዩት አሪፍ ፊልም ነው።
#share @ethiofreetech
#AfricanDevelopmentBank
የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓለም አቀፍ ሰራተኞቹን በአስቸኳይ #ከኢትዮጵያ ሊያስወጣ ነው።
ባንኩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከአንድ ወር በፊት ዋና የኢትዮጵያ ተወካዩ እና ሌላ የባንኩ ሰራተኛ ላይ በፀጥታ አካላት ድብደባ መፈፀሙን ተከትሎ ነው።
በወቅቱ ባንኩ ቅሬታውን ለመንግስት አቅርቦ የነበረ ሲሆን መንግስትም አስቸኳይ ማጣራት አድርጎ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ ገልፆ ነበር።
አሁን ባንኩ ዓለም አቀፍ ሰራተኞቹን " በአስቸኳይ " ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ሊያደርግ የወሰነው ድብደባውን ፈፅመዋል በተባሉት የፀጥታ አካላት ዙርያ ስለተደረገው ምርመራ የኢትዮጵያ መንግስት ለባንኩ መረጃ ባለማጋራቱ እንዲሁም በሰራተኞቹ ዘንድ በደህንነታቸው ዙርያ ሙሉ እምነት ሊያገኝ ባለመቻሉ እንደሆነ የባንኩ ፕሬዝደንት ዶ/ር አኪንዉሚ አዴሲና አሳውቀዋል።
ምንም እንኳን ባንኩ ዓለም አቀፍ ሰራተኞቹን ከኢትዮጵያ በአስቸኳይ ለማስወጣት ውሳኔ ላይ ቢደርስም በኢትዮጵያ ያለው ቢሮው ክፍት ሆኖ እንደሚቆይና ውሳኔው ከኢትዮጵያ የተቀጠሩ ሰራተኞችን እንደማይመለከት ገልጿል።
እነዚህ ከኢትዮጵያ የተቀጠሩ ሰራተኞች በስራ ገበታቸው እንደሚቀጥሉና በባንኩ ሙሉ የስራ ስምሪት ውስጥ / የባንኩ ሰራተኞች ሆነው እንደሚቆዩ ማረጋገጫ ተሰጥቷል።
አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የባንኩ የኢትዮጵያ ቢሮ ሰራተኛ ከኢትዮጵያ ባስቸኳይ እንዲወጡ የሚደረጉት ዓለም አቀፍ ሰራተኖች ወደ ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ ሊዛወሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
እንደ ሬውተርስ ዘገባ የአፍሪካ ልማት ባንክ ኢትዮጵያ ውስጥ የ308 ሚልዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ስምንት ፕሮጀክቶች አሉት።
Credit - Journalist Elias Meseret