ኢትዮ ቴክኖሎጂ ( Ethio technology )
6.9K subscribers
2.19K photos
74 videos
101 files
1.28K links
✔️በቻናላችን✔️
📲 የAndroid መተግበሪያ
💻 የPC SoftWare
📌 አዲስ ለሆኑ የቴክኖሎጂ ምርቶች ልዩ ዘገባ

👉ለአስተያየትና ሌሎች ፕሮግራሞችን ለማግኘት ይቀላቀላሉ
Download Telegram
ኢትዮ ቴክኖሎጂ ( Ethio technology ) via @dooxbot
የበይነ - መረብ ንግድ (Online Business) ይህን ቻናል ከጀመርን ጀምሮ፤ በቢዝነስ ዙርያ ብዙ ምክረ - ሃሳቦችን እያጋራን ሰንብተናል። አብዛኛው ተደራሲም (የቻናላችን ቤተሰቦች) በመረጃዎቹ እየተጠቀሙ እና እየተማሩ መሆኑን በውስጥ መስመር እና በሃሳብ መስጫ (Comment Box) ሲያጋሩን ነበር። የተለያዩ ጥያቄዎች እየተጠየቁ ምላሽ በተናጠል ስንሰጥ ነበር። ነገር ግን ከአብዛኛው ቤተሰብ፤ አንድ…
🔸የበይነ - መረብ ንግድ (Online Business)

🎈ክፍል 2 (ከትላንቱ የቀጠለ)

▫️አሁን ወደ ተነሳንበት የበይነ - መረብ ንግድ (Online Business) እንመለስ። ከላይ ባብራራነው ጽንሰ ሃሳብ መሰረት የበይነ - መረብ ንግድ መጀመር እና ሌላ የገቢ ምንጭ መፍጠር ይቻላል። ነገር ግን ከዘልማዳዊው "ያበላል ወይስ አያበላም" አይነት ያልተጨበጠ ጥያቄ መውጣት እና መጠነኛ የገበያ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል።

፨ ምን ይፈለጋል? ህብረተሰቡ በጣም የሚፈልገው እና የጎደለው ነገር ምንድነው?

▫️ይህ ጥያቄ የትኛው ቢዝነስ ትርፋማ እንደሆነ በራሱ ጠቋሚ ነው። ይህን ጥያቄ ስትጠይቁ መልሱ፦

፨ ወይ ያ ህብረተሰቡ የሚፈልገው ነገር ጭራሽ የለም፤ አልተፈጠረም።

፨ ወይንም አለ፤ ነገር ግን ከፍተኛ እጥረት አለበት።

▫️ስለሆነም በነዚህ ስሌት መነሻነት አንድ ሰው ወይ ፈጣሪ (Innovator) ይሆናል። አልያም ያለን የጎደለን ነገር በማቅረብ በቀላሉ ወደ ንግዱ ይገባል ማለት ነው።

▫️ወደ Online business ስትገቡም በዚህ ጥያቄ መነሻነት ቢሆን መልካም ነው። መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር የግል ስራን መጀመር ቀላል እንዳልሆነ ነው። ቢዝነስ ሲባል ባጠቃላይ እስኪጠነክር እና እውቅናን አትርፎ ደንበኞችን እስኪይዝ ድረስ ውጣ ውረዶች አሉት ። የበይነ መረብ ንግድም ከዚህ አይለይም። ገበያው ላይ ሰርጎ ለመግባት የሚወስደው ጊዜ እና ትእግስት አለ። ይህን ከተረዳን እና ከተስማማን Online biz ለመስራት ( እንደ ስራው አይነት) የሚያስፈልጉ ቁሳቁስ አሉ። ስማርት ስልክ፣ ኢንተርኔት፣ ኮምፒውተር ፣ ካሜራ እና መሰል ኤሌክትሮኒክስ የሚያስፈልጉ ሲሆን ስማርት ስልክ እና ኢንተርኔት መሰረታዊ እቃዎች ናቸው።

▫️እነዚህን ቁሳቁስ በመጠቀም ልንሰራቸው የምንችላቸው የonline biz አይነቶች በብዛት አሉ። በውጩ አለም በዚህ መንገድ በጣም ብዙ የሚሰሩ ስራዎች ያሉ ሲሆን ወደኛ አገር ስንመጣ ግን በመንግስታዊ ህጎች መጥበቅ፣ አዳዲስ ፈጠራዎች ባለመኖራቸው እና የኢንተርኔት ተደራሽነቱም አናሳ በመሆኑ በበይነ መረቡ (online) ላይ የሚሰሩ ስራዎች ውስን ናቸው። የተወሰኑት እና ከእኛ ሀገር ህግና ገበያ ጋር የሚሄዱትን ከዚ ቀጥሎ ለማየት እንሞክራለን።

1⃣ Youtube ፕሮግራሞች ማዘጋጀት

▫️ይሄ በጣም ቀላል እና አለም ላይ በጣም ብዙ ሰዎች እየተጠቀሙበት ያለ አንድ የገቢ ምንጭ ነው። ሙሉ ስራው አለቃ እና አዛዥ ሳይኖርባችሁ በራሳችሁ ተነሳሽነት እና ፈጠራ ብቻ የምትሰሩት ስራ ነው። ዩቱብ አዘጋጅ ለመሆን ደሞ የሞባይል ስልካችሁ ካሜራና ኢንተርኔት በቂ ናቸው። በዚህ መነሳት እና ወደተሻለ ጥራት ማደግ ይቻላል። ነገር ግን ከስራችሁ ተጠቃሚ እና ትርፋማ ለመሆን የምታዘጋጇቸው ቪድዮዎች የሰውን ቀልብ የሚገዙና የሚወደዱ መሆን አለባቸው። ምክንያቱም ትርፋችሁ እና ገቢያችሁ የሚወሰነው ስራዎቻችሁን በሚያይላችሁ የሰው ብዛት ስለሆነ።

▫️አሁንም ከላይ እንደጠቀስነው በዚህም ስራ ትርፋማ ለመሆን "ሰው ምን ይፈልጋል?" የሚለው ጥያቄ ወሳኝ ነው። በዚህ መሰረት በየእለቱም ሆነ በየሳምንቱ ቪድዮዎችን በማዘጋጀትና በመልቀቅ አንድ የገቢ ምንጭ ማግኛት ይቻላል። የአከፋፈል ሁኔታውን፣ መጠኑን እና ትርፉን google በማድረግ ማወቅ ትችላላችሁ። ወይንም በዚህ ቻናላችን ወደፊት እንዳስሰው ይሆናል።

ጥቆማ፦

ኦንላይን ትምህርቶችን በዩቱብ ማዘጋጀት (እንደ ጊታር ማሰልጠን፣ የ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኞችን ማብቃት ወይ ገለጻ ማድረግ፣ ኤሌክትሮኒክስ ጥገና በቀላል አማርኛ፣ ቤት አጠጋገን እና ቀለም አቀባብ) ወዘተ...ህብረተሰቡ ራሱን ሊረዳባቸው እና ሊያሻሽልባቸው የሚችሉ እውቀቶችን ማካፈል፤ ማቅረብ፤


▫️ማሳሰቢያ፦ በተቻለ መጠን የጥላቻ ንግግሮችን እና ፖለቲካ አፍራሽ ነገሮች በመጠቀም ገቢ ለማግኘት አንጣር!!! ሃገር አፍርሶ ህዝብ አጋጭቶ የሚመጣ ገቢ ገደል መግቢያ ነው!

2⃣ Online ሱቆች

▫️እነዚህ አሁን ላይ እኛ ሃገር በጣም በብዛት እየተሰራበት ይገኛል። ብዙ ተቋማት እና ግለሰቦች በfacebook እና በቴሌግራም ግብይት መፈጸም ከጀመሩ ሰነባብቷል። እናንተም የራሳችሁ ቻናል እና facebook page በማዘጋጀት የራሳችሁ Online business ሊኖራችሁ እና ልትሰሩ ትችላላችሁ። ነገር ግን አሁንም " What's the demand in the market" ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። ምንም ነገር ውስጥ ዘው ብሎ መግባት ሩቅ መንገድ አያስኬድም። ብዙ ኦንላይ ቢዝነስ አለ፤ ታድያ እንዴት መስራት እችላለሁ? ስራው ተይዟል ካላችሁ እነዚህ ቢዝነሶች ገበያውን ሰብረው የገቡበት መንገድ ትምህርት ይሆነናል፦

📶 ሼባ ሰአቶች እና ጌጣጌጦች። የራሱን መልክ ፣ ስም እና ፈጠራ ይዞ ስለመጣ ከነበሩት እጅግ ብዙ ንግዶች ጎልቶ ወጥቷል።

📶 ጦማር መጻህፍት አቅራቢ። መጻህፍትን ( የጠፉትን ሳይቀር ) ለገዢዎች ቤታቸው ድረስ የሚያደርስ

📶 TIKVAH-Ethiopia። በጣም ብዙ የዜና እና የሚድያ ተቋማት ስራው ላይ ቆይተውበት እያለ ይህ የቴሌግራም ቻናል ግን አቀራረቡን በመቀየር እና በመርህ በመሄድ ስኬታማ ሆኗል።
ስልኮ እየተጠቀሙበት በመሃል መስራት ያቆማል? ለምን? መፍትሄውስ
Fix: Unfortunately, settings has stopped error ስልኮ ከተለመደዉ በላይ ይዘገያል ወይስ እንዲያ ከናካቴዉ አልሰራም ብሎ ቀጥ ብሎ ይቆማል፡፡

እንግዲህ ስልኮ በጣሙን የሚዘገይ አልያም አልታዘዝ ካሎት ስልኮ የሆነ ችግር ገጥሞታል ማለት ሲሆን ለዚህ አይነት ችግር መንስዔ የሚሆኑ መነሾዎችን ከነመፍትሄዎቻቸዉ ጋር
እንደሚከተሉት አቅርበንሎታልና ይተግብሯቸዉ፡፡

🔑 ከስልኮ ላይ የአላስፈላጊ አፕሊኬሽኖች መኖር ከስልኮ ላይ አላስፈላጊ አፕሊኬሽኖችን ያጥፉ፡፡
ስልኮ ላይ ብዙ አላስፈላጊ አፕሊኬሽኖች
🔸ለምሳሌ ጌሞች ፣ የፎቶ እና ቪዲዮ ማሳመሪያ (ኤዲትኢንግ) ሶፍትዌሮች የተለያዩ የሙዚቃም ይሁን የቪዲዮ ማጫወቻ(ፕሌየሮች) ስልኮ ላይ ካለ በተቻለ መጠን የሚፈልጉትን አፕሊኬሽን
ሶፍሮች ብቻ ትተዉ ሌላዉን በአብዛኛዉ
የማይጠቀሙባቸዉን አፕሊኬሽኖች ያጥፉ፡፡

🔑 የስልኮ ዳታ መያዣ(ስቶሬጅ) በፋይሎች መጨናነቅ በስልኮ ሜሞሪ ላይ ብዛት ያላቸዉ ሙዚቃዎች፣ ቪዲዮች፣ያልጫኑት ሶፍትዌር አፕሊኬሽኖች አስቀምጠዉ ከሆነ በተቻለ መጠን የማይፈልጉትን ቢያጠፉ አልያም ከቆይታ በኋላ ብፈልጋቸዉ አላገኛቸዉም ካሉ በሌላ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ቐት(ሜሞሪ) ያስቀምጡት፡፡

🔑የስልኮን ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና ስልክዎ ላይ ያለን ሶፍትዌር አለማደስ
ስልኮ ያሉትን ሶፍተዌሮች እና ስልኮን ያለማደስ ስልኮን ለሌላ ቫይረስ አልያም ጎጂ ሶፍትዌር ያጋልጣል ይህም የስልኮን ፐሮግራሞች ሳይዘጉ ከኋላ እንዲነሳ(background play) ስለሚያደርገዉ ስልኮንና የሚጠቀሙበትን ሶፍትዌር ያደሱት፡፡

🔑 ካች (Cache) ዳታን አለማፅዳት
ካች ዳታ የምንላዉ አብዛኛዉን ጊዜ
የምንጠቀምባቸዉን ሶፍትዌሮችና ፋይሎች ስልካችን የሚያስቀምጥበት ቦታ ሲሆን ስልካችንን መረጃን በማመላለስ (loading data) ጊዜን እና ቦታ ተጣቦ ከመዘግየትና ከመቆም ያደናል ስለዚህ የስላካችንን ከች ማፀዳት ተቃሚ ያደርገናል፡፡

🔑 Widgets መጠቀምን ማብዛት
አንድሮይድ ስልኮች ከሚሰጡን የተለየ ጥቅም አንዱ ዊጄትስ ቢሆንም ያን ያህልም የሚሰሩትን ካልገደብን ስልካችንን በማጨናነቅና እንዲቆም
(ስታክ) እንዲያደርግ በማድረግ ረገድም ከፍ ያለ ድርሻ ያላቸዉ በመሆናቸዉ ዊጄትስን በመቀነስ ካልሆነም በማጥፋት ስልኮ በየጊዜዉ መቆሙን አላያም መንቀራፈፉን ማስቆም አማራጭ ነዉ፡፡

ፋብሪካዉ ሲያመርተዉ ወደነበረበት
ማሰተካከያ መመለስ(reset factory setting) የስልኮ ማርጀት አልያም ለብዙ ጊዜያት መጠቀም ስልኮን እንዲቀራፈፍ አልያም በየማሃሉ እንዲቆም ለመሆኑ ምክንያት ላይሆን ይችላል፡፡
አንዳንድ የማስተካከያ(ሴቲንግ) ለዉጦች ወይም አቅጣጫ መጠቆምያ ጂፒስ ኦን ማድረግ (ማብራት) ለስልኮ መንቀራፈፍ ምክንያት ሊሆኑ ስለሚችሉ የስልኮ በመሃል በመሃል መቆም (ስታክ) ሲያጋጥሙ ስልኩ ሲዘጋጅ ወደነበረበት
መመለስ (reset factory setting) ችግሩን ሊቀርፍ ይችላል፡፡

🔑 ዎልፔፐር (Wallpaper) መጠቀም
ስልኮ ለዓይን እንዲስብ አልያም በአንድ አንድ አቋራጭ ቴክኒኮች ምክንያት ስልኮ ላይ ላይቭ ዎልፔፐር (Live Wallpaper) መጠቀም አንዱ
የአንድሮይድ ስልኮች ገፀ-በረከት ቢሆንም ለስልኮ መዘግየትም ይሁን መቆም(ስታክ ማድረግ) ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ማጥፋቱ መንቀራፈፉን አልያም ሰታክ ማድረጉን ሊያስቆም
ይችላልና ይሞክሩት፡፡

🔑 ስልኮ አቧራ ከሞላዉ የሚሰሩበት ቦታ አልያም የሚዉልበት አከባቢ አቧራማ ከሆነ ስልኮን ማፅዳትና ከተፀዳም በኋላ መልሶ በአቧራ እንዳይሞላ መከላከያ መጠቀም፡፡
ከተጠቀሱት አማራጮች ዉስጥ አንዱን ብቻ መርጦ በመተግበር ሳይሆን ሁሉንም አልያም አብዛዛኛዉን መፍቴዎች በአንድ ላይ በመተግበር ዉጤት ስለሚያስገኝ ከመፍቴዎች ዉስጥ
በመምረጥ ሳይሆን ከቻሉ ሁሉንም መፍትሄዎች ስልኮ ላይ መተግበር ካልሆነም የተቻሉትን መከወን እንደመፍተሄ ይሆናል፡፡
══════❁✿❁ ══════
ዛሬ ይዘን የመጣነዉ ሁሉም ሰዉ ስልኩ ላይ ሊኖረዉ የሚገባ አሪፍ የሆነ አፕሊኬሽን ነዉ

📌ስሙ -Google Lens ይባላል።

ይህ አፕሊኬሽን ምንም አይነት የማናዉቀዉን ነገር በቀላሉ እንድናዉቅ ይረዳናል።

💢ለምሳሌ:

መኖሪያ ቤታቹ አከባቢ የሚገኙ ማንኛዉም አይነት እቃዎች መረጃቸዉን ለማግኘት፣ የምንጠቀማቸዉ የመድሀኒት አይነቶች እና ምንነቱን መረጃ ለማግኘት፣ ሌሎችንም ስራዎች ይሰራል።

💢ይህን አፕሊኬሽን ለመጠቀም ስልኩ አሪፍ የሆነ የካሜራ ጥራት ቢኖረዉ ይመረጣል ምክንያቱም እኛ ስለፈለግነዉ ነገር መረጃ ስንፈልግ ያንን ነገር ፎቶ ማንሳት ስለሚያስፈልግ ነዉ።

Mobile Data(Package ቢሆን ይመረጣል) ወይም #WIFI አስፈላጊ ነው።

📌የምንፈልገውን ነገር #ፎቶ_ካነሳን በኋላ ከኢንተርኔት🌐 ጋር ማገናኘት ይኖርብናል።

አፑን ሊንኩን በመጫን ከ Google play store ማውረድ ትችላላቹ👇👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.google.ar.lens
🔸የእንግዳ ፍጡራን ፍለጋ በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን

▫️በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሚገኝ ዓለም አቀፍ የተመራማሪዎች ቡድን እንግዳ ፍጡራን (alien) እና ሥልጣኔያቸውን የማፈላለግ መርሓ ግብር ይፋ አደረገ፡፡

▫️መርሓ ግብሩ ጋሊሊዮ ፕሮጀክት ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ተፈጥሯዊ ያልሆኑ የሥነ-ፈለክ ቁሶችን የሚለይ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስልተ-ቀመር ፍጡራኑን ለማፈላለግ ለሚደረገው ጥረት እንደሚበለፅግ ስካይ ኒውስ አስነብቧል፡፡

▫️ስልተ-ቀመሩ የሰው ልጅ ያልሆኑ ሳተላይቶችን እና በፍጡራኑ ቴክኖሎጂዎች (extraterrestrial technology) ምክንያት የሚፈጠሩ ያልተለመዱ የሕዋ ክስተቶችን የመለየት አቅም እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡

▫️የከሰሙ ወይም በተግባር ላይ ያሉ የፍጡራኑን ቴክኖሎጂዎች በመፈለጉ ሂደት በሥነ-ፈለክ ቅኝት የሚገኙ ዳታዎች እና የቴሌስኮፕ ምልከታዎች ቡድኑ በተጨማሪነት የሚጠቀምባቸው መረጃዎች ናቸው፡፡

▫️የቡድኑ መሪ ፕሮፌሰር አቪ ሎብ ከሰው ልጅ ሥነ-ፍጥረት እና የሥልጣኔ መዳረሻ የሚለዩ ሌሎች ፍጡራን አሉ ብለው ያምናሉ፡፡ ለዚህም ይመስላል ከመሬት ውጭ ስላሉ ፍጡራን ያለውን መላ ምት ሳይንስ ሊያጣጥል አይገባም በሚል ቡድናቸው የፍለጋ ስራውን የሚያከናውነው።
════❁✿❁ ═══════
ኢትዮ ቴክኖሎጂ ( Ethio technology ) via @dooxbot
🔸የበይነ - መረብ ንግድ (Online Business) 🎈ክፍል 2 (ከትላንቱ የቀጠለ) ▫️አሁን ወደ ተነሳንበት የበይነ - መረብ ንግድ (Online Business) እንመለስ። ከላይ ባብራራነው ጽንሰ ሃሳብ መሰረት የበይነ - መረብ ንግድ መጀመር እና ሌላ የገቢ ምንጭ መፍጠር ይቻላል። ነገር ግን ከዘልማዳዊው "ያበላል ወይስ አያበላም" አይነት ያልተጨበጠ ጥያቄ መውጣት እና መጠነኛ የገበያ ጥናት ማድረግ…
🔸የበይነ - መረብ ንግድ (Online Business)

🎈ክፍል 3 (ከለይ ካለዉ የቀጠለ)

3️⃣ የግል ቴሌግራም ቻናል

▫️ቴሌግራም በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሪነቱን እየወሰደ ነው። ብዙ ሰዎች ለብዙ ስራ ቀዳሚ ምርጫቸው እያደረጉት ነው። ስለሆነም የግል ቴሌግራም ቻናል በመክፈት እና ተፈላጊ እና ተወዳጅ ነገሮችን በመልቀቅ ብዙ ተከታይ ማፍራት። ከዛም በቻናላችሁ ላይ ማስታወቂያ ተከፍሏችሁ በመስራት፣ የፕሪምየም (ልዩ ዝግጅቶች) በማዘጋጀት በክፍያ ማስተላለፍ፣ Podcast በማዘጋጀት እና በክፍያ ለአባላቶች ማቅረብ፣ የራሳችሁ የሆነን ፈጠራ (ስእሎች፣ የአርት ስራዎች፣ የመስታወት እና ብርጭቆ ላይ ህትመቶች...) በመሸጥ ወዘተ አይነት ዘዴዎችን በመጠቀም ገቢ ማግኘት ይቻላል።

4️⃣ App እና Website ግንባታ

▫️እነዚህ ስራዎች በርግጥ ትምህርት እና ልምድ ይጠይቃሉ። በዚህ የሰለጠነ ሰው ከቋሚ ስራው ጎን ለጎን ለግለሰቦችም ሆነ ለተቋማት በቅናሽ ዋጋ ድረገጾችን በመገንባት ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ይችላል።

▫️ከዚህ በፊት ያልተሰሩ እና ለህብረተሰቡ ጠቀሜታ የሚሰጡ App Develop በማድረግም ከባድ ትርፍ (ምናልባትም ሕይወትን የሚቀይር) ማግኘት ይችላል። ለዚህ አንድ ቀላል ማሳያ

☑️ በቅርቡ የእቁብ App Develop ያደረገችው ወጣት የስራ ፈጠራ ባለቤት

☑️ Ride

☑️ Afrotie የኦንላይን ግብይት App


ማጠቃለያ

▫️ከላይ መግቢያው ላይ እንደጠቀስኩት በእኛ ሃገር በተለያዩ ሰንሰለታማ ምክንያቶች የበይነ - መረብ ንግድ መሄድ ያለበትን ርቀት አልሄደም። ምቹ ሁኔታዎች ብዙም ስላልተፈጠሩለት። ይህም ወደ ኦንላይን ቢዝነስ ለመግባት ላሰበ ሰው አንድ ተግዳሮት ነው።

▫️በርግጥ በውስጥ መስመር ሲመጡልን ከነበሩ "Online Business" እንዴት እንጀምር የሚሉ ጥያቄዎች አብዛኞቹ የፈለጉት እንደ ቅጥር አይነት ስራን ይመስለኛል። የጥያቄዎቹ ስሜት እንደዛ ነው። የሆነም ስራ ኦንላይን መስራት፤ ከዛ ለእሱ ክፍያ መቀበል። ትክክል ነው። ይህ አሰራር በውጩ አለም በስፋት እየተሰራበት ነው። እኛ ሃገር ግን እንደዚህ አይነት ስራዎች ባደረኩት መጠነኛ ፍለጋ አላጋጠሙኝም። በርግጥ አንዳንድ እንደ መረጃ መሰብሰብ (Surveying) አይነት ስራዎች አልፎ አልፎ ከትምህርት እና የምርምር ተቋማት አካባቢ ይታያሉ። ሆኖም እነሱም ወቅታዊ ስራዎች ስለሆነ አያዛልቁም ወይም ቋሚ የገቢ ምንጭ አይሆኑም። One Time Job ናቸው። ስለሆነም ብቸኛው እና የሚያዋጣው አማራች የራስን የኦንላይን ቢዝነስ መመስረት እና የሚያስፈልገውን ጥረት አድርጎ ገበያው ላይ ዘልቆ በመግባት ስራውን መስራት አንዱ መፍትሄ ነው ብዬ አምናለሁ።

መልካም ስራ እና እድል! 🙌
የሪሲቨሮች ሶፍትዌር ከየት ይገኛል?
በመጀመሪያ ሶፍትዌር ከመፈለጋችን በፊት የምንጠቀምበት ሪሲቨር ሶፍትዌር ያስፈልገዋል ወይስ አያስፈልገውም የሚለው ሀሳብ ተገቢነት አለው። ፍላጎታችን የትኛውን የነጻ የእግርኳስ ቻናል/መዝናኛ ለማስገጠም ነው?
🌹 ለምሳሌ ፍላጎታችን ቫርዚሽን ለማስገጠም ከሆነ ፦
ሶፍትዌር የሚያስፈልጋቸው HD ሪሲቨሮች ibox እና supermax ብቻ ናቸው።
🌹 በተለየ ሁኔታ የተወሳሰበ መቆለፊያን ስለሚጠቀም የትኛውም አይነት Varzish or Foot ball ena Amos 5 የሚከፍት ሪሲቨር ሁሉ ሶፍትዌር ያስፈልገዋል።
_
የሚከተሉት ዌብሳይቶች የታወቁ የሪሲቨሮች ሶፍትዌር ማውረጃ ሳይቶች ናቸው።
www.seasathd.net የሁሉም ibox ሪሲቨሮች
www.newprog.net የሁሉም supermax ሪሲቨሮች
www.freesat.cn/forum የሁሉም freesat ሪሲቨሮች
www.peacesat.com የLEG,Lifestar,Corronet ሪሲቨሮች
www.pctvlab.com/forum የሁሉም Gsky ሪሲቨሮች
_
🌞ከላይ የተጠቀሱት ዌብሳይቶች የራሳቸው እንደመሆናቸው መጠን የሀሰት ሶፍትዌር አይኖርባቸውም ነገር ግን የዌብሳይታቸው የመያዝ አቅም እንዳይሞላ በሚል በ.zip ፋይል መሠረት ስለሚያስቀምጧቸው ካወረድን በኋላ ወደ ኮምፒዩተር በመውሰድ (ስለምንቀርብ አፕ በመጫን) extract ማድረግ ያስፈልጋል።
🔸ለ90 ተከታታይ ቀናት እየበረረች መቆየት የምትችለው አውሮፕላን
===================
▫️የአሜሪካን ባህር ኃይል ያለ ማቋረጥ ለ90 ተከታታይ ቀናት እየበረረች መቆየት የምትችል ሰው አልባ አውሮፕላን እየሰራ መሆኑ ተዘገበ፡፡ ስካይድዌለር የሚል ስያሜ የተሰጣት አውሮፕላኗ በስፔን-አሜሪካዊው የኤሮስፔስ ኩባንያ ስካይድዌለር ኤሮ አማካኝነት የምትመረት ይሆናል፡፡ አገልግሎት ላይ ስገባም ለወራት የባህር ኃይሉን ጦር መርከቦች በማጀብ በዙርያቸው ያሉ አካባቢዎችን መቃኘት የምትችል ይሆናል ተብሎላታል፡፡

▫️አውሮፕላኗ ከዚህ ቀደም ተሰርታ በአውሮፓውያኑ 2015 እና 2016 ዓለምን በዞረችው ኢምፐልስ 2 የተሰኘች ሰው ጫኝ አውሮፕላን ላይ ተመስርታ የተሰራች ናት፡፡ ሆኖም ኩባንያው ይህች አውሮፕላን የነበሯት የአብራሪ መቀመጫዎቿን በማውጣት ንድፏን ሲቀይረው ነፃ የተደረጉት ቦታዎች ከሌሎች ማስተካከያዎች ጋር ተዳምረው አውሮፕላኗ ረዘም ላለ ጊዜ እንድትጓዝና መጫን የምትችለው ቁሳቁስ መጠንም እንዲጨምር አስችሏታል፡፡

▫️ከተደረገላት ማስተካከያ በኋላ አውሮፕላኗ 72 ሜትር በሚረዝሙት ክንፎቿ ላይ 270 ካሬ ሜትር የሚሸፍኑ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች ተገጥሞላቸዋል፡፡ ይህም 2ኪሎ ዋት የሚሆን ኃይል እንድታመነጭ አስችሏታል፡፡ በተጨማሪም በውስጧ ከ360 ኪ.ግ በላይ ክብደት ያላቸው የራዳር እና ካሜራ ግብዓቶችን የመሸከም አቅም እንዲኖራት ሆኗል፡፡

▫️እንደ ስካይድዌለር ኤሮ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሮበርት ሚለር ከሆነ አውፕላኗ በቅድሚያ ራሷን ችላ እንድትበር፣ በመቀጠልም ራሷን ችላ እንድትነሳና እንድታርፍ፣ በመጨረሻም ሙሉ በሙሉ ራሷን ችላ በረራን እንድታከናውን የሚያደርጉ ሙከራዎችን የምትፈፅም ሲሆን እነዚህ ሙከራዎች ከተጠናቀቁ በኋላም ለ90 ቀናት የመበርረር ሙከራዋን ወደማድረግ የምትገባ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ኩባንያው አውሮፕላኗ ላይ የሀይድሮጅን ፊውል ሴሎችን ገጥሞ ብቃቷን ማሳደግያ አልያም የአየር ፀባዩ ተስማሚ በማይሆንበት ጊዜ መጠባበቂያ እንዲሆናት አቅዷል፡፡

▫️ረዘም ላለ ሰዓት መብረር በተለያዩ ወታደራዊ ተልዕኮዎች ላይ ጠቃሚ ነገር ቢሆንም አሁን ላይ የአሜሪካን ባህር ኃይል የሚጠቀማቸው በመጠን ከፍ ከፍ ያሉት ሰው አልባ አውሮፕላን ወይም ድሮኖች እንኳን አየር ላይ እየበረሩ መቆት የሚችሉት ለሰላሳ ሰዓታት ብቻ ነው፡፡

ምንጭ፤ Futurism
Forwarded from ELA TECH💡 (ŴĬŹ ĚŁÃ MÂŇ)
👋ሰላም ሰላም ቤተሰቦች እንዴት ናቹ ዛሬ አንድ ሚገርም የቀን የ Card ወጪያችንን የምንዘጋበት ምርት የ Telegram Bot ልጋብዛችሁ።

🎈ይሄን ቦት ከዚ በፊትም ቻናላችን ላይ ልከነዉ ነበር አሁንም እንደ አዲስ ልከነዋል ከዚ በፊት የላክነዉን ያላያችሁ ከታች ባለዉ ሊንክ በመግባት ወደ ቦቱ ስራዉን ማስጀመር ትችላላችሁ

🎈በዚ Bot ከ 5birr_1000birr መስራት ትችላላችሁ ሁሉም ብር የሚላክላቹ በካርድ መልኩ ነዉ በይበልጥም ቻናልና ግሩፕ እንዲሁም ብዙ Contact ላላችሁ አሪፍ ቦት ነዉ ምክንያቱም ብር ምትሰሩት ሰዎችን በመጋበዝ ስለሆነ ቦቱ መቁጠር ሚጀምረዉ አንድን ሰዉ ወደ ቦቱ Invite አድርጋችሁ ቦቱን Start ሲያረግ እና ቻናሉን Join ሲልላችሁ ነዉ።

🎈ስለዚ እኛም እንድንጠቀም በኛ በራሳችን Link በመግባት ቦቱን /start እና የሚያመጣላችሁን ቻናል Join በማለት ለኛም ጥቅም እንዲሁም ለናንተም ጥቅም ስለሆነ ቦቱን ይጠቀሙበት።

🎈100% ይሰራል ለ5 ሰዉ በመጋበዝ 5 ብር በቀላሉ መስራት ይችላሉ ስለ አጠቃቀሙ ከላይ ልከናል እሱን ያንብቡ ቻናሉን መቀላቀል እንዳይረሳ የቦቱ ሊንክ👇👇
https://telegram.me/ask_anything_ethiopia_bot?start=i1025465399
https://telegram.me/ask_anything_ethiopia_bot?start=i1025465399
✳️ YouTube News ፡ ዩቲዩብ ከሰሞኑ በጣም አስደሳች ዜና ይዞ ብቅ ብሏል። 1000 Subscribers እና 4000 watch hours ሳንሞላ በ Short ቪዲዩ ብቻ ገንዘብ መስራት ተችሏል። 😍

◽️ይሄ ዜና ሞኒታይዝ ላልሆኑ ሰዎች በጣም ትልቅ ዜና ነው። Short ቪዲዮዎችን ብቻ በመልቀቅ ተከፋይ መሆን ይቻላል። እንዴት ለሚለው ጥያቄዩቲዩብ Short ቪዲዩ ለሚሰሩ ሰዎች ለማበርታቻ በሚል 100 Million Dollar ፈንድ አዘጋጅቷል።

◽️እና Short ቪዲዩ ስትለቁ ብቻ አይደለም የሚከፍላቹህ። በመጀመሪ የምትለቁትን ቪዲዩ ያጣራል ከዛም በስትክክል የምትሰሩ ከሆነ በ Email መልዕክት ይልክላቹሀል።

◽️በመቀጠልም ከ AdSense ጋር አካውንታቹን Connect እንድታደርጉ ይጋብዛቹሀል። ያኔ ነው ገንዘብ መስራት የምትችሉት።‼️ ነገር ግን አዲስ ህግ አለ

◽️የምትለቁት ቪዲዩ ላይ ምንም አይነት Logo ወይም Watermark መኖር የለበትም። ይህንንም ያደርገበት ምክንያት የ TikTok ቪዲዮችን ለማስቀርት ነው። ማለት ዩቲዩብ ላይ እንዳይለቁ ማለት ነው።

◽️የተቀሩት ደሞ የድሮዎቹ ህጎች ናቸው።
©Mame_Tech
🔸የCareer Mode ማሻሻያዎች

🔻የCareer Gameሮች ተዘምነው ማየት ከሚፈልጉት የጨዋታው ዋና ክፍሎች አንዱ ነው።

🔻የሥልጠና ሥርዓት የተጫዋች ዕድገትን የበለጠ ተለዋዋጭ ሲያደርግ Fifa 21 ወደ ግጥሚያዎች ውስጥ እና ወደ ውስጥ መግባት የሚችሉበትን ‹Quick Sim› አማራጭን አክሏል።

🔻የተሻሻሉ AI እና የዝውውር አማራጮችም ጨዋታው የበለጠ ህይወት እንዲኖረው አድርገዋል ፣ ግን አሁንም በFifa 22 ውስጥ ተጨማሪ ማሻሻያዎች የሚጠይቁ አሉ።

🔻አድናቂዎች ስለ የመስመር ላይ የሙያ ሁኔታ መጨመሩን ገምተዋል ፣ ግን ለዚህ ገና Official ማረጋገጫ የለም።
©Plus ethio
════❁✿❁ ═══════
ከብዙወቻችሁ #bot እንዴት ነዉ ሚንሰራው የሚል ጥያቄ ስለተነሳ በቻልነው ፍጥነት ሰርተን አቅርበንላችኋል
#step

1, @BotFather ትገባላችሁ

2, #start ትሉታላችሁ

3, /newbot create new bot የሚለዉን ትነካላችሁ

4, ስም ትፅፋላችሁ ለ #ቡታችሁን ማለት ምትፈልጉትን

5, ከዛ #user name tesatutalachu እናንተ የፈለጋችሁትን

6, congratulations bot created successfully ይላችኋል

7, use this token access የሚለው ቦታ ላይ ያለዉን #code copy ታደርጉና


8, @LivegramBot ገብታችሁ #start ትላላችሁ

9, connect new bot ንኩት

10, #term and service የሚለውን ንኩትና

11, ቅድም #copy ያደረጋችሁትን #code #past አድርጉ አለቀ ማንኛውም ሰዉ በ #bottachu በኩል ልያገኛችሁ ይችላል። 🙏🙏
ኢትዮ ቴክኖሎጂ ( Ethio technology )
✳️ YouTube News ፡ ዩቲዩብ ከሰሞኑ በጣም አስደሳች ዜና ይዞ ብቅ ብሏል። 1000 Subscribers እና 4000 watch hours ሳንሞላ በ Short ቪዲዩ ብቻ ገንዘብ መስራት ተችሏል። 😍 ◽️ይሄ ዜና ሞኒታይዝ ላልሆኑ ሰዎች በጣም ትልቅ ዜና ነው። Short ቪዲዮዎችን ብቻ በመልቀቅ ተከፋይ መሆን ይቻላል። እንዴት ለሚለው ጥያቄዩቲዩብ Short ቪዲዩ ለሚሰሩ ሰዎች ለማበርታቻ በሚል 100…
✳️ ባለፈው ዩቲዩብ ለ shorts ቪዲዮ ለሚሰሩ ሰዎች $100,000,000 ፈንድ እንደለቀቀ አሳውቂያቹህ ነበር። ይሁን እንጂ እስካሁን ይህንን እድል መጠቀም የሚችሉት ሀገራት

India, Brazil, Indonesia, Nigeria, SA (South Africa), USA, UK, Japan, Mexico እና Russia ብቻ ናቸው።

◽️YouTube Team እንዳሳወቀው ሌሎች ሀገሮችን በቅርቡ በማካተት update እንደሚያደርግ አሳውቋል። አዲስ መርጃ ካለ አሳውቃቹሀለው 👍
🔐እንዴት የ ማንኛዉንም Windows Computer Administrator Password ማለፍ እንችላለን?

Requirements:
ማንኛዉም የwindows operating system የተጫነበት cd ወይም usb
Eg. Windows7 os or windows 8 os

Let’s begin………..
computrሩን ከ cd ወይም ከusb ማስነሳት(boot from cd or usb)
ልክ boot አርጎ ከተነሳ በኋላ shift+F10 መጫን ከዛ command promote ይከፈታል
ምናልባት command promote ካልከፈተ shift+fn+F10 ሞክሩት
Type “cd c:” without quotation then hit enter
Type “dir” hit enter

► Windows የሚለው ዝርዝር እስከሚመጣ ድረስ ፊደሉን እየቀያየሩ መሞከር
Eg. “D:” hit enter then “dir” hit enter then check “windows”
“E:” hit enter then “dir” hit enter then check “windows”
ከዛ በ ስእሉ ላይ የሚታየዉን በትክክል ይጻፉ
“cd windows/system32” hit enter

► Type “rename osk.exe osk.old” hit enter
Type “rename cmd.exe osk.exe” hit enter

► አሁን 75% ሚሆነዉን ስራ ጨርሰናል ከዚ ቀጥሎ computerun restart ማድረግ
ከስር በግራ በኩል የሚታየዉን icon መጫን
On-Screen Keyboard የሚለዉን መምረጥ

► command promote display ሲሆን ስእሉ ላይ ያለዉን command ማስገባት
Type ”net user” hit enter
Type ”net user help *” hit enter —---- help ማለት የ computeru ስም ነው

► ከዛ ምትፈልጉትን password ማስገባት
► Password እንድይኖረው ከፈለጋቹ ደሞ hit enter ሁለቴ

► አሁን Passwordu ተቀይሯል ማለት ነው
የቀየራቺሁትን Password አስግብታቹ login ማረግ::
ቋንቋዎችን ወደ ፕሮግራሚንግ ኮድ የሚቀይረው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት

ኦፕንኤአይ (OpenAI) የተባለው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የምርምር ተቋም ተፈጥሯዊ ቋንቋን ወደ ፕሮግራሚንግ ኮድ የሚቀየር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት ማበልፀጉን አስታወቀ፡፡

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓቱ ኮዴክስ የሚል መጠሪያ እንደተሰጠው ቬንቸር ቢት አስነብቧል፡፡

ከዚህ ቀደም ለተመሳሳይ ዓላማ በተቋሙ በልፅጎ አገልግሎት ሲሰጥ በቆየው ኮፓይለት (Copilot) በተባለው ሥርዓት መነሻነት አዲሱ ሥርዓት ከፍተኛ ማሻሻያ ተደርጎበት መውጣቱን ዘገባው አመላክቷል፡፡

አዲሱ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተጻፉ ዓረፍተ ነገሮችን በመረዳት ወደ ፕሮግራሚንግ ኮድ የመቀየር አቅም እንዳለው በዘገባው ተገልጿል፡፡ በውጤቱም ኮምፒዩተሮች የሰዎችን ፍላጎት በተሻለ ሁኔታ መረዳት የሚያስችል አቅም እንደሚሰጣቸው ይጠበቃል፡፡

ፕሮግራሚንግ ኮድ ሶፍትዌሮች የሚጻፉበት የቀመሮች ስብስብ መሆኑ ይታወቃል፡፡
📍. LNB ምንድን ነው?

- LNB የእንግሊዝኛ አህፅሮተ ቃል ሲሆን ሲተነተን (Low Noise Block )የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል ይይዛል።
- LNB የራዲዮ ሞገድን ከዲሽ ላይ በመቀበል ወደ ሲግናል ከቀየረ በኋላ በኬብል አማካኝነት ወደ ሪሲቨሮች የሚልክ ዲሽ አናት ላይ የሚገጠም መሳሪያ ነው ።

📍. የLNB አይነቶች ስንት ናቸው?

በመሠረታዊነት አገራችን ውስጥ የሚስተዋሉት የLNB አይነቶች ሁለት ቢሆኑም የዘርፉ ባለሙያዎች ግን በዓለም ላይ 4 እና ከዚያ በላይ እንደሆኑ ያስረዳሉ።
ለመሆኑ አገራችን ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውሉት የLNB ዓይነቶች እነማን ናቸው እስኪ እንመልከታቸው። ብዙ ሰዎችም በእነዚህ በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ሲያወዛግባቸው እንመለከታለን።

1. KU Band LNB

በተለምዶ Ku band የሆኑ ፍሪኩየንሲዎችን ለመቀበል የሚያስችል መሳሪያ ነው።
12522

📍ባህሪያቸው:-

- ባለ 5 ዲጅት ፍሪኩየንሲን ይቀበላል።
- የፍሪኩየንሲ ወሰኑ ከ11700-12220 GHzነው።
- ትልቅ የፍሪኩየንሲ መጠን መያዛቸው አጭር የሞገድ ርዝመት አንዲኖራቸው አድርጓቸዋል።
- በአጭር ሞገድ ርዝመት መስራታቸው በትንንሽ ዲሾች (offset dishes) እንዲሰሩ አስችሏቸዋል።
ለምሳሌ፦(ዲያሜትራቸው ከ30-65ሳ.ሜ የሆኑ ዲሾች ላይ እንዲሰሩ አስችሏቸዋል።)
- በዚህም የተነሳ ብዙ አገራትን የማይሸኑ ከመሆናቸውም በላይ ለተለዋዋጭ የአየር ጸባይ ተጋላጭ ናቸው።
(ለምሳሌ:- እንደ ዝናብ እርጥበት አዘል አየር....ወዘተ)
- በLNBው ውስጥ የሚኖረው የርግብግቦሽ (oscillation) መጠን ከፍ ሲል 10600 እንዲሁም ዝቅ ሲል 9750 ነው:: አለማቀፋዊ የሆኑ KU Band LNBዎች የLNB freq 9750/10600 ነው።

2. C Band LNB
በተለምዶ C band የሆኑ ፍሪኩየንሲዎችን ለመቀበል የሚያስችል መሳሪያ ነው።
4103

📍ባህሪያቸው:-

- ባለ 4 ዲጅት ፍሪኩየንሲን ይቀበላል።
- የፍሪኩየንሲ ወሰኑ ከ3700-4200 GHzነው።
- ትንሽ የፍሪኩየንሲ መጠን መያዛቸው ረጅም የሞገድ ርዝመት አንዲኖራቸው አድርጓቸዋል።
- በረጅም ሞገድ ርዝመት መስራታቸው የግዴታ ትልልቅ መጠን ላቸው ዲሾችን (prime focus dishes) እንዲጠቀሙ አድርጓቸዋል።
📍ለምሳሌ ፦(ዲያሜትራቸው ከ180-240ሳ.ሜ የሆኑ ዲሾች ላይ እንዲሰሩ አድርጓቸዋል።)
- ይህም የሳተላይት ሽፋኑ ብዙ አገራትን እንዲያካልል ከማገልገሉም በላይ ለተለዋዋጭ የአየር ፀባይ እንዳይጋለጡ አግዟቸዋል ።
- ብዙ አገራትን እንደማካለላቸው መጠን አብዛኛዎቹ ቻናሎች አለማቀፋዊ ቋንቋን ይጠቀማሉ ይዘታቸውም በዚያው ልክ መልካም የሚባል ነው።
- በLNBው ውስጥ የሚኖረው የርግብግቦሽ (oscillation) መጠን አንድ ጫፍ ሲሆን 5150 ነው።
💢የትኛውም ስልክ📱 ጠጋኝ ስልካችሁን #ስትሰጡት መጀመሪያ #Check የሚያደርገው Setting ነው ➡️ እሱ ካልሆነ Software ላይ ችግር ካለ Format (Restore) ➡️ ከዛ ካለፈም ስልኩን Flash ያደርገዋል።

Setting 50-100 ብር ያስከፍላችኋል።
Format 80- 120 ብር ያስከፍላችኋል።
Flash ከ150-300ብር ያስከፍላችኋል።

📌የPlus ኢትዮ አንዱ አላማ የትኛውም የቻናሉ ቤተሰብ ቢያንስ ከላይ ያሉትን ችግሮች በራሱ👍 መፍታት እንዲችል ነው።

⬆️እነዚን ሞክራችሁ ብትሳሳቱ እንኳን #በቀላሉ መስተካከል ይችላሉ፤ ⚠️Flash ስታደርጉ ግን ተጠንቀቁ።

💢ሰሪው ስልኩ... ከላይ ባሉት መፍትሔዎች እንደማይስተካከል ካሰበ (ከሞከረ) ወደ Hardware ይሸጋገራል።

🔆የየትኛውም ስልክ Hardware ችግር መፍትሔ #YouTube ላይ አለላችሁ።

⚠️ልምድ ከሌላችሁ እንድትሞክሩት አልመክርም፤ ግን ፍላጎቱ ያላችሁ እጃችሁን አጣጥፋችሁ አትቀመጡ።🙏

ለምሳሌ: እኔም ለመጀመሪያ ጊዜ ስልክ ስሰራ ባትሪ ሳላወጣ በይጄ ፀጥ ያረኩት፤ ሌላም ብዙ ተሳስቻለሁ... ፍላጎቱ ያላችሁ በቀላል እቃ ሞክሩ።🙏
ቴሌግራም ላይ በቀላሉ ገንዘብ ይስሩ! 💵

ፖስቶችን ቴሌግራም ላይ ሆነው በቀላሉ ለሌሎች ሰዎች ማጋራት ተከፋይ የሚሆኑበት የቴሌግራም ቦት ነው። እንዲህም በቀላሉ በርሶ Link ለሰው በማጋራት ገንዘብ መልቀም ትችላላቹ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መጀመር ትችላላችሁ 👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/Share251bot?start=shnfzvbmk6
https://t.me/Share251bot?start=shnfzvbmk6
100% ይሰራል
​​✳️ ሞባይላችንን ተጠቅምን ቢሮ፣ ሱቅ ወይንም እቤት ውስጥ ያለን ኮምፒወተራችንን መንካት ሳያስፈልግ፣ ካለንበት ስፍራ እንዴት መቆጣጠር እንችላለን?

◽️ ድርጅት ኖሯችሁ ባጋጣሚ እሩቅ ቦታ ቢሆኑና ሂሳብ ለመዝጋት (Zreport) በሞባይሎ ትዛዝ ማውጣት እንደሚችሉ ያውቃሉ?

◽️ ኮምፒውተሮት አዲስ አበባ ሆኖ እርሶ ሆነ ለመዝናናት ውጭ ሃገር ከሆነ ያሉት፣ ያሉበት ሆነው ማን በኮምፒውተሮት ምን እየተጠቀመ እንደሆነ በደንብ መከታተል እንደሚችሉስ ያውቃሉ?

◽️ ለስራም ባሉበት ሆነው ኮምፒውተሮ ላይ የሆነ ነገር ቢበላሽ የኮምፒውተር ባለሞያው መምጣይ ሳያስፈልገው ካለበት ሆኖ ችግሩን እንዲፈታስ?

◽️ ምን እሱ ብቻ ባሉበት ሆነው ሙዚቃ መቀየር ፣ሰራተኛ በስንት ሰአት እንደገባ፣ጌም ማን እየተጫወተ እነደሆነ፣ በቀን ምን ያህል እንደተሰራ ፣ልጆቾት ምን አይነት ፊልም እያዩ እንደሆነ በተጨማሪም እቤትዎ ትንሽ ካሜራ ካሎት የትም ሆነው ማን እንደገባደረገ ነው የሚለውን መከታተልስ?

🔺መልሳችሁ አዎ ከሆነ ምኞቶን የምታሳካ አሪፍ ዘዴ ይዘንላችኅል።

◽️ በመጀመሪያ ለዚህ ስራ የሚጠቅመን በሞባይላችን እና ኮምፒውተር ላይ የምንጭነው ቲም ቪወር (Team Viewer) የተባለ ሶፍትዌር ዳውንሎድ ማድረግ አለብን። ለ ኮምፒዩተራቹ ከዚህ በይነ መረብ ታገኙታላቹ።

◽️ ሶፍትዌሮቹን ዳውንሎድ ካደረግን በኅላ በፕሮግራሙ ያጫጫን step መሰረት በኮምፒተራችን እና ስልካችን ላይ እንጭናለን። ይህን ስናደርግ ፕሮግራሙ በራሱ መለያ ወይንም መገናኛ ኮድ እና መግቢያ ፓስዎርድ ይሰጠናል።

◽️ ፓስዎርድ በራሱ ጊዜ ኮምፒውተራችንን ስንከፍት ስለሚቀያየር ለሁልጊዜ የሚሆን የራሳችንን ፓስዎርድ Team Viewer ፓስወርድ Setting ውስጥ በመግባት "Setup Unattended Access" የሚለውን ምርጫ ነክተን የራሳችንን እንሰጠዋለን።

◽️በመቀጠል ስልካችን ላይ የጫነውን ፕሮግራም ከፍተን ቅድም ኮምፒውተራችን ላይ የሰጠንን ID እናስገባና connect እንልዋልን። በዚ ጊዜ ፓስዎርድ ስለሚጠይቅ ኮምፒውተሩ ላይ የፈጠርነውን ፓስዎርድ በማስገባት በቀላሉ መቆጣጠር እና መጠቀም እንጅምራለን ማለት ነው።

◽️ ይህ ዘዴ በምንኛው ግዜ የኢንተርኔት አገልግሎት በኮምፒውተሩም በሞባይላችንም ላይ ሊኖረን ይገባል።

◽️ የፈጠርነውን ፓስዎርድ እና ID ለስራ ካልሆነ ለሌላ ሰው ማሳየት የለብንም ምክንያቱም ሌሎች ሰዎች በፈለጉት ጊዜ ገብተው ችግር ሊፈጥሩብን ይችላሉ።
‼️ ማስጠንቀቂያ ለሁሉም‼️

✳️ ሰላም ውድ የethio technologyቤተሰቦች ሰላምና ጤና ለናንተ ተመኘሁ🙏 ዛሬ ብዙ ሰዎች እያወሩት ስላለው እና አብዛኞቻቹ ስለጠየቃቹኝ ስለ ቴሌ ነፃ ፓኬጅ አገልግሎት አንዳንድ ነገሮች ልበላቹህ።

◽️ይሄንን ፁሁፍ እስከፃፍኩበት ሰዓት ድርስ በነፃ ፓኬጅ መግዛት ትችላላችሁ። አንዳንድ ሰዎች ቴሌ የሳይበር ጥቃት ደርሶበታል የሚል ወሬ እያወሩ ነው።

◽️እውነት ይሁን አይሁን በእርግጠኝነት ለመናገር ይከብዳል። ነገር ግን አንዳንድ ነገሮች ያጠራጠራሉ።

1. ፓኬጅ በነፃ መስራቱ ነው። እርግጥ ነው ይሄ ምንም የሚያሳምን ነገር የለውም ልትሉ ትችላላችሁ። ወደ ሁለተኛው እንሂድ

2. ሲማቹህ ላይ ምንም ብር ሳይኖር ወደ ሌላ ሰው ስትደውሉ የደወላቹት ስልክ ይነሳል አስተውሉ ስልካቹህ ላይ ምንም ብር ሳይኖር ማለት ነው። እና ይነሳል ግን ምንም ድምፅ የለውም ሁኔታው ግራ የሚያጋባ ነው።

3. ቴሌ እንኳን ቅናሽ ቢያደርግ እንጀዚህ ሙሉ ለሙሉ Free አያርገውም። ምክንያቱም ያከስርዋል። ብቻ የሳይበር ጥቃት ቴሌ ላይ ስለመድርሱ በትክክል የሚገልፅ መርጃ ስላልወጣ እርግጠኛ መሆን አይቻልም። በዚህ ጎዳይ ቴሌ እስካሁን ምንም ያለው ነገር የለም።

‼️አንድ ጓደኛዬ እንደዚ ዳታ በነፃ ነው ሲባል ሰምቶ ማታውን ሞከርው እናም ሰራለት። በጣም ብዙ ሰዓት እንደፈለገ ተጠቀመ። ጥዋቱን ግን ስልኩን ከፍቶ ሲያየው - 423 ብር ተደርገበት

‼️እና ወደ 994 ደውሎ ሁኔታውኝ አስርዳቸው እነሱም ማታውን የተጠቀመውን እያወራረዱ እንደሆነ ነው የነገሩት። ይሀው ልጁ አሁን ሲሙን ልጣለው ወይስ ምን ብሎ ሀሳብ ውስጥ ገብቷል 😂

◽️እና በአጭሩ ምን ልላቹህ ፈልጌ ነው ይሄ ነፃ ፓኬጅ የተባለው ነገር ይሰራል ነገር ግን ሲስተሙ በስትክክል መስራት ሲጀምር ልክ እንደ ልጁ በተጠቀማቹት ልክ ያወራርዳሉ ማለት ነው።

©mame tech
✳️ የኮምፒውተር ቫይረስ ሰለባ መሆንዎን እንዴት ማወቅ ይችላሉ


◽️ ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቋረጥ፡ ከዚህ ቀደም ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቆራረጥ አጋጥሞዎት በተደጋጋሚ ሰማያዊ ቀለም ያለው ገጽታ የሚያሳይ ከሆነ ኮምፒውተርዎ አደጋ ላይ መውደቁን ጠቋሚ ነው፡፡

◽️ የኮምፒውተር ስርዓት ማዝገም Slow System በሲስተምዎ ላይ ብዙ ቦታ የማይፈልጉ መተግበሪያዎችን (Apps) ሳይጠቀሙ የኮምፒውተር ስርዓቱ ዝግ ማለት የኮምፒውተርዎ ስርዓት በቫይረስ መጠቃትን ሊያመለክት ይችላል።

◽️ ከልክ ያለፈ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴ (Excessive Hard Drive Activity) ምንም እንኳን ኮምፒተርዎ ስራ እየሰራ ባይሆንም ጥቂት የማይባሉ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴን ካስተዋሉ ይህ ምናልባትም በቫይረስ ስለመጠቃትዎ የማስጠንቀቂያ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡

◽️ ያልተለመዱ የዊንዶው ምልክቶች ሲስተዋሉ፡ ኮምፒውተርዎን በሚከፍቱበት ወቅት እንግዳ የሆኑ ነገሮች ብቅ ካሉ እና በተለይ በኮምፒተርዎ ላይ የተለያዩ ድራይቭዎች Drive ከጠፉ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡

◽️ የተለዩ መልእክቶች፡ በተለያዩ መልእክቶች ወደ እርስዎ የመልእክት መለዋወጫዎች ሲገቡ እና ፋይሎችን በሚከፍቱበት ጊዜ ካልተከፈተ የተፈጠረ ችግር አለ ማለት ነው፡፡

◽️ መጥፎ የፕሮግራም እንቅስቃሴ፡- ፕሮግራሞችዎ ከጠፉ ፣ ከተበላሹ ፣ ወይም ያለ እርስዎ ፍቃድ እራሳቸውን በራሳቸው መክፈት ከጀመሩ ፣ እንዲሁም ያለ እርስዎ ትእዛዝ ኢንተርኔት ለመድረስ እየሞከረ መሆኑን የሚገልጽ ማሳሰቢያ ከደረሰዎ ይህም የቫይረስ ሰለባ መሆንዎን ጠቋሚ ነው፡፡

◽️ የዘፈቀደ አውታረ-መረብ እንቅስቃሴ Random Network Activity ምንም ጉልህ የሆኑ ፕሮግራሞችን ወደስራ ሳያስገቡ አልያም ከፍተኛ የበይነ-መረብ ዳታን በማይጠቀሙበት ጊዜ የእርስዎ ራውተር በቋሚነት ብልጭ ድርግም የሚል ምልክት የሚያሳይ ከሆነ ፣ የሆነ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡

◽️ የተሳሳቱ የኢሜይል መልእክቶች፡- እርስዎ ለማንም ኢ-ሜይል ባይልኩም ከእርስዎ የኢሜይል አድራሻ ለእርስዎ ኢ-ሜይል መልእክት ከደረስዎ የእርስዎ ስርዓተ ኮምፒውተር ተጥሷል (ወይም የኢ-ሜይል የይለፍ ቃልዎ እንደተሰረቀ የሚያሳይ ጠንካራ ማስረጃ ነው)

◽️ የአይፒ አደራሻዎ በበይነመረብ ፕሮቶኮል አድራሻ በጥቁር መዝገብ ከተቀመጠ Blacklisted IP Address የእርስዎ የአይፒ አድራሻ በጥቁር መዝገብ መያዙን የሚገልጽ ማስታወቂያ ከደረሰዎት ኮምፒተርዎ በጥሩ ሁኔታ ላይ አለመሆኑን የሚያሳይ ምልክት፡፡

◽️ ያልተጠበቀ የፀረ-ቫይረስ አገልግሎት መቆም፡- ብዙ ተንኮል-አዘል ሶፍትዌር malware ፕሮግራሞች ፀረ-ቫይረስ አገልግሎት የማስተጓጎል ወይም ከጥቅም ውጪ የማድረግ ተልእኮ በመያዝ የተቀየሱ ናቸው፡፡ ስለሆነም የፀረ-ቫይረስ ስርዓትዎ በድንገት የማይሠራ ከሆነ የኮምፒውተር ስርዓቱ ትልቅ ችግር ላይ መውደቁን የሚያሳይ በመሆኑ የመፍትሄ እርምጃዎችን መውሰድ የግድ ይላል፡፡
ቤቲካ ላይ ይወራረዱ! ያሸንፉ!
እጅግ ብዙ የማሸነፊያ አማራጮች ከአሪፍ የጨዋታ ኦዶች ጋር!
አሁኑኑ  ይወራረዱ! በ  https://t.me/betikaethiopia የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ!