Ethiopian Reporter Magazine
1.07K subscribers
37 photos
32 links
የኢትዮጵያ ሪፖርተር መጽሔት በሚዲያና ኮምዩኒኬሽንስ ሴንተር እየታተመ የሚወጣ ወርኃዊ መጽሔት ሲሆን፣ የሚያተኩረውም በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ፣ ባህላዊና የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡

www.ethioreportermagazines.com
Download Telegram
ሪፖርተር መጽሔት በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ፣ ባህላዊና የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሚያተኩረ የ መጋቢት ሕትመት https://ethioreportermagazines.com/e-paper

ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይከተሉን:

FB: facebook.com/ethiopianreportermagazine
Twitter: twitter.com/ethreporter_mag
Telegram: t.me/ethioreportermagazine
ኮሮና ቫይረስ በ1937 መኖሩ በምርምር መረጋገጡን የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ሪፖርተር መጽሔት፣ በሙያቸው ጠቅላላ ሐኪም የሆኑትንና ፒፕል ቱ ፒፕል ዩኤስኤ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር፣ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ክፍል ከፍተኛ አማካሪና በኮንቨርሴሽን ስሩ ኔትዎርክ (Conversation Through NetWork) የኢትዮጵያ ተወካይ የሆኑትን ዶ/ር ቅድስት ተሾመን እንግዳ አድርገናቸዋል፡፡
https://bit.ly/2WWrXfO

@EthioReporterMagazine
ከጦር ጀግኖች ባሻገር . . .
“ለኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ የሚጠቅም ነገር አላቸው” ከጦር ጀግኖቻችን ባሻገር በኢኮኖሚው ዘርፍ፣ በሕክምና፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በሙዚቃ፣ በሥዕል አስተዋፅኦ ያደረጉ ሰዎቻችንን እንደ ብሔራዊ ጀግና መመልከት ላይ ደካሞች ነን፡፡ https://bit.ly/3669ba0

@EthioReporterMagazine
ድል አብሳሪዎቹ ጀግኖች ኢትዮጵያውያት

ይህቺ ታሪካዊት ቀን ለአፍሪካውያን እንደ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ይቆጥሯታል፡፡

“በሳል፣ በጉንፋን የምትሞተውን ሞት ከሩቅ አገር እኛን ለማጥቃት ለመጣው ጠላታችን ባገርህና በርስትህ በቤትህ ላይ ሁነህ መመከት አቅቶህ ላገርህ ኢትዮጵያ ሞት ብትነፍጋት፣ ደምህንም ሳታፈስ ብትቀር በፈጣሪህ የምትወቀስበት በዘርህ የምትረገምበት ነውና የተለመደ የጀግንነት ልብህን ሳታበርድ፣ ወደፊት የሚቆይህን ታሪክህን እያሰብህ ጠንክረህ ለመዋጋት ቆርጠህ ተነሣ” https://bit.ly/2XaNgtW

@EthioReporterMagazine
በ ኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው የ ኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ብዛት ሥጋት ፈጥሯል

አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ -19) ተጠቂዎች ቁጥር ከመቶ በላይ መድረሱ በተለይ በ አዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ሥጋት ፈጥሯል፡፡

አብዛኛዎቹ የቫይረሱ ተጠቂዎች ከአዲስ አበባና ከሶማሌ ክልል የተገኙ ቢሆንም ከትግራይ፣ ከአማራ፣ ከኦሮሚያና ከደቡብ ክልልም በመገኘታቸው ወረርሽኙ ወደ ክልሎችም እየተሠራጨ መሆኑን ያሳያል፡፡
https://bit.ly/3g16Kdm

@EthioReporterMagazine
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያመሰቃቀለው የትምህርት ሥርዓት

የኮሮና ቫይረስ በዓለም የትምህርት ሥርዓት ላይ ትልቅ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡ በዓለም ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጭ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የሕጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) ይህንን ቁጥር 1.6 ቢሊየን እንደሚደርስ ይገልፃል፡፡ ይህን ያህል ቁጥር ያለው ተማሪ ከትምህርት ገበታው ሲናጠብ በዓለም ላይ ይህ የመጀመሪያው ክስተት እንደሆነም ይናገራል፡፡

https://bit.ly/2zSB6ho

@EthioReporterMagazine
መንግሥትንና ተፎካካሪ ፓርቲዎችን እያወዛገበ ያለው አገር አቀፍ ምርጫ

ከአምስት ዓመታት በፊት በ2ዐዐ7 ዓ.ም. በተደረገው አምስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ፣ መቶ በመቶ አሸናፊ የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞከራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) አንድ ዓመት እንኳን ሳይሞላው ከሁለት ጊዜ በላይ ካቢኔውን ቢቀያይርም አገሪቱን በተረጋጋ ሁኔታ መምራት ባለመቻሉ የበላይ አመራሩ በ2ዐ1ዐ ዓ.ም. መጋቢት ወር መገባደጃ ላይ ተቀይሯል፡፡
https://bit.ly/36gQVL8

@EthioReporterMagazine
ኮሮና ቫይረስ እየደቆሳቸው ያሉ አነስተኛና ጥቃቅን ነጋዴዎች

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱ ይፋ ከተደረገ ሁለት ወር ሞልቶታል፡፡ ምንም እንኳን እስካሁን የቫይረሱ ሥርጭት በአንጻራዊነት (ቫይረሱ በስፋት ጉዳት ካደረሰባቸው አገሮች አንጻር) አነስተኛ ቢሆንም ወረርሽኙ በኢኮኖሚው ላይ ትልቅ ጉዳት ማድረሱን ቀጥሏል፡፡ የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት ሲባል እየተወሰዱ ያሉ እንቅስቃሴዎችን የመግታት፣ ስብሰባዎችንና ሁነቶችን የመሰረዝ፣ ትምህርት ቤቶችን የመዝጋት ወዘተ እርምጃዎችን ተከትሎ፣ የምርታማነት መቀነስ፣ ፍላጎትና የአቅርቦት አለመጣጣም፣ የእሴት ሰንሰለት መዳከም በመፈጠሩ ምክንያት በርካታ የንግድ ሥራዎች ላይ መዳከም እያስከተለ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን ኢኮኖሚያዊ ጉዳቱ…….

Read More at: https://bit.ly/3gdGrjZ
Like Our Facebook Page at https://bit.ly/3bQvdys

@EthioReporterMagazine
ከኮቪድ-19 ለኢትዮጵያውያን የተጻፈ ደብዳቤ

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች፣ እኔ ኮቪድ-19 ውዲቷን አገራችሁን ልጎበኝ ከመጣሁበት ዕለት ጀምሮ የየዕለት ኑሯችሁን በጥልቀት እንድታዘብ ከፍተኛ ዕድል አግኝቻለሁ፡፡ ዋነኛ የመወያያ ርዕሰ ጉዳያችሁ በመሆኔ ስለእኔም ሆነ ስለእናንተ ብዙ እንዳውቅ ረድታችሁኛል፡፡ በቆየሁባቸው ጊዜያት ስላለፈ ታሪካችሁ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎቻችሁ ብዙ ሰምቻለሁ፡፡ ብዙም አይቻለሁ፡፡ የእኔንም የእናንተንም መጨረሻ ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንብኝ ይችን ደብዳቤ አስቀድሜ ልጽፍላችሁ ወደድኩ፡፡ የምር ግን ንትርካችሁን ተዋችሁት?

read more at: https://bit.ly/3d4x709
like our facebook page at https://bit.ly/3bQvdys

@EthioReporterMagazine
“የሕዝብ ጥቅም እራሱን ችሎ ሕግ ሊወጣለትና በዝርዝር ሊቀመጥ ይገባል”

ስለ ጥቅም ሲነሳ ሊታሰቡ የሚችሉ የተለያዩ ዓይነት ጥቅሞች አሉ፡፡ የግል፤ የቡድ፤የሕዝብና የመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጣቸው ናቸው፡፡ ጥቅም የራሱ መገለጫና ዓይነት ቢኖረውም፤ በዋናነት የሕዝብ ጥቅም ግን ለየት ይላል፡፡ መክንያቱ ደግሞ ጥቅል ስለሆነና ምን ማለት እንደሆነ በሕግ በዝርዝር ባለመቀመጡ ነው፡፡ የሕዝብ ጥቅም ትርጉም ተሰጥቶት በግለጽ ባለመቀመጡ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝን መሆኑን በርካቶች ሲናገሩ ይሰማል፡፡ የሕዝብ ጥቅም የሚለው በጥቅል በመቀመጡ፤ መንግስት የፖለቲካ መሳሪያ አድርጎ ዜጎችን ማሰሪያና መፍቻ በማድረግ እንደፈለገ እየተጠቀመበት ነው የሚሉም አሉ፡፡

ሪፖርተር መጽሔትም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙትንና ከ 30 ዓመታት በላይ በሕግ ኤክስፐርትነት፤ በዳኝነት፤ በዩኒቨርስቲ መምህርነት፤ በጥብቅናና አማካሪነት ሰፊ ልምድ ያላቸውን፤ ታዋቂውን የሕግ ባለሙያ አቶ ፊሊጶስ ዓይናለምን “የሕዝብ ጥቅም ምንድን ነው ” በሚለው ጥያቄ ዙሪያ የአደባባይ አምዱ እንግዳ አድርጓቸዋል፡፡

read more at: https://bit.ly/2ypEPTf
like our facebook page at https://bit.ly/3bQvdys

@EthioReporterMagazine
የፍርድ ቤቶች መዘጋት በማረሚያ ቤት ከሚገኙ እስረኞች መብት አንፃር እንዴት ይታያል?

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 መግቢያ ላይ፣ ኮሮና (ኮቪድ-19) በዓለም አቀፍ ደረጃ በፍጥነት እየተሠራጨና ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለ ወረርሽኝ በመሆኑና በመደበኛ የመንግሥት አሠራር ሥርዓት ሥርጭቱን መከላከልና መቆጣጠር የማይቻል ስለሆነ፣ የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጁን የማውጣት አስፈላጊነት በግልጽ አስቀምጧል፡፡ https://bit.ly/2A1qqgv

@EthioReporterMagazine
የዱር እንስሳት በአንድነት ፓርክ

በቀደመው ዘውዳዊ ዘመን፣ ታች ግቢ ይባል የነበረው ታላቁ ቤተ መንግሥት ዘዳግማዊ ምኒልክ፣ በቅርቡ በመንግሥት በተደረገለት የማሻሻልና የማዘመን ሥራ የዱር እንስሳት ፓርክ ባለቤት መሆን ችሏል፡፡ ፓርኩ የተለያዩ አራዊትንና ሌሎች እንስሳትን በእቅፉ ይዟል፡፡ ፎቶዎቹ የፓርኩን ከፊል ገጽታዎች ያስቃኛሉ፡https://bit.ly/2X0kxJH

ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ ይከታተሉን:
Telegram:https://bit.ly/2X3oOdZ
Facebook: https://bit.ly/3bQvdys
Twitter: https://bit.ly/2AVPBBG

@EthioReporterMagazine
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየምን ምን አጠፋው?

የሰው ዘር አመጣጥ ሙዚየም ዕቅድ እምን ደረሰ?
ከካዛንቺስ ስድስት ኪሎ ተሳፋሪዎችን ይዞ ሚኒባስ ታክሲ እያመራ ነው፡፡ በሚያዝያ 27 አደባባይ በኩል አራት ኪሎንና ቅድስት ማርያምን ሲያልፍ ከተሳፈሩት ሁለቱ ወጋቸውን ቀየሩ፡፡ ‹‹አንተዬ ብሔራዊ ሙዚየም ስሙ ተቀይሯል፣ የለም እየተባለ ነው›› ይለዋል፡፡ https://bit.ly/36qnNRy

ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ ይከታተሉን:
Telegram:https://bit.ly/2X3oOdZ
Facebook: https://bit.ly/3bQvdys
Twitter: https://bit.ly/2AVPBBG

@EthioReporterMagazine
ዕድሜ ጠገቡ የኢትዮጵያ ዝሆን ሕይወት አለፈ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኘው ጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ይኖር የነበረው ዕድሜ ጠገቡና ዝነኛው ዝሆን፣ ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም. ሕይወት ማለፉን የፓርኩን ኃላፊ ጠቅሶ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ https://bit.ly/2ZBTeXI

ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ ይከታተሉን:
Telegram:https://bit.ly/2X3oOdZ
Facebook: https://bit.ly/3bQvdys
Twitter: https://bit.ly/2AVPBBG

@EthioReporterMagazine
እንስሳትን በሰላም የማሰናበት እንቅስቃሴ
በብዛት የአዲስ አበባ ጥግ ላይ ቆመው ሲተክዙ ይታያሉ፡፡ የሆነ ነገር በመጠበቅ ላይ ያሉም ይመስላሉ፡፡ እንቅስቃሴ የላቸውም በዚያው ተፈጥረው እዚያው ኖረው እዚያው የሚሞቱ ነው የሚመስሉት፡፡ ነገር ግን ሀቁ ሌላ ነው፡፡ https://bit.ly/3d5PAt9

ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ ይከታተሉን:
Telegram:https://bit.ly/2X3oOdZ
Facebook: https://bit.ly/3bQvdys
Twitter: https://bit.ly/2AVPBBG

@EthioReporterMagazine
ፈታኝ ጊዜያትን ለማለፍ ጥንቃቄና ብልሃትን መሣሪያ ማድረግ ግድ ይላል!

የሰው ልጅ በሠራቸው ከጅምላ ጨራሽ እስከ ነፍስ ወከፍ የጦር መሣሪያዎች አንዱ በሌላው ላይ ለመንገሥ በሚያደርገው ሽኩቻ፣ ዓለም በቀውስ ውስጥ ሆና መቀጠል እንዳለ ሆኖ፣ ሁሉንም እኩል ያደረገና ማንም በማንም ላይ ኃይሉን የማያሳይበት ሌላ የዓለም ፈተና ወረሽኝ ከተከሰተ ወራት ተቆጥረዋል፡፡ ኖቭል ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) በቻይና ሁቤ ግዛት ውሃን ከተማ ውስጥ ባለፈው ዲሴምበር መጨረሻ ላይ የተከሰተው ይህ ወረርሽኝ በአራት ወራት ውስጥ ከ290,000 በላይ ሰዎችን ሕይወት አጥፍቶ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ደግሞ የቫይረሱ ተጠቂዎች እንዲሆኑ አድርጓል፡፡https://bit.ly/2XioUA1

ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ ይከታተሉን:
Telegram:https://bit.ly/2X3oOdZ
Facebook:https://bit.ly/3bQvdys
Twitter: https://bit.ly/2AVPBBG

@EthioReporterMagazine
ለ2013 በጀት ዓመት ከ476.3 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ቀረበ

የሚኒስትሮች ምክርቤት ለ2013 በጀት ዓመት 476,012,952,445 ብር ረቂቅ በጀት እንዲያጸድቅለት፡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ግንቦት 29 ቀን 2012 ዓ.ም ውሳኔ አሳልፎ ልኳል።

ምክር ቤቱ ለፌደራል መንግስት መደበኛ ወጪ 133,321,561,063 ብር፣ለካፒታል ወጪዎች 160,329,788,483 ብር፣ለክልሎችየሚሰጥ ድጋፍ 176,361,602,899 ብር እና ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያ ድጋፍ 6,000,000,000 ብር ፡ በድምሩ 476,012,952,445 ብር ረቂቅ በጀት አጽድቆ ለምክር ቤቱ ልኳል።

ሙሉውን ጽሑፍ ለማንበብ
https://bit.ly/30eZG7d

ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ ይከታተሉን:
Telegram:https://bit.ly/2X3oOdZ
Facebook:https://bit.ly/3bQvdys
Twitter: https://bit.ly/2AVPBBG

@EthioReporterMagazine
“ኢትዮጵያ በኢየሩሳሌም” ዓውደ ጥናት

በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን ጋር በመተባበር “ኢትዮጵያ በኢየሩሳሌም” በሚል ርዕስ ያዘጋጀው ዓውደ ጥናት (ዌብናር ሲምፖዚየም) ሰኔ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደሚጀመር አስታወቀ፡፡

ሙሉውን ጽሑፍ ለማንበብ
https://bit.ly/2MBbatZ

ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ ይከታተሉን:
Telegram:https://bit.ly/2X3oOdZ
Facebook:https://bit.ly/3bQvdys
Twitter: https://bit.ly/2AVPBBG

@EthioReporterMagazine
ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመስደብ ብለው የተቋቋሙ ሚድያዎች እንዳሉና እነሱንም በገንዘብ የሚደግፉ ባለሀብቶች እንዳሉ እንደሚታወቅም ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ(ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ተናገሩ።

ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ ይከታተሉን:
Telegram:https://bit.ly/2X3oOdZ
Facebook:https://bit.ly/3bQvdys
Twitter: https://bit.ly/2AVPBBG

@EthioReporterMagazine