ስብዕናችን #Humanity
27.8K subscribers
1.66K photos
76 videos
23 files
54 links
🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot
Download Telegram
ለምሽታችን
💚

እነሆ ሃይማኖተኛ! እነሆ ሙስሊም!

-----
ናይጄሪያዊው የ84 ዓመት አዛውንት ኢማም አብዱላሂ አቡበከር በሰኔ 2018 በናይጄሪያ
ተከስቶ በነበረው ሃይማኖታዊ ግጭት የ300 መቶ ክርስቲያኖችን ህይወት በመታደግ
የመጀመሪያውን "የዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነፃነት" ሽልማት ከአሜሪካ ተበርክቶላቸዋል።
--------
የ84 ዓመቱ አዛውንት የእራሳቸውን ህይወት ለአደጋ አጋልጠው ክርስቲያን ሴቶችን ቤታቸው
ውስጥ ወንዶችን ደግሞ መስጊድ ውስጥ በመደበቅ ነው ህይወታቸውን ከፉላኒ የከብት
ጠባቂዎች ጥቃት የታደጉላቸው። ከኢማሙ በተጨማሪ በእዚሁ ስነ ስርዓት ላይ የብራዚል፣
የኢራቅና የሶሪያ ዜጎች ሽልማት አግኝተዋል።
---------
በአለማችን እንደ እነዚህ ዓይነት ቅን ሰዎች ባይኖሩ ምን ይውጠን ነበር?

----------------------------------------


በረካ ሁን! !!!

ሸርም በረካ ሁን ፤
ኸይርም በረካ ሁን ፤
ከተዘራህበት ታፈራለህ አሁን ።

ሸጋ ምሽት ይሁንልን !💚💛❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@balmbaras
ለውብ ጁመኣ

💚

የሱፊው ባህሉል አንድ ቀን ንጉሱን ሀሩንን ለማግኘት ችቦ ለኩሶ ወደ ቤተመንግሥታቸው
ይሄዳል።


ለረዥም ቀናት ጠፍቶና ሳያዩት የከረመው አጫዎቻቸው ባህሉል ሲመጣ ተመልክተው
ንጉሱ ቢደሰቱም በእጁ በእሳት የተቀጣጠለ ችቦ ይዞ ሲመለከቱ ደግሞ መልሠው ደነገጡ።


ባህሉል! የት ጠፍተህ ከረምህ?" ይሉታል


ባህሉልም ንጉሥ ሆይ!ገሀናም ሄጄ ነበር "
ይላቸዋል።


በባህሉል መልሥ ፈገግ ያሉት ንጉሥ ታድያ በእጂህ የያዝከው እሳት ከዚያ የመጣ መሆኑ
ነው? ይሉታል።


የለም ንጉሥ ሆይ! በገሀናም እሳት ሥለሌለ እንድለኩስ መልሰው ወደምድር ልከውኝ ነው
ይላል።


ንጉሡም በገሀናም እሣት የለም እንዴ? በማለት ተደንቀው ቢጠይቁት?


ባህሉል ንጉሥ ሆይ እያንዳንዱ ሠው የራሱን እሣት እየለኮሰ ወደ ገሀናም ይገባል እንጂ
በዚያ የተዘጋጀ እሳት የለም በማለት መለሠላቸው።

ሸጋ ጁምኣ!!💚💚💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
🌨ትዕግስት

🌧ትንሽ ትግስት ስላለህ ብቻ ምን ያህል ችግር ተቋቁመህ እንዳለፍክ እስኪ ወደኋላ ዞር ብለህ ተመልከት፡፡

🌧ሰዎች የሆነ ነገር ለመግዛት ሲፈልጉ አቅሙ እስኪኖራቸዉ ድረስ ታግሰዉ ቢቀመጡ ስንት የእዳ ክምር እንደሚቀንሱ ታዉቃለህ?

🌧ትግስት የህይወት እንዱ ቅመም ነዉ፡፡ የማይመቹ መንገዶች ህይወትህን ቢሞሉትም ትንሽ ታገስ...ነገሮች ይለዋወጣሉ: የዛኔ መታገስህ ለመልካም እንጂ ለክፉ እንዳልሆነ ታዉቃለህ

🌧 ትግስት አይታለፉም የተባሉ ክፉ ጊዜያትን እንድታልፍ ያደርግሃል፡፡አምላክህን ትእግስት እንዲሰጥህ እየጠየቅክ ነገሮችን ዝቅ ብሎ ማሳለፉ ለነገ ወሳኝ ሚና ይጫወታል

🌧ትግስት አጥቶ ስንቱ ሰዉ አላማዉን እንዳይነሳ አድርጎ ገደለዉ?ተስፋዉን እንዳይለመልም አድርጎ ቆረጠዉ!

🌧አንተም ከማይታገሱት ጎራ እንዳትሆን እራስህን መልካም ፍሬ ባለበት በትእግስት ሰፈር አሳርፍ!

መልካም ቀን ለሁላችን!
ከልብ እንወዳችኋለን🙏
🌧🌧🌧🌧🌧🌧🌧🌧🌧🌧
👉@Ethiohumanity @Ethiohumanity
የተሰማችሁን ሀሳብ አስተያየት መሰጠት ላይ አትርሱን @Abysiniansbot
ለምሽታችን
💚💚💚

እውነትም የት ነበርሽ! !!!!!!
በ1997አም በነበረው የምርጫ ሰሞን አዲስ አበባ ላይ ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ በተባለ
ድርጅት እየተሰናዳ የሚቀርብና በፖለቲከኞች መሃከል የሚደረግ የውይይት መድረክ ነበር ።
ከእለታት አንዱ ቀን በነበረ የፖለቲካ ውይይት ላይ ክርክሩ ጣእም እያጣ ሲመጣ በድንገት
ከተወያዮቹ መሃከል አንዲት ማየት የተሳናት ትንታግ ወጣት እጅግ አስገራሚና ውይይቱን
ነፍስ የሚዘራበት ንግግር ይዛ ስትገለጥ መድረኩን ሲመሩ የነበሩት ጠበቃ ማርቆስ
ወልደሰንበት በንግግሯ ሃይልና ለዛ ተማርከው ኖሮ '''"" እውነትም የት ነበርሽ! !!!"" " ሲሉ
ታዳሚውን በሳቅ ገደሉት ። ያኔ በቴሌቪዥን የተመለከታት ህዝብ እደጊ ተመንደጊ ብሎ
ያልመረቃት አልነበረም ።
ይህች ሳተና ሴት ወይዘሮ የትነበርሽ ንጉሴ ናት ። እጅግ ገጠራማ ከሚባለው ደቡብ ወሎ
አማራ ሳይንት ምድር የበቀለችው ይች ጀግና አካል ጉዳትና የገጠር ልጅነት ሳይበግራት
ፈተናውን ሁሉ አልፋ በአዲስ አበባ university ህግ ትምህርት ክፍል የህግ ትምህርቷን
ከጨረሰች በሃላ ከአካል ጉዳተኝነት ጋር በተያያዘ በርካታ ስራዎችን በመስራት የብዙዎች
አካል ጉዳተኞችን ህይወት የሚለውጥ ስራ በመስራቷ በአለም አቀፍ ደረጃ ከNobel Prize
ጋር የሚተካከለውን የ 2017 Right Livelihood Award የተሰኘውን ከፍተኛ ሽልማት
ያሸነፈች ሲሆን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ተሸልማለች ። በነገራችን ላይ የትነበርሽ
ንጉሴ ባለ ብዙ ተሰጥኦ ሴት ስትሆን ከህግ ሙያዋ በተጨማሪ የግጥምና የሙዚቃ ተሰጥኦ
ያላትና በአነቃቂ ንግግሮችዋ ተሰምታ የማትጠገብ አርአያነት የሞላባት ጀግናችን ናትና
ይህን ሽልማት በማግኘትዋ ሃገራችን ልትኮራ ይገባታል! !!! ይህችን የምታሳሳ እህታችንን
ፈጣሪ አምላክ ተሰጥኦ ፤ ችሎታና መልካምነትን አሟልቶ የሰጣት በመሆኑ ገና ገና አለምን
የሚያነጋግር ታሪክ ሰርታ እንደምታስደስተን ዛሬም ነገም እናምናለንና ጤናና እድሜ አብዝቶ
ይሰጣት ዘንድ ምኞታችን ነው! !!!
አንች ጀግና ልጅ ኩራታችን ነሽና በረካ ሁኝ! !! እውነትም የት ነበርሽ!!!!
-------------------------------------------------

የት ነበርሽ? ?!!

ከጦቢያ ሴት መሃል ፤
ፈልጌ ነበረ ፤
ልክ እንደተዋበች ልክ እንደጣይቱ ፤
ተራራ የሚያፈርስ ድብ የሚነቀንቅ ፤
በገሞራ ወኔ፤ በውብ አንደበቱ ።
አጥተን ተስፋ ቆርጠን በተቀመጥንበት፤
ፈልገን ፈልገን ከቆላ እክከ ደጋ ፤
በቀያችን ጠፍቶ ፤
ልክ እንደጣይቱ ፤
ሙልት ባለው ልቡ ፤
ጉም የሚተረትር ፤ ጨለማ ሚያስነጋ ።
ይቅር በቃ ብለን ፥
ደክሞን ተዝለፍልፈን ፤
እጅ ልንሰጥ ሲያምረን ፤
እንደ ማታ እንግዳ ፤
እንደ ብራ ኮከብ ድንገት የተገኘሽ ፤
ሰው አጥተን ስንባጅ ፥
እስከዛሬ ድረስ አንች ልጅ የት ነበርሽ? ??
እውነትም የት ነበርሽ? ???!!!!!


((( ጃኖ ))(💚💛❤️

ሸጋ ሸጊቱ ምሽት!!!!💚💛❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@balmbaras
ለቅዳሚታችን
💚


ነጻነት ዓላማ ከሌለው፣ በሰው ልጆች ልብ ውስጥ የተቀረጸውን ሕግ ለማወቅም
ካልተመኘና የኅሊናንም ድምጽ መስማት ከተሳነው፣ ኅብረተሰብንና የሰው ልጅን ማጥፋት
ይጀምራል።


ሊዮ ቶልስቶይ እንደሚለው ነፃነትን መገንዘብ ያልቻለ ሰው ሕይወትንም መገንዘብ
አይችልም፣ …ምክንያቱም የሰው-ልጅ ጥረት ሁሉ፣ ለሕይወት ያለው ስሜት በሙሉ፣
‘ነፃነት’ን ለማሳደግ ብቻ ሲባል የሚደረግ ነው።
------------------------------------------

የኔ መንገድ!!!!!


ከባርነት ጫጉላ፤
ከግርድና ማጀት፤
ና ውጣ ተብየ፤
የተጠራሁበት፤
የተቀባሁበት፤
የተመረጥኩበት፤
የልቤን ከነአን፤
በነፍሴ ሰሌዳ፤ በደም ቀለም ፅፌ፤
እንደ ኢያሱ ካሌብ፤
ከነአንን ወረስኳት፤
የሞት ውሽንፍሩን፤ ባህሩን አልፌ።


ፈርኦን ሞኝ ነው፤
ተከትሎኝ ነበር፤
በግዞት ማድጋ ፤
መልሶ ሊግተኝ፤ የምሬት ሰፍነጉን፤
ተመለስ እያለ፤
እያግተለተለ፤
የፉከራ ሰልፉን፤ የትእቢት ፈረሱን።


እናም እንደዚህ ነው፤
በሰው መንገድ ቀንተው፤
በሄድኩበት ዱካ፤
እንሂድ እናስቀረው፤ ብለው የፎከሩ፤
ባህሩ ተከፍሎ፤
መልካውን ስሻገር፤
መንገዱ በላቸው፤ ውሃ ሆነው ቀሩ።


ይኸው በኔ ቀዬ፤
የሰው መንገድ ጥጉ፤
ለነሱም የሚሆን እየመሰላቸው፤
በሰው መንገድ ቀንተው፤
ከመንገድ ሊያስቀሩኝ፤
መንገድ የጀመሩ፤
እንደ ፈርኦን ጦር፤ ቀይ ባህር ዋጣቸው።

((( ጃ ኖ )))💚💛❤️

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!!!

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@balmbaras
🤔እኔ ማን ነኝ ብለህ እራስህን ጠይቀው ማንነትህን ጠንቅቀህ ስታውቅ ዋጋህን ታውቀዋለህ ።
የምትኖርበትን እና የምትኖርለትን ትለያለህ ።
💟ወደ አዚች ምድር የመጣኧው ለምክንያት ነው ፣ ለዓላማም ጭምር ።
አንተ የዚህች አለም ገፅ ውብ እና ሙሉ ይሆን ዘንድ እንደ አንዱ ጡብ ነህ ።
ዋጋህን ባለመኖርህ አትተምን በመኖርህ እንጂ።
የአንተ መኖር ለሌሎቹ ጡቦች ድጋፍ እንዲሁም ለግንባታው ውበት አስፈላጊ ነው።
👉አስታውስ አንተን መሆን የሚችል ምትክ የለህምና እራስህን ጠብቅ።
💡💡💡💡💡💡💡💡💡
@ethiohumanity @ethiohumanity
ለሰንበታችን
💚

የባለ ቅኔው ፈላስፋውና ሰዓሊው ካህሊል ጅብራንን አንብበህ ስታበቃ ራስህን መርምር
ለመረዳትም ሞክር እነሆ በረከት፦


የባለቅኔው ( የገጣሚው) ድምፅ


የሰው ልጅ በመሆንህ ብቻ ወንድሜ ነህ። ሁለታችንም የቅዱስ መንፈስ ልጆች ነን።
ከአንዲት ምድር የተሰራን ፍጡራን።


በሕይወት ጎዳና አብረኸኝ ትጓዝ ዘንድ የእውነታን ምሥጢር እንድንረዳ ታግዘኝ ዘንድ ጓደኛዬ
ነህ። የሰው ልጅ ነህ – ለኔ ይህ በቂዬ ነው – እንደ ወንድሜ እወደሀለሁ። አንተ
እንደፈቀድህ ልትነግረኝ ትችላለህ። ነገ ሲደርስ ንግግርህን እንደማስረጃ ቆጥሮ
ይፈርድበሀል።


ንብረቴን ልትቀማኝ ትችላለህ። ስግብግብ በመሆኔ ያካበትኩት ሀብት ካስደሰተህ
ውሰደው። የፈቀድከውን ልታደርገን ትችላለህ። ነገር ግን "እውነቴን" ልትነካት አትችልም ።


ደሜን ማፍሰስ፤ ሥጋዬን ማቃጠል ትችላለህ። ሆኖም መንፈሴን መጉዳት አትችልም።
እግርና እጄን በሰንሰለት አስረህ ጨለማ ውስጥ ልታሥረኝ። ትችላለህ። ሆኖም ግን ነፃ
አስተሳሰቤ በሰፊ ሰማይ ላይ ትንሳፈፋለችና ማን ሊያሥራት ይችላል?


ወንድሜ ነህና እወድሀለው። ባንተ ቤተ ክርስቲያን አመልካለሁ ፤ በመቅደስህ እንበረከካለሁ
፤ በመስጊድህ እሰግዳለሁ። እኔና አንተ የአንድ ሀይማኖት ልጆች ነን።
የሃይማኖት መንገዳችን ቢለያይም መንገዶቻችን በሙሉ የአንድ ፈጣሪ እጅ ጣቶች ናቸው።
የፈጣሪ እጅ ለሁላችን ሙላትና የመንፈስ ስጦታ የተዘረጋ ነው።


በእውቀት ዐይኔ ባላየውም ስለ እውነታ ስል እወደሀለሁ። የሁለታችን እውነቶች
በሚመጣው ዓለም እድ ለእጅ ተያይዘው አንድ ዘላለማዊ እውነት በመሆን ይመርጣሉ።
በፍቅር በውበት ለዘላለም ይኖራሉ።


በጨቋኝ ፊት ደካማ ፤ በስግብግብ ባለፀጋ ፊት ደግሞ ደሃ በመሆንህ እወደሀለሁ።
በዚህም ምክንያት እያነባሁ አቅፍሃለሁ።


የእንባዬ ጀርባ የፍትህን እጅ አቅፈህ ተፈረዱብህን ይቅር ስትል አይሃለሁ። ወንድሜ ነህና
እወደሀለሁ።



ፍቅር ወደ ፈጣሪ መድረስ ማለት ነው❗️❗️

መልካም ሰንበት !!!

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@EthioHumanity
ለውብ ቀን
💚

ፍቅር መስጠት እና መቀበል ነው፡፡ የሰጠውም አልተጐዳም የተቀበለውም አላተረፈም፡፡
ሙሉነትን ለመመዘን ጐዶሎ ማነፃፀሪያዎች አያገለግሉም፡፡


ወሳኙ የምትሰጠው መጠን ትንሽነትና ትልቅነት ሳይሆን በምትሰጠው ነገር ላይ
የምትጨምረው ፍቅር ነው።

ውብ ቀን!💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
💚💛❤️ እራስን ሆኖ መጓዝ ብልህነት ነው‼️
. . . . ብሎ የተነሳው የስብዕና ቻናላችን. . .
በአብሮነት ከእናንተው ጋር ተጉዞ አሁን ላይ ደርሷል
. . . ከጎናችን በመሆን አጋርነታቹን እደምሰሶ ላፀናቹልን ቤተሰቦቻችን ልባዊ ምስጋናችንን እያቀረብን . . !!

እደትላንቱ ዛሬም ታስፈልጉናላቹ እና ቤታችንን በአዲስ መልክ እንድንገባ
. . . *🌱ምን ይጨመር?
. . * 🌱ምንስ ይቀነስ?
. . . . .ስለቻናሉ የሚሰማቹን. . 🌱

የተሰማቹን አጋሩን!!! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣
ሃሳባቹን እዚች ላይ ፃፍፍ አርጉልን
👇👇👇👇
@Abysiniansbot @Abysiniansbot


🙏. . . .ለአብሮነቶ እናመሰግናለን!!!

ሁሉም የለንምና በእናንተ ሀሳብ
የጎደለውን እንሞላለን!!💛
@EthioHumanity @EthioHumanity
ለምሽታችን
💚💚💚

እንደ አውሮፓዊያን የዘመን ቀመር በ 1926 አንድ ታዋቂ የሩሲያ ደራሲ በድብርትና በሐዘን
ስሜት በመሰቃየቱ ህክምና ለማግኘት ወደ ስነ ልቦና ሐኪም ጎራ አለ።


ከምርመራው በኋላ
የሐዘን ስሜት የሚያጭሩ ተረቶችን ከማንበብ ታቅቦ በምትኩ ደስታና ሳቅ የሚፈጥሩትን
እንዲያነብ ሐኪሙ መከረው። እንዲያውም አስቂኝ የሆኑትን የሚኻኤል ዞሼንኮን (Mikhail
Zoshchenko) ድርሰቶች ቢያነብ በጤናው ላይ አመርቂ ለውጥ እንደሚያመጣ አበክሮ
አስረዳው።

ግና ደራሲው የሰጠው መልስ ሐኪሙን በድንጋጤ እንዲዋጥ አደረገው-
«ሚኻኤል ዞሼንኮ ማለት እኔ ነኝ» ብሎ።


አሜሪካዊው ጸሐፊ አልበርት ሐበርድ
«ለሌሎች የመጽናኛ እና የደስታ ስሜት ፈንጣቂ የሆኑ ብቁ ሰዎች ብዙ ጊዜ ራሳቸውን
ለማጽናናት ሳይቻላቸው ይቀራሉ» ይለናል። ራስህ የፈጠርከው መድሃኒት ለሌሎች ፍቱን
ሆኖ ያንተን በሽታ ለማርከስ ሲሰንፍ እንደማለት ነው።

---------------------------------------------


የማይነጋ ሕልም ሳልም
የማያድግ ችግኝ ሳርም
የማይድን በሽታ ሳክም
የሰው ሕይወት ስከረክም
እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም፡፡

©ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን💚💛❤️



ሸጋ ምሽት💚!

@EthioHumanity
@EthioHumanity
🌊ካህሊል_ጂብራን የተወለደው እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር ጥር 6 ቀን 1883 ዓ.ም. ብሻሪ በምትባል የሊባኖስ አካባቢ ነበር፡፡ ይህ የጥበብ ሠው ወጣት እያለ ከቤተሠቦቹ ጋር በመሆን ወደ አሜሪካ በስደት አቀና፡፡ በአሜሪካም የጥበብና የስነፅሁፍ ትምህርቶችን ጀመረ፡፡ ካህሊል ጂብራን በአረብኛ እና በእንግሊዘኛ መፃፍ ይችል ነበር፡፡

💨በዓረቡ ዓለም ካህሊል ጂብራን የስነፅሁፍና የፖለቲካው አማፂና ተቃዋሚ ተደርጎ ነው የሚታየው፡፡ የካህሊል ጂብራን ግነት የበዛበት የአፃፃፍ ስልቱ የዘመናዊውን የዓረብ ስነፅሁፍ እንዲነሳሳ ሞተር ሆኖ አገልግሏል፡፡ የዚህ ምርጥ የጥበብ ሠው የስነፅሁፍ አፃፃፍ ዘይቤ ጥንታዊውን የዓረብ የስነፅሁፍ ትምህርት አሽቀንጥሮ እንዲጥል አድርጎታል፡፡ በሊባኖስ ካህሊል ጂብራን እስካሁን ድረስ የስነፅሁፍ ጀግና በመባል ይዘከራል፡፡

💨ካህሊል ጂብራውን በእንግሊዘኛ ተናጋሪ አድናቂዎቹ ዘንድ የሚታወቀው እንደ እ.ኤ.አ. በ1923 ዓ.ም. ያሳተመው ‹‹The Prophet›› በሚለው መፅሃፉ ነው፡፡ ይህ መፅሃፍ ልቦለዳዊ ይዘት ያለው ቢሆንም በውስጡ ግን ሠዎችን የሚያነሳሱ፣ ፍልስፍናዊ ይዘት ያላቸው ፅሁፎች እና ግጥምን በዝርው የአፃፃፍ ስልት በመጠቀም ለዓለም ያበረከተው ድንቅ መፅሐፉ ነበር፡፡

🔱ካህሊል ጂብራን በዓለም ዘንድ ከሼክስፔርና ከላኦዝ ቀጥሎ ምርጡ ሶስተኛ ገጣሚ ነው፡፡

ምርጥ_20_የካህሊል_ጂብራን_አባባሎች 🔱

1. ‹‹ ቁንጅና ያለው ፊት ላይ አይደለም፡፡ ቁንጅና በውስጣችን የሚገኝ የልብ ብርሃን ነው፡፡ ››

2. ‹‹ አዋቂ ሠው ሁለት ልብ አለው፡፡ አንዱ ሲደማበት በሁለተኛው ይታገሳል፡፡ ››

3. ‹‹ እምነት እውነትነቱን ከማረጋገጥ ባሻገር በልብ ውስጥ የሚገኝ እውቀት ነው፡፡ ››

4. ‹‹ ኢምንቷ የደግነት ስራ ትልቁን ነገር ለማድረግ ከማሰብ በላይ ዋጋ አላት፡፡ ››

5. ‹‹ ፍቅር የሚያንቀጠቅጥ ደስታ ነው፡፡ ››

6. ‹‹ እውነት እርቃኑን በባዶው መራመድ ይችላል፡፡ ውሸት ግን ሁልጊዜ አምሮና ደምቆ መልበስን ይፈልጋል፡፡ ››

7. ‹‹ ኩሩ መሆን ማለት ከምትፈልገው በታች መውሰድ ማለት ነው፡፡ ››

8. ‹‹ ፍቅር የመለያያ ሠዓቱ እስኪደርስ ድረስ የራሱን ጥልቀት አይረዳም፡፡ ››

9. ‹‹ ወንድ ሁለት ሴቶችን ይወዳል፡፡ አንደኛዋ በአዕምሮው የሚስላት ስትሆን ሁለተኛዋ ግን ገና አልተወለደችም፡፡ ››

10. ‹‹ ልክ እንደ አበባ ሁን፡፡ ፊትህን ወደ ፀሃይ ብርሃን አዙር፡፡ ››

11. ‹‹ ሐዘንና ደስታ የማይነጣጠሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ሁለቱም አብረው ይመጣሉ፡፡ ነገር ግን አንዱ ብቻውን ከጎንህ ሲሆን አንደኛው መኝታ ቤትህ እንደተጋደመ አትርሳ፡፡››

12. ‹‹ በአንድ ሕይወት ውስጥ ወደ ኋላ እየተመለከቱ መደሠት መቻል ሁለቴ መኖር ማለት ነው፡፡ ››

13. ‹‹ ፍቅርና ደግነት የድክመትና የተስፋ መቁረጥ ምልክቶች ሳይሆኑ የጥንካሬና የውሳኔ ሠጪነት መገለጫ ናቸው፡፡

14. ‹‹ ትናንት ለዛሬ ትዝታ ነው፡፡ ነገ ደግሞ የዛሬ ህልም ነው፡፡ ››

15. ‹‹ ጓደኛህ የፍላጎትህ መልስ ነው፡፡ ››

16. ‹‹ የሠውን ልጅ ልብና አዕምሮ ለመረዳት እስካሁን ያሳካቸውን አትይ፡፡ ከእሱ ይልቅ ወደፊት ሊያደርጋቸውን የሚመኛቸውን ተመልከት፡፡ ››

17. ‹‹ የምትወደውን ሠው የፈለገበት ይሄድ ዘንድ ተወው፡፡ ሄዶ ወደአንተ ከተመለሠ ቀድሞውኑ ያንተ ነበር፡፡ ካልተመለሠ ግን ቀድሞውኑም የአንተ አልነበረም፡፡ ››

18. ‹‹ ልክ ወንዝና ባህር አንድ እንደሆኑት ሁሉ ሕይወትና ሞትም አንድ ናቸው፡፡

19. ‹‹ ጓደኝነት የሁልጊዜ ጣፋጭ ሃላፊነት እንጂ አጋጣሚ አይደለም፡፡ ››

20. ‹‹ ፍቅር አልባ ሕይወት አበባ ወይም ፍሬ እንደሌለው ዛፍ ነው፡፡ ››
💨💨💨💨💨💨💨💨💨💨
👉 ለሌሎች በማስተላለፍ በማስተማር እንማር @EthioHumanity @EthioHumanity
ሀሳቦቻችሁን አድርሱን @ABYSINIANSBOT
ለምሽታችን
💚💚💚




ሂትለር የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ነው።ሰይጣን ሰፈር መጠጥ የማይጠጣና
የማይሰክር ሰው በመብራት ፈልጎ ማግኘት ባይቻልም ፤ ሂትለር ግን ወደር የማይገኝለት
ጠጥቶ ንቅንቅ የማይል ፤ ጠጥቶ በቃኝ የማያውቅ ሽንቁር ገንቦ በመሆኑ ነው። ሚስቱ አንድ
ልጁን ቡቾን አስታቅፋው ከሄደች ወዲህ ደሞ ብዙ ይጠጣል። እቤቱ ሲገባ ዋነኛ ተግባሩም
ቡቾን ማሰቃየት ነው። በቀበቶ ይተለትለዋል፤ ቁልቁል አንጠልጥሎ በበርበሬ ያጥነዋል፤
እጅና እግሩን አስሮ ያሳድረዋል። ይሄን ሁሉ የሚያደርገው ሚስቱን ለመበቀል ነው።
" አንተ ተኩላ ! እናትህም በልታ የማትጠግብ የሰው አሳማ ነበረች። በቀን ሁለት ዳቦ
በልተህ ራበኝ ብለህ ታለቅሣለህ!" ሂትለር ይጮሃል።
" አላለቅስም አባዬ፣ ሁለተኛ አላለቅስም!" ቡቾ ያላዝናል።
" አባቴ - አትበለኝ- አባት ይንሳህና! የናትህን ጉድ ያልሰማውልህ መሰለህ? አንተ የኔ ልጅ
ሣትሆን የጣልያኑ የሲኞር ፖውሎ ዘበኛ ልጅ ነህ። ይሄን የጥንቸል ጆሮ የመሰለ ሾጣጣ
ጆሮህን ስመለከት ሁል ጊዜም ይደንቀኝ ነበር- ገና ልጅ ሣለህ ጀምሮ። የዚያ የመንደሩ
አውደልዳይ ኮርማ፤ የሲኞር ፖውሎ ዘበኛም ጆሮው እንዳንተ ሾጣጣ ነበር። ቀበሮ፣ የሰው
ቀበሮ! . . . "ግርፊያው ቀጥሏል፤ የልጅ ጀርባ ይጮሃል፤ አፉ ይለማመጣል።
" እናትህ የት እንዳለች ታውቃለህ?"
"አላቅም፣ አባይዬ"
" አንድ ሸማኔ አግብታ ጥበብ ለብሳለች አሉ። ጧት ላይ ያጠለቀችው ጌጥ ቢሸጥ እኔና
አንተን ይገዛል አሉ። አንተም እንደ እናትህ ብልጥ ነህ?"
"አይደለሁም አባዬ"
"እንግዲህ በአባትህ ወጥተህ ይሆናል። የሲኞር ፖውሎ ዘበኛም እንዳንተው ነጉላ ነበር።
ለመሆኑ ከትምህርት ዓይነቶች የትኛውን ትመርጣለህ?"
"ሣይንስን አባዬ"
" ውሸታም ልጅ ውሸታም ትምህርት ቢመርጥ አይደንቀኝም። ሣይንስ ውሸት ነው። ዝንብ
የጤና ጠንቅ ነች ይላል። የዚህ የሰይጣን ሰፈር ሕዝብ በሚሊዮን ከሚቆጠሩ የዝንብ አብሮ
አደግ ወዳጆቹ ጋር በመከባበርና በመተባበር ሲኖር እንጂ፣ ተቅማጥና ሞት ቀርቶ ቁርጠት
ይዞት አይተሃል?"
"አላየሁም አባዬ!"
"ታዲያስ? እንዳንተ ውሸታም ሣይንስ ግን 'ብርድ የኒሞኒያ መንስኤ ነው' ይላል። እስኪ
በዚህ መንደር እርቃናቸውን ከሚንጦለጦሉ ህፃናት አንድ እንኳን ታሞ የተኛ አይተሃል?!"
"አላየሁም አባዬ"
"ሣይንስ ለዚህ ምን መልስ ይሰጥሃል? የህፃናቱ ቆዳ ከአዞ የተሠራ ነው ሊልህ ነው?
የሣይንስ ውሸት በዚህ ብቻ አያቆምም። 'ጉንፋን ከቆሻሻና ከመጥፎ ሽታ ይመጣል'
ይልሃል። ለመሆኑ እዚሁ ሰይጣን ሰፈር ጠላ ቤቱ አጠገብ የተከመረው ቆሻሻና የሽንት ፍሳሽ
ይታይሃል? ጠላ ነጋዴዋ አሮጊት እንኳን ጉንፋን ሊይዛቸው ሲያስነጥሳቸው ሰምተሃል?!"
"አልሰማሁም አባዬ!" ይላል ቡቾ እየተንቀጠቀጠ
"ሣይንስ ውሸት ነው! አንተም ውሸታም ነህ! የፖውሎ ዘበኛም ውሸታም ነበር"
" ልክ ነህ አባዬ"
"ሌላ የምቶደው ትምህርት ምንድን ነው?" ግርፋቱን ቀጥሏል።
"ህብረት! አባዬ ህብረት!"
ሂትለር ከትከት ብሎ ይስቃል። " 'ከድጡ ወደ ማጡ' አሉ። ህብረት? ይሄም ለኛ ሀገር
አይሠራም። በወፈረ በቀጠነው ለሚጯጯህ፣ አጥንት ላይ እንደ ሰፈረ የውሻ መንጋ እርስ
በእርሱ በሚናጭ ህዝብ መሃል ህብረት ብሎ ትምህርት ውሸት ነው! አንተም ውሸታም ነህ፤
ልክ እንደ ዘበኛው! ሌላ አምጣ!"
"እሽ - ታሪክ አባዬ"
ሂትለር ድምጹን ከፍ አድርጎ ከጣራ በላይ ይስቃል። " ታሪክም ውሸት ነው! እንደኔ፣
እንዳንተ፣ እንደ ሰይጣን ሰፈር ላሉ ነዋሪዎች አይሠራም። ቀድሞ ነገር ደሃ ምን ታሪክ
አለው? የድሃ ታሪክ ቀን ከሌት የማይተኛ ሆዱን ለማሸነፍ የሚያደርገው ተጋድሎ ነው።
ታሪክን ለባለ ታሪኮች ተውላቸው። የሰው አሳማ! ሠርተህ ሆድህን የምትሞላበት ትምህርት
አትመርጥም?!"
"ሂሣብ!" አለ ቡቾ ሲፈራ ሲቸር። ሂትለር ይስቃል። "አሁን ገና ልክ እንደ እናትህ ጦጣ
ሆንክ። ሂሣብ ምን ጊዜም ትክክል ነው። አንድ ብርና አንድ ብር ዘለዓለሙን ያው ሁለት ብር
ነው። እንደ ሣይንስ አይዋሽም። እንደ ህብረት አያፌዝም፣ እንደታሪክ ጀንበር ስትጠልቅ
አይለዋወጥም"
"ልክ ነህ አባዬ"
"ብራቮ ቡቾ ! አራቱን የሂሣብ መደቦች አጣርተህ ካወቅህ ይበቃሃል። እውነቱን ይዘሃል
ማለት ነው። አራቱን የሂሣብ መደቦች አውቀህ ስትጨርስ ንገረኝ። ከዚያ በኋላ ወደ
ትምህርት ቤት አትሄድም። ተምረህ ከምታብድ፣ ደንቁረህ ብትራብ ይሻላል! እሺ ቡቺ?!"
"እሺ አባዬ"
ሂትለር ይኸኔ ልጁን አቅፎ ይስማል። ራሱንም እያሻሸና ከጉያው እያስገባው "ይሄ ሾጣጣ
ጆሮህ ባይኖር እወድህ ነበር ቡቾ" ይለዋል።
"ታዲያ ለምን ሁልጊዜ እሱን እያየህ ከምትደበድበኝ በምላጭ ከርክመህ
አታስተካክልልኝም? ያንተን ሊመስሉ ይችሉ የለም?" የሚል ምላሽ ሲሰጠው ሂትለር ደረቱን
ደግፎ ትንፋሽ እስኪያጥረው ይስቃል።

ከደረጄ በቀለ
"ህያው ፍቅር"
ገፅ 42-44

ሸጋ ምሽት!!💚💚💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
ለውብ ቀን!
💚💚💚

ኢትዮጵያ ሆይ፥ እኛ አንቺን ለምንል ሁሉ ከአንቺ አልጋ የመውረድን ገፊ ምኽኛት ሳናይ
ምጽኣት ይምጣ!
--------
እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ! የምገለጠውም ሆነ ሙሉነት የሚሰማኝ ኢትዮጵያ በያዘችውና
ባቀፈችው ሁሉ የኢትዮጵያዊነት ትርክትና ንግርት ነው።
የሃገሬ "ቅርንጫፎች ግንድ መሆን" ቢያምራቸው በቆየው ስርና ግንድ የኢትዮጵያነት ማማ
ላይ የምቆይ እንጂ ተገንጣይ ቅርንጫፎች ላይ ልወጣ ፍጹም አልሻም። በማያውቁት አዲስ
ጎጆ መውጣት ናፍቆት ነሁልለው በነጻውና ሰፊው አዳራሽ መኖር ሰልችቷቸው፣ በዘር
ማንዘራቸው ስም የቆመ ጠባብ ቀፎ አገር ናፍቋቸው፣ ከሽለመጥማጥ ያምልጥ አያምልጥ
ባላወቁት "እጭ" ውስጥ ገና ያሉ ግርር ብለው ለመብረር፣ የሚንደፋደፍ "አውራቸውን"
ጠባቂ ተፈልፋይ ተስፈኛ ንቦችን ባየሁ ጊዜ አገርን ማፍረስ ጎጆ የመቀለስን ያክል ቀለለ
እንዴ? እላለሁ።


እንዲህም እላለሁ፥ ከትናንት ዛሬ ይበልጣል፥ለብልህም ከዛሬም ነገ ይ'በጃል። ትናንት
ኢትዮጵያዊነት "እኔን አልነበረም" ላሉም ሆነ "ነበርን" ለሚሉ ነገን የተሻለ እናድርግ ቢሉ
ሁላቸውንም የምትመስል ኢትዮጵያን ለመስራት ቀኑ ዛሬ ነው።
ደግሜም እላለሁ፥
የሆነው ሁሉ የኔ ነው!! በሃገሬ ላይ የሆነውን ሁሉ ያደረገ በየዘመኑ የኖረ "በጎና መጥፎ"
ትውልድ እንጂ ማንም አደል! በጎም ይሁን መጥፎው ትውልድም የኔው ነው። በመጥፎው
በጎውን አልጥልም! በመጥፎው የትናንት ትዝታ የዛሬ ቤቴን አላቃጥልም። በትናንት በጎ
አለቅጥ ጭፈራም ዛሬን ያስጥልም ይሆናል። ብቻ በተተረክልኝ ትርክት ብስጭት የዛሬ
ወንድሞችንና እህቶቼን አልከስም፥ አልገፋም፣ አልጠላም። ዛሬን ለማበጀት ብቻ ጅማቴን
እገትራለሁ!!
በኢትዮጵያ ሰማይና መሬት የሆነው ሁሉ በእናትና አባቴ ቤት ምሰሶ ስር የሆነ ነው ብየ
አስባለሁ። በእናትና አባቴ ቤት የሆነውን ደግ ምግባር የማወሳ ቢሆን እንጂ መጥፎውን
ብለፍፈው ገመናው የማን ሊሆን? እንዲያስ ቢሆን ሰው በጻፈው ታሪክ ውስጥ በጎና መጥፎ
ተለያይተው ያውቃሉን? የገለማ ትናንትን እያኘክኩና እያማሰልኩ የቤቴን የዛሬ መልካም
ጠረን ከማበላሽ፣ በተስፋ ጠኔ ከምመታ፣ ተለዋዋጭ ለሆነው ነብሴና መንፈሴ ስለምን
አዲስ ታሪክ ዛሬ ለነገ አልጽፍም?
ኢትዮጵያ ሆይ፥ እኛ አንቺን ለምንል ሁሉ ከአንቺ አልጋ የመውረድን ገፊ ምኽኛት ሳናይ
ምጽኣት ይምጣ!

(( ያሲን መሀመድ ))💚💛

@EthioHumanity
@EthioHumanity