ለውብ ቀን!
🖤
አብሮ መጨፈርን ሰጥቶ፣ አብሮ ማልቀስን ማን ነጠቀን?
ሁሉም ከሳሽ ፤ሁሉም ምሁር ፤ሁሉም ጨዋ፤ ሁሉም ወቃሽ ፤ሁሉም ሊቅ፤ ሁሉም አዛኝ፤ ሁሉም አቅጣጫ ጠቋሚ ፤ ሁሉም አውሪ ፤ሁሉም ብያለው ባይ ፤ ሁሉም ጆሮ አልባ ነው።
ተመሳሳይ ሃሳብ፤ ተመሳሳይ ምልከታ፤ ተመሳሳይ ህልም ፤ተመሳሳይ ዜና ፤ተመሳሳይ ክስ ፤ተመሳሳይ ውዳሴ ፤ተመሳሳይ አቋም ፤ተመሳሳይ ድጋፍ ፤ተመሳሳይ ሙግት ።
የቡድን ጀግና፤የቡድን ተቆርቋሪ ፤የቡድን ተከራካሪ ፤የቡድን ተከላካይ ፤ቡድናም እይታ ፤የቡድን ጭብጨባ ፤ የቡድን ሳቅ ፤የቡድን ሙሾ ፤ የቡድን ሙግት ፤የቡድን መልስ ። የቡድን ጩኸት
ሃላፊነት የሚወስድ አንድም የለም ። ዝቅጠት ላይ አስተዋፅዖ እንደ አበረከተ የሚያወራ ።አንድም የለም። ሁሉም ጣት ቀሳሪ ፤ ሁሉም ዳር -ነኝ ባይ ነው ።
ሃይማኖታችን ጥንጥ ሞራል ፤ጥንጥ ርህራዬ ትንሽ መተዛዘን ካልፈጠረልን ምን ይሰራልናል ???
የሃይማኖት ስፍራዎች ለምን ግንባቸው ተሸንሽኖ ቤት አልባ ሰዎች አይኖሩበትም??
መስበኪያ ስፍራዎች ለምን ወደ መበየጃ ወደ መሸመኛ ፤ወደ መጥለፍያ ቦታዎች አይቀየሩም ።
እምነት አልባ ህዝብ ውስጥ ይሄ ሁላ ማምለክያ ግንብ ምን ይረባል !!
በዚህ ደረጃ እርስ በእርስ ተጠያይፈን እርስ በርስ ተጨካክነን እርስ በእርስ እየተሳደድን ምን ያስተሳስረናል ???
እርስ በእርስ በሚበላላ ህዝብ ውስጥ ያለች አገርን እንደምን ማፍቀር ይቻላል? ?? ምኗ ይናፍቃል ??
ከዚህ በኋላ የትኛው አገዳደል ፤የትኛው አበዳደል ፤የትኛው ግፍ ያስበረግገን ይሆን ??
የቱም !
ይታክታል!!! እውነት ይታክታል!!!!!
@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

ይፈለጋል !
ዝም የሚል የማይጠይቅ ፤ ሲነገረው አሜን አሜን የሚል፤ የግንኙነት ድንበር የማያበጅ፤ሲናቅ የማይቆረቁረው ፤ የበዛ ይሉንተኛ ፤ከቦታ ቦታ የሚለያይ አቋም የሚያንፀባርቅ ፤ ልምጥምጥ ፤ አቋሙን ፈርጠም ብሎ የማይናገር፤ ሳያስቀው የሚስቅ ፤ አላምንበትም የማይል ። ማብራርያ የማይጠይቅ። ቅሬታውን የማይናገር ፤ሸንጋይ ፤በየቦታው የሚያጨበጨብ ።ይገባኛል(ሲጠብቅ) የማይል ፤ ስለመብት እና ግዴታ የማይዘበዝብ
በጣም ነው የምንፈልገው !¡¡
በነገራችን ላይ
የምንፈልገው ልንገለው ነው¡¡¡¡

ለጁምኣችን!
💚
«ሌባው» የመስጂድ ኢማም
ባልና ሚስት ከረመዷን ወራት ባንዱ በሰፈራቸው የሚገኙትን ታዋቂ የመስጂድ ኢማም ለፊጥራ ጋበዟቸው። ኢማሙም ግብዣውን በክብር ተቀበሉ። የቤቱ እማወራ የምግብ ማዕዱን ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ እያለች ሳለ ገንዘቧን ጠረጴዛው ላይ ጥላ ወደ ኩሽና አመራች። ፊጥራው ተጠናቀቀ። ኢማሙም ሄዱ። ሚስት ገንዘቧ እንደጠፋ አስተዋለች። «ገንዘቡን የሰረቀው ማን ነው?» ተብሎ አይጠየቅ ነገር ባልና ሚስት ልጆች የሏቸውም። በወቅቱ ወደቤት የመጡት የመስጂዱ ኢማም ብቻ ናቸው። ውስጧ በጥርጣሬ ተናጠ። ታሪኩን ለባለቤቷ አጫወተችው። የመስጂዱን ኢማም እንዲያማክራቸውና ጉዳዩን እንዲያረጋግጥ ጠየቀችው። «ኧረ ነውር ነው ፤ ባይሆን ከኢማሙ ጋር የፈጠርነውን ስር የሰደደ ግንኙነት አቋርጠን ፋይሉን እንዘጋለን እንጂ እንዲህ አይነት ጥያቄ ማንሳት የማይታሰብ ነው» በማለት መለሰላት።
ቀናት በንፋስ ፍጥነት ከነፉ። ቀጣዩ ረመዷን ገባ። ባል ከሚስቱ ጋር ተቀመጠ። «እንግዲህ የእዝነት እና የይቅርታ ወር ስለገባ ያለፈውን መርሳት አለብን። እንደምታውቂው ኢማሙም ቤተሰብ የላቸውም። የኛው ስለሆኑ ዘንድሮም ቢሆን ፊጥራ ልንጋብዛቸው ይገባል» በማለት ሚስቱን አማከራት። ሚስት ለአፍታ ዝም ካለች በኋላ «በሃሳብህ እስማማለሁ፤ ነገር ግን የማስቀምጠው ቅድመ ሁኔታ ይኖራል። እርሱም የባለፈው ዓመት ረመዷን ላይ ስለተሰረቀው የገንዘብ ጉዳይ በግልጽ እንድታወሩ እፈልጋለሁ» አለችው። ባቀረበችው ሃሳብ ተስማማ።
የመስጂዱ ኢማም ግብዣውን ተቀብለው ከቤት መጡ። ፊጥራውን ከጨረሱ በኋላ የቤቱ አባወራ ጉዳዩን በይፋ አነሳው። ስለ ገንዘቡ ሁኔታ በቀጥታ ጠየቃቸው። ከፍተኛ የሀፍረት ስሜት ተሰማቸው። እንባቸው በጉንጮቻቸው ላይ ተንኳለለ። ካቀረቀሩበት ቀና አሉ። አይኖቻቸው የእንባ ቋጠሯቸውን እንደፈቱ ነው። ሚስት ፈጠን ብላ «ኢማም ሆይ! ምን ሆነው ነው የሚያለቅሱት ?» በማለት ጠየቀቻቸው። «አዎ! ገንዘቡን ያነሳሁት እኔ ነኝ። ያስቀመጥኩትም የመጽሃፍት መደርደሪያው ላይ ከተቀመጠው ብቸኛ ቁርኣን ውስጥ ነው። እንባዬ የፈሰሰውም ረመዷንን ጨምሮ ለ 365 ቀናት ያህል የአላህን መጽሃፍ ገልጣችሁ አንድ ፊደል እንኳ ባለመቅራታችሁ ውስጤን ተሰምቶት ነው» በማለት ምላሽ ሰጡ። በዚህ ጊዜ የቤቱ አባወራ በፍጥነት መደርደሪያው ላይ ወደተቀመጠው ቁርኣን አመራ። ገንዘቡንም የቁርኣኑ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ምዕራፍ መሃል ላይ ተቀመጦ አገኘው። ሚስት እንባዋ ግድቡን ጥሶ ፈሰሰ። ኢማሙን በክፉ በመጠርጠሯም ይቅርታ ጠየቀቻቸው። «ልጄ ሆይ! እኔ ደካማ የአላህ ባሪያ ነኝ፤ ይልቅ አመቱን ሙሉ ቁርኣኑን ችላ በማለትሽ ይቅርታና ምህረት ከአላህ ጠይቂ» በማለት መከሯት።
👉 እኛስ መቼ ይሆን ለመጨረሻ ጊዜ የአላህን (የፈጣሪን) ቃል ከፍተን ያነበብነው ? ነፍሳችንን ሳንዋሽ እውነቱን ለራሳችን እንገረው‼‼‼
ወገኖቼ የአላህ (የፈጣሪ) ቃል እየጠራን ቢሆንም ችላ ብለነዋል።
ሸጋ ጁምኣ!💚
📝መሀመድ አህመድ

👍1
ነገ ሸጋዋ ቅዳሚት ነች !
❤
የ20❤+ዓመታት የሙዚቃ መልክ!!
ኤልያስ የሙዚቃው ሊቅ ተወርዋሪው ኮከብ....እንቅልፉን ሰጥቶን ሙዚቃውን በሰረገላ ከፍ አድርጓት ከሔደ ዛሬ ዓመት ከመንፈቅ ሆነው።
ኩልል ያለ የጠራ ንፁህ ውበት!!
የልማድን ቅጥር እንደመናድ...በአምክንዮ ነባራዊውን እውነታ እንደመጋፈጥ...
ደፈር ተባ ብሎ የይሉኝታን እስራት እንደመበጠስ... የጥላቻን ገደል ደፍኖ የፍቅር ድልድይ እንደማነፅ... የባርነትን ቀንበር ሰብሮ የነፃነት ብርሃን እንደመፈንጠቅ...በቅንነት ቀና ብሎ በፅድቅ መንገድ በኩራት እንደመራመድ... ከጃጀ ቀኖና አፈንግጦ ቅቡል ተአማኒ ስርዓት እንማፅደቅ...
የተዛባን ፍርድ አቃንቶ ፍትህን በሰው ልጆች ሁሉ እንደማስፈን..
እንደዚህ ሁሉ...ማነው..? ኤልያስ መልካ!!!
ከኤልያስ መልካ ስራዎች እጅግ በጣም የምወደው ሁሌም ሰርክ አዲስ የሚያስገርመኝ አንዱ "መልክሽ አይበልጥሽም" ሙዚቃ ተጋበዙልኝ!!
ሰላም እደሩልኝ!❤ ለኢትዮጵያችን ናካይታ!💚

እምወድሽዋ!❤ቅዳሜዋ!❤ሸጋዬዋ❤
እቴ!❤'ለነገ ብለሽ ፊት የምትነሺው ትላንት አለ'
ደባሪውን ትላንትን ካስተያየሺው ፤ፊት ከሰጠሺው ይጎትትሻል። ንፍጣም ነው ቀሚስሽን ይዞ አያራምድሽም ፤ላባብለው ካልሽ ዝርክርክ ነው አይፅናናም ።አይጠራም ያጨማልቅሻል ነገሽን ፤ህልምሽን ፤ሳቅሽን ያንገራግጨዋል ።
ዛሬሽን ይኮረሽምብሻል ። ውበት እና እድሜሽ ከሚኮረሸሙት ዋነኛቹ ናቸው።
እና የትላንት ጎታች ፊት ነስተሽ ነገ ላይ መንጠራራት ይበልጣል ትላንት ላይ ከማጎንበስ viva ነገ💪🏾💪🏾💪🏾✌️
ድምቅምቅ ያለች ቅዳሚት!❤

Audio
✨ስብዕና(Personality)
💛በዶ/ር ወዳጄነህ ማህርነ
፨ የሰዓት ፍጆታ፦ 25 ደቂቃ
፨ ሳይዝ የቦታ ይዞታ፦ 6.0MB
ውብ ቅዳሜ❤️
✨✨✨✨✨✨✨✨✨
🔆ምርጫችሁ ስለሆንን ስናመሰግኖት ከልብ ነው !!!
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanitybot
💛በዶ/ር ወዳጄነህ ማህርነ
፨ የሰዓት ፍጆታ፦ 25 ደቂቃ
፨ ሳይዝ የቦታ ይዞታ፦ 6.0MB
ውብ ቅዳሜ❤️
✨✨✨✨✨✨✨✨✨
🔆ምርጫችሁ ስለሆንን ስናመሰግኖት ከልብ ነው !!!
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanitybot
☮ሁለት ሱፊዎች በመንገድ ላይ ሲሄዱ ይገናኙና በመተቃቀፍ ተሳስመው አንዱ የቋጠረውን ስንቅ በጋራ ሊመገቡ ተቀመጡ ። ይኸንን ትዕይንት ለአፍታ የተመለከተው የክርስቲያን ልዑል ወደሁለቱ ሰዎች ተጠግቶ ስለትውውቃቸው ጠየቃቸው ።
💟 መመገባቸውን ሳያቋርጡ አንዱ ቀና ብሎ ፦
"ካለዛሬ አይቼው አላውቅም ..." አለው ።
" ምናልባት የአንድ ሀገር ልጆች ትሆኑ ...?" ሲል ጠየቀ ልዑሉ ።
"ሀገሩንም አላውቅም ..." አለ ሰውየው አሁንም መመገቡን ሳያቋርጥ ።
"ታዲያ ለምንድ ነው እንዲህ ዓይነት ፍቅር ያሳየኸው...?" አለ ልዑሉ ተደንቆ
"በእኔ መንገድ ላይ ሲጓዝ ስላገኘሁት ነው" አለው ።
☯ልዑሉም ተደንቆ ዝም ብሎ አልሄደም ። በዚያ ቦታ ለሱፊዎች ማረፊያ የሚሆን ትልቅ አዳራሽ ሰራ ። ዛሬ አዳራሹ ዘመናዊ መልክ ተገንብቶ የሱፊዎች መፍለቂያ "ዩኒቨርስቲ" ሆኗል ።
📖ጥበብ ከጲላጦስ
☯ሰው መሆን እኮ እንዲህ ነው ፣ በሀይማኖት ተለያይቶ ፣ በደም ሳይተሳሰሩ ፣ በባህል ሳይገናኙ ፣ ነገር ግን ለመረዳዳት ፣ አብሮ ለመብላት ፣ እንደሰው ተያይቶ አብሮ ችግርን መካፈል ማለት ነው ፣ ባጠቃላይ በፍቅር ለመኖር ሰው መሆንና እንደ ሰው ማስተዋል ብቻ በቂ ነው ።
መልካም ቀን💜
☮☯☮☯☮☯☮☯☮☯

💫ራሳችሁ ላይ ስሩ!
✨ከአንድ ሰው ጋር ያላችሁ ግንኙነት በቤተሰብ አባልነት፣ በጓደኝነት፣ በፍቅር ግንኙነት፣ በትዳርም ሆነ በሌሎች የቅርብ ወዳጅነት ዘርፎች ይሁን፣ ለዚያ ግንኙነት የሚመጥን ቅርበትንና ትኩረትን የመስጠታችሁ ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ ከእነሱ በሚነሳ አጉል ባህሪይ ወይም የትኩረት መለዋወጥ ምክንያት በቶሎ እንዳትደናገጡ ከፈለጋችሁ ራሳችሁ ላይ ስሩ፡፡ እነሱ እንዶለወጡ መጠበቅ ትክክለኛ ቢሆንም፣ አስተማማኙ መንገድ ግን ራስ ላይ መስራት ነው፡፡
💫ራስ ላይ መስራት ማለት ለእነሱ የምትሰጡትን መሰረታዊ ፍቅርና አክብሮት ሳትቀንሱ ራስን በመቀበል መደላደል፣ የግልን ዓላማ በማወቅ መንቀሳቀስ፣ አልፎ አልፎ ከእነሱ ውጪ የግል ጊዜን በመውሰድ ራስን ማድመጥና የመሳሰሉትን ልምምዶች ማዳበር ማለት ነው፡፡ ከሰዎች ጋር ምንም ያህል ብትቀራረቡና ራሳችሁን ብትሰጧቸውም እንኳን ማንነታችሁን መካድ ግን አትችሉም፡፡
✨ከእነሱ ጋር መቀራረብ ማለት ከራስ ጋር መራራቅ ማለት አይደለም፡፡ እነሱን መደገፍ ማለት ራስን መጣል ማለት አይደለም፡፡ ይህንን መርህ መከተል የሚጠቅማችሁ ከእነሱ የማትጠብቁትን ጎጂ ነገር ስታገኙ ወይም የምትጠብቁትን መልካም ነገር ስታጡ ከልክ ባለፈ መልኩ ከመጎዳትና ግራ ከመጋባት ራሳችሁን ትጠብቃላችሁ፡፡
✍ ዶ/ር እዮብ ማሞ
የሰላም እንቅልፍ ይሁንላችሁ!❤️

ዛሬ የጀግና ሰው ልደት ነው!
🔥🔥🔥🔥🔥
ህመማችንን የከተበልን! ህመማችንን የታመመልን ጥኡም ልሳን! መልካም ልደት!🔥🔥🔥
ሁሉም ነፍስ የየራሱ መክሊት አላት። የሰው ልጅ ከራሱ "ነፍስ" ....... ( ከነፍሱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸውን ነፍሶች ያጠቃልላል) .....በላይ የሚወደው የሚያስበልጠው ነገር ከሌለው ያሰው ለእኔ ተራ ሰው ከሚባሉት ውስጥ ነው (እሄንም ጨምሮ ብዙሀኖቻችን ማለት ነን።) ግን አንድ ሰው ከነፍሱ በላይ አሻግሮ ማየት ከተቻለው እና ማረግ በሚችልበት አቅሙ ማረግ ከቻለ ያ ሰው ነው ጀግና ነው!!ከጫንቃችን ላይ ያለውን የተጫነብንን የባርነት ቀንበር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሰብሮ ነፃነትን ለመጎናጸፍ ሌት ተቀን የሚተጋ እንዳለ ሁሉ ከባርነት ጋር በጦፈ ፍቅር ወድቆ ባርነትን እያሽሞነሞነ ዘመኑን የሚገፋ ጋዜጠኛ በሞላባት ሀገር እንደ አንተ አይነቱን ልበ ተራራ አብዮተኛ ሳይ ሀገሬ ሰው አላት እላለሁ!!🔥 ትላንት ሁሉም በሚያጉረመርምበት አንተ ወጥተህ የተጋፈጥክ ብዙ መስዋትነት የከፈልክ ጀግና ነህ!🔥 አንተን እስር አያገንህም መጀመሪያም ጀግና ነህ!🔥 ጀግንነት ስሙም ግብሩም አንተ ነህ!🔥
በዕውቀቱ ስዩም እንዲህ ይለዋል.....
ገለል በሉለት- አንድ ጊዜ ለሱ
የወረቀት ዛር -ቀለም ነው ምሱ
በዱር ሳይሸምቅ -ወጥቶ አደባባይ
ጥይት ሳይተኩስ-በቃል ሲያደባይ
የሚያንቀጠቅጥ-ጉልበት አለኝ ባይ።
በዘመን ሰፌድ -እያንጉዋለሉ
ቢያንጠረጥሩት-ዳሩ ማሃሉ
ፍሬ ብቻ ነው- የለውም አሠር
ልቡ እንደ ገላው የማይታሠር !!
🔥🔥🔥🔥🔥🔥
@EthioHumanity
@EthioHumanity
@balmbaras

💚"[Love] is a feeling beyond the feeling. It is a total ineffable something that you are. It makes you know that you are one with everything.
💛Everyone is your brother and sister, including the flowers, the trees, the animals, ... the sick people, the healthy people, the poor people, the rich people. When you can look at everyone ... and not differentiate, then you're in love.
❤️But when you pick out somebody special and you think that one you're totally in love with because he or she has the right features, the right figure, the right assets that you want, this is infatuation. This only lasts ... until you get what you want. But true love never changes. It doesn't go away because it never came from anywhere. It's just something that is and you are that."
✍ Robert Adams
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

❤1
❤️ደስተኛ ለመሆን ነፃ ሁን፣በፍቅር ውስጥ ወጥመድ የለም፡፡ ደስተኛ ከሆንክ ሁሉም ድርጊትህ ደስታን መፍጠር ይችላል፣ ስቃይን ከመረጥክ፣ሁሌም በውስጥህ ስቃይን ታመርታለህ ፣የአዕምሮህ መጥፎ ሀሳብ ካሸነፈ አንተንም ሆነ ሌሎችን ይመርዛል።
❤️እራስህን በሰላም ፣ በብርሃን ፣ በጥበብ ፣ በንቃተ-ህሊና ሸፍነው፡፡ የአንተ ሃላፊነት ይህ ነው ፡፡ደስታ እና ርህራሄ በህይወት መንገድህ አይለዩህ፣ ከተፈጥሮ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘህ ኑር ፡፡ ይህን ለማድረግ ሁሌም ከልብህ ጀምር።
ሁሌም ይህን አድርግ፣ሁሌም ይህንን ሁን ፡፡
መልካም ምሽት❤️

ጥቆማችሁ ያስፈልገናል!🙏
ኢትዮጵያ ዉስጥ ለማህበረሰቡ እና ለሀገራቸዉ ባሉበት የስራ ዘርፍ ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረጉ ነገር ግን ማህበረሰቡ ፣ ሚዲያው እና መንግስት እስከ መኖራቸዉም ትዝ የማይላቸዉ የስራ ዘርፎች ምን እንደሆኑ በእናንተ እይታ ብትጠቁሙን....?
ይኽን ጥቆሞ ከሰጡን እኛም በእናንተ መልሶች እና ላይ ተነስተን የራሳችንንም ጥናት አክለን....እስከ ያልገታው አስተዋፆ ለማድረግ አስበናልና ጥቆማችሁን እንሻለን🙏🙏
#ከትላንት ጀምሮ ብዙዎቻቹ ልካችሁልናል እናመሰግናለን የአብዛኞቻቹ መልሶች መምህር ፣ ወታደር ፣ የመንገድ ላይ ፅዳት ሰራተኞች ይበዙበታል.....🙏እናመሰግናለን በጣም የተለየ አለ ብላቹ የምታስቡትን ካለ ከታች በተቀመጡ ሊንኮች ይላኩልን..🙏 ሸጋ ቀን!💚