ስብዕናችን #Humanity
25.3K subscribers
1.66K photos
79 videos
23 files
54 links
🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot
Download Telegram
🌊"If you don’t have peace within yourself, it is very difficult to work for peace. [During the Vietnam war] our thinking was, the other person is not our enemy. Our enemies are misunderstanding, discrimination, violence, hatred, and anger. With that kind of insight, we conducted the peace movement.

❄️If you are filled with anger, you create more suffering for yourself than for the other person. When you are inhabited by the energy of anger, you want to punish, you want to destroy. That is why those who are wise do not want to say anything or do anything while the anger is still in them.

🌊So you try to bring peace into yourself first. When you are calm, when you are lucid, you will see that the other person is a victim of confusion, of hate, of violence transmitted by society, by parents, by friends, by the environment. When you are able to see that, your anger is no longer there...”

~Thich Nhat Hanh~
❄️🌊❄️🌊❄️🌊❄️🌊❄️🌊❄️🌊❄️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
ስብዕናችን #Humanity
🗣🗣ጉዞ ወደ ሀሳብ.......... በጣም በተደጋጋሚ ከብዙ ሰዎች የምሰማው አባባል አለ "የኢትዮጵያ አምላክ አይተኛም ኢትዮጵያን ይጠብቃታል" የሚባለው አባባል " አድዋን ተዋግተን ያሸነፍነው ጊዮርጊስ በፈረስ ላይ ሆኖ በጎራዴው የጣሊያኖችን አንገት እየቀላልን ነው ብላቹ ታምናላቹ..? እንደዛ ከሆነ ሌሎች ሀገራቶችን በጣሊያን ሲገዙ ፣ እንደ እቃ ሲሸጡ እና ሲለወጡ ፣ ሲገደሉ አምላክ እንዴት ዝም…
ለጠየቅነው ጥያቄ .....ከተሰጡን መልሶች መካከል......👇👇👇



Zenit Simeneh:👇👇

እነሱም ፩ አድዋን ተዋግተን ያሸነፍነው መልዕክ በፈረስ ላይ ሆኖ በጎራዴው የጣልያኖችን አንገት እየቀላልን ነው ብላቹ ታምናላችሁ? በደንብ አምናለሁ ይሄ ሀሳብ እኛ ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳንሆን የዛኔ የተዋጉት ጣልያኖች እንዴት ነበር ውጊያው ተብለው ሲጠየቁ የመለሱት መልስ ነው በዛን ጊዜ የነበረ ጋዜጣ አንብብ ቃልበቃል ታገኘዋለህ። የቤት ስራ ይሁን ሲቀጥል አንተ ስታስበው እውነት ዘመናዊ መሳሪያ እስከ አፍንጫው የታጠቀ እና ሙሉ ወታደራዊ ስልጠና ያለውን ሰራዊት እንዴት ነው በገጀራ እና በገበሬ ልናሸንፍ የምንችለው ይሄ እኮ ፊልም አይደለም እውነተኛ ታሪክ እንጂ ፊልም እንኳን ሲቀጣቀጡ እንኳን ተቀራራቢ የጦር መሳሪያ ይዘው ነው ይሄ የሚያሳየው ኢትዮጽያዊነት ሚስጥር፣ ሀይል መሆኑን እና የሚጠብቃት እንደማይተኛ ነው። ሲሰልስ ሚኒሊክ እምነቱ በጣም የሚያስደንቅ ነው ገጀራው ላይ ሳይቀር የሚኒሊክ ተስፋው እግዚአብሔር ነው ይላል። ሂድ እምነትህ አድኖሃል ተብሎ እንደተፃፈ በቅዱስ መፅሐፍ ተዋጊህ ወይም ሰልፉን የሚመራው እግዚአብሔር ነው ብለህ እሱን ስታምን ጉልበት የሱ መሆኑን ስታውቅ እና እሱን ስታስቀድም በተቃራኒው ደሞ በወታደር እና በታንክ ስትመካ ይለያያል።
🔑 ሌሎች ሀገሮች በጣልያን የተገዙት እምነት እና የኢትዮጵያዊያን አይነት ወኔ እና ስሜት ስሌላቸው ነው በርሊን ስምምነት ላይ እኮ እጣ ሲከፋፈሉ ሶስት ምርጫ አስቀምጠውልን ነው በፍላጎት,፣ በግድ እና በስምምነት አብዛኛው እምነት ስላልነበራቸው ሊገዙ ሆኗል እምነት ለምንም ነገር መሰረት ነው ጎልያድ በጠጠር የተሸነፈው በእምነት ነው።
እንደ ዕቃ ሲሸጡ እና ሲለወጡ፣ሲገደሉ አምላክ እንዴት ዝም ይላል ካልክ ለምንድን ነው አንድአንዶች በሞቀ ቤት እየተኙ፣እየበሉ እና እየጠጡ በቤታቸው ውሻን እና ድመትን አንደላቀው እየኖሩ ለምን የጎዳና ልጆች ለምን ይራባሉ፣ይጠማሉ፣ራሳቸውን ለማሞቅ ለምን ቤንዚን ይስባሉ አየህ እግዚአብሔር አለም ላይ አንዱን ሀብታም አንዱን ደሀ አንዱን አካለ ጎዶሎ አንዱን "ሙሉ አካል"አርጎ የሚፈጥረው እኔ እንደወደድኳችው እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ የሚለውን የራሱን ሀይለ ቃል እኛ እርስ በእርሳችን በመረዳዳት እንድንፈፅመው እና በኃላ በፍርድ ጊዜ ሲመጣ ብራብ ብጠማ አላበላችሁኝም አላጠጣችሁኝም እንደሚል ቃሉ እናም እኛ ምን ያህል እሱን እንደምንታዘዝ ለማወቅም ጭምር ነው ስለዚህ እግዚአብሔር ኢፍትሃዊነት አያሳይም።
በሚኒሊክ ጊዜ ያለውን ሁነት በሌላ ጊዜ አንብቤ እከሰታለው ለዚህ ብዬ ለዛሬ የሚሆነውን መልስ ለነገ ማስተላለፍ ስላልፈለኩ ነው።

፪ ማሳያ ኢትዮጵያ ላይ እንደተሴረው ሴራ የእውነት ኢትዮጵያ አሁን ላይ ትኖር ነበር???
፫ ማሳያ ኮረናን ተመልከት እውነት ኢትዮጵያ ላይ ኮረና ያልሰለጠነው የተባሉትን መመርያዎች ተግብረን ነው ውሃ በሌለበት(በሶስት ቀን አንዴ ) በሚመጣበት ሀገር እጃችንን ታጥበን ነው? በጠባብ ቤት ውስጥ ፮ እና ፯ ሰው እየኖረ እርቀታችንን ጠብቀን ነው?
፬ የእውነት በበይነ መረብ ብሄርን መሰረት ያደረጉ ምሁር ነን ባዮች በሚፅፉት፣በሚያፅፉት እና በሚከራከሩበት መጠን እውነት እነሱ ጋር ያለ አስተሳሰብ ህዝቡ ጋር ቢኖር የእውነት ኢትዮጵያ ውስጥ ወጣት ብሎም ሰላም የሚባል ነገር ይኖር ነበር?? ሌላ ብዙ ማሳያ መፃፍ ይቻላል ለዛሬ ግን እዚህ ላይ ላብቃ።ይሄ ሁሉ ችግር ስዘረዝር እንዳፈራ የሀገራችን አምላክ አይተኛም ሀገራችንን ይጠብቃታል!!!

አፍሪቃውያን የኢትዮጵያ አምላክ ቸርች እስከመገንባት ደርሰው ነበር

ክብር ከብረው ላስከበሩን ጀግኖች አያት አባቶቻችን!!!
ሞተው ላኖሩን ጀግኖች ማርያምን!!!!!

ተቆራርጦ ስለደረሰህ በጣም ይቅርታ ቢያልፍም መልካም መቶ ሀያኛ የአድዋ ድል ይሁንልን!!!!!


👇👇👇👇

ስላም እንደት ነህ/ሽ
"አምላክ ኢትዮጵያን በተለየ መልኩ ይመለከታታል ? ማሳያዎችስ አሉት?" የሚል ጥያቄ አንስተህ/ሽ እንድንወያይ ስለጋበዛችሁን አመሰግናለሁ።
እኔ አዎ በሚገባ ባይ ነኝ፡፡ ነገር ግን በእኔ አቅም ሊብራራ የማይችል ሲሆን የተቻለኝን ልሞክር
መጀመሪያ ፈጣሪ እንዲረዳን በእርሱ ማመን እና እርሱን የምንፈልገዉን መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ ምሳሌ እኔ ከራበኝ ምግብ እንዲሰጡኝ ቤተሰቦቼን መጠየቅ አለብኝ፡፡ ስለዚህ ፈጣሪ እንዲረዳቸዉ ሌሎችም እንደ እምየ ምኒልክ አምነዉ መጠየቅ አለባቸዉ፡፡ ክርስቶስ ለኛ ነጻ ፈቃድ ነዉ የሰጠን፡፡ 38 ዓመት የአልጋ ቁራኛ የነበረዉን ወጣት ሲያድነዉ ዝም ብሎ ተነስ አልጋህን ተሸክመኅ ሒድ አላለዉም መጀመሪያ መዳን እንደሚፈልግ ከጠየቀ በኋላ አዳነዉ እንጅ፡፡ ስለዚህ እኛም እንዲረዳን መጠየቅ አለብን፡፡ የእምየ ምንሊክን የክተት አዋጅ ስናይ እንዲህ ይላል “እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፋፍቶ አኖረኝ እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ” በዚህ ዉስጥ ስንመለከት እስካሁንም እምየ ስልጣን ላይ የቆዩት በእርሳቸዉ ሀይል ብቻ ሳይሆን በፈጣሪም ቸርነት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ይቀጥሉ እና ”……….. ከእንግዲህም ያሳፍረኛል ብየ አልጠራጠርም” በዚህ ዉስጥ ደግሞ እምየ ፈጣሪን ይዘዉ ጦርነቱን እንደሚያሸንፉ ምንም ጥርጣሬ የላቸዉም፡፡ ይሄንንም እራሳቸዉ ጣሊያኖች ”አንድ ሰዉ በነጭ ፍረስ ሆኖ ፈጀን ከፊታቸዉ አላስደርሰን አለ” ብለዉ መጽሀፋቸዉ ላይ እንደጻፉ ይነገራል፡፡ በዚህ ዉስጥ ደሞ እምየ ምኒልክ የሰማዕቱን የቅዱስ ጊዮርጊስን ታቦት ይዘዉ እንደዘመቱ ይታወቃል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ፈረስ ደግሞ ነጭ ነዉ፡፡ ስለዚህ ሰማዕቱን ቅዱስ ጊዮርጊስ አብሮ አድዋ ላይ ተዋግትዋል፡፡ እንግዲህ እናንተ በጎደል ሙሉበት ፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡


👇👇👇👇

አሁን ያነ ሳሀቸው ሀ ሳቦች እውነትም እንደጠየቅከው አይነት ጥያቄ ጭንቅላት ውስጥ ያጭራሉ....

ግን ምን አለ መሰለህ......

አዎ አምላክ ኢትዮጵያን በተለየ አይን ያያታል

ለምን አልሽ ካልክ .... ያልኩበትን ሰበብ ልዘርዝር

1.ኢትዮጵያን ለቅድስት ድንግል ማርያም እንደስጦታ ሲሰጣት(ያስራት ሀገርሽ ብሎ) "ሳያዩ የሚያምኑ ህዝቦች የሚኖሩባት ምድር ናት" ብሎ ራሱ መስክሮልናል
2. ትንቢተ አሞፅ ላይ "እናንት የእስራኤል ልጆች ሆይ ለኔ እንደኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን"ብሎ ምን ያህል እንደሚወደን መስክሯል
3.አምላክ ነጋ ጠባ የሚመሰገንባት አገር ናት... ሙስሊሙ ክርስትያኑ ፕሮቴስታንቱ ጆሆባው ሌላውም... ሳያመሰግን አይውልም አያድርም
ምሳሌ ልስጥህ... ሰንበት ሰንበት ይቀደሳል... አርብ አርብ ጁማ ነው... አለመግባባት ላይ "በህግ አምላክ!" ይባላል.... ስላምታ ላይ "እግዛብሔር ይመስገን" " አላህ ይመስገን" ይባላል... ሌላው የገዳማውያን ፀሎትም አይረሳም
4. "ኢትዮጵያ ታበፅዕ እደዊሀ ኀበ እግዚአብሔር" (እጇን ወደ እግዛብሔር ትዘረጋለች) ተብሎላታልም....
ስብዕናችን #Humanity
🗣🗣ጉዞ ወደ ሀሳብ.......... በጣም በተደጋጋሚ ከብዙ ሰዎች የምሰማው አባባል አለ "የኢትዮጵያ አምላክ አይተኛም ኢትዮጵያን ይጠብቃታል" የሚባለው አባባል " አድዋን ተዋግተን ያሸነፍነው ጊዮርጊስ በፈረስ ላይ ሆኖ በጎራዴው የጣሊያኖችን አንገት እየቀላልን ነው ብላቹ ታምናላቹ..? እንደዛ ከሆነ ሌሎች ሀገራቶችን በጣሊያን ሲገዙ ፣ እንደ እቃ ሲሸጡ እና ሲለወጡ ፣ ሲገደሉ አምላክ እንዴት ዝም…
1ኛ ,3ኛ እና 4ኛ ማስረጃዎች (አንድ በል).... ......
አለም ሁሉ አምላክ የለም ወደ ማለት በደረሰበት በዚ ግዜ ሳይታጎል ሚመሰገንበትን ሕዝብናምድርን በተለየ አይን ማየቱ (ሁለተኛ) የአምላካዊ ባህሪውን ይሸረሽረል ብዬ አላምን...... ህጉን የጠበቀ ነውና በረከቱን የሚያገኘው

ሌላው ደግሞ ይኼን ክፉ ወረርሽኝ እንመልከት..... በውጭ ያሉ ወገኖች ሲረፈረፉ የኛ ወገን እንደተፈራው ያልተረፈረፈው በምን ይመስልሀል??? ...ተጠንቅቀን?... ነጭሽንኩርቱ??.. ወይስ... በምትሀት??? .... በአምላክ ልዩ ጥበቃ ነው

ሌላም ላምጣልህ.... እቺ ማነች... ሶርያ.... እና ሌሎችም ማላስታውሳቸው ሀገሮች አይፈርሱም የተባሉት ይኸው ብትንትናቸው ወጥቶ የለም እንዴ... እኛስ እስካሁን በቋፍ ቢሆንም ተ ሰብስበን ያለነው በምናችን ነው??? እጃችንን በምዘረጋለት በጠባቂያችን አይደለምን??

ሰው በሰው ላይ ...መንግስት በመንግስት ላይ... ወንድም በወንድም... ህዝብ በህዝብ...ላይ የመነሳቱ ጉዳይ.... ይህ የጊዜው ጉዳይ ነው.... በመፅሀፉም በግልፅ እንዳለው የግዜው መክፋት የፍፃሜው መቃርቢያ ምልክት ነው....
ደግሞ....
ኢትዮጵያውንያን ከማንም በላይ በማመን ይታወቃሉ! ያመነ ደግሞ ይሆንለታል! ይድናል! በ23 ብንዋጋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ይረዳናል ብለው ስላመኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ ረዳቸው. ዳኑ! አበቃ!

ይህ የኔ ሀሳብ ነው! ብዙ እውቀት የለኝም ግን የተሰማኝን ከማውቀው አንፃር ገልጫለው... የተሳሳትኩት ካለ ልታረም ዝግጁ ነኝ...

👇👇👇👇

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን በርሱ አምነው እንደ ሃሳቡ ለሚጓዙ ሁሉ ሊራዳ ይመጣል። ይህን አሳብ በደንብ ለመረዳት የእስራኤልን ታሪክ (በብሉይ ኪዳን ያለውን) ማንበብ ይረዳል። በርሱ ስታምን እርሱም ይታመናል በኃይልህ እና በጉልበትህ ስትታመን ደግሞ ለኃይልህ እና ለጉልበትህ አሳልፎ ይሰጥሃል በጉልበትህ ልክ ትዋጋለህ። እስራኤልን በኤርትራ ባህር አሳልፎ ፈርኦንና ሰራዊቱን ሲያሰጥም ብቸኛው ልዩነት እምነታቸው ነው። እኒህ በርሱ ኃይል እነዚህ በሠራዊት ብዛት ። ከመንገዱ ፈቅ ባሉ ጊዜ ደግሞ ከነርሱ በሚያንስ ሠራዊት ሲረቱም አይተናል። the bottom line is እግዚአብሔር ይረዳል። ይህም ፍትሃዊነቱን አያዛባም። ተበዳይ እና በዳይ መካከል ያለውን ልዩነት እንኳን እሱ እኛ እንረዳለን።

ሌላው መልአክ በፈረስ መጣ የሚል ታሪክ የለንም። ይልቁንም ጊዮርጊስ የሚባል ሰማእት በምልጃው ተራዳን ነው የሚባለው። በነገርህ ላይ እርሱም ሮማዊ ነው። ለዘር ሳይሆን ግን ለእውነት እና ለእምነት አድልቷል። ደግሞ ሰይፍ ይዞ ተዋጋ ማለት ሳይሆን ለሚዋጉት ብርታት ሆናቸው ማለት ነው።
ለምን በሁለተኛው ጦርነት አልመጣም ላልከው ከላይ ያወራነው በደንብ የሚያስረዳ ይመስለኛል። በእምነታችን ልክ ይረዳናል። ትንሽነታቸውን አምነው እርሱን ተስፋ አድርገው ተኳሽ ወታደርና ቀዳሽ ካህን ይዘው በወጡ ጊዜ ጉልበት ሆናቸው። በተቃራኒው የአውሮፓ ኅብረትን አምነው እጃቸውን ወደነርሱ በዘረጉ ጊዜ ደግሞ ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጣቸው።

Anyways ይህን ሁሉ ለመርዳት አማኝ መሆን ሳያስገልግ አይቀርም።


የሌሎቻቹን መርጠን የምናቀርብ ይሆናል!

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@balmbaras
❤️የፍቅር ቦታው ልብ ነው። ልብ ደግሞ ንፁህ ወርቅ ነው። ፈጣሪ በመለኮታዊ ሃይሉ ያነጠፈው፤ ያብረቀረቀው ወርቅ ቢኖር ልብ ነው።

❤️የፍቅር ፀዳል ውበት የሚንፀባረቀው በልብ መስታወት ውስጥ ነው። ነፀብራቁ፣ ደግሞ፣ በፈጣሪ ፍቅር፣ ይገለፃል።

ውብ አዳር❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity
ለጁምኣችን!
💚

ከዕውቀት አይነቶች በላጩ «ልክህን ማወቅ» ነው እራስን መሆን፤ እራስን መግዛት ፤እራስን ማክበር ፤ራስን ማሸነፍ ፤ እራስን ማወቅ የድሎች ሁሉ መጀመርያ ይመስለኛል።ራስን ማሸነፍ ባላንጣን ከማሸነፍ በላይ ጀግና ያስደርጋል።
ሌሎች ነገሮችን ከመርታት የራስን ፍላጎት ማሸነፍ እውነተኛው ጀግንነት ነው።" አቅም ሲኖርህ ከራስህ ትወዳደራለህ። ራስህን ትተቻለህ። ከትናንትህ መሻልህን ትመዝናለህ። ዋናው የምታስብበት ቦታ ፣ የምትመኘው ሆነ መድረስ የምትፈልግበት ቦታ አለመድረስህ
አያደለም ትልቁ ነጥብ ያለው # የነበርክበት ቦታ አለመገኘትህ ነው። ጉዞ የጀመረ ይደርሳል።ግን እንዳትረሳ "ልክህን ማወቅ ለመንገድህ ጠቃሚ ነው"

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta
👍1
በዲግሪ የተመረቀ/ች
3 አመት የስራ ልምድ ያለው/ት
ብዛት 1
ላይሰንስ ያለው/ት

የስራ ቦታ እሪቼ ባቡር ፌርማታ መስከረም ማዞሪያ የድሮው መስከረም ሆቴል ፊት ለፊት

@Nagayta
ነገ ሸጋዋ ቅዳሚት ነች ዛሬ ዋዜማዋ ነው ለዋዜማዋ እንካቹ.......



የ ክ ራ ር ግርፋት እየሰማሁ የቃሎቻችንን ዋጋ እመዝናለሁ። እንደጉም እያየነው ስለተበተነው ትዝታችንም እተክዛለሁ። በእኛ መለያየት መውደቂያ ስለሚያጡ የቀትር ሕልሞቻችንም እጨነቃለሁ። በስስት የተሳሳምንባቸውንም ከንፈሮቻችንን በሚረሱ ሸክም ገላዎቻችን አፍራለሁ።

እ ን ደ ቃ ሎ ቻ ች ን ፥ እንደሕልሞቻችን ዘልዓለማዊነት ቢሆን ጀርባ ስንሰጣጥ ብቻ ሞተናል። ያ ፈጣሪ እንኳ በቃሉ ዓለምን የሠራ ከዘፍጥረት ቀድሞ ዋሾነታችንን አወቀብንና ቃሎቻችንን ኀይል ነሣ። ልንል በምንችለውና ልናደርግ በምንሻው መሀል ፈቃድን ሰጠን። ከእንግዲህ ወዲህ ያልነውን እስከምንሆን ብዙ ፈተና አለብን። ቃላችንና ግብራችን እስከሚገጥም ድረስ ፍጹም መጽደቅ የለም።

ለ ቃ ላ ች ን ስለማንሞት ውብ ሐረጋትን ብቻ የሚተፉ ሕያው መሣሪያዎች ሆነናል። እያንዳንዱ ሰው አዲስ ሰው ሲተዋወቅ በአንደበቱ ከዚህ በፊት ምንም ያለበት አይመስልም። እናም ዛሬም ፥ ነገም ፥ ከነገ ወዲያም እንግዳ ሰው እንቀርባለን። እናሞኛለን ፥ ፍቅርን ከመላመድ እናምታታለን ፥ እንተኛለን ፥ እንከዳለን ፥ ዘወር እንላለን። አዲስ እንለምዳለን። ሌላም ፥ ሌላም ፥ ሌላም።

“እ ን ዲ ህ ብለሺኝ እንዳልነበር
እንዲህ ብለኸኝ እንዳልነበር”

ስ ለ አ ለ ፈ ው ቃል ማን ይጠይቀናል? ቢጠይቀንስ የት ይደርሳል? በመጨረሻስ ሄዶ ሄዶ ምን ያመጣል? እያየን ፥ እየተመለከተን ያልነው ጠፍቶ የወለድነው ያድጋል። ልጃችንም ቢጤያችን ነውና ለቃሉ ሽረት ሞት አያውቅም። ማዕተብ አያሥረውም። ከተማውን ሸንጋይ ሞላው። በተራ ቃሎቻችን ምክንያት ቃላት በውስጣቸው የሚይዙት የትርጉም ልዕልና እየረከሰ ሄደ።

“እወድ ሻ/ሃ ለሁ (!)
አፈቅር ሻ/ሃ ለሁ (!)
እሞትልሻ/ሃ ለሁ (!)
ካን ተ/ቺ በቀር (!)
እስከ ዘልዓለም (!)”

ብ ን ል ም ቃሉ የትርጉም ጥልቀት የለውም። መዋደዳችን ፥ ፍቅራችን ሲፈተን — ዘልዓለማችንም አጭር ነው። አለማፈር ብቻ ሕይወታችንንና ኑሯችንን አራመደው።

እ ና ም ፍቅር ስለማናውቅ ቃሉ አፋችን ላይ አያምርብንም። ባይሆን ዝቅ ያለው ሙዚቃ ድምፁ ከፍ ቢል መልካም ነው።

“አ ራ ት መቶ ፍቅር ፥ ሦስት መቶ ትዝታ
የምችለው ስጠኝ ፥ አቤት የ'ኔ ጌታ”

እሱባለውአበራ ንጉሴ


@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta
እምወድሽዋ! ቅዳሜዋ!ሸጋዬዋ


ፌቨን ትባላለች ፤ ፍቅረኛዋን ትወደዋለች ። ሁሌ በትንሹም በትልቁም ታነሳዋለች ፤ ከእለታት በአንዱ እለት ምኑን በደንብ ትወጂለታለሽ ???አልኳት

እ.............የምወድለት

ለኔ ያለውን ግዙፍ ፍቅር ፤ በየስፍራው በየጊዜው ይዳስሰኛል ። ሲፈልገኝ ፤ሲቀና፤ ሲጠረጥረኝ ፤ ለኔ ያለውን የፍቅር አሻራ በነካሁት እና ባየሁት ቁጥር እወድዋለሁ።

የለም

በደንብ የምወደው መልካምነቱን ነው ። በዙርያዎቹ ያሉቱን ሰዎች ፤ሲቆረቆርላቸው ፤ሲጠቅማቸው፤ሲሞገትላቸው ።ለተጠቃ ድምፅ ሲሆን እንድወደው አድርጎኛል ።

ኖ ......እሱም አይመስለኝም

ሲወስበኝ ያለውን ጀብደኝነቱ ነው የምወደው ። ወሲብ ላይ ያለው ወኔ ድፍረት እና ብልግናውን ነው የምወድለት ።

እሱም ብቻ አይደለም !?

ለአምላኩ ያለውን ታማኝነት፤ሃቀኝነቱን ለሚያምንበት ነገር የሚሄደውን ርቀት፤ ብቻውን የመቆም አቅሙን ፤ ሁሉም ታዝቦት ላገኘው ሰው ሁሉ ትክክል ነኝ እያለ ሙሾ አለማውረዱን ነው የምውድለት !!

ኖ ሳቁን ነው

ደመቅ ብሎ ለዛ ያለው ሳቁን ነው የምወድለት ። ያቺ ልቤን የምታርደው ሳቁን ነው የምወድለት ። ያቺ ከልቡ ሲስቀው ብቻ የሚስቃትን ሳቁን ነው የምወድለት ።

ኖ .....የለም

ሲያወራ የሚያወናጭፈው አለንጋ ጣቱ ናቸው የሚስቡኝ ። አወራሩ ጀንተል ብሎ በስሜት ቃል አጣጣሉ ነው የሚማርከኝ

እ..... ይሄ ን ብቻ ግን አይለም የምወድለት

ያለውን Commitment ። ከብዙ ሰው ጋር ሆ አለማለቱን ነው !! ከመዘባረቁ በፊት ስለሁኔታው ለመረዳት አጠያየቁን ፤ አነባበቡን ነው የምወድለት
.
.
ግን ምክንያቴ ነው ብዬ ከዘበዘብኩት በላይ አስሬ የማጣቅሰው ምክንያት ። የመንሰፍሰፌ ምንጭ ምክንያት አንድ ይመስለኛል .........የኔ ስለሆነ( ።)


የኔ ስለሆነ ነው የሚተችበትን ሳይቀር የማቆለባብሰው

ከካደኝ ፤ከተወኝ፤ ከጠላኝ፤ ሀይማኖተኝነቱን አክራሪ እለዋለው፤ ጠያቂነቱን መንቻካ እላለሁ፤ መልካምነቱን ብኩን ማለቴ አይቀርም ።

ማስታወሻ
ከውበት በላይ ፍቅር ያሱባል !!!


የተገማሸረ ደርባባ ቅዳሜ ይሁንላችሁ !

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta
🔑Conditioned Mind

"It is not because things are difficult that we do not dare; it is because we do not dare that things are difficult." - Seneca
---
🔆በሕንድ መንደሮች ውስጥ ሲዘዋወር የቆየ አንድ እንግዳ ሰው ነዋሪዎቹ ዝሆኖቻቸውን የሚጠብቁበት መንገድ ግራ አጋብቶታል... እጅግ ግዙፍ የሚባሉ ዝሆኖች በቀላሉ ሊበጠሱ በሚችሉ ገመዶች ታስረው በጸጥታ የመቆማቸው ምስጢር እውነትም እንቆቅልሽ ነበር... 'እንዴት ሊሆን ይችላል?'...

⚜️ግራ መጋባቱ እየቀጠለ ሲሄድ ወደ አንድ የዝሆኖች አሰልጣኝ ዘንድ ቀርቦ 'ይህን እንዴት ማድረግ ቻላችሁ?... ዝሆኖች በምድር ላይ በጉልበታቸው ተስተካካይ የሌላቸው ፍጥረታት መሆናቸው ይታወቃል... በዚህ ሰላላ ገመድ ታስረው እንዲቆዩ ያደረጋቸው ምስጢር ምንድነው?...' ሲል ጠየቀ... 'ደህና...' አለ ዝሆኖችን የሚገራው ሰው... በእንግዳው ሰው ጥያቄ አንዳችም መገረም ሳያሳይ... 'በዚህ ገመድ መታሰር የሚጀምሩት ከደረጁ.. ጉልበት ካበጁ በኋላ አይደለም... ገና ግልገል ሳሉ ነው... በዚያ የማለዳ ዕድሜ አሁን የምታየው ገመድ እነርሱን አስሮ ለመቆየት በቂ ነበር... እየቆዩ ሲሄዱ ገመዱን የሚበጥስ አቅም ቢፈጥሩም በልጅነታቸው የታተመባቸው እምነት ግን ዛሬም ገመዱን መበጠስ እንደማይችሉ ይነግራቸዋል'...

🔆ሰውየው በጥበባቸው ተገረመ... ግዙፉን ዝሆን ለማሰር ግዙፍ ሰንሰለት አላስፈለጋቸውም... አስተሳሰባቸውን የሚያስር የማለዳ ልማድ በቂ ነበር... ነገሩ ሰንሰለት ካሰረው ልማድ ያሰረው ነው... 'ልማድ ከብረት ይጠነክራልና' ሼክስፒር እንዳለው...

🔆የኑረት ውበት በየደረሱበት መጠየቅ... የሰውነት ከፍታም በየመዳረሻው መርቀቅ ቢሆንም ከተነገረው ዘሎ 'ለምንና እንዴት' ለማይል አዕምሮ የነበረን ማስጠበቅ እንጂ 'አዲስ ነገር' ማፍለቅ አይሆንለትም... የኑረት ስኬትም ሆነ ውድቀት በእምነትህ ልክ ይገነባል... ቡድሃ "All that we are is the result of what we have thought. The mind is everything. What we think we become. " የሚለውን ቃል በትምህርቱ መጀመሪያ ላይ ያስቀመጠው ለዚሁ ነበር...

💫የምታምናቸውን ነገሮች ለምን እንዳመንካቸው ጠይቀህ ታውቃለህ?... የተቀበልካቸውን እሳቤዎች ልክነት በ'እንዴት' ዓይን መዝነህ ታውቃለህ?... የነገሩህን መጽሐፍትና ያስተማሩህን አንደበቶች መርምረህ ታውቃለህ?... እርግጠኛ ስለሆንክባቸው ጉዳዮች ቢያንስ ለራስህ በታማኝነት የምታቀርበው መልስ አለህ?... ወይስ እንደ ግዙፉ ዝሆን በሰላላ የአስተሳሰብ ወደሮ ታብተሃል?... መጠየቅስ አድክሞህ ይሆን?... Wynn Bullock የተባለ ሰው... "If you stop searching, you stop living, because then you're dwelling in the past. If you're not reaching forward to any growth or future, you might as well be dead." ብሎ ነበር... ሶቅራጥስ በበኩሉ "The unexamined life is not worth living" ብሏል...

ከማለዳ ውልደት እስከ ውድቅት ህልፈት የምትሳበው ኑረት ሁለንተናዋ በጠነከረ ልማድ የተቀየደ ነው... ከመጋረጃ ጀርባ ሆኖ የትወናዋን አካሄድ የሚወስንላት መራሔ ተውኔት ልማድ ወይም እምነት ይባላል... የምታምነውን ነው የምትሆነው... ግና.. የማለዳ እምነትህ ረፋድ ላይ... የረፋድ እሳቤህ ቀትር ላይ... የቀትር ግንዛቤህ በተሲዓት... የተሲዓት እውነትህ በምሽት ካልተመረመረ ከልማድ እስረኛነትህ ሳትፈታ ውድቅትህ ይመጣል... "The world is a prison and we are the prisoners.Dig a hole in the prison wall and let yourself out." ይልሃል ሩሚ...

🔑'ተለምዷል' የሚልህ ሰው ሲበዛ ጠርጥር... ቅኝት ነው... 'ምንም ማድረግ አይቻልም' ካለህ ተቃኝቷል በቃ... 'ያለ ነው'... 'ባሕል ነው'... 'አሰራር ነው'... 'እከሌ የሚባል ሰው ወይም መጽሐፍ ላይ ሰፍሯል'... ወዘተረፈዎች የቅኝት መገለጫዎች ናቸው... እዚህ መንደር ውስጥ 'ለምን' ባይ የተገኘለት የእብደት ታፔላ ይለጠፍለታል...

🔆ዕድሜ ልኩን ጥርሱን ሳያጸዳ የኖረ ሰው ለተወሰኑ ቀናት ብሩሽ ተጠቅሞ በመተዉ የአፉን ሽታ ቢያስተውል ሊል የሚችለው አንድ ነገር 'የጥርስ ሳሙና አፍ ያሸታል' ነው... ብሩሽ ከመጠቀሙ በፊት ሽታውን ተላምዶት ስለቆየ 'አፍህ ይሸታል' ቢሉት አይቀበልም ነበር... ብሩሹ ካለመደው ንጽህና በኋላ ግን የትኛውንም ሽታ መረዳት ይጀምራል... ተለማምዶ እስኪዘነጋው ድረስ... ጠረን እንድትለይ የሚረዱህን 'ብሩሾች' ስንቴ 'ያሸታሉ' ብለህ ጣልክ?... ስንቴስ ወደ ቀደመ ሽታህ ተመለስክ?...

ኒቼ በተወልን ድንቅ መስመር የማያልቀውን እንጨርስ... "If you have a 'why' to live by, you can live with any 'how'."

የ'ለምን' እና 'እንዴት' ድፍረት ይስጠን!!
ሰላም...❤️

ደምስ ሰይፉ
🔆🔑🔆🔑🔆🔑🔆🔑
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
ደስታችሁ በግልፅ የሚታይ ሀዘናችሁ ነው ። ሳቃችሁ የሚመነጭበት የዓይናችሁ ጉድጓድም አብዛኛውን ጊዜ በራሳችሁ እንባ የተሞላ ነው ። ከዚህስ ሌላ እንዴት ሊሆን ይችላልን? ....

💙 << ሀዘን የበለጠ ጠልቆ በውስጣችሁ በተቀረፀ ቁጥር የበለጠ ደስታ ማግኘት ትችላላችሁ . . .

💜<< ደስ ሲላችሁ ዘልቃችሁ ወደ ልባችሁ ውስጥ ተመልከቱ ። የዚያኔ ደስታን እየሰጣችሁ ያለው ያ ሀዘን ሰጥቷችሁ የነበረ ነገር ብቻ እንደነበር ትደርሱበታላችሁ . . .

<< ሀዘን ባጠላባችሁ ጊዜም እንደገና ወደ ልባችሁ ውስጥ ጠልቃችሁ ተመልከቱ ። አሁንም በእውነቱ የምታለቅሱት በዚያ ደስ ሲያሰኛችሁ በነበረው ነገር መሆኑን ትገነዘባላችሁ . . .

💙<<አንዳንዶቻችሁ <ሀዘን ከደስታ ያይላል> ትላላችሁ ። ሌሎቻችሁ ደግሞ <የለም የሚያይለው ደስታ ነው> ትላላችሁ ። እኔ ግን የማይነጣጠሉ መሆናቸውን እነግራችሁዋለሁ . . .

💜 የሚመጡትም አብረው ነው ። አንዱ ለብቻው ገበታችሁ ላይ ሲቀመጥ ፣ ሌላኛው በአልጋችሁ ላይ መተኛቱን አስታውሱ . . .

እውነት እውነት እላችዋለሁ ፣ ልክ እንደ ሚዛን በሀዘናችሁና በደስታችሁ መካከል ተንጠልጥላችሁዋል ። ሳታጋድሉ ሚዛናችሁን ጠብቃችሁ የምትቆዩት፣ባዶ በሆናችሁ ጊዜ ብቻነው ።
ካህሊል_ጅብራን

ውብ አሁን❤️
💜💙💙💙💙
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
1
ሰዓት እላፊ!
💚


"ሌሎችን በማፅናናት የተዋጣላቸው ሰዎች ራሳቸውን ማፅናናት ግን አይቻላቸውም"

ጊዜው 94 ዓመታትን ወደ ኃላ ይወስደናል... በወቅቱ አንድ ራሺያዊ ከያዘው ድብርት እና ጭንቀት እንዲገላግለው ምክር ፍለጋ ወደ ሳይካትሪስት ይሄዳል... ዶክተሩም አስፈላጊውን ምርመራ ካደረገ በኃላ እንዲ ሲል ምክርን ለታማሚው ይለግሳል...
"አሁን ካለህበት ለመውጣት አስጨናቂ እና አሳዛኝ ከሆኑ ነገሮች መራቅ ይኖርብሃል... ይህ በዕለት ተዕለት ህይወትህ እንደ ልማድ ካደረከው ንባብ ላይም ጭምር ይሁን... አስጨናቂ ፣ ዘግናኝ ፣ አስፈሪ እና አሳዛኝ ታሪክ ካላቸው ንባቦች መራቅ አለብህ... በምትኩም አስደሳች እና አዝናኝ (Comic Stories) ማንበብ አለብህ ለምሳሌም የሚካኤል ዙሽንኮ (Mikhail Zushenko) ፁሁፎችን አንብብ "
ይሄን ጊዜ ታማሚው ለዶክተሩ የሰጠው ምላሽ ዶክተሩን አስገረመው
"እኔኮ ሚካኤል ዙሽንኮ ነኝ"

ለፁሁፉ መጀመሪያ የተጠቀምኩት የ Albert Hubbard አባባል ይህን የ ሚካኤል ዙሽንኮን ታሪክ በትክክል ገላጭ ነው
Those who are good at comforting and comforting others often fail to console themselves...


➬ ሰላም እደሩ!💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta
ተማሪ ነው ለሱፊው መምህሩ ጥያቄውን ያቀረበው ፡-
‹‹ለመሆኑ ሰው በአምላኩ የሚረካው መቼ ነው?›› የመምህሩ ምላሽ ታዲያ ድንቅ ነው!

💡‹‹በበረከቱ ግዜ የሚያገኘውን ደስታ በመከራው ጊዜ መግለጥ ከቻለ በርግጥም በአምላኩ ረክቷል ማለት ነው››፡፡

❤️በአሁና ደቂቃ ብቻ የተሰጠንን በረከት ብንቆጥር፤ ያለንን መልካም ነገር ብናስተውል ………..
ወደ መሬት ጎንበስ ብለን የምናመሰግንበት አንድ ሺ አንድ ምክንያቶች አሉን!! አንድ ሺ አንድ !!!!

መልካም ዛሬ!!!

💡💡💡💡💡💡💡💡💡
@EthioHumanity
@EthioHumanity
🌗"ትጋት የተስፋ ልጅ ናት።"

🌗 "ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው በሕይወቴ ውስጥ መልካም ነገሮች ወይም ስኬት ብዬ ከማስባቸው ውስጥ ማስተርስ ዲግሪዬ ወይም ዶክትሬት ዲግሪዬ አይደለም፡፡ ልጆቼ፡ ትዳሬ፡ ቤቴ ናቸው! በሕይወቴ ትልቁ ቁም ነገር ትልቁ ስኬት እነርሱ ናቸው! እናም አሁን ሳስበው የተጓዝኩበት የሕይወቴ አቅጣጫ ትክክል ነበር፡፡ አካሒዴም በእኔ ምኞት እና መምህሬ ባሰበልኝ ሳይሆን ፈጣሪ በመረጠልኝ ስለነበር በጎ መሆኑን የኋላ ኋላ ተገንዝቢያለው፡፡

🌙እናም በሰዎች ዘንድ ተስፋ የሌለን ብንመስልም እንኳን ዋናው ነገር በፈጣሪ ዘንድ ያለው ተስፋችን ነው፡፡ ሕይወት ጠመዝማዛም ብትሆን ውብና ተስፋን የተሞላች ናት! በዚህ ዓለም ሁሉም ነገር አበቃ አከተመ! ባልንበት ጊዜ የሚቀጥል የተሻለ እድል! የምናውቀውና የተለመደው በር የተከረቸመ ቢመስልም ወለል ብሎ የሚከፈት ሌላ በር ዙሪያችን! ጭው ያለ በርሃ ቢሆንም የለመለመ መስክ የሆነ ስፍራ ላይ እንዳለ ተምሪያለው፡፡

🌗ዕድል ፊቷን ያዞረችብን በመሰለን ጊዜም ቢሆን እንኳን አብዝቶ በትጋት መጓዝ እንጂ ተስፋ መቁረጥ አይገባም፡፡ ትጋት የተስፋ ልጅ ናት። ተስፋ ደግሞ በእኛ እና በፈጣሪ መካከል የእምነት ድልድይ ስለመኖሩ ማረጋገጫ ነውና! "

🗞ከሰበዝ መጽሃፍ የተመዘዘ/ገጽ 97/

ጣፋጭ እንቅልፍ❤️❤️
🌗🌙🌗🌙🌗🌙🌗🌙🌗🌙🌗🌙
@EthioHumanity
@EthioHumanity
ለጁምኣችን!
💚

በመካ ከተማ አንድ ሰው ግራ ቀኙን እየቃኘ በመንገድ ሲያልፍ አንዲት አሮጊት እርጅና ባጎበጠው እድሜ ባሰለላቸው እጆቻቸው እየተንቀጠቀጠቀጡ ምግብ የሚያበስሉበትን እንጨት ተሸክመው ወደቤታቸው ሊሄድ ሲያጣጥሩ ይመለከታል። በአሮጊቷ ተግባር ልቡ የተነካው ይህ ሰውም በቀስታ ወደሴትየዋ ተጠግቶ « ቤትዎን ያሳዩኝ እኔ ተሸክሜ አደርስልዎታለሁ» አላቸው።
የሴትየዋ ቤት እጅግ እሩቅ ከመሆኑ ባሻገር ጸሀዩ ሲጠብሰው የዋለው አሸዋ ልክ በጋለ ፍም ላይ የመራመድ ያክል እግርን ክፉኛ ይለበልብ ነበር! ጸሀዩዋም መካ ብቻ ጓዟን ጠቅላ የሰፈረች ይመስል እንደእሳት ትፋጃለች። በነፋሱ እየተንሳፈፈ የሚመጣው የአሸዋ ብናኝም ፊትን በሀይል ይጋረፋል! እንግዲህ ይህን ፈተና ችሎ ነው ሰውየው የአሮጊቷን የደረቁ እንጨቶች ለመሸከም የወሰነው
በሰውዬው ድርጊት እየተገረሙና እየተደነቁ ቤታቸው የደረሱት ምስኪኗ አሮጊትም መልካሙን ሰውዬ ትኩር ብለው እየተመለከቱ እንዲህ አሉት ..
«ልጄ ሆይ እንዲያው ባሮጊት አንደበቴ እመርቅሀለሁ እንጂ ላደረግህልኝ ነገር መካሻ ይሆን ዘንድ የምሰጥህ አንዳች የሌለኝ ምስኪን ደሀ ነኝ ልጄ እባክህ ከሰማኸኝ አንድ ምክር ልለግስህ። ወደህዝቦችህ ወደመካ ስትመለስ እዚያ አንድ ነብይ ነኝ የሚል ሙሀመድ የሚሉት ደጋሚ ሰው አለ። በፍጹም እሱን እንዳትከተል እንዳታምነውም!» አሉት።
ሰውዬውም ረጋ ብሎ «ለምን?» ብሎ ጠየቀ!
አሮጊቷም «ልጄ እርሱ መጥፎ ስነምባር ነው ያለው ሲሉ ሰምቻለሁ» ብለው መለሱ።ሰውዬው በሴትየዋ ንግግር ተገርሞ «እኔስ ሙሀመድ ብሆን?» አላቸው። ሴትየዋም የሰሙት ነገር በጣም አስገርማቸው ለካስ ይህ ደግ ሰው ራሳቸው ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.አ.ወ) ነበሩ። አስተውሉ ... ነብዩ ለአሮጊቷ ቸርነትን ሲያደርጉ ሀይማኖታቸውን ፈፅሞ አልጠየቁም። ፍቅር የሀይማኖትን ድንበር፣ የዘርና የጎሳን አጥር እንደሚያልፍ ያውቁ ነበርና። ስብከት ያልሰበረውን ልብና ትምህርት ያላንበረከከውን ማንነት ፍቅር ብቻ ትህትናና በጎ ምግባር ብቻ ያንበረክከዋል!

ያማረ ጁምኣ!💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta