Book club
2.87K subscribers
234 photos
21 videos
1.68K files
1.58K links
በዚህ ቻናል ላይ ቆየት ያሉ አዳዲስ በገበያ ላይ የሌሉ መጽሐፍት በ pdf የሚለቀቅ ይሆናል
Download Telegram
14/10/2016
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ሉቃስ 21:12-14


ከዚህም ሁሉ በፊት እጃቸውን በላያችሁ ይጭናሉ ያሳድዱአችሁማል፤ ስለ ስሜም ወደ ምኵራብና ወደ ወኅኒ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ወደ ነገሥታትና ወደ ገዥዎችም ይወስዱአችኋል፤ ይህም ለምስክርነት ይሆንላችኋል።

ዕብራውያን 12:7-15
2 ጴጥሮስ 2:9-14
ሐዋ.ሥራ 27:1-7

ምስባክ
መዝሙር 68:10-11


ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ

በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ

ይባእ ቅድሜከ ገዓሮሙ ለሙቁሐን
Book club
በክርስትና አስተምሕሮት ውስጥ ስለምን በጣም ማወቅ ትፈልጋላቹ?
በዚ መሰረት ስለክርስትና ማወቅ ምትፈልጉትን ጽፋቹዋል ቀጣይ ሳምንት ከነዚ አንዱ ተመርጦ መጽሐፍት ግብዣ እና ትንሽ ጽሁፍ በሁለተኛው ቻናል የሚለቀቅ ይሆናል
15/10/2016
                     የዕለቱ የወንጌል ክፍል
                       ማቴዎስ 13:44-51


      “ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ። “ደግሞ መንግሥተ ሰማያት መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች፤ ዋጋዋም እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ በአገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት። “ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለች ከሁሉም ዓይነት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች፤ በሞላችም ጊዜ ወደ ወደቡ አወጡአት፥ ተቀምጠውም መልካሙን ለቅመው በዕቃዎች ውስጥ አከማቹ ክፉውን ግን ወደ ውጭ ጣሉት። “በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፤ መላእክት መጥተው ኃጢአተኞችን ከጻድቃን መካከል ይለዩአቸዋል፥ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”

ኤፌሶን 7:10-ፍጻሜ
1 ዮሐንስ 4:16-ፍጻሜ
ሐዋ.ሥራ 25:1-13


                ምስባክ
          መዝሙር 78:19-20


ውእተ አሚረ ተናገርኮሙ በራእይ ለደቂቅከ

ወትቤ እሬሲ ረድኤተ በላዕለ ኃይል

ወአልዐልኩ ኅሩይየ እምሕዝብየ
እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል... ራእይ 3:20
ባለፈው ስለ ክርስትና ማወቅ ምትፈልጉት በሚለው አብዛኞቻቹ ማወቅ ምትፈልጉትን ጽፋችኋል ለቀጣይ ሳምንት ማለትም ከነገ ጀምሮ ለሚኖረው ሳምንት በምሥጢረ ሥላሴ ዙሪያ ከተለያዩ መጽሐፍ በሁለተኛው ቻናላችን የሚለቀቅ ይሆናል ያው ስንለቅ ስተት ካለ ይሄን አስተካክሉ ሃሳብ አስተያየት እንድሰጡን እና የከበዳቹ ነገርም ካለ በመልእክት ማስቀመጫው ወይም በግሩፑ ላይ መጠየቅ ትችላላቹ በዚ አይተነው መልካም ከሆነ በየሳምንቱ በተለያየ ርእስ የምንማማር ይሆናል

ለሳምንቱም በዛ ርእስ የሚያተኩር አኔድ መጽሐፍ ይለቀቃል ሁላችንም አንብበው በዚሁ የምናየው ይሆናል
ምንባባት ዘጰራቅሊጦስ
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ዮሐንስ 14:1-25


ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ። ወደምሄድበትም ታውቃላችሁ፥ መንገዱንም ታውቃላችሁ። ቶማስም፦ “ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን?” አለው። ኢየሱስም አለው፦ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር። ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል።” ፊልጶስ፦ “ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል፡” አለው። ኢየሱስም አለው፦ “አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ፦ ‘አብን አሳየን፡’ ትላለህ? እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል። እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።” “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ። እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ። ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”

ኤፌሶን 4:1-17
1 ዮሐንስ 2:1-14


ሐዋ. ሥራ 2:1-14

   በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው። እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው። በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር። ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፤ ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፥ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ። ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ፦ “እነሆ፥ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን? የጳርቴና የሜድ የኢላሜጤም ሰዎች፥ በሁለት ወንዝም መካከል በይሁዳም በቀጰዶቅያም በጳንጦስም በእስያም፥ በፍርግያም በጵንፍልያም በግብፅም በቀሬናም በኩል ባሉት በሊቢያ ወረዳዎች የምንኖር፥ በሮሜም የምንቀመጥ፥ አይሁድም ወደ ይሁዲነትም የገባን፥ የቀርጤስና የዓረብ ሰዎች፥ የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለን።” ሁሉም ተገረሙና አመንትተው እርስ በርሳቸው፦ “እንጃ ይህ ምን ይሆን?” አሉ።  ሌሎች ግን እያፌዙባቸው፦ “ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል፡” አሉ።

ምስባክ
መዝሙር 67:18-19


ዐረገ ውስተ ዓርያም ፄዊወከ ፄዋ

ወወሀብከ ጸጋከ ለእጓለ እመሕያው

እስመ ይክህዱ ከመ ይድኅሩ
ሰላም እንደምን አደራቹ ምሥጢረ ሥላሴ ላይ የተወሰነ ነገር በዚ ሳምንት እንማማራለን ባልነው መሰረት ከዛሬ ማታ ጀምሮ በሁለተኛው ቻናል እግዚአብሔር በፈቀደ መልኩ የምንማማር ይሆናል
17/10/2016
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ሉቃስ 6:20-24


እርሱም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዓይኑን አነሣ፥ እንዲህም አላቸው፦ “እናንተ ድሆች ብፁዓን ናችሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት የእናንተ ነውና። እናንተ አሁን የምትራቡ ብፁዓን ናችሁ፥ ትጠግባላችሁና። እናንተ አሁን የምታለቅሱ ብፁዓን ናችሁ፥ ትስቃላችሁና። ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ። እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና።

2 ጢሞቴዎስ 1:1-10
ያዕቆብ 5:14-17
ሐዋ.ሥራ 13:44-49


ምስባክ
መዝሙር 1:4-5


አኮ ከመዝ ኃጥአንሰ አኮ ከመዝ

ዳዕሙ ከመ መሬት ዘይግሕፎ ነፋስ እምገጸ ምድር

ወበእንተዝ ኢይትነሥኡ ረሢዓን እምደይን
ምሥጢረ ሥላሴ የመጀመሪያው ክፍል ተለቋል ገብታቹ አንብባቹ ትንሽም ብቶን ምጠቅማቹን ነገር ውሰዱ አስተያየታቹንም ጻፉልን
18/10/2016
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ማቴዎስ 18:15-19


“ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤ ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤ እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ። እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።

2 ጢሞቴዎስ 3:1-ፍጻሜ
2 ጴጥሮስ 2:9-14
ሐዋ.ሥራ 17:5-13


ምስባክ
መዝሙር 54:17-18


ሠርከ ወነግሀ ወመዓልተ እነግር

አየድዕ ወኢሰምዑኒ ቃልየ

አድኅና በሰላም ለነፍስየ እምእለ ይትቃረቡኒ
19/10/2016
                    የዕለቱ የወንጌል ክፍል
                       ማቴዎስ 24:8-13


      እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። “በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ “ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች...

1 ተሰሎንቄ 1:1-8
1 ዮሐንስ 2:14-20
ሐዋ.ሥራ19:11-18


                      ምስባክ   
                 መዝሙር 70:1-11


ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ

በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ

ይባእ ቅድሜከ ገአሮሙ ለሙቁሐን
20/10/2016
                  የዕለቱ የወንጌል ክፍል
                    ሉቃስ 4:24-38


    እንዲህም አለ፦ “እውነት እላችኋለሁ፥ ነቢይ በገዛ አገሩ ከቶ አይወደድም። ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ፥ በኤልያስ ዘመን ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ሰማይ ተዘግቶ ሳለ በምድር ሁሉ ብርቱ ራብ በነበረ ጊዜ፥ በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ፤ “ኤልያስም በሲዶና አገር ወዳለች ወደ ሰራፕታ ወደ አንዲት መበለት እንጂ ከእነርሱ ወደ አንዲቱ አልተላከም። በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች ነበሩ፥ ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነርሱ አንድ ስንኳ አልነጻም።” በምኵራብም የነበሩ ሁሉ ይህን ሰምተው ቍጣ ሞላባቸው፥ ተነሥተውም ከከተማ ወደ ውጭ አወጡት፥ ይጥሉትም ዘንድ ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበረች ወደ ተራራው አፋፍ ወሰዱት፤ እርሱ ግን በመካከላቸው አልፎ ሄደ። ወደ ገሊላ ከተማም ወደ ቅፍርናሆም ወረደ። በሰንበትም ያስተምራቸው ነበር፤ ቃሉ በሥልጣን ነበርና በትምህርቱ ተገረሙ። በምኵራብም የርኵስ ጋኔን መንፈስ ያደረበት ሰው ነበረ፥ በታላቅ ድምፅም ጮኾ፦ “ተው፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄሃለሁ፥ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱሱ፡” አለ። ኢየሱስም፦ “ዝም በል ከእርሱም ውጣ” ብሎ ገሠጸው። ጋኔኑም በመካከላቸው ጥሎት ሳይጐዳው ከእርሱ ወጣ። ሁሉንም መደነቅ ያዛቸው፥ እርስ በርሳቸውም፦ “ይህ ቃል ምንድር ነው? በሥልጣንና በኃይል ርኵሳን መናፍስትን ያዝዛልና፥ ይወጡማል፡” ብለው ተነጋገሩ። ዝናም በዙሪያው ባለች አገር ወደ ስፍራው ሁሉ ስለ እርሱ ወጣ......

1 ቆሮንጦስ 14:29-34
2 ጴጥሮስ 3:1-8
ሐዋ.ሥራ 13:38-44


                     ምስባክ
                 መዝሙር 65:5-6


ግሩም ምክሩ እምጓለእመሕያው

ዘይሬስያ ለባሕር የብሰ

ወበተከዚ የሐልፉ በእግር
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ፊልጵስዩስ 4:4
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ 1 ኛ ተሰሎንቄ 5:16
21/10/2016
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ማቴዎስ 16:13-20

ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?” ብሎ ጠየቀ። እነርሱም፦ “አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው፥ ይላሉ፡” አሉት። እርሱም፦ “እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?” አላቸው። ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ፡” አለ። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ። እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል”።

ኤፌሶን 2:13-ፍጻሜ
1 ጴጥሮስ 2:4-11
ሐዋ.ሥራ1:12-15


ምስባክ
መዝሙር 45:4-5


ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል

እግዚአብሔር ውስተ ማእከላ ኢትትሐወክ

ወይረድእ እግዚአብሔር ፍጽመ
"ለዛቲ ቤት አነጻ ወልድ፤
ወፈጸማ መንፈስ ቅዱስ።"

​​​​እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!

ሰኔ 20 እና 21

ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል።

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸችው በዛሬዋ ቀን ነው፤ አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።

ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ።

ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር።

ከማኅበራዊ ሚዲያ የተወሰደ
22/10/2016
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ማቴዎስ 5:39-ፍጻሜ

እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤ እንዲከስህም እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት፤ ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ። ለሚለምንህ ስጥ፥ ከአንተም ይበደር ዘንድ ከሚወደው ፈቀቅ አትበል። ‘ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ፡’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።”

1 ቆሮንጦስ 5:6-ፍጻሜ
ያዕቆብ 5:14-ፍጻሜ
ሐዋ.ሥራ13:44-ፍጻሜ


ምስባክ
መዝሙር 36:7-8


ወኢትቅናዕ ላዕለ ዘይዴሎ በሕይወቱ

ወላዕለ ሰብእ ዘይገብር ዓመፃ

ኅድጋ ለመዓት ወግድፋ ለቁጥዓ
24/10/2016
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ዮሐንስ 12:20-26


በበዓሉም ሊሰግዱ ከወጡት አንዳንዶቹ የግሪክ ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም ከገሊላ ቤተ ሳይዳ ወደሚሆን ወደ ፊልጶስ መጥተው፦ “ጌታ ሆይ፥ ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን፡” ብለው ለመኑት። ፊልጶስም መጥቶ ለእንድርያስ ነገረው፤ እንድርያስና ፊልጶስ መጥተው ለኢየሱስ ነገሩት። ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል፦ “የሰው ልጅ ይከብር ዘንድ ሰዓቱ ደርሶአል። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች። ነፍሱን የሚወድ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም በዚህ ዓለም የሚጠላ ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል።

ሮሜ 9:24-ፍጻሜ
1 ዮሐንስ 1:4-ፍጻሜ
ሐዋ.ሥራ 14:1-7


ምስባክ
መዝሙር 31:4-5


ኃጢአትየ ነገርኩ ወአበሳየ ኢኀባዕኩ

ወእቤ አስተዋዲ ርእስየ ኀበ እግዚአብሔር በእንተ ኃጢአትየ

ወአንተ ኅድግ ጽለሑቶ ለልብየ
26/10/2016
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ማቴዎስ 13:36-44

በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው፦ “የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን፡” አሉት። እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው። እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል። “የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ”.......

ዕብራውያን 4:1-14
2 ጴጥሮስ 1:19-ፍጻሜ
ሐዋ.ሥራ 7:35-44


ምስባክ
መዝሙር 134:10-11


ወቀተለ ነገሥተ ጽኑዓነ

ለሴዎን ንጉሠ አሞሬዎን

ወለዓግ ንጉሠ ባሳን
27/10/2016
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ማቴዎስ 16:19-ፍጻሜ


የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል”። ያን ጊዜም እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለማንም እንዳይነግሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው። ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር። ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ፦ “አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም፡” ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ። እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ “ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል፡” አለው። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?“የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል። እውነት እላችኋለሁ፥ የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ እዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ።”

1 ቆሮንጦስ 12:28-ፍጻሜ
1 ዮሐንስ 2:27-ፍጻሜ
ሐዋ.ሥራ 9:10-20


ምስባክ
መዝሙር 68:29-30


ነዳይ ወቁሱል አነ

መድኃኔ ገጽየ እግዚአብሔር ተወክፈኒ

እሴብሕ ለስመ አምላኪየ በማኅሌት