Book club
2.87K subscribers
234 photos
21 videos
1.68K files
1.58K links
በዚህ ቻናል ላይ ቆየት ያሉ አዳዲስ በገበያ ላይ የሌሉ መጽሐፍት በ pdf የሚለቀቅ ይሆናል
Download Telegram
06/10/2016
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ሉቃስ 12:32-41

“አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ። ያላችሁን ሽጡ ምጽዋትም ስጡ፤ ሌባ በማይቀርብበት ብልም በማያጠፋበት በሰማያት የማያልቅ መዝገብ የሚሆኑትን የማያረጁትንም ኮረጆዎች ለራሳችሁ አድርጉ፤ መዝገባችሁ ባለበት ልባችሁ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።” “ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤ እናንተም ጌታቸው መጥቶ ደጁን ሲያንኳኳ ወዲያው እንዲከፍቱለት ከሰርግ እስኪመለስ ድረስ የሚጠብቁ ሰዎችን ምሰሉ። ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል ቀርቦም ያገለግላቸዋል። ከሌሊቱም በሁለተኛው ወይም በሦስተኛው ክፍል መጥቶ እንዲሁ ቢያገኛቸው፥ እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው። ይህን ግን እወቁ ባለቤት በምን ሰዓት ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ፥ ቤቱም እንዲቆፈር ባልፈቀደም ነበር። እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና.....

2 ቆሮንጦስ 9:5-13
ያዕቆብ 1:12-19
ሐዋ.ሥራ 5:26-33


ምስባክ
መዝሙር 111:9-10

ዘረወ ወወሀበ ለነዳይ

ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም

ወይትሌዓል ቀርኑ በክብር

ትርጉም

በተነ ለችግረኞችም ሰጠ

ጽድቁ ለዘላለም ዓለም ይኖራል

ቀንዱ በክብር ከፍ ከፍ ይላል
ከዕርገት እስከ ጰራቅሊጦስ በቅዳሴ የሚነበቡ ምንባባት

ወንጌሉ ሉቃ 24:45-ፍጻሜ
ሮሜ 10:1-ፍጻሜ
1ጴጥሮስ 3:15-ፍጻሜ
ሐዋ.ሥራ 1:1-12
ምስባክ 46:5-6


እንኳን አደረሳቹ
08/10/22016
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ዮሐንስ 4:1-15

እንግዲህ፦ “ኢየሱስ ከዮሐንስ ይልቅ ደቀ መዛሙርት ያደርጋል፡ ያጠምቅማል፡” ማለትን ፈሪሳውያን እንደ ሰሙ ጌታ ባወቀ ጊዜ፥ ይሁዳን ትቶ ወደ ገሊላ ደግሞ ሄደ፤ ዳሩ ግን ደቀ መዛሙርቱ እንጂ ኢየሱስ ራሱ አላጠመቀም። በሰማርያም ሊያልፍ ግድ ሆነበት። ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ ወደምትሆን ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤ በዚያም የያዕቆብ ጕድጓድ ነበረ። ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ ደክሞ በጕድጓድ አጠገብ እንዲህ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ስድስት ሰዓት ያህል ነበረ። ከሰማርያ አንዲት ሴት ውኃ ልትቀዳ መጣች። ኢየሱስም፦ “ውኃ አጠጪኝ፡” አላት፤ ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበርና። ስለዚህ ሳምራዊቲቱ፦ “አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ?” አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና። ኢየሱስ መልሶ፦ “የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ‘ውኃ አጠጪኝ፥’ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ፡ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር፡” አላት። ሴቲቱ፦ “ጌታ ሆይ፥ መቅጃ የለህም፡ ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውኃ ከወዴት ታገኛለህ? በእውኑ አንተ ይህን ጕድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? ራሱም ልጆቹም ከብቶቹም ከዚህ ጠጥተዋል፡” አለችው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላት፦ “ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ።” ሴቲቱ፦ “ጌታ ሆይ፥ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ፡” አለችው።

ኤፌሶን 2:13-ፍጻሜ
1 ጴጥሮስ 1:10-13
ሐዋ.ሥራ 7:44-51


ምስባክ
መዝሙር 77:15-16


ወአስተዮሙ ከመ ዘእምቀላይ ብዙኅ

ወአውኀዘ ማየ ከመ ዘእም አፍላግ

ወአውጽአ ማየ እም እብን
ከእርገት በኋላ ያለ እሁድ
                       የዕለቱ የወንጌል ክፍል
                           ሉቃስ 24:45-ፍጻሜ

 
በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥ በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል፡ ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል። እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ። እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ። እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ። እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ።

ሮሜ 10:1-ፍጻሜ
1ጴጥሮስ 3:15-ፍጻሜ
ሐዋ.ሥራ 1:1-12


  ምስባክ
                መዝሙር 46:5-6


ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ

ወእግዚእነ በቃለ ቀርን

ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ

ትርጉም

አምላክ በእልልታ

እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ

ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ
10/10/2016
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ማቴዎስ 11:20-ፍጻሜ


በዚያን ጊዜ የሚበዙ ተአምራት የተደረገባቸውን ከተማዎች ንስሐ ስላልገቡ ሊነቅፋቸው ጀመረ እንዲህም አለ፦ “ወዮልሽ ኮራዚ፤ ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ፤ በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው አመድም ነስንሰው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበርና። ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል። አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ፤ በአንቺ የተደረገው ተአምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን፥ እስከ ዛሬ በኖረች ነበርና። ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከአንቺ ይልቅ ለሰዶም አገር ይቀልላታል።” በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፦ “አባት ሆይ፥ የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ፤ አዎን፥ አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና። ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም። እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና......

1 ቆሮ 7:25-35
1 ዮሐንስ 1:4-ፍጻሜ
ሐዋ.ሥራ 15:30-36


ምስባክ
መዝሙር 89:14-15


ተፈሣሕነ ወተሐሠይነ በኩሉ መዋዕሊነ

ወተፈሣሕነ ህየንተ መዋዕል ዘአሕመምከነ

ወህየንተ ዓመት እንተ ርኢናሃ ለእኪቶ

ትርጉም

በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን

መከራን ባሳየኸን ዘመን ፈንታ

ክፉም ባየንባቸው ዘመኖች ፋንታ ደስ ይለናል
11/10/2016
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ማቴዎስ 10:16-32

“እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤ ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ። አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና። “ወንድምም ወንድሙን፥ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ ይገድሉአቸውማል። በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም። “ደቀ መዝሙር ከመምህሩ፥ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም። ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!” “እንግዲህ አትፍሩአቸው፤ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና። በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ። ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል። እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ።”

2 ቆሮንጦስ 5:1-11
1 ጴጥሮስ 6-12
ሐዋ.ሥራ 16:35-ፍጻሜ


ምስባክ
መዝሙር 90:5-6


ወኢትፈርህ እምግርማ ሌሊት

እምሐፅ ዘይሠርር በመዓልት

ወእምግብር ዘየሐውር በጽልመት
የበረሃው ምስጢር ሙሉ መጽሐፍ በ ሁለተኛው ቻናላችን ተለቆዋል ገብታቹ አንብቡት
12/10/2016
                      የዕለቱ የወንጌል ክፍል
                       ማቴዎስ 25:14-31


    “ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና  ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ። አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ። “ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው። አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ፦ ‘ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት፡’ አለ። ጌታውም፦ ‘መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ፡’ አለው። ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ “ጌታ ሆይ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት፡” አለ። ጌታውም፦ ‘መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ፡’ አለው። አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ‘ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ፡’ አለ። ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፦ ‘አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንሁባትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፥ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር። ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አሥር መክሊትም ላለው ስጡት፤ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል። የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል’።”
13/10/2016
                     የዕለቱ የወንጌል ክፍል
                        ሉቃስ 18:18-23


    ከአለቆችም አንዱ፦ “ቸር መምህር፥ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ?” ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም፦ “ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም። ትእዛዛቱን ታውቃለህ፥ አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አባትህንና እናትህን አክብር፡” አለው። እርሱም፦ “ይህን ሁሉ ከሕፃንናቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ፡” አለ። ኢየሱስም ይህን ሰምቶ፦ “አንዲት ገና ቀርታሃለች፤ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ፡” አለው....

1 ጢዎቴዎስ 6:7-20
1 ጴጥሮስ 1:13-ፍጻሜ
ሐዋ.ሥራ 8:20-26


                            ምስባክ
                      መዝሙር 36:21-22


ይትሌቃሕ ኃጥእ ወኢይፈዲ

ወጻድቅሰ ይምህር ወይሁብ

እስመ እለ ይባርክዎ ይወርስዋ ለምድር
በክርስትና አስተምሕሮት ውስጥ ስለምን በጣም ማወቅ ትፈልጋላቹ?
14/10/2016
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ሉቃስ 21:12-14


ከዚህም ሁሉ በፊት እጃቸውን በላያችሁ ይጭናሉ ያሳድዱአችሁማል፤ ስለ ስሜም ወደ ምኵራብና ወደ ወኅኒ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ወደ ነገሥታትና ወደ ገዥዎችም ይወስዱአችኋል፤ ይህም ለምስክርነት ይሆንላችኋል።

ዕብራውያን 12:7-15
2 ጴጥሮስ 2:9-14
ሐዋ.ሥራ 27:1-7

ምስባክ
መዝሙር 68:10-11


ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ

በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ

ይባእ ቅድሜከ ገዓሮሙ ለሙቁሐን
Book club
በክርስትና አስተምሕሮት ውስጥ ስለምን በጣም ማወቅ ትፈልጋላቹ?
በዚ መሰረት ስለክርስትና ማወቅ ምትፈልጉትን ጽፋቹዋል ቀጣይ ሳምንት ከነዚ አንዱ ተመርጦ መጽሐፍት ግብዣ እና ትንሽ ጽሁፍ በሁለተኛው ቻናል የሚለቀቅ ይሆናል
15/10/2016
                     የዕለቱ የወንጌል ክፍል
                       ማቴዎስ 13:44-51


      “ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ። “ደግሞ መንግሥተ ሰማያት መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች፤ ዋጋዋም እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ በአገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት። “ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለች ከሁሉም ዓይነት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች፤ በሞላችም ጊዜ ወደ ወደቡ አወጡአት፥ ተቀምጠውም መልካሙን ለቅመው በዕቃዎች ውስጥ አከማቹ ክፉውን ግን ወደ ውጭ ጣሉት። “በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፤ መላእክት መጥተው ኃጢአተኞችን ከጻድቃን መካከል ይለዩአቸዋል፥ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”

ኤፌሶን 7:10-ፍጻሜ
1 ዮሐንስ 4:16-ፍጻሜ
ሐዋ.ሥራ 25:1-13


                ምስባክ
          መዝሙር 78:19-20


ውእተ አሚረ ተናገርኮሙ በራእይ ለደቂቅከ

ወትቤ እሬሲ ረድኤተ በላዕለ ኃይል

ወአልዐልኩ ኅሩይየ እምሕዝብየ
እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል... ራእይ 3:20
ባለፈው ስለ ክርስትና ማወቅ ምትፈልጉት በሚለው አብዛኞቻቹ ማወቅ ምትፈልጉትን ጽፋችኋል ለቀጣይ ሳምንት ማለትም ከነገ ጀምሮ ለሚኖረው ሳምንት በምሥጢረ ሥላሴ ዙሪያ ከተለያዩ መጽሐፍ በሁለተኛው ቻናላችን የሚለቀቅ ይሆናል ያው ስንለቅ ስተት ካለ ይሄን አስተካክሉ ሃሳብ አስተያየት እንድሰጡን እና የከበዳቹ ነገርም ካለ በመልእክት ማስቀመጫው ወይም በግሩፑ ላይ መጠየቅ ትችላላቹ በዚ አይተነው መልካም ከሆነ በየሳምንቱ በተለያየ ርእስ የምንማማር ይሆናል

ለሳምንቱም በዛ ርእስ የሚያተኩር አኔድ መጽሐፍ ይለቀቃል ሁላችንም አንብበው በዚሁ የምናየው ይሆናል
ምንባባት ዘጰራቅሊጦስ
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ዮሐንስ 14:1-25


ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ። ወደምሄድበትም ታውቃላችሁ፥ መንገዱንም ታውቃላችሁ። ቶማስም፦ “ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን?” አለው። ኢየሱስም አለው፦ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር። ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል።” ፊልጶስ፦ “ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል፡” አለው። ኢየሱስም አለው፦ “አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ፦ ‘አብን አሳየን፡’ ትላለህ? እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል። እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።” “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ። እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ። ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”

ኤፌሶን 4:1-17
1 ዮሐንስ 2:1-14


ሐዋ. ሥራ 2:1-14

   በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው። እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው። በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር። ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፤ ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፥ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ። ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ፦ “እነሆ፥ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን? የጳርቴና የሜድ የኢላሜጤም ሰዎች፥ በሁለት ወንዝም መካከል በይሁዳም በቀጰዶቅያም በጳንጦስም በእስያም፥ በፍርግያም በጵንፍልያም በግብፅም በቀሬናም በኩል ባሉት በሊቢያ ወረዳዎች የምንኖር፥ በሮሜም የምንቀመጥ፥ አይሁድም ወደ ይሁዲነትም የገባን፥ የቀርጤስና የዓረብ ሰዎች፥ የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለን።” ሁሉም ተገረሙና አመንትተው እርስ በርሳቸው፦ “እንጃ ይህ ምን ይሆን?” አሉ።  ሌሎች ግን እያፌዙባቸው፦ “ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል፡” አሉ።

ምስባክ
መዝሙር 67:18-19


ዐረገ ውስተ ዓርያም ፄዊወከ ፄዋ

ወወሀብከ ጸጋከ ለእጓለ እመሕያው

እስመ ይክህዱ ከመ ይድኅሩ
ሰላም እንደምን አደራቹ ምሥጢረ ሥላሴ ላይ የተወሰነ ነገር በዚ ሳምንት እንማማራለን ባልነው መሰረት ከዛሬ ማታ ጀምሮ በሁለተኛው ቻናል እግዚአብሔር በፈቀደ መልኩ የምንማማር ይሆናል