Ethiopian National Dialogue Commission/የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
4.57K subscribers
2.67K photos
190 videos
9 files
418 links
ይህ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎችና ሃሳቦች የሚጋሩበት ነው፡፡ ስለተወዳጁን እናመሰግናለን!
ሀገራዊ ምክክር
ለሀገራዊ መግባባት!
Download Telegram
ሰበር ዜና


የሃይማኖት ጉዳዮች እና የሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሃሳቦቻቸው መግባባት ላይ ደረሱ


ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም


የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ጀምሮ እያካሄደ ባለው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በኮሚሽኑ ምክር ቤት በተለዩ ስምንት አጀንዳዎች ላይ ምክክር እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡


አጀንዳዎቹ 500 አባላት ባሏቸው ስምንት የስራ ቡድኖች ምክክር እየተደረገባቸው ይገኛሉ፡፡ በኮሚሽኑ የአሰራር ሥነ-ዘዴ መሰረት 500 አባላት ያሉት አንድ ቡድን በአንድ አጀንዳ ላይ እየተመካካረ ይገኛል፡፡


በዚህም በሃይማኖት ጉዳዮች እና በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ለይ ሲመካካሩ የቆዩት ሁለት ቡድኖች ዛሬ ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም በተጠናቀሩ ምክረ ሃሳቦቻቸው ላይ ተስማማተው በተዘጋጀው ቃለ ጉባኤ ላይ ተፈራርመዋል፡፡


የሌሎች አጀንዳዎች ተመካካሪዎችም በቀጣይ ቀናት በተመሳሳይ መልኩ የአጀንዳ ሃሳቦቻቸውን የጋራ አድርገው በቃለ ጉባኤዎቻቸው ላይ በመፈራረም እንደሚስማሙ ይጠበቃል፡፡
12👎1
ተጨማሪ መረጃ
ሁለት ተጨማሪ የሥራ ቡድኖች በተመካከሩባቸው ምክረ-ሃሳቦች ላይ መግባባት ላይ ደረሱ
ነሐሴ 05 ቀን 2018 ዓ.ም
👉በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ እንዲሁም የፖለቲካ ሥርዓት፣የፖለቲካ ውክልና እና የምርጫ ስርአት
👉በሙስና እና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች
ሲመካከሩ የቆዩት እያንዳንዳቸው 500 አባላት ያሏቸው የሥራ ቡድኖች ተጠናቅረው በቀረቡ የአጀንዳ ምክረ-ሀሳቦች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውን በተዘጋጁት የቃለ-ጉባኤ ሰነዶች ላይ በመፈረም አረጋግጠዋል።
ምክክር እየተደረገባቸው ከሚገኙ 8 አጀንዳዎች መካከል እነዚህ ሁለት ተመካካሪ ቡድኖች ተጠቃሽ ሲሆኑ በእነዚህ አጀንዳዎች ላይ በተለያዩ የቡድን አደረጃጀቶችና እርከኖች ሲመካከሩ መቆይታቸው የሚታወስ ነው።
17👏2👍1
የስራ ቡድኖች የአጀንዳ ምክረሃሳቦቻቸውን ለሚያደራጀው ቡድን እያቀረቡ ነው
ነሀሴ 8/2018 ዓ.ም
የስራ ቡድኖች ሁሉም ቡድኖች ያዘጋጇቸውንና የተስማሙባቸውን ምክረ-ሀሳቦች እንዲያናብብ፣ እንዲያጣጥም እና እንዲያደራጅ ለተቋቋመው እና 120 አባላት ላሉት ቡድን በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡
ይህ ቡድን ከስምንቱ ባለ 500 አባላት የስራ ቡድን በተመረጡ 15 አባላት የተዋቀረ ሲሆን መግባባት የተደረሰባቸውን የሁሉንም አጀንዳዎች ምክረሃሳቦች አዳምጦ የሚያጣጥም፣ በሚቀርቡ ሀሳቦች መካከል መጣረስ እንዳይኖር ጥንቃቄ የሚያደርግና ለጠቅላላ ሀሳቦቹ ወጥነት በመፍጠር 4ሺ አባላት ላሉት ዋናው ጉባኤተኛ አደራጅቶ የሚያቀርብ ነው፡፡
ቡድኑ በአሁኑ ሰዓት ከእያንዳንዱ የስራ ቡድን የመጡ ምክረሃሳቦችን በማዳመጥ ላይ ነው፡፡
🥰96
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ውሎ መግለጫ- በምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ
ነሀሴ 11/2018 ዓ.ም
👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ውሎ መግለጫ- በምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ

ነሀሴ 13/2018 ዓ.ም
👍1
ተቀናጅተው የቀረቡ የአጀንዳ ሃሳቦች ለሥራ ቡድኖች ቀረቡ፡፡
ነሀሴ 13/2018 ዓ.ም
ከየሥራ ቡድኑ የተወከሉ 120 ተመካካሪዎችን ያካተተው የአጀንዳ አቀናጅ ቡድን ለየስራ ቡድኖቹ የተቀናጁትን ምክረ ሃሳቦች ዛሬ አቅርቧል፡፡ በ8 ቡድን ተደራጅተው የተዘጋጁት ምክረ-ሃሳቦችም ለእያንዳንዱ ቡድን ቀርቧል፡፡
የስራ ቡድኖች በየራሳቸው አጀንዳዎች ላይ የመጨረሻ ግብዓት ሰጥተው አጠናቃሪ አባላቶቻቸው የመጨረሻ ምክረሃሳብ አእንዲያዘጋጁ መልሰዋል፡፡
የሚቀርቡ ምክረ-ሃሳቦች ላይ ሊኖሩ የሚችሉ የሃሳብ መጣረሶችን እና ድግግሞሾችን ለማስቀረት የተዘጋጀው ይህ ሂደት ላላፉት ቀናት ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል፡፡https://web.facebook.com/?_rdc=1&_rdr#
4