ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
220K subscribers
10.9K photos
165 videos
55 files
1.2K links
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Download Telegram
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
Photo
በአዲስ አበባ ከተማ በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በግብረ ኃይል የማስከፈት ስራ ተጀመረ‼️

በአዲስ አበባ በከተማ ተለያዩ አካባቢዎች በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በግብረ ኃይል የማስከፈት ሾል በትናንትናው ዕለት  መጀመሩን የከተማዋ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ።ባለስልጣኑ ይህን እርምጃ መውሰድ የጀመረው፣ ከሳምንታት በፊት በከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን አጥረው የዘጉ ግለሰቦች መንገዶቹን ከታኅሣሥ 4 ቀን 2018 ዓ.ም.  ጀምሮ ባሉት ሰባት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ክፍት እንዲያደርጉ የሰጠው ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ ባለመሆኑ ነው።

ባለስልጣኑ ትናንት ባጋራው መረጃ፣ የደቡብ አዲስ አበባ መንገድ ኔትዎርክ ማኔጅመንት ቡድን መሪ ኢንጅነር ቢሊሱማ በዬቻ፤ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በግለሰቦች በአጥር መዝጋታቸው፤ የህብረተሰቡን በመንገድ መሰረተ ልማት የመጠቀም መብት የሚጋፋና ለትራፊክ ፍሰት መስተጓጎል መንስኤ እየሆነ እንደሚገኝ ገልፀዋል ብሏል፡፡

በመሆኑም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቃሊቲ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ፤ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በአጥር የዘጉ አካላት፣ አጥሩን እንዲያነሱ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ቢሆንም፤ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ባለመነሳቱ ከወረዳው የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በግብር ኃይል እንዲነሳ መደረጉን ገልጸዋል።

የደቡብ አዲስ አበባ የመንገድ ኔትዎርክ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት የአስተዳደርና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ አብይ ኪዳኑ በበኩላቸው፤ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በአጥር በመዘጋታቸው ነፍሰጡር እናቶች ሌሊት ላይ ወደ ህክምና ተቋም ለመሄድና የአደጋመካከል ሥራዎችን በአግባቡ ለማከናወን አስቸጋሪ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ፤ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የተበላሹ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ለመጠገን የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ጭምር እያስተጓጎለ መምጣቱን የጠቀሱት አቶ ዓብይ ፤ በግብረ ኃይል እንዲነሳ መደረጉ በየአካባቢው ህብረተሰቡ ለሚያነሳው የመንገድ አገልግሎት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡በቀጣይ ቀናትም ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ይህንኑ ተግባር በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤175👍11😁2
👍51❤13😁13😱1
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
Photo
ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ‼️

ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ መልዕክቶች ተደራሽነታቸው የበዛ በመሆኑ በትውልዱ ላይ የሚያሳድሩት አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ማህበራዊ ሚዲያን በአግባብና በኃላፊነት መንፈስ ከተጠቀሙበት ትውልድን በስነ ምግባር ለማነፅና ለማፅናት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አመልክቷል፡፡

ነገር ግን ከዚህ በተፃራሪ የተሰለፉ አንዳንድ ግለሰቦች ለማየትና ለመስማት አጸያፊ የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶችን ሲሰሊ እንደሚታዩ ፖሊስ ገልጿል፡፡    

በዚህም መሰረት ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ ከነበሩ ግለሰቦች አንዱ የሆነውን ነዋሪነቱ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሚገኝ ናትናኤል ባደግ ገብሬ የተባለን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው የአዲስ አበባ ፖሊስ የገለፀው፡፡

ተጠርጣሪው የማህበራዊ ሚዲያን በተለይም ዩቱዩብ እና ቲክቶክን በመጠቀም በንግግር ልቅ ፆታዊ ግንኙነትን የሚያበረታታና የሚያስፋፋ አፀያፊ መልዕክቶችን ሲያሰራጭ መቆየቱ ተጠቁሟል።

ተጠርጣሪው በተለምዶአዊው ንግግር ሊገለፁ የማይችሉ አስፀያፊ ቃላትን በመጠቀም በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር እንደነበር እና መሰል ይዘቶችን በተደጋጋሚ ጊዜ በመስራት በማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ሲያሰራጭ እንደነበርም ፖሊስ አብራርቷል፡፡

ፖሊስ በቁጥጥር ስር በዋለው ናትናኤል ባደግ ወይም "የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ወይም ይዘት ፈጣሪ ነኝ" በሚለው ግለሰብ ላይ ምርመራ መጀመሩን ጠቅሷል።

በአንዳንድ ኃላፊነት በማይሰማቸው ግለሰቦች በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከህብረተሰቡ ሞራል ባህልና እሴት ባፈነገጠ ሁኔታ አሉታዊ መረጃዎች እየተሰራጩ መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ፤ ይህም በማህበረሰቡ በተለይም ታዳጊ በሆኑ ህፃናት ሥነ-ልቦናና ሞራል ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን ገልጿል፡፡    

የአዲስ አበባ ፖሊስ አክሎም፤ በቀጣይ ተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ በሚገቡ ግለሰቦች ላይ ተገቢውን ህጋዊ ርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤240👍70👏28💔18😡5😁1
በናይጄሪያ መስጊድ በሰላት ወቅት ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ቢያንስ 5 ሰዎች ሲገደሉ 35 ሰዎች ቆሰሉ‼️

በናይጄሪያ ሰሜናዊ ምስራቅ ቦርኖ ግዛት ሀሙስ በምሽት ሰላት ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ቢያንስ አምስት ሰዎች ሲገደሉ 35 ያህል ሰዎች ቆስለዋል ሲሉ የፖሊስ ቃል አቀባይ ኤኤስፒ ናሆም ዳሶ ኬኔት የማህበራዊ ሚዲያ ድረ-ገጽ በሆነዉ ፌስቡክ ላይ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡

በመግለጫው መሰረት፣ ባለስልጣናት በግዛቱ ዋና ከተማ ማይዱጉሪ የተፈጸመው ፍንዳታ በአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ ነው ብለው እንደሚጠረጥሩ በማንሳት ምስክሮች ከሰጡት ቃል እና በአጥፍቶ ጠፊነት ከተጠረጠረው ልብስ ውስጥ ቁርጥራጮች መገኘታቸውን ገልጸዋል።

ኃላፊዎቹ የችግሩን መንስኤና ሁኔታ ለማወቅ ምርመራውን ቀጥሏል ብለዋል ።የቦርኖ ግዛት ለዓመታት በታጣቂዉ ቦኮ ሃራም እና መሰል ቡድኖች ስትታመስ ቆይታለች።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤122😭116👍18🔥8👏3😁2
ከ100 የሚበልጡ ስደተኞች በሜድትራንያን ባህር ላይ ህይወታቸው አለፈ።

117 ሰዎችን ጭኖ ከሊቢያ በመነሳት አውሮፓ ለመድረስ የሞከረ መርከብ ከሰጠመ በኋላ 116 ሰዎች ሲሞቱ በህይወት የተረፈው አንዱ ብቻ ነው።

አደጋው ባለፈው ሳምንት ማጋጠሙ የተዘገበ ሲሆን በህይወት የተረፈው ግለሰብ ወደ ሆስፒታል መወሰዱ ተነግሯል።

በህይወት የተረፈው ግለሰብ የተገኘው አደጋው ከደረሰ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው ሲባል ያገኙት በእንጨት በተሰራ ጀልባ አሳ የሚያጠምዱ ቱኒዛውያን ናቸው።

መርከቧ ከሊቢያ ተነስታ ጥቂት እንደተጓዘች ድጋፍ እንደሚያስፈልጋት መልዕክት ብትልክም በሳተላይትም በአየር ፍለጋም ልትገኝ አልቻለችም።

በህይወት የተረፈው ግለሰብ ከሊቢያ ጥቂት እንደተጓዙ መጥፎ የአየር ንብረት መፈጠሩን ገልጿል።

በወቅቱ በሰዓት 40 ኪሎ ሜትር የሚነፍስ ነፋስ ነበር ሲባል አደጋውም በዚህ ምክንያት እንደደረሰ ታምኗል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
😭180❤137💔31👏8😱1
የ2 አመት ህፃን ልጁን ከደፈረ በኋላ በጨርቅ ያነቃት አባት በእስራት ተቀጣ‼️

በሐረሪ ክልል ድሬ ጠያራ ወረዳ  ውስጥ ነዋሪ የሆነ ፍሮምሳ አብዱሰመድ የተባለ የ30አመት ተከሳሽ ከለሊቱ 6 ሰአት ላይ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው።

ተከሳሽ  የ2አመት ህፃን ልጁን በተኛችበት  ከደፈራት በኋላ አንገቷን በማነቅ ለመግደል መሞከሩን የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዳሬክተር የሆኑት ኮማንደር አበበች ሽዋረጋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ተከሳሽ ከደፈራት በኋላ  ለወላጅ አባቱ ልጄ በተኛችበት ሞታለች በማለት ይናገራል የህፃኗ አያት የሆኑት አባትም  እንዴት ጤነኛ የነበረች ልጅ ልትሞት ቻለች ብለው ሄደው ሲመለከቷት መደፈሯንና የታነቀችበት አንገቷ የተከረከረ መሆኑን ይመለከታሉ አባት ያልታመመች ልጅ እንዴት ልትሞት ትችላለች በማለት ዱላ በማንሳት አንተን ከመግደሌ በፊት ያደረከውን ንገረኝ ብለው ሲያስፈራሩት ከደፈራት በኋላ ለመግደል እንዳነቃት ለወላጅ አባቱ እንደተናገረና አባት ይዘውት ለህግ እንዳቀረቡት ተገልጿል ።

በሐረሪ ክልል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ሲጣራ ቆይቶ መዝገቡን ለጠቅላይ አቃቢ ህግ በመላክና በማስከፈት ታህሳስ 17/4/ 2018 በዋለው ችሎት በ25 አመት እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን  ኮማንደር አበበች ሽዋረጋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
😭482❤218😡71💔46😱37😁14🔥10
ጤና ሚኒስቴር በዳሰነች ወረዳ በድሮን የታገዘ የማርበርግ ቫይረስ የክትባት ስርጭት አካሄደ‼️

ጤና ሚኒስቴር ከ ኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በመተባበር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዳሰነች ወረዳ በድሮን የታገዘ የክትባት ስርጭት ማካሄዱን አስታወቀ።ሚኒስቴሩ፣ የማርበርግ ቫይረስ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታትና ራቅ ያሉ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎችን ለመታደግ ህይወት አድን መድኃኒቶችንና ክትባቶችን በድሮን የማድረስ ስራ በትላንትናው ዕለት ተከናውኗል ብሏል።

ዳሰነች ወረዳ ካለው ራቅ ያለ መልክዓ ምድር አኳያ በመኪና ለማጓጓዝ ረጅም ሰዓታት ይወስድ የነበረውን ጉዞ፣ በድሮን በመታገዝ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ክትባቱን በ –80°C ቅዝቃዜ ጠበቆ በማድረስ ለአካባቢው ማህበረሰብ ክትባቱን መስጠት ተጀምሯል ሲልም ገልጿል።

ይህም ተግባር የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት (EPSS) የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም ወረርሽኞችን ቀድሞ የመከላከልና የመቆጣጠር አቅሙን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገሩን በተግባር ያሳየበት ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ወረርሽኞችን ለመመከት የራሷን የውስጥ አቅም እና የቴክኖሎጂ ውጤቶች መጠቀም መጀመሯን የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ ነው ያለው ሚኒስቴሩ፣ በቀጣይም ይህ በድሮን መድኃኒት የማድረስ አገልግሎት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብሏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
2❤194😁50👍34👏9🕊4😭3🎉2
የማኀበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች የንግድ ስራ ግብር ሊከፍሉ መሆኑ ተነገረ‼️

የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም በዓመት ከ2ሚሊየን በላይ ገቢ የሚያገኙ ግለሰቦች ግብር እንዲከፍሉ የሚያስችል ረቂቅ ህግ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

በዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ ታክስ የሚጣልበት ሁኔታ በዝርዝር የተቀመጠው የገንዘብ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የገቢ ግብር ረቂቅ ደንብ ላይ መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ይህ ረቂቅ ደንብ፤ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች "ማስታወቂያዎች እና ስፖንሰርሺፖችን" ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች ያገኙትን "ሁሉንም የገቢ መጠን" የሚያሳይ "የሂሳብ መዝገብ" እንዲይዙ ያስገድዳልም ተብሏል።

የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የገቢ ግብር ከፋይ ዝርዝር ውስጥ የገቡት ባለፈው ዓመት ሐምሌ 2017 ዓ.ም. በጸደቀው "የገቢ ግብር አዋጅ" መሆኑ ይታወሳል።

አሁን በተዘጋጀው ረቂቅ ህግ ላይ ደግሞ ግብር የሚከፍሉት ከምን ያህል ገቢ ጀምሮ የሚያገኙ ይዘት ፈጣሪዎች እንደሆኑ የተካተተ ሲሆን ሊሎች በአዋጁ ላይ የተቀመጡ ዝርዝር ጉዳዮችን እንደያዘ ተገልጿል።

በመሆኑም ግብሩ የሚከፈለው እነዚህ የይዘት ፈጣሪዎች የተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ከሚያገኙት ማንኛውም ገቢ እንደሆነም ተመላክቷል።

ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቅ ያለበት ይህ ረቂቅ ደንብ፤ እስካሁን ድረስ ከታክስ ሥርዓቱ ውጪ ሆነው የቆዩትን ይዘት ፈጣሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ መደበኛው የግብር አሰራር የሚያስገባ ነውም ተብሎለታል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤173😁171👍38😭16😱15👏9💔7
የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል‼️

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር የአለም የነዳጅ ዋጋን መነሻ በማድረግ ከታሕሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በታሕሳስ ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን እወቁልኝ ብሏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤220👍83😁19🔥16👏3🎉1
​በአዲስ አበባ ከተማ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ውስጥ ከፍተኛ ቅዝቃዜ ሊከሰት እንደሚችል ተነገረ‼️

ዝቅተኛው የሙቀት መጠን እስከ 1.4 ዲግሪ ሴልሺየስ ሊወርድ እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስጠነቅቋል።

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አሳምነው ተሾመ ለመናኸሪያ ሬዲዮ እንደገለጹት፤ ባለፉት አስር ቀናት የታየው ደረቅና ቀዝቃዛማ የአየር ሁኔታ በቀጣዮቹ ቀናትም ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የትንበያ መረጃዎች አመልክተዋል።

​ከዋና ከተማዋ በተጨማሪ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በመካከለኛው ደቡብ እና በደጋማ የሀገሪቱ ክፍሎች የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ እጅግ ከፍተኛ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
በእነዚህ አካባቢዎች በብዙ ቀናት የሙቀት መጠኑ ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም በደጋማ ስፍራዎች ለሚኖሩ ነዋሪዎችና ለግብርና ስራዎች ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ይጠበቃል።

​የዘንድሮው የበጋ ወቅት መደበኛና ከመደበኛ በታች የሆነ የዝናብ መጠን እንደሚኖረው የተተነበየ ቢሆንም፣ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ግን በተወሰኑ አካባቢዎች ለውጥ ሊታይ ይችላል።

በዚህም መሰረት በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በመጨረሻዎቹ ቀናት አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልጸዋል።

​የኢንስቲትዩቱ መረጃ እንደሚያሳየው፣ ይህ ብርቱ ቅዝቃዜ ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተጠናከረና እየተስፋፋ የመጣ ክስተት ነው። በመሆኑም ህብረተሰቡ በተለይም ለቅዝቃዜ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የአየር ሁኔታ መረጃዎችን በንቃት እንዲከታተሉ መልዕክት ተላልፏል።

​@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤252😁33👍28😱28🔥11😭3🎉1
አሳዛኝ ዜና🕯🕯

ተወዳጁ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

ነፃነት በአጋጠመው ድንገተኛ ህመም ነው ዛሬ ረፋድ ላይ ከዚህ አለም የተለየው።

በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነት፣ በተዋናይነትና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ውስጥ ስመጥር እና ተወዳጅ ከሆኑ የጥበብ ሰዎች አንዱ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባደረበት ህመም በድንገት ከዚህ ዓለም ተለይቷል፡፡

ለበርካታ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት ነበር፡፡

ለወዳጅ፣ ዘመዶቹና ለአድናቂወቹ መፅናናትን እንመኛለን።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
😭780💔175❤149🕊20👍16😱11👏5