በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከፒኤችዲ (PhD) ተማሪዎች ጋር የፓናል ውይይት ተካሄደ
**
ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ
በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ያስጀመረውን የ3ኛ ዲግሪ (PhD) መርሃ-ግብር ተማሪዎች የትምህርት ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ ያለመ የልምድ ልውውጥና የፓናል ውይይት ተካሄደ።
የፓናል ውይይቱ ዋና ዓላማ የፒኤችዲ (PhD) ተማሪዎች የትምህርትና የምርምር ሂደታቸውን በተደራጀ መልኩ እንዲመሩ ለማስቻል ሲሆን ፣ በውይይቱም ላይ በርካታ ገንቢና ስትራቴጂካዊ ሀሳቦች ተነስተዋል።
ተማሪዎቹ የይቻላል መንፈስን ሰንቀው፣ በቁርጠኝነት ተግዳሮቶችን እንዴት ማለፍ እንዳለባቸው እንዲሁም ውጤታማ ሊያደርጓቸው የሚችሉ የጥናትና የምርምር ቴክኒኮችን እንዲተገብሩ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ ፕሮፌሰሮችና ዶክተሮች ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በመጨረሻም ተማሪዎቹ የዚህ ታሪካዊ መርሃ-ግብር የመጀመሪያው ዙር በመሆናቸው ፣ የተሰጠው የተግባር ተሞክሮና ምክረ-ሀሳብ እጅግ ወሳኝና አስፈላጊ መሆኑን በማንሳት ፣ ለቀጣይ የትምህርትና ምርምር ሂደታቸው ታላቅ ግብዓት እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

👍79❤51😁1