Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በ አርሲ "የሰው ልጆች እየሞቱ ነው"
ኦርቶዶክሳውያን አልሞቱም ለማለት ነው እንዲህ የሚዘበራርቀው።እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ኦርቶዶክስ መሳይ የሥርዐቱ ሰላዮች ናቸው።ይኽ ልጅ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በኦርቶዶክሳውያን ሞት ሲሳለቅ ነበር አሁንም ከጥፋቱ ሊማር አልቻለም።መፍትሔው unfollow ማድረግ ነው።

👍10😢1
ይኽ ቄስ ባለፈው ጠቅላላ ጉባኤው ላይ "ሰው አሳስረናል"በማለት ሪፖርት ያቀረበ ነው።ሌሎችን እያሳደደና እያሳሰረ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ግል ርስቱ የሚጠቀም ዘራፊ ነው።
፩ የሀዲያ ስልጤ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ
፪ አዲስ አበባ ሰሚት መድኃንዓለም ቤ/ክያን ስብከተ ወንጌል ሀለፊ
፫ ሆሳዕና ጎልጎታ መድኃነአለም ቤተክርስቲያን አስተደደር
ሚስቱም ልጆቹም አዲስ አበባ ነው ያሉት።አዲስ አበባ ሆኖ ነው ሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከትን የሚመራው።
ቤተ ክህነት የሚባለው መዋቅር ሠርጀሪ መሠራት አለበት።

❤9💔5👍1
Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
ከሁለት ዓመት በኋላ ደግሞ መጋቤ ሐዲስ ብለው ይሾሙሃል ።እነ የኔታ ገብረ መድኅን እንየውን የመሰሉ ሊቃውንት የሚሳደዱበት በአንጻሩ ደግሞ የአፈር ነጋዴ ቲክቶከሮች የነገሡበት በድኑ ቤተ ክህነት።
👍14🔥5😁2😱1
በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር በደራ ወረዳ በ፩ኛ ደረጃት ትምህርት ቤት ላይ ሥርዐቱ የድሮን ጥቃት ፈጽሟል።ከታጠቀ ኀይል ጋር ተዋግቶ ማሸነፍ ወይም መሸነፍ የጦርነት ህግ ነው።ንጹሃንን ማጥቃት ግን ፋሽስታዊነት ነው።
😢29❤3
Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
ሥርዐታዊ፣መዋቅራዊና ርዕዮተ ዓለማዊ ጥቃት
አንድ ማኅበረሰብ ለሥርዐታዊ (Systemic)፣ ለመዋቅራዊ (Structural) እና ለርዕዮተ-ዓለማዊ (Ideological) ጥቃት ተጋልጧል የምንለው ጥቃቱ በግለሰቦች ደረጃ በሚፈጸም አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን፣ የማኅበረሰቡን ሙሉ የሕይወት እንቅስቃሴ በያዙት ሥርዓቶች፣ መዋቅሮች እና አስተሳሰቦች ውስጥ ታቅዶና ሥር ሰዶ ሲገኝ ነው።
እነዚህ ሦስት የጥቃት ዓይነቶች እርስ በእርስ የተሳሰሩ ሲሆኑ፣ ማኅበረሰቡ ውስጥ በሚታዩት ግልጽ ምልክቶች እንደሚከተለው ከፍለን ማየት እንችላለን፦
1. ርዕዮተ-ዓለማዊ ጥቃት (Ideological Attack)
ርዕዮተ-ዓለማዊ ጥቃት የሌሎቹ ጥቃቶች መነሻና መሠረት ነው። ጥቃቱን ሕጋዊና ተቀባይነት ያለው ለማስመሰል የሚቀረጹ የእምነት፣ የፍልስፍና እና የትረካ (Narrative) ስብስብ ነው።
የማንነትና የባህል ዝቅተኝነት ትረካ መገንባት፦ የማኅበረሰቡን ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ባህል ወይም እሴት እንደ "ኋላቀር"፣ "አደገኛ" ወይም "ደረጃው ዝቅ ያለ" አድርጎ የሚያቀርብ የፕሮፓጋንዳ እና የትምህርት ሥርዓት ሲዘረጋ።
ሰውነትን ማሳጣት (Dehumanization)፦ የማኅበረሰቡን አባላት ፍላጎት፣ መብትና ህልውና የሚያንኳስሱ፣ ለጥቃትና ለእስራት ክፍት የሚያደርጉ አሉታዊ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ትረካዎች በስፋት ሲሰራጩ።
ታሪክን ማዛባትና ማደብዘዝ፦ የማኅበረሰቡን ታሪካዊ አወንታዊ አስተዋጽኦዎች ማጥፋት፣ የማንነት መገለጫዎችን ማገድ ወይም የታሪክ ድርሰቶችን ለፖለቲካዊ ጥቅም ተበጅተው እንዲቀርቡ ማድረግ።
2. መዋቅራዊ ጥቃት (Structural Attack)
መዋቅራዊ ጥቃት ርዕዮተ-ዓለማዊ አስተሳሰቡን ወደ ሕግ፣ ፖሊሲ እና ሀብት ክፍፍል በመቀየር የማኅበረሰቡን መሠረታዊ የሰው ልጅ ፍላጎቶች እንዳያገኝ የሚያግድ ነው።
የሕግና የፖሊሲ አድልዎ፦ የሀገሪቱ የሕግ ማዕቀፎች፣ የመሬትና የሀብት ክፍፍል ፖሊሲዎች የማኅበረሰቡን አባላት የመጠቀሚያ እድል በግልጽ ወይም በተዘዋዋሪ የሚያጠቡ ሆነው ሲቀረጹ።
የኢኮኖሚና የማኅበራዊ እድል መዘጋት፦ በማኅበረሰቡ አባላት ላይ ያተኮረ የሥራ እድል መከልከል፣ ጥራት ያለው ትምህርት፣ የጤና እና የመሠረተ ልማት አቅርቦት በጥናት ላይ ተመሥርቶ እንዲነፈጋቸው ሲደረግ።
የፖለቲካዊ ውሳኔ ሰጪነት ማገለል፦ ማኅበረሰቡ በራሱ ጉዳይና በሀገራዊ ውሳኔዎች ላይ የመደራጀት፣ የመምረጥ፣ የመመረጥ ወይም ድምፁን የማሰማት መብቱ በሕግና በኃይል ሲገደብ።
3. ሥርዐታዊ ጥቃት (Systemic Attack)
ሥርዐታዊ ጥቃት ከላይ የተጠቀሱትን ርዕዮተ-ዓለማዊ እና መዋቅራዊ ጥቃቶች አጣጥሞና አቀናጅቶ፣ በተቋማት (በፖሊስ፣ በፍርድ ቤት፣ በትምህርት ቤቶች፣ በሜዲያ) በኩል በየቀኑና በዘላቂነት እንዲፈጸም የሚያደርግ የሕይወት መደበኛ ክፍል ነው።
ተቋማዊ በደልና ፍትሕ ማጣት፦ ሕግ አስከባሪዎችና ፍርድ ቤቶች በማኅበረሰቡ አባላት ላይ አድልዎ ሲፈጽሙ፣ ያለአግባብ ሲያሰሩ ወይም ለሚፈጸሙ ጥቃቶች ተጠያቂነትን ሲያጡ።
በደልና ጥቃትን እንደ መደበኛ ነገር መቁጠር (Normalization)፦ በማኅበረሰቡ ላይ የሚፈጸመው ግፍ፣ መገለልና መብት መገፈፍ በሌላው ዘንድም ሆነ በተቋማት እንደ መደበኛ ክስተት ተቆጥሮ የፍትሕ ጥያቄዎች ሲታፈኑ።
የትውልድ ቅብብል ጉዳት (Intergenerational Impact)፦ ጥቃቱ በጥቂት ግለሰቦች አልፎ የሚቆም ሳይሆን፣ በማኅበረሰቡ አባላት የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ፣ የስነ-ልቦና እና የማኅበራዊ እድገት ላይ ጠባሳ ጥሎ ለቀጣይ ትውልድ ሲተላለፍ።
ማጠቃለያ
አንድ ማኅበረሰብ ለነዚህ ሦስት ጥቃቶች ተጋልጧል የምንለው፦
👉ጥቃቱ መርህና ትረካ (ርዕዮተ-ዓለም) ተበጅቶለት፣
👉በሕግና በፖሊሲ (መዋቅር) ተደግፎ፣
👉በተቋማት አሠራር (ሥርዓት) አማካኝነት በዘላቂነትና በማይቀየር ሁኔታ ሲፈጸምበት ነው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሦስቱም ጥቃቶች ዒላማ ስለሆነች ነው መከራዋ ሊቆም ያልቻለው።
https://t.me/Eyo21e

[ርዕዮተ-ዓለማዊ ጥቃት] ──► (የጥቃቱን ትረካና ምክንያት ያዘጋጃል)
│
▼
[መዋቅራዊ ጥቃት] ──► (መብትና ሀብት በመንፈግ አቅም ያሳጣል)
│
▼
[ሥርዐታዊ ጥቃት] ──► (በደሉን በተቋማት በኩል የዕለት ተዕለት ያደርገዋል)
│
▼
[ማኅበረሰባዊ ድንዛዜ] ──► (ሕዝቡ ተስፋ ቆርጦና ደንዝዞ ዝም ይላል)
│
└─────────────► (የሕዝቡ ዝምታ ለጥቃቶቹ መቀጠል መንገድ ይከፍታል!)

❤10
Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
ማኅበረሰባዊ ድንዛዜእና የሃይማኖት መሪዎች
ማኅበረሰባዊ ድንዛዜ ማለት አንድ ማኅበረሰብ በዙሪያው ለሚፈጸሙ ኢ-ፍትሃዊነቶች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ የሰው ልጅ ሥቃይ ወይም አጠቃላይ አገራዊና ማኅበራዊ ውድቀቶች ምንም ዓይነት የስሜት ተፅዕኖ (Empathy)፣ የቁጣ ምላሽ ወይም የመፍትሔ እንቅስቃሴ ማሳየት የማይችልበት የአእምሮና የሥነ-ልቦና ደረጃ ላይ ሲደርስ ነው።
የሃይማኖት መሪዎች ሕዝቡን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለትልቅ ማኅበረሰባዊ ድንዛዜ ሊያጋልጡ ይችላሉ። የሃይማኖት ተቋማት በማኅበረሰቡ ውስጥ ያላቸው ተሰሚነትና የሞራል የበላይነት ከፍተኛ በመሆኑ፣ የሚያስተላልፉት መልእክት፣ የሚወስዱት አቋም ወይም የሚያሳዩት ዝምታ የማኅበረሰቡን የአስተሳሰብና የስሜት አቅጣጫ የመቅረፅ ትልቅ ኃይል አለው።
የሃይማኖት መሪዎች ሕዝቡን ለድንዛዜ የሚያጋልጡባቸው ዋና ዋና መንገዶችና አሠራሮች የሚከተሉት ናቸው፦
1. በደልንና ጥቃትን በሃይማኖት ሰበብ ማጸደቅ
"የእግዚአብሔር ቁጣ/ፈተና ነው" የሚል ትረካ፦ በሕዝብ ላይ የሚደርሱ መዋቅራዊና ሥርዓታዊ በደሎችን፣ ፍትሕ ማጣትን ወይም ጭቆናን "የእግዚአብሔር ፍርድ ወይም የኃጢአት ውጤት ነው" በማለት ብቻ ሲያቀርቡ። ይህ አመለካከት ሕዝቡ የችግሩን ምድራዊና ፖለቲካዊ መነሻዎች እንዳይመራመር እና የመፍትሔ አካል እንዳይሆን ያደርገዋል።
ታግሦ ማለፍን ከተገቢው ውጭ ማስተማር፦ ትዕግሥትና ይቅርታ ታላላቅ መንፈሳዊ እሴቶች ቢሆኑም፣ ለፍትሕ አለመቆም እና በደልን ዝም ብሎ መቀበል እንደ ታላቅ መንፈሳዊነት ተደርጎ ሲሰበክ፣ ሕዝቡ መብቱን የመጠየቅና የመታገል ወኔው ይሞታል።
2. የመንግሥታት ሽፋን መሆን
የበደል ተባባሪ ወይም ዝምተኛ መሆን፦ የሃይማኖት መሪዎች ከተቋማዊ ጥቅም፣ ከፖለቲካዊ ሥልጣን ወይም ከፍርሃት የተነሳ በሕዝብ ላይ የሚፈጸሙ ግልጽ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ግፎች ሲፈጸሙ ዝምታን ሲመርጡ።
ፍትሕ የሌለው "የሰላም ጥሪ"፦ እውነተኛውን በደልና የጉዳት መነሻ ሳይናገሩ፣ የተበደለውንና በዳዩን እኩል አድርጎ የሚመዝን የውሸት ሰላም ጥሪ ማቅረብ፤ ይህም ተበዳይ አቤቱታውን የሚያሰማበትን ቀዳዳ ይዘጋዋል።
3. ሕዝብን በመከፋፈል የርኅራኄ ድንበር ማበጀት
"የእኛ" እና "የእነሱ" ክፍፍል፦ መሪዎች የራሳቸውን መንጋ/ተከተይ ጥቅም ብቻ ለማስጠበቅ ሲሮጡ እና በሌሎች ላይ የሚደርሰውን ሥቃይ እንደ ባዕድ ነገር ሲመለከቱት።
ይህ አሠራር በማኅበረሰቡ መካከል ያለውን የጋራ ሰብዓዊነት እና የርኅራኄ ስሜት (Empathy) ያጠፋዋል፤ ሕዝቡ ከእሱ ወገን ውጭ ባለው ሰው ላይ ለሚደርስ አደጋ እንዲደንዝዝ ያደርገዋል።
4. የተስፋ መቁረጥና የአቅም ማጣት ስሜት መፍጠር
የሃይማኖት መሪዎች ሕዝቡ የሚያምነባቸውና እንደ መሸሸጊያ የሚያያቸው የሞራል አባቶች ናቸው። እነዚህ አባቶች ፍርሃት ሲያሸንፋቸው፣ እውነትን ሲደብቁ ወይም ለጥቅም ሲያደሉ ሲታዩ፣ ሕዝቡ "አባቶች እንኳ ከጨከኑብን እኛ ምን ልናደርግ እንችላለን?" ወደሚል ከባድ የተስፋ መቁረጥና የስነ-ልቦና ስብራት ይወርዳል።

❤8
Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሥርዐቱ አደራጅነት፣ ስንቅና ትጥቅ አቅራቢነት እንዲሁም ሽፋን ሰጪነት ፣በ ቤ ተክህነቱ ተባባሪነት ዘራቸው እየጠፋ ያለው የአርሲ ኦርቶዶክሳውያን
😭3❤2
Daboo daguuggaa sanyii kiristaanotaa irratti qooda fudhattoonii eenyuu faadha?👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿
1,Abbaa kiristaanota(hoolota)sana tiksuu sun yeroo hoolan Isaa nyaatamtu cal jedhe iyyashee osoo dhagahuu diiga isheerra tarkaanfatee yeroo galuu qooda fudhataa Isa jalqabaati.
Abban hoola cal jennan Yeyyin dhiiga hoola mi'eeffatte Abba hoolayyuu in kajeeltii.kun immo in oolu.
2,Barsiisota Qacaramtoota.
Tajaajiltoota osoo hin taanee Qacaramtoota yoo dubbatan mindaa isaanii waan dhabaniif ciisaa lafa sana irra waan ka'aniif kiristaanotaf sagalee ta'u caalaa callisuu filatan.
Tajaajiltoota gooftaa waan hin taaneef hoolonni gooftaa isaan hin marartu😭
✍🏿Barsiisonnii hojin isaanii kiristaanota giddisuu ture barsiisonni si'anaa garuu waa sadii guddifatu.
❌Mindaa ofii guddifachuu
❌Angoo guddifachuu.
❌ Miidiyaa guddifachuu.
3, Dhaloota si'anaa kan duuti kiristaanootaa homaa itti hin fakkanneefiidu'a obboleessa isaaf sagalee ta'u caalaa gara Siyaasa tti kan harkisu,Amma isarra gahuutti kan hin dammaqne gara oofaniitti kan deemu.
dhaloota gara oofaniitti deemuu kana kan omeeshe barsiisota Si'anaa kana.
✍🏿 Dhaloota gaafa Siyaasa hiriira bahuuf daandii cufutu gaafa kiristaanni obboleessi Isaa du'u garuu Isa hooksisuu dadhabe hammam hadoonnee Akka jurruufii amantaa keenya tti qorroo Akka taane waan mullisi natti fakkaata.
✍🏿isaan Kun sadan daboo kana irratti hirmaataniiru.
✍🏿Yaa dhaloota nana dammaqi🥲 obboleessa keef sagalee ta'i.
4,warra ajjesaniif garuu ajjeesuun hojii saaniiti.
@ Lema Kenea

ሕዝቡ መከራውን አይቶ የሚሰጠውን ገንዘብ የካድሬ መሸለሚያ አደረጉት። ከሁለት ሳምንት በፊት የተሾመ አዲሱ የድሬደዋ ከተማ ከንቲባ ነው።ምን ሠርቶ ነው የተሸለመው? የቁልቢ ብር ሞልቶ ፈሰሰ አይደል! ይኽን የመከነ መዋቅር አለመታገል በ ቤተ ክርስቲያን ላይ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ሁሉ እንደመተባበር ነው የሚቆጠረው።
👍18😢6
አሁን ከመሸ ከ 2:40 ጀምሮ መርቲ ወረዳ አጋንዳ በሚባል አከባቢ ጥቃት ተከፍቷል የኦርቶዶክሳውያን ቤቶች እየተቃጠሉ መሆናቸውን መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።
😢33😁1