Eotc Task Force
8.66K subscribers
1.93K photos
446 videos
12 files
504 links
ወቅታዊ ጉዳይ
Download Telegram
❤5
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" ከመብዛቱ የተነሳ ስለተለመደ ስለማይሰማ እንጅ ጥቃቱ አልቆመም። ምዕመናን ተገድለዋል " - የወረዳ ቤተክህነቱ እና የዞኑ ሀገረ ስብከት

በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን ተደጋጋሚ ጥቃት በታጣቂዎች ከሚፈጸምባቸው ቦታዎች መካከል ሆንቆሎ ዋቤ እና ሺርካ ወረዳዎች ውስጥ በተፈጸመ አዲስ ጥቃት 6 ምዕመናን ሲገደሉ ሌሎች መታገታቸውን የሺርካ ወረዳ ቤተክህነት እና የዞኑ ሀገረ ስብከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ከአርሲ ሀገረ ስብከት አንድ አመራር ጉዳዩን አጣርተው በሰጡን ገለጻ፣ "በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ሦስት ምዕመናን ተገድለዋል" ብለዋል። ግድያው የተፈጸመው ከዚህ በፊት ተደጋጋሚ ጥቃት ባስተናገደ "መጪቱ ላሎ" በሚባል ቦታ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ/ም መሆኑን ገልጸዋል።

ከሺርካ ወረዳ ቤተክህነት አንድ አመራር በሰጡን ቃል፣ "ጥቃቱ በአዲስ መልክ ቀጥሎ ምዕመናን ተገድለዋል" ብለዋል። የሟቾች ቀብር ትናንት እና ከሰሞኑ መፈጸሙን ገልጸዋል።

"የተለመደው ግድያ ነው የተፈጸመው ጥቅምት 2 እና 7 ቀን 2019 ዓ/ም ሦስት ምዕመናን ተገድለዋል። አምስት ሰዎች ደግሞ ታግተው ተወስደዋል። ቆስሎ ሆስፒታል የገባም አለ። የተለያዩ ሰዎች የሆኑ ወደ 50 ከብቶች በታጣቂዎች ተወስደዋል" ሲሉም ተናግረዋል።

" በጎረቤት ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ/ም ሶስት ሰዎች ተገድለዋል። ሆንቆሎ ላይ ይህን ጥቃት ካደረሱ በኋላ ነው በቀን 7 ደግሞ ሺርካ ላይ መጥተው ጥቃት የፈጸሙት" ነው ያሉት።

" 50 ሰዎች ታግተው ተወሰዱ" የሚል መረጃ እየተሰራጨ ሲሆን፣ የሺርካ ወረዳ ቤተክህነት አመራር ደግሞ "ያን እኔም አይቸዋለሁ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተለጥፎ፤ ግን የተወሰዱት #50_ከብቶች ናቸው፤ ሰዎች አይደሉም። ሺርካ ላይ የታገቱት አምስት ሰዎች ናቸው" በማለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በአካባቢው የሚስተዋለውን ሁኔታ ሲያስረዱ፣ "ትናንሹ ጥቃት ከመብዛቱ የተነሳ ስለተለመደ ስለማይሰማ እንጅ ጥቃቱና ስጋቱ አልቆመም" ብለዋል።

ሀገረ ስብከቱ በበኩሉ የሟቾና ታጋቾችን ስም ዝርዝር አጋርቶ፣ ለጥቃቱ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቋል።

በ​ጥቅምት 2/2019 ዓ/ም የሺርካው ጥቃት፥ ጌቱ አሰፋ የተባሉ ግለሰብ የእርሻ ሥራ ላይ እያሉ ከቀኑ 7 ሰዓት መገደላቸውን አስታውቋል።

​ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ/ም እንደገና በሺርካ ወረዳ ለሊት በሄላ ዘንባባ ቀበሌ፦
1. ​አቶ ዘውዴ ኃብቴ
2. ​ወ/ሮ አስራሱ ተስፋዬ ተገድለዋል።
1. ​አቶ ፍርዴ አሰፋ
2. ​አቶ ገናና አሰፋ
3. ​አቶ እፋ ዘነበ
4. ​አቶ አስናቀ ዘውዴ
5. ​ወ/ሮ ወጋየሁ መርሻ በታጣቂዎች ታግተው ተወስደዋል ብሏል። ቀሲስ ናርዶስ አሰፋ ተቆስለው በሆስፒታል መግባታቸውን ገልጿል።

በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ​ጥቅምት 5/2019 ዓ/ም፦
1. ​አቶ ዘነባ ነጋሽ
2. ​አቶ ሳሙኤል ዋሌ
3. ​አቶ ብሩህ አበራ ተገድለዋል ብሏል።

​በተለያዩ ወረዳዎች በተደጋጋሚ በሚከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት ምዕመናን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተገደሉ፣ ከቀያቸው እና ከንብረታቸው እየተፈናቀሉ፣ ለከፍተኛ ችግሮች እየተጋለጡ እንደሚገኙ ገልጾ፣ የሚመለከተው አካል እነዚህን ችግሮች አጣርቶ ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቋል።

ከቀያቸው እንዲሁም ከንብረታቸው ለተፈናቀሉም አስፈላጊው ሁሉ ጥበቃና ክትትል ተደርጎላቸው ወደ ቀያቸውና ንብረታቸው እንዲመለሱ አስፈላጊው ድጋፍ እንያረግላቸው እንዲሁም በአካባቢው ለሚገኙ ለቀሩት ሕዝብ አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላቸው አጥብቆ አሳስቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
😭11❤4
👉እንደዜጋ የማትቆጥረን ሀገር ሀገራችን ልትሆን አትችልም
👉በሃይማኖታችን ምክንያት የሚገድለን የሚያፈናቅለን መንግሥት መንግሥታችን ሊሆን አይችልም
👉 ሊጠብቀን ሊታደገን ሲገባው ከገዳይ ጋር ተባብሮ በሞታችንን የሚሳለቅ ሞታችን የሚሸፋፍን እረኛ አባት ሊሆነን አይችልም!!
👍7
አዲስ አበባን ከኦርቶዶክሳውያን ለማጽዳት የሚተገበሩ ስልቶች
❤15👍3
ሌባና ቀጣፊ፣ምንደኛና ተኩላ ስሙ ሲነሳ "ኡኡኡኡ ያዙን ልቀቁን፣ሲኖዶስ ተደፈረ፣አባቶች ተዋረዱ፣ ቤተ ክርስቲያን ተደፈረች" እያሉ የሚንጫጩ ሰዎች፦
፩ የግለሰቦቹ አምላኪዎች ናቸው
፪ ተከፈይ የሚዲያ ሠራዊቶቻቸው ናቸው
፫ ቤተ ክርስቲያን እንድትፈራርስ የሚፈልጉ ናቸው

ሌቦችን፣ቀጣፊዎችን ምንደኞችና ተኩላዎችን ተከተሉ የሚል የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የለም።
👍17
<<ከሁሉም በላይ በሆነች>> ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን"

ማንም ቢሆን ከቤተ ክርስቲያን በታች ነው።
👉ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ፓትርያርክ የለም
👉ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ጳጳስ የለም
👉ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ መነኩሴ የለም
👉ከ ቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ካህን የለም
👉ከ ቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ሊቅ የለም
👉ከ ቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ሰባኪ የለም
👉ከ ቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ዘማሪ የለም
👉ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ምዕመን የለም
👉ከ ቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ቤተ ክህነት የለም
👉ከ ቤተ ክህነት የሚበልጥ ሰንበት ትምህርት ቤት የለም
👉ከ ቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ማኅበር የለም
👍16❤7
አርሲ 

1)ሆንቆሎ ዋቤ፦ ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ሌላ ያልተሰማ ግድያ ተፈጽሟል።አቶ ደቤ ቢልቶ ይባላል። ባለ ስድስት ልጆች አባት ነው።ሲበዛ ደግና ሰው አክባሪ በአከባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ ተወዳጅ ነው። አክራሪ ታጣቂዎቹ  ቤቱን አቃጥለውበት ከብቶቹን ሲነዱበት "ከብቶቼን አትውሰዱብኝ "በማለቱ ብቻ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለው ጥለው ሄደዋል።ጥቃቱ የተፈጸመው ጥቅምት 5/2019ዓ.ም ነው።

2) ሽርካ፦  በቀን 09/02/2019ዓ.ም  ጋለማ  የሚባል ደጋማ ስፍራ ላይ የመንግስት ታጣቂዎች መኪና በማስቆም  የኦርቶዶክሳውያን ወጣት ሲያፍሱ ነው የዋሉት። ከአንድ መኪና  6 ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ተነጥለው መታፈሳቸውን  የዓይን እማኞች ተናግረዋል።የሚገደለው ኦርቶዶክስ ታፍሶ ወደ ግንባር ሄዶ እንዲሞት የሚደረገውም ኦርቶዶክስ ።ሥርታዊ ጥቃት ማለት ይኽ ነው።

3) አሰኮ፦ሀ)በአሰኮ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመው እገታ ተባብሶ ቀጥሏል ።ጎመን ሸጠው መራራ ኑሮን እየገፉ ልጆቻቸውን የሚያሳድጉ ሴቶች ሳይቀር ከገበያ ሲመለሱ በጅምላ ታግተው እስከ 500ሺ ብርና ከዚያ በላይ እየተጠየቀባቸው ነው።

  ለ) የመከላከያ ልብስ የለበሱ የእስልምና ታጣቂዎች ገበያ ውለው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ ያሉ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ጥቃት በመክፈት 2ቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ 3ቱ ለ ከፍተኛ ጉዳት ተዳርገዋል።አክራሪዎቹ በገዛ ሕዝባቸው ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት "ኦርቶዶክሶች እስልምና እያጠቁ ነው" የሚል የውሸት ፕሮፓጋንዳ ለማሰራጨትና ሕዘበ ሙስሊሙ ነቅሎ ወጥቶ ኦርቶዶክሱ ላይ ጥቃት እንዲከፍት አስበው ነው።ይኽን እንጂ የጥቃቱ ሰለባ ሆነው በሕይወት የተረፉት ጥቃቱን የፈጸሙባቸው  አክራሪዎቹ መሆናቸውን አጋልጠዋል።

ሐ) ባለፈው ዓመትና ከዚያ በፊት  የተፈናቀሉ ኦርቶዶክሳውያን እስካሁን ወደ አከባቢያቸው አልተመለሱም።ያ ቤተ ክርስቲያን ሲያሠራ፣ደግሶ ያበላ የነበረው ሕዝብ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጧል

4) ሮቤ ፦በሮቤ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠሩ  የግድያና የእገታ ጥቃቶች እየተፈሙ ይገኛሉ

5)መርቲ፦ሀ) በወርቲና በወለንጪቲ መካከል በምትገኝ  ላዩ ቦታ ጎልጎታ ላይ ከሁለት ቀናት በፊት 2ኦርቶዶክሳውያን ወንድማማቾች  መገደላቸውን የዓይን እማኞች ተናግረዋል።
ለ) በመርቲ  ከገጠሩ አከባቢ የተፈናቀሉ ኦርቶዶክሳውያን እስካሁን ወደ መኖሪያ ቤታቸው አልተመለሱም
አቶ ደቤ ብልቶ
❤9🥰1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በ አርሲ "የሰው ልጆች እየሞቱ ነው"

ኦርቶዶክሳውያን አልሞቱም ለማለት ነው እንዲህ የሚዘበራርቀው።እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ኦርቶዶክስ መሳይ የሥርዐቱ ሰላዮች ናቸው።ይኽ ልጅ  ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በኦርቶዶክሳውያን ሞት ሲሳለቅ ነበር አሁንም ከጥፋቱ ሊማር አልቻለም።መፍትሔው unfollow ማድረግ ነው።
👍10😢1
ይኽ ቄስ ባለፈው ጠቅላላ ጉባኤው ላይ "ሰው አሳስረናል"በማለት ሪፖርት ያቀረበ ነው።ሌሎችን እያሳደደና እያሳሰረ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ግል ርስቱ የሚጠቀም ዘራፊ ነው።
፩ የሀዲያ ስልጤ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ
፪ አዲስ አበባ ሰሚት መድኃንዓለም ቤ/ክያን ስብከተ ወንጌል ሀለፊ

፫ ሆሳዕና ጎልጎታ መድኃነአለም ቤተክርስቲያን አስተደደር

ሚስቱም ልጆቹም አዲስ አበባ ነው ያሉት።አዲስ አበባ ሆኖ ነው ሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከትን የሚመራው።

ቤተ ክህነት የሚባለው መዋቅር ሠርጀሪ መሠራት አለበት።
❤9💔5👍1
ከሁለት ዓመት በኋላ ደግሞ መጋቤ ሐዲስ ብለው ይሾሙሃል ።እነ የኔታ ገብረ መድኅን እንየውን የመሰሉ ሊቃውንት የሚሳደዱበት በአንጻሩ ደግሞ የአፈር ነጋዴ ቲክቶከሮች የነገሡበት በድኑ ቤተ ክህነት።
👍14🔥5😁2😱1
በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር በደራ ወረዳ በ፩ኛ ደረጃት ትምህርት ቤት ላይ ሥርዐቱ የድሮን ጥቃት ፈጽሟል።ከታጠቀ ኀይል ጋር ተዋግቶ ማሸነፍ ወይም መሸነፍ የጦርነት ህግ ነው።ንጹሃንን ማጥቃት ግን ፋሽስታዊነት ነው።
😢29❤3
ሥርዐታዊ፣መዋቅራዊና ርዕዮተ ዓለማዊ ጥቃት


አንድ ማኅበረሰብ ለሥርዐታዊ (Systemic)፣ ለመዋቅራዊ (Structural) እና ለርዕዮተ-ዓለማዊ (Ideological) ጥቃት ተጋልጧል የምንለው ጥቃቱ በግለሰቦች ደረጃ በሚፈጸም አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን፣ የማኅበረሰቡን ሙሉ የሕይወት እንቅስቃሴ በያዙት ሥርዓቶች፣ መዋቅሮች እና አስተሳሰቦች ውስጥ ታቅዶና ሥር ሰዶ ሲገኝ ነው።
እነዚህ ሦስት የጥቃት ዓይነቶች እርስ በእርስ የተሳሰሩ ሲሆኑ፣ ማኅበረሰቡ ውስጥ በሚታዩት ግልጽ ምልክቶች እንደሚከተለው ከፍለን ማየት እንችላለን፦
1. ርዕዮተ-ዓለማዊ ጥቃት (Ideological Attack)
ርዕዮተ-ዓለማዊ ጥቃት የሌሎቹ ጥቃቶች መነሻና መሠረት ነው። ጥቃቱን ሕጋዊና ተቀባይነት ያለው ለማስመሰል የሚቀረጹ የእምነት፣ የፍልስፍና እና የትረካ (Narrative) ስብስብ ነው።
የማንነትና የባህል ዝቅተኝነት ትረካ መገንባት፦ የማኅበረሰቡን ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ባህል ወይም እሴት እንደ "ኋላቀር"፣ "አደገኛ" ወይም "ደረጃው ዝቅ ያለ" አድርጎ የሚያቀርብ የፕሮፓጋንዳ እና የትምህርት ሥርዓት ሲዘረጋ።
ሰውነትን ማሳጣት (Dehumanization)፦ የማኅበረሰቡን አባላት ፍላጎት፣ መብትና ህልውና የሚያንኳስሱ፣ ለጥቃትና ለእስራት ክፍት የሚያደርጉ አሉታዊ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ትረካዎች በስፋት ሲሰራጩ።
ታሪክን ማዛባትና ማደብዘዝ፦ የማኅበረሰቡን ታሪካዊ አወንታዊ አስተዋጽኦዎች ማጥፋት፣ የማንነት መገለጫዎችን ማገድ ወይም የታሪክ ድርሰቶችን ለፖለቲካዊ ጥቅም ተበጅተው እንዲቀርቡ ማድረግ።
2. መዋቅራዊ ጥቃት (Structural Attack)
መዋቅራዊ ጥቃት ርዕዮተ-ዓለማዊ አስተሳሰቡን ወደ ሕግ፣ ፖሊሲ እና ሀብት ክፍፍል በመቀየር የማኅበረሰቡን መሠረታዊ የሰው ልጅ ፍላጎቶች እንዳያገኝ የሚያግድ ነው።
የሕግና የፖሊሲ አድልዎ፦ የሀገሪቱ የሕግ ማዕቀፎች፣ የመሬትና የሀብት ክፍፍል ፖሊሲዎች የማኅበረሰቡን አባላት የመጠቀሚያ እድል በግልጽ ወይም በተዘዋዋሪ የሚያጠቡ ሆነው ሲቀረጹ።
የኢኮኖሚና የማኅበራዊ እድል መዘጋት፦ በማኅበረሰቡ አባላት ላይ ያተኮረ የሥራ እድል መከልከል፣ ጥራት ያለው ትምህርት፣ የጤና እና የመሠረተ ልማት አቅርቦት በጥናት ላይ ተመሥርቶ እንዲነፈጋቸው ሲደረግ።
የፖለቲካዊ ውሳኔ ሰጪነት ማገለል፦ ማኅበረሰቡ በራሱ ጉዳይና በሀገራዊ ውሳኔዎች ላይ የመደራጀት፣ የመምረጥ፣ የመመረጥ ወይም ድምፁን የማሰማት መብቱ በሕግና በኃይል ሲገደብ።
3. ሥርዐታዊ ጥቃት (Systemic Attack)
ሥርዐታዊ ጥቃት ከላይ የተጠቀሱትን ርዕዮተ-ዓለማዊ እና መዋቅራዊ ጥቃቶች አጣጥሞና አቀናጅቶ፣ በተቋማት (በፖሊስ፣ በፍርድ ቤት፣ በትምህርት ቤቶች፣ በሜዲያ) በኩል በየቀኑና በዘላቂነት እንዲፈጸም የሚያደርግ የሕይወት መደበኛ ክፍል ነው።
ተቋማዊ በደልና ፍትሕ ማጣት፦ ሕግ አስከባሪዎችና ፍርድ ቤቶች በማኅበረሰቡ አባላት ላይ አድልዎ ሲፈጽሙ፣ ያለአግባብ ሲያሰሩ ወይም ለሚፈጸሙ ጥቃቶች ተጠያቂነትን ሲያጡ።
በደልና ጥቃትን እንደ መደበኛ ነገር መቁጠር (Normalization)፦ በማኅበረሰቡ ላይ የሚፈጸመው ግፍ፣ መገለልና መብት መገፈፍ በሌላው ዘንድም ሆነ በተቋማት እንደ መደበኛ ክስተት ተቆጥሮ የፍትሕ ጥያቄዎች ሲታፈኑ።
የትውልድ ቅብብል ጉዳት (Intergenerational Impact)፦ ጥቃቱ በጥቂት ግለሰቦች አልፎ የሚቆም ሳይሆን፣ በማኅበረሰቡ አባላት የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ፣ የስነ-ልቦና እና የማኅበራዊ እድገት ላይ ጠባሳ ጥሎ ለቀጣይ ትውልድ ሲተላለፍ።

ማጠቃለያ
አንድ ማኅበረሰብ ለነዚህ ሦስት ጥቃቶች ተጋልጧል የምንለው፦
👉ጥቃቱ መርህና ትረካ (ርዕዮተ-ዓለም) ተበጅቶለት፣
👉በሕግና በፖሊሲ (መዋቅር) ተደግፎ፣
👉በተቋማት አሠራር (ሥርዓት) አማካኝነት በዘላቂነትና በማይቀየር ሁኔታ ሲፈጸምበት ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሦስቱም ጥቃቶች ዒላማ ስለሆነች ነው መከራዋ ሊቆም ያልቻለው።
https://t.me/Eyo21e
[ርዕዮተ-ዓለማዊ ጥቃት] ──► (የጥቃቱን ትረካና ምክንያት ያዘጋጃል)
         │
         ▼
[መዋቅራዊ ጥቃት]     ──► (መብትና ሀብት በመንፈግ አቅም ያሳጣል)
         │
         ▼
[ሥርዐታዊ ጥቃት]      ──► (በደሉን በተቋማት በኩል የዕለት ተዕለት ያደርገዋል)
         │
         ▼
[ማኅበረሰባዊ ድንዛዜ]  ──► (ሕዝቡ ተስፋ ቆርጦና ደንዝዞ ዝም ይላል)
         │
         └─────────────► (የሕዝቡ ዝምታ ለጥቃቶቹ መቀጠል መንገድ ይከፍታል!)
❤10