Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
ተጠናክሮ የቀጠለው #የኦርቶዶክሳውያን ፍጅት
ላለፉት ሦስት ዓመታት የኦርቶዶክሳውያን መታረጃ ቄራ ሆና የቆየችው የአርሲ ምድር አሁንም ፍጅቱ ተባብሶ እንደቀጠለ ነው።
ትናንት ጥቅምት 7/2019ዓ.ም በሽርካ ወረዳ ሄላ ዘምባባ ቀበሌ ዘምባ ማርያም ቤተ ክርስቲያን አከባቢ ሌሊት 4:00 በተከፈተ ጥቃት፦
👉 2 ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል
👉 አንድ ካህን በጥይት ተመተው ሆስፒታል ገብተዋል
👉5 ኦርቶዶክሳውያን ታግተው ተወስደዋል
ይኽ ጥቃት ከመፈጸሙ ከአንድ ቀን በፊት (ዐርብ)ሕዝቡ አክራሪ ታጣቂዎቹ በአከባቢው ላይ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ለወረዳው ባለሥልጣናት ቢያሳውቅም ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አላደረጉም።አክራሪ ታጣቂዎቹ ቅዳሜ ሌሊት ወጥተው ጥቃት ከፈቱባቸው።
በዚሁ በወረዳ ያሉ ከተለያዩ ቀበሌዎች 20,000(20ሺ) ኦርቶዶክሳውያን ተፈናቅለዋል (ከኦሮሚያ ክልል መዋቅር የተላኩት ሰዎች ግን 7ሺ ቀንሰው ወደ 13ሺ አውርደውታል) ።እነዚህ ኦርቶዶክሳውያን ለከፍተኛ ረሃብ ተጋልጠዋል።ይኽ ሁሉ ግፍ በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየተፈጸመ አቡነ ኤልሳዕና የሀገረ ስብከቱ ሀላፊዎች ዝምታን መርጠዋል።

😭19❤6
Forwarded from ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)
የእናንተን ኢየሱስ አላውቀውም!!
Karl marx's ካርል ማርክስ የተናገረው ነው። ሰውየው የጀርመን ፈላስፋ ነው። ሶሻሊስዝም በማቀንቅንና በመምራት በአብዮተኝነት ይታወቃል። በነርሱ እብደት ዓለም ለዓመታት ተመርቷል።
ኮሚኒዝም ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በራሺያ አብዮት አስነስቶ ሀገሪቱን ለዓመታት መርተዋታል። በዋናነት ኮሚኒዝም ሕዝቡን ለማነሳሳት የተጠቀሙበት ማርክስ የቤተ ክርስቲያንን ጉልላት ጳጳሳቱ የሚቀመጡበትን፣ የሚሄዱበትን ቀይ ምንጣፍ ያያል ቤተክርስቲያን በር ላይ የተቀመጡትን በየሀገሩ በረሃብ የሚሰቃየውን ሕዝብ አየ።
አንድ ቀን ቤተ ክርስቲያን ጳጳሱን ሕዝብ በረሃብ እየሞተ እናንተ ቤተ ክርስቲያን በወርቅ ታንጻላችሁ በቀይ ምንጣፍ ላይ ትሄዳላችሁ አላቸው። "እስቲ ምን ብለው ይጸልያሉ" አላቸው "አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር" ሲሉ አቁሙ አቁሙ አላቸው እንዲህ ማለት ጀመረ "አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር እዛው ቆይ እኔ ለነዚህ በምድር ላይ እግዚአብሔር እሆናቸዋለሁ" አለ። our father who art in heaven stay there. የእናንተን ኢየሱስን አላውቀውም የምትሰብኩት ኢየሱስ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለው ኢየሱስ አይደለም አላቸው።
ከዚያ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያንን ማመሰቃቀል ጀመረ። ሰውን ያደነቆራችሁት እናንተ ናችሁ። ከድኃ ሰብስባችሁ በቅምጥል ሕይወት የምትኖሩ እናንተ ናችሁ በማለት በነሱ የመጣው ችግር ቤተ ክርስቲያንን እስኪበቃት አዳከማት። አብዮቱ ቤተክርስቲያን የሰበሰበችውን ገንዘብ ሁሉ ዘረፈ ንብረቷን ቀማት።
ዛሬም በሀገራችን ችግራችንና ለችግራችን መፍትሔ ለመስጠት የምንሄድበት መንገድ ተለያይቷል። ቤተክርስቲያን ውስጥ የምናደርገው ድርጊት ሀብት ንብረት መሰብሰብ፣ ከቤተክርስቲያን አጀንዳ ውጭ መጠመዳችን፣ አለማዊነት መንገሡ የውጭ ጠላትን ጋብዞ አመጣው። ቁሻሻ ዝንብን እንደሚሰበስባት።
ሕንጻና ገንዘብ ላይ እንደ ዋና ነገር እያተኮርን ነው። ሰው ከሃይማኖት ወጥቷል። ሕንጻ እናስመርቃለን፣ ቀኖና ተጥሶ ጵጵስና በጎሳ እንሾማለን። ቅምጥሉና ድሎቱ ሕዝብ መከራ ላይ ያለ መኾኑን የሰማን ኹሉ አይመስልም። በታላላቅ ገዳምት ብዙ ውድመት ደርሷል። መነኮሳት ካህናት ተገድለዋል። የእኛ አባቶች ባለስልጣናት መስቀል ላይ እንዳይረበሹ ጥንቃቄ እናድርግ ላይ ናቸው።
ንዋይ ካሳሁን

❤12
Forwarded from ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
◈በሥሁት ሥርዓት እና በግለ ሰቦች የማሰቢያ አጥር ውስጥ እንድናስብ የሚፈልጉ ብዙ ናቸው።
◈እኛን የሠራችን ቅድስት ኵላዊት ኦርቶዶክስ አያውቁም ማለት ነው?
◈ኦርቶዶክስ የሆን ዕለት የመላእክትና የደቂቀ አዳም፣የሥውራን እና የገሐዳውያን፣ተጋድሏቸውን የጨረሱና በተጋድሎ ጎዳና ካሉት ጋራ አንድ ማኅበርተኛ ሁነናል።
◈በዚህ ልዑል ጉባኤ ሥር ያለን ክርስቲያኖች ዝቅ ብለን በሥሁት ፍጡራዊ ማያ ልንወሰን አንችልም።

👍2
Forwarded from ሞዐ ተዋሕዶ / Mo'aa Tawaahido / MOA Orthodox (Eotc)
ፖለቲካና ሃይማኖት ይለያያል❓
የአጭበርባሪ ሰባኪዎችና የከሀዲ ፖለቲከኞች የጋራ ስብከት ወይስ እውነት❓
ለእኔ:-
👉 ለድንዝዞቹ የዘር ፖለቲካ ባሮች፣
👉 መገንጠልን ነፃነት ለሚሉ የጨለማ ልጆች፣
👉 ፖለቲካና ከገርን ለእኛ ተዉልን ለሚሉ ሴኩላሪስት/አቴይስቶች ትድረስልኝ፦
አምላክ ሰው ከሆነ በኋላ ሁሉ ነገር ግልጽ ሆኗል። የሚዳሰሰውን፣ ውሱን የሆነውን ከመሬት የተገኘ ሥጋ፣ የማይወሰነው ሰማያዊ አምላክ ከተዋሀደው፣ ውሱን ለሆነው የዓለም ማስተዳደሪያ ማሪያ የሆነውን ፖለቲካ ከማይወሰነው አምላክ የተወለድነው እኛ ክርስቲያኖች ለማን እንድንተው ይፈለጋል?
ብርሃን ክርስቶስን ባለማወቃቸው በጨለማ ውስጥ ሆነው በነፃነት ስም አገር ለሚያፈርሱት መተዋችን ስሕተት ነበር። ክህደትም ነው።
ከአሁን በኋላ ፖለቲካና ሃይማኖት ይለያያል በሚል ያልተብራራ ማደንዘዣ እንድታጠፉን አንፈቅድም‼️
ለድኅነታችን ሳይሆን ለኑሮአቸው ወንጌል የሚሸቅጡ አደንዛዥ ሰባኪዎችንም አንሰማቸውም። ምልክቶቻችን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ታላቁ ባስሊዮስ፣ አግናጥዮስ፣ አትናቴዎስ፣ ጎርጎሪዮስ ዘኑሲስና ነገሥታትን የተጋፈጡ ሰማዕታት ናቸው። በቃ‼️

❤9
#ምንደኞችና #ኦርቶዶክሳውያን ያሉበት ዓለም ይለያያል
#የኦርቶዶክሳውያን ዓለም
👉የግድያ የእርድ ዓለም
👉የስደትና የመፈናቀል ዓለም
👉 ሀገር አልባ የመሆን ዓለም
👉የመታሰር ዓለም
👉የመታገት ዓለም
👉 ከኢኮኖሚ ከፖለቲካ፣ማኅበራዊ፣ከሥራእና ከሀገራዊ ተሳትፎ የመገለል ዓለም
👉 የመራብ፣የመጠማትና የመታረዝ ዓለም
👉መሪ አልባ ዓለም
👉 አባት አልባ ዓለም
👉 መንግሥት አልባ ዓለም
👉አልባሽ አጉራሽ አልባ ዓለም
👉ዘመድ አልባ ዓለም
👉የመከራ የሰቆቃ ዓለም
#የምንደኞች ዓለም
👉 ሳይሠሩ የመሸላለም ዓለም
👉 ዘመናዊ መኪና የመቀያየር ዓለም
👉 ሚሊየነር የመሆን ዓለም
👉 አራት አምስት ፎቅ የመሥራት ዓለም
👉 ዋጋቸው ውድ በሆኑ በግሪክ ልብሶች የማጌጥ ዓለም
👉በወርቅ በስቀል የማጌጥ ዓለም
👉 የመዝናናት ዓለም
👉 ልደት እያከበሩ ኬክ የመቁረስ ዓለም
👉 የሀብታም ቤት ላይ እየዞሩ ማዕድ የመባረክ ዓለም
👉 ቤተ ክርስቲያንን የመዝረፍ የማራቆት ዓለም
👉 ቅንጡ ሕይወት የመኖር ዓለም
👉ከተማ ላይ ብቻ የመኖ ርዓለም
👉ከገዳይ ጋር እየተሻሹ እየተሸላሉሙ እየተሞጋገሱ የመኖር ዓለም
https://t.me/EotcTaskForce

❤7😭1
Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
#Update
በቀን5/2/2019ዓ.ም በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ላሎ ቀበሌ የተገደሉ ኦርቶዶክሳውያን ስም ዝርዝራቸው ደርሶኛል፦
1 ዘነበ ነጋሽ
2 ሳሙኤል ዋሌ
3 ብሩ አበራ

💔4
የአንድ ሌሊት የ93 ዘመዶች ቅጥር!
ገና በቆርቆሮ የተሠራ፣ ገና በጅምር ላይ ያለ ገላን ጉራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪው ፍቃድ ወጥተው በሄዱበት በአንድ ሌሊት ብቻ 93 የቢሮ ሰራተኞች ተቀጥረው እንዲያድሩ ተደርጓል። የሚያስገርመው ደግሞ እነዚህ ተቃጣሪዎች የትምህርትና ሥራ ልምድ ውድድር አልፈው ሳይሆን፣ የአንድ ቤተሰብ አባላት እና የቅርብ ዘመዶች መሆናቸው ነው!
በደብሩ ምክትል ሊቀመንበር እና በሰበካ ጉባኤው አማካኝነት በአንድ ጀንበር የተቀጠሩት ሠራተኞች መዋቅር ሲታይ የሴራውን ስፋትና የታቀደበትን ዝረፋ ያሳያል።ከተቀጠሩት መካከል የተወሰኑት፦
- 17 የስታቲስቲክስ ሠራተኞች
-12 የሒሳብ ሠራተኞች
-12 የዕቃ ግዥ ሠራተኞች
- 9 ተላላኪዎች
- 8 ጉዳይ አስፈጻሚዎች
-6 የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዎች
- 6 የመዝገብ ቤት ሠራተኞች
ገና በቂ ገቢ ማሰባሰብ ያልጀመረ ደብር ውስጥ ይህ ሁሉ ሠራተኛ የተቀጠረው አገልግሎትን ለማፋጠን ሳይሆን የቤተ ክርስቲያኗን ሀብት ለመቦጨቅ ታስቦ የተዘረጋ የዘረፋ መዋቅር ነው።እኔ ለቤተ ክርስቲያን ብር መስጠት ካቆምሁ 4ዓመት ሆኖኛል ምናልባት በገጠር አስታዋሽ የሌላቸው ካልሆኑ በቀር ። በአባትነት በአገልጋይነት ስም ቤተ ክርስቲያንቱን የሚዘርፉ ማፊያዎችን አልቀልብም። በመዝሙር አስጨፍረው ስሜታዊ አድርገው "እልል በሉ አጨብጭቡ ያጨበጨባችሁት እጃችሁን ወደ ኪሳችሁና ቦርሳችሁ አስገቡ" እያሉ ለሚያታልሉ ዘራፊዎች ብራችሁን የምትሰጡ ኦርቶዶክሳውያን ንቁ።ሌባ መቀለብ ያስኮንናል እንጂ አያፀድቅም።

❤12🤬2👍1
Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወጣት ሳሙኤል ዋሌ
Dargaggoo Saamu'eel Waalee
በዚሁ ሁኔታ ከቀጠልን አርሲ ያለችው ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ መሰደዷ የማይቀር ነው።በየቀኑ ልጆችዋን እየተነጠቀች ነው።

🥰2😭1
#update
በአርሲ ምድር ሽርካ ወረዳ ሄላ ዘምባባ ቀበሌ በቀን 7/2/2019ዓ/ሌሊት ከ3:00-4:30 በተፈጸመ ጥቃት የተገደሉ ፣ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውታ የታገቱ ኦርቶዶክሳውያን መረጃ፦
የተገደሉት
1 ዘውዴ ሀብቴ
👉የ ስድስት (6) ልጆች አባት(2ወንዶች 4 ሴቶች)
2 ወ/ሮ አስረሱ ተስፋዬ
👉አባት የሌላቸው ሁለት(2) ልጆችን የምታሳድግ
👉ህጻኗን እንደተሸከመች ነው የገደሏት
👉ከገደሏት በኋላ አካሎችዋን በስለት ቆራርጠዋል
ቀሲስ ናርዶስ አሰፋ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል
በዚሁ እለት የታገቱ
1 ኢፋ ዘነበ
2 ገነነ አሰፋ
3 ፍርዴ አሰፋ
4 አስናቀ ዘውዴ(የሟቹ የዘውዴ ሁብቴ ልጅ)
5/ወ/ሮ ወጋየሁ መርሻ
የቆሰሉ
በእምነታቸው የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ የጸጥታ አካላት ቪድዮ ቀርጻችሁ ፎቶ አንስታችሁ መረጃ ሰጥታችኋል በማለት በአከባቢው ላይ ያሉ ካህናትንና ምዕመናንን እያሳደዱ ይገኛሉ።
በዚሁ ወረዳ መስከረም 2/2019ዓ.ም
ጌቱ አሰፋ የተባለ ሰው በአዝመራ ላይ ሲገደል 50 የምእመናን ከብቶች መወሳዳቸው በአከባቢው ላይ የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች ጥቃቱን ለማስቆም ፈቃደኞች እንዳልነበሩ መዘገባችን የሚታወስ ነው።

አርሲ ምድር መርቲ ወረዳ ያላችሁ ምን አዲስ ነገር አለ እስኪ መረጃ አድርሱን።በሌሎች ወረዳዎች ያላችሁም እንደዚያው።
@Orthopia123
@Orthopia123
Forwarded from ሞዐ ተዋሕዶ / Mo'aa Tawaahido / MOA Orthodox (Eotc)
ራስህን ተከላከል‼️
መንግሥታዊ ክርስቲያን የማጽዳት ዘመቻውን ሽፋን ለመስጠት በየሳምንቱ ታቦት አንግሦ ማንጫጫት፣ ሕንፃ መመረቅ፣ የገንዘብ ገቢ መዘገብ፣ የጉብኝት ቪዲዮ መለጠፍ የዘሠናችን የብልጽግና ወንጌል ምርኮኛ የጎሳ ጳጳሳት ሥራ ሆኗል።
ክርስቲያን ምእመንና ከልቡ እምነት ያለው ካህን መተባበር፣ መነጋገር፣ መንቃት፣ መደራጀት፣ ራስን ከዚህ ዘር አጥፊ ሥርዓት እና የፖለቲካ መዋቅራት መከላከል አማራጭ የለዉም‼️

❤7😢6😁2
◈ከማጥቃት ወደ ማጽዳት፦
◈ባሳለፍናቸው ስምንት የመከራ ዓመታት በአሩሲና በመሳሰለው የቀጠለው ኦርቶዶክሳውያንን ከማጥቃት ወደ ማጽዳት የተሸጋገረው ሥርዓት ከአሩሲ ከፍ ብሎ ኦርቶዶክሱ የሚኖርበትን ሰሜኑን አካባቢ ታርጌት አድርጎ ሰውነቱንም ቅርሱንም እያጠፋ መጥተዋል።
◈በአሩሲና በሌሎች አካባቢዎችም በተለያየ ሰበብ ኦርቶዶክሳውያን ያስተናገዱት እና እያስተናገዱ ያሉት መከራ ከመግለጽ በላይ ነው።
◈ለዚህ ሁሉ መከራ የዳረገን ግን ከጸረ ኦርቶዶክሳውያን በላይ ዋነኛው እኛ በሥሁት አስተሳስብ መከልና እና በጥቁር ለባሽ ካድርዎች እና በመለካውያን አባቶች መደንዘዛችን ነው።
◈አሁንም ከትናንቱ የከፋ፤ከአሩሲ የገፋ ኦርቶዶክሱ በሚበዛበት አካባቢ በትግራይና በአማራው የሞት ፕሮጀክት በውክልናም በአካልም እንደቀጠለ ነው።
◈በአሥራ-አምስተኛው ክፍለ ዘመን ግራኝን እያገዙ ኦርቶዶክስን ያወደሙ ሀገራት ዛሬም በውክልና የግራኝ ቢጤውን እያገዙ ኦርቶዶክሳውያንን በማጥፋት ላይ ናቸው።
◈ይሄ የግራኝ እጅ ያልተገለጠልህ ኦርቶዶክስ ካለህ በቁመህ የበደንህ ነህ!
◈እየተደረገ ያለው ነባር እምነት፣እሴት፣ታሪክ፣ቅርስ፣ባህል፣አስተሳስብ፣ሀገር በቀል ዕውቀት፣ ያለውን ኦርቶዶክሱን ማኅበረ ሰብ የማዳከምና የማጥፋት ዘመቻ ነው።
◈በጦርነት ብለውት ብለውት የተረፈውን ደግሞ ተረጅ ማኅበረ ሰብእ ይፈጥሩና ድኅረ ጦርነት"ሰሜኑን ለወንጌል"ብለው በእርዳታ ሰበብ በኑ-ፋ-ቄ ገብተው ሁለንተናዊ ጸጋውን ይሰልቡታል።
◈የሄ ጨካኝ ጸረ ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓት ከመገ-ድል ውጪ ማዳን የማያውቅ፣ከማውደም ውጭ አንዳች መልካም ጸጋ የሌለው፣ነባር ጸጋዎችን ከመደምሰስ ውጪ ማንበር የማይችል በኦርቶዶክሳውያን ላይ የተዘረጋ የጥፋት ስብስብ ነው።
◈በተለያየ ሰበብ፣በጦርነት፣በማስራብ፣በማፈናቀል፣የክርስቲያኖችን ቀየ በማውደም፣ አብያተ ክርስቲያናትን በማቃጠል፦ሚልዮን ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶቻችንን አጥፍቷል አሁን በማጥፋት ላይ ነው፣ጥንታውያን ንዋያቶቻችን አውድሞል አሁንም በማውደም ላይ ነው፣ቅዱሱን ሐዋርያዊ መንበራችንን በሰፈር ሲኖዶስ ነቅንቋል አሁንም በማማሰን ላይ ነው፣ኦርቶዶክሳዊ አንድነታችንን አዳክሟል አሁን ልዩነትን በመስበክ ኦርቶዶክሳውያንን በማጥፋት ላይ ነው።
◈ገብቶናል የምንል ሰዎች የኦርቶዶክሳውያን ሕዝቦችን አንድነት በመመለስ ኦርቶዶክሳዊነትን ለትውልድ እናትርፋት።
◈ሰው ከሌለ በረቀት ላይ የሰፈረ አስተምሮ ኢምንት ነው።
◈ካለዚያ እንዲህና እንዲያ ሆነ እያሉ ማለቃቀስ መፍትሄ አይሆንም!!
የኔታ ገብረ መድኅን እንየው

❤6
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" ከመብዛቱ የተነሳ ስለተለመደ ስለማይሰማ እንጅ ጥቃቱ አልቆመም። ምዕመናን ተገድለዋል " - የወረዳ ቤተክህነቱ እና የዞኑ ሀገረ ስብከት
በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን ተደጋጋሚ ጥቃት በታጣቂዎች ከሚፈጸምባቸው ቦታዎች መካከል ሆንቆሎ ዋቤ እና ሺርካ ወረዳዎች ውስጥ በተፈጸመ አዲስ ጥቃት 6 ምዕመናን ሲገደሉ ሌሎች መታገታቸውን የሺርካ ወረዳ ቤተክህነት እና የዞኑ ሀገረ ስብከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ከአርሲ ሀገረ ስብከት አንድ አመራር ጉዳዩን አጣርተው በሰጡን ገለጻ፣ "በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ሦስት ምዕመናን ተገድለዋል" ብለዋል። ግድያው የተፈጸመው ከዚህ በፊት ተደጋጋሚ ጥቃት ባስተናገደ "መጪቱ ላሎ" በሚባል ቦታ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ/ም መሆኑን ገልጸዋል።
ከሺርካ ወረዳ ቤተክህነት አንድ አመራር በሰጡን ቃል፣ "ጥቃቱ በአዲስ መልክ ቀጥሎ ምዕመናን ተገድለዋል" ብለዋል። የሟቾች ቀብር ትናንት እና ከሰሞኑ መፈጸሙን ገልጸዋል።
"የተለመደው ግድያ ነው የተፈጸመው ጥቅምት 2 እና 7 ቀን 2019 ዓ/ም ሦስት ምዕመናን ተገድለዋል። አምስት ሰዎች ደግሞ ታግተው ተወስደዋል። ቆስሎ ሆስፒታል የገባም አለ። የተለያዩ ሰዎች የሆኑ ወደ 50 ከብቶች በታጣቂዎች ተወስደዋል" ሲሉም ተናግረዋል።
" በጎረቤት ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ/ም ሶስት ሰዎች ተገድለዋል። ሆንቆሎ ላይ ይህን ጥቃት ካደረሱ በኋላ ነው በቀን 7 ደግሞ ሺርካ ላይ መጥተው ጥቃት የፈጸሙት" ነው ያሉት።
" 50 ሰዎች ታግተው ተወሰዱ" የሚል መረጃ እየተሰራጨ ሲሆን፣ የሺርካ ወረዳ ቤተክህነት አመራር ደግሞ "ያን እኔም አይቸዋለሁ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተለጥፎ፤ ግን የተወሰዱት #50_ከብቶች ናቸው፤ ሰዎች አይደሉም። ሺርካ ላይ የታገቱት አምስት ሰዎች ናቸው" በማለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በአካባቢው የሚስተዋለውን ሁኔታ ሲያስረዱ፣ "ትናንሹ ጥቃት ከመብዛቱ የተነሳ ስለተለመደ ስለማይሰማ እንጅ ጥቃቱና ስጋቱ አልቆመም" ብለዋል።
ሀገረ ስብከቱ በበኩሉ የሟቾና ታጋቾችን ስም ዝርዝር አጋርቶ፣ ለጥቃቱ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቋል።
በጥቅምት 2/2019 ዓ/ም የሺርካው ጥቃት፥ ጌቱ አሰፋ የተባሉ ግለሰብ የእርሻ ሥራ ላይ እያሉ ከቀኑ 7 ሰዓት መገደላቸውን አስታውቋል።
ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ/ም እንደገና በሺርካ ወረዳ ለሊት በሄላ ዘንባባ ቀበሌ፦
1. አቶ ዘውዴ ኃብቴ
2. ወ/ሮ አስራሱ ተስፋዬ ተገድለዋል።
1. አቶ ፍርዴ አሰፋ
2. አቶ ገናና አሰፋ
3. አቶ እፋ ዘነበ
4. አቶ አስናቀ ዘውዴ
5. ወ/ሮ ወጋየሁ መርሻ በታጣቂዎች ታግተው ተወስደዋል ብሏል። ቀሲስ ናርዶስ አሰፋ ተቆስለው በሆስፒታል መግባታቸውን ገልጿል።
በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ጥቅምት 5/2019 ዓ/ም፦
1. አቶ ዘነባ ነጋሽ
2. አቶ ሳሙኤል ዋሌ
3. አቶ ብሩህ አበራ ተገድለዋል ብሏል።
በተለያዩ ወረዳዎች በተደጋጋሚ በሚከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት ምዕመናን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተገደሉ፣ ከቀያቸው እና ከንብረታቸው እየተፈናቀሉ፣ ለከፍተኛ ችግሮች እየተጋለጡ እንደሚገኙ ገልጾ፣ የሚመለከተው አካል እነዚህን ችግሮች አጣርቶ ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቋል።
ከቀያቸው እንዲሁም ከንብረታቸው ለተፈናቀሉም አስፈላጊው ሁሉ ጥበቃና ክትትል ተደርጎላቸው ወደ ቀያቸውና ንብረታቸው እንዲመለሱ አስፈላጊው ድጋፍ እንያረግላቸው እንዲሁም በአካባቢው ለሚገኙ ለቀሩት ሕዝብ አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላቸው አጥብቆ አሳስቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

😭11❤3