Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
የኦርቶዶክሳውያን መታረጃ ቄራ በሆነችው በአርሲ ምድር ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ሥርዐቱ ስንቅና ትጥቅ ሰፍሮ ባሰማራቸው በአክራሪ የእስልምና ታጣቂዎች የተገደሉ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች
😭9❤2
Forwarded from ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)
የእመቤታችን ስደት ዛሬም አልቆመም ይኽንን ማሰብ የሚፈልግ ግን የለም። የማኅሌት ድምቀት የወረብ ውዝዋዜ የከበሮ ሽክርክሪት ነው የእመቤታችን ኀዘን እያልን ያለነው።
ወቅቱ አዘክሪ ድንግል ... ድንግል ኾይ የደረሰብሽን ስደት ረሃብ ጥም አሳስቢ ነው የሚለው።
እኛ ግን.....

❤15
Forwarded from ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
◈አንድ ሰው ከጥፋት ጋራ ከተስማማ ስራ አቁሟል ማለት ነው።
◈ከጸረ ኦርቶዶክሳውያን ጋራ የማይስማማ ከሆነ እየሠራ ነው ማለት ነው።
◈ቤተ ክርስቲያንን በሥር ነቀል እያመነመኑ ካሉ አካላት ጋራ የምትሸላለም ከሆነ የጥፋት ዱላ ሁነሀል ማለት ነው።
◈ያመኑ መስሎ መካድ፣እያስመሰሉ ማመን ይሄ ነው።

❤11👍1
Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
#እረኞቻችን በመጽሐፍ #ሲመዘኑ
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የዚህ ትምህርት ማዕከልና ፍጹም ማሳያ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፣ በቤተ ክርስቲያን ያሉ አባቶችና መንፈሳዊ መሪዎች የእርሱን ፈለግ በመከተል መንጋውን እንዲጠብቁ ተጠርተዋል።
የእውነተኛ እረኛ መገለጫዎች፦
1. #መንጋውን የሚወድና #ሕይወቱን አሳልፎ የሚሰጥ
እውነተኛ እረኛ ከራሱ ጥቅም፣ ምቾትና ሕይወት ይልቅ የበጎቹን (የምእመናንን) ደህንነት ያስቀድማል።
“እውነተኛ እረኛ እኔ ነኝ፤ እውነተኛ እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።” (ዮሐንስ 10:11)
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በዮሐንስ ወንጌል ትርጓሜው ላይ እንደሚያስተምረው፡ “ክርስቶስ እውነተኛ እረኛ የተባለው መንጋውን ከነፍስ አዳኝ (ከዲያብሎስ) ታደገ፤ በገዛ ደሙም ዋጃቸው። ሞያተኛው (ቅጣሪው) አደጋና መከራ ሲመጣ በጎቹን ትቶ እንደሚሸሽ፣ እውነተኛው እረኛ ግን ስለ በጎቹ ሲል ሕይወቱን አሳልፎ ይሰጣል።”
2. #በበሩ (በክርስቶስ) የሚገባና #በሃይማኖት የጸና
እውነተኛ እረኛ ወደ መንጋው የሚገባው በትክክለኛው መንገድና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንጂ በቋንቋ ፣በዘር ወይም በሥልጣን ጥመኝነት አይደለም።
“ወደ በጎቹ በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ነጣቂም ነው፤ በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው።” (ዮሐንስ 10:1-2)
ቅዱስ ቄርሎስ እንደሚያስተምረው፡ “በሩ ክርስቶስ ነው። በበሩ የሚገባ እረኛ ማለት በክርስቶስ እውነተኛ እምነት አምኖ፣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ሕግ (በካህናት እጅና በሲኖዶስ ቡራኬ) የተሾመ ነው። በሌላ መንገድ (በገንዘብ፣ በኃይል፣ በስም ወይም በራሱ ፈቃድ) የሚገባ ግን ሌባና ነጣቂ ነው፤ መንጋውን ሊያጠፋ እንጂ ሊጠብቅ አይመጣም።”
3. #በጎቹን በስም የሚያውቅና #በፍቅር የሚያገለግል
እውነተኛ እረኛ ከሕዝቡ ጋር የጠበቀና የቀረበ መንፈሳዊ ግንኙነት አለው፤ በሩቅ ሆኖ አይገዛም።
“እረኛው በጎቹን በየስማቸው ይጠራቸዋል፥ ይመራቸውማል። ... በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል።” (ዮሐንስ 10:3-4)
ቅዱስ ጎርጎርዮስ እረኝነትን “የጥበቦች ሁሉ ጥበብ (Art of Arts)” ብሎ ይጠራዋል። እረኛ የሰዎችን ነፍስ የሚፈውስ ሀኪም በመሆኑ በጎቹን በኃይልና በጭካኔ ሳይሆን በፍቅር፣ በትዕግሥትና በትሕትና ይመራቸዋል። አብሮአቸው ይደሰታል፣ በሕመማቸውና በኃጢአታቸውም አብሮ ይታመማል፤ በትምህርትና በንሰሐ ያክማቸዋል።
4. #ንጹሕና ያልተበረዘ #መንፈሳዊ ምግብ የሚያቀርብ
የእረኛ ዋና ተግባር መንጋውን በጥሩ መስክ ማሰማራትና ንጹሕ የሃይማኖት ምግብ መገበብ ነው።
“እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝ የለም። በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል።” (መዝሙረ ዳዊት 23:1-2)
ቅዱስ አትናቴዎስ እንደሚያስተምረው እውነተኛ እረኛ ቅዱሳት መጻሕፍትንና የአበውን እምነት ሳይበርዝ፣ ሳይጨምርና ሳይቀንስ እውነተኛውን የሃይማኖት ምግብ ለምእመናን ያቀርባል። መንጋው በሐሰተኛ ትምህርትና በምንፍቅና አየር እንዳይበከል ሌሊትና ቀን ይጠብቃቸዋል።
5. #የጠፋውን የሚፈልግና #የሚያስብ (የምሕረት እረኛ)
እውነተኛ እረኛ የወደቁትን፣ የደከሙትንና የተሳሳቱትን አይጥላቸውም፤ ይልቁንም በፍቅር ይፈልጋቸዋል።
“ከእናንተ መቶ በግ ያለው አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ማን ነው?” (ሉቃስ 15:4)
ሊቃውንቱ እንደሚያስተምሩት፣ ፍጹሙ እረኛ ክርስቶስ የጠፋችዋን አንዲቷን በግ (አዳምን/የሰው ልጅን) ፍለጋ እስከ ሲኦል ድረስ በመውረድ፣ በስጋውና በደሙ መግቦ ወደ ቀደመ ክብሩ መልሷታል። በቤተ ክርስቲያን ያሉ እረኞችም ኃጢአተኞችን በመኮነን ፈንታ በንሰሐና በፍቅር ወደ እግዚአብሔር መንጋ የመመለስ ኃላፊነት አለባቸው።
6. #በትሕትናና በፈቃደኝነት #የሚያገለግል
እውነተኛ እረኛ ለገንዘብ፣ ለዝና ወይም ለሥልጣን ብሎ አያገለግልም።
" በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ"
(1ጴጥር5:2-3)
የዚህ ዘመን #እረኞቻችን 98% ከላይ ከተጠቀሱት #መስፈርቶች አንዱንም እንኳ አላሟሉም።ለዚህ ነው እውነተኛ #እረኞች ሳይሆኑ #ምንደኞች ናቸው የምንለው።ምንደኞችን መከተል "እውነተኛ እረኛ እኔ ነኝ"ዮሐ (10:11) ያለንን አምላክ መካድ ነው።ከሃዲ ደግሞ በሰማይ ቦታ የለውም።
https://t.me/Eyo21e

❤4👍2
Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
ተጠናክሮ የቀጠለው #የኦርቶዶክሳውያን ፍጅት
ላለፉት ሦስት ዓመታት የኦርቶዶክሳውያን መታረጃ ቄራ ሆና የቆየችው የአርሲ ምድር አሁንም ፍጅቱ ተባብሶ እንደቀጠለ ነው።
ትናንት ጥቅምት 7/2019ዓ.ም በሽርካ ወረዳ ሄላ ዘምባባ ቀበሌ ዘምባ ማርያም ቤተ ክርስቲያን አከባቢ ሌሊት 4:00 በተከፈተ ጥቃት፦
👉 2 ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል
👉 አንድ ካህን በጥይት ተመተው ሆስፒታል ገብተዋል
👉5 ኦርቶዶክሳውያን ታግተው ተወስደዋል
ይኽ ጥቃት ከመፈጸሙ ከአንድ ቀን በፊት (ዐርብ)ሕዝቡ አክራሪ ታጣቂዎቹ በአከባቢው ላይ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ለወረዳው ባለሥልጣናት ቢያሳውቅም ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አላደረጉም።አክራሪ ታጣቂዎቹ ቅዳሜ ሌሊት ወጥተው ጥቃት ከፈቱባቸው።
በዚሁ በወረዳ ያሉ ከተለያዩ ቀበሌዎች 20,000(20ሺ) ኦርቶዶክሳውያን ተፈናቅለዋል (ከኦሮሚያ ክልል መዋቅር የተላኩት ሰዎች ግን 7ሺ ቀንሰው ወደ 13ሺ አውርደውታል) ።እነዚህ ኦርቶዶክሳውያን ለከፍተኛ ረሃብ ተጋልጠዋል።ይኽ ሁሉ ግፍ በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየተፈጸመ አቡነ ኤልሳዕና የሀገረ ስብከቱ ሀላፊዎች ዝምታን መርጠዋል።

😭19❤6
Forwarded from ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)
የእናንተን ኢየሱስ አላውቀውም!!
Karl marx's ካርል ማርክስ የተናገረው ነው። ሰውየው የጀርመን ፈላስፋ ነው። ሶሻሊስዝም በማቀንቅንና በመምራት በአብዮተኝነት ይታወቃል። በነርሱ እብደት ዓለም ለዓመታት ተመርቷል።
ኮሚኒዝም ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በራሺያ አብዮት አስነስቶ ሀገሪቱን ለዓመታት መርተዋታል። በዋናነት ኮሚኒዝም ሕዝቡን ለማነሳሳት የተጠቀሙበት ማርክስ የቤተ ክርስቲያንን ጉልላት ጳጳሳቱ የሚቀመጡበትን፣ የሚሄዱበትን ቀይ ምንጣፍ ያያል ቤተክርስቲያን በር ላይ የተቀመጡትን በየሀገሩ በረሃብ የሚሰቃየውን ሕዝብ አየ።
አንድ ቀን ቤተ ክርስቲያን ጳጳሱን ሕዝብ በረሃብ እየሞተ እናንተ ቤተ ክርስቲያን በወርቅ ታንጻላችሁ በቀይ ምንጣፍ ላይ ትሄዳላችሁ አላቸው። "እስቲ ምን ብለው ይጸልያሉ" አላቸው "አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር" ሲሉ አቁሙ አቁሙ አላቸው እንዲህ ማለት ጀመረ "አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር እዛው ቆይ እኔ ለነዚህ በምድር ላይ እግዚአብሔር እሆናቸዋለሁ" አለ። our father who art in heaven stay there. የእናንተን ኢየሱስን አላውቀውም የምትሰብኩት ኢየሱስ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለው ኢየሱስ አይደለም አላቸው።
ከዚያ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያንን ማመሰቃቀል ጀመረ። ሰውን ያደነቆራችሁት እናንተ ናችሁ። ከድኃ ሰብስባችሁ በቅምጥል ሕይወት የምትኖሩ እናንተ ናችሁ በማለት በነሱ የመጣው ችግር ቤተ ክርስቲያንን እስኪበቃት አዳከማት። አብዮቱ ቤተክርስቲያን የሰበሰበችውን ገንዘብ ሁሉ ዘረፈ ንብረቷን ቀማት።
ዛሬም በሀገራችን ችግራችንና ለችግራችን መፍትሔ ለመስጠት የምንሄድበት መንገድ ተለያይቷል። ቤተክርስቲያን ውስጥ የምናደርገው ድርጊት ሀብት ንብረት መሰብሰብ፣ ከቤተክርስቲያን አጀንዳ ውጭ መጠመዳችን፣ አለማዊነት መንገሡ የውጭ ጠላትን ጋብዞ አመጣው። ቁሻሻ ዝንብን እንደሚሰበስባት።
ሕንጻና ገንዘብ ላይ እንደ ዋና ነገር እያተኮርን ነው። ሰው ከሃይማኖት ወጥቷል። ሕንጻ እናስመርቃለን፣ ቀኖና ተጥሶ ጵጵስና በጎሳ እንሾማለን። ቅምጥሉና ድሎቱ ሕዝብ መከራ ላይ ያለ መኾኑን የሰማን ኹሉ አይመስልም። በታላላቅ ገዳምት ብዙ ውድመት ደርሷል። መነኮሳት ካህናት ተገድለዋል። የእኛ አባቶች ባለስልጣናት መስቀል ላይ እንዳይረበሹ ጥንቃቄ እናድርግ ላይ ናቸው።
ንዋይ ካሳሁን

❤12
Forwarded from ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
◈በሥሁት ሥርዓት እና በግለ ሰቦች የማሰቢያ አጥር ውስጥ እንድናስብ የሚፈልጉ ብዙ ናቸው።
◈እኛን የሠራችን ቅድስት ኵላዊት ኦርቶዶክስ አያውቁም ማለት ነው?
◈ኦርቶዶክስ የሆን ዕለት የመላእክትና የደቂቀ አዳም፣የሥውራን እና የገሐዳውያን፣ተጋድሏቸውን የጨረሱና በተጋድሎ ጎዳና ካሉት ጋራ አንድ ማኅበርተኛ ሁነናል።
◈በዚህ ልዑል ጉባኤ ሥር ያለን ክርስቲያኖች ዝቅ ብለን በሥሁት ፍጡራዊ ማያ ልንወሰን አንችልም።

👍2
Forwarded from ሞዐ ተዋሕዶ / Mo'aa Tawaahido / MOA Orthodox (Eotc)
ፖለቲካና ሃይማኖት ይለያያል❓
የአጭበርባሪ ሰባኪዎችና የከሀዲ ፖለቲከኞች የጋራ ስብከት ወይስ እውነት❓
ለእኔ:-
👉 ለድንዝዞቹ የዘር ፖለቲካ ባሮች፣
👉 መገንጠልን ነፃነት ለሚሉ የጨለማ ልጆች፣
👉 ፖለቲካና ከገርን ለእኛ ተዉልን ለሚሉ ሴኩላሪስት/አቴይስቶች ትድረስልኝ፦
አምላክ ሰው ከሆነ በኋላ ሁሉ ነገር ግልጽ ሆኗል። የሚዳሰሰውን፣ ውሱን የሆነውን ከመሬት የተገኘ ሥጋ፣ የማይወሰነው ሰማያዊ አምላክ ከተዋሀደው፣ ውሱን ለሆነው የዓለም ማስተዳደሪያ ማሪያ የሆነውን ፖለቲካ ከማይወሰነው አምላክ የተወለድነው እኛ ክርስቲያኖች ለማን እንድንተው ይፈለጋል?
ብርሃን ክርስቶስን ባለማወቃቸው በጨለማ ውስጥ ሆነው በነፃነት ስም አገር ለሚያፈርሱት መተዋችን ስሕተት ነበር። ክህደትም ነው።
ከአሁን በኋላ ፖለቲካና ሃይማኖት ይለያያል በሚል ያልተብራራ ማደንዘዣ እንድታጠፉን አንፈቅድም‼️
ለድኅነታችን ሳይሆን ለኑሮአቸው ወንጌል የሚሸቅጡ አደንዛዥ ሰባኪዎችንም አንሰማቸውም። ምልክቶቻችን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ታላቁ ባስሊዮስ፣ አግናጥዮስ፣ አትናቴዎስ፣ ጎርጎሪዮስ ዘኑሲስና ነገሥታትን የተጋፈጡ ሰማዕታት ናቸው። በቃ‼️

❤9
#ምንደኞችና #ኦርቶዶክሳውያን ያሉበት ዓለም ይለያያል
#የኦርቶዶክሳውያን ዓለም
👉የግድያ የእርድ ዓለም
👉የስደትና የመፈናቀል ዓለም
👉 ሀገር አልባ የመሆን ዓለም
👉የመታሰር ዓለም
👉የመታገት ዓለም
👉 ከኢኮኖሚ ከፖለቲካ፣ማኅበራዊ፣ከሥራእና ከሀገራዊ ተሳትፎ የመገለል ዓለም
👉 የመራብ፣የመጠማትና የመታረዝ ዓለም
👉መሪ አልባ ዓለም
👉 አባት አልባ ዓለም
👉 መንግሥት አልባ ዓለም
👉አልባሽ አጉራሽ አልባ ዓለም
👉ዘመድ አልባ ዓለም
👉የመከራ የሰቆቃ ዓለም
#የምንደኞች ዓለም
👉 ሳይሠሩ የመሸላለም ዓለም
👉 ዘመናዊ መኪና የመቀያየር ዓለም
👉 ሚሊየነር የመሆን ዓለም
👉 አራት አምስት ፎቅ የመሥራት ዓለም
👉 ዋጋቸው ውድ በሆኑ በግሪክ ልብሶች የማጌጥ ዓለም
👉በወርቅ በስቀል የማጌጥ ዓለም
👉 የመዝናናት ዓለም
👉 ልደት እያከበሩ ኬክ የመቁረስ ዓለም
👉 የሀብታም ቤት ላይ እየዞሩ ማዕድ የመባረክ ዓለም
👉 ቤተ ክርስቲያንን የመዝረፍ የማራቆት ዓለም
👉 ቅንጡ ሕይወት የመኖር ዓለም
👉ከተማ ላይ ብቻ የመኖ ርዓለም
👉ከገዳይ ጋር እየተሻሹ እየተሸላሉሙ እየተሞጋገሱ የመኖር ዓለም
https://t.me/EotcTaskForce

❤7😭1
Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
#Update
በቀን5/2/2019ዓ.ም በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ላሎ ቀበሌ የተገደሉ ኦርቶዶክሳውያን ስም ዝርዝራቸው ደርሶኛል፦
1 ዘነበ ነጋሽ
2 ሳሙኤል ዋሌ
3 ብሩ አበራ

💔4
የአንድ ሌሊት የ93 ዘመዶች ቅጥር!
ገና በቆርቆሮ የተሠራ፣ ገና በጅምር ላይ ያለ ገላን ጉራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪው ፍቃድ ወጥተው በሄዱበት በአንድ ሌሊት ብቻ 93 የቢሮ ሰራተኞች ተቀጥረው እንዲያድሩ ተደርጓል። የሚያስገርመው ደግሞ እነዚህ ተቃጣሪዎች የትምህርትና ሥራ ልምድ ውድድር አልፈው ሳይሆን፣ የአንድ ቤተሰብ አባላት እና የቅርብ ዘመዶች መሆናቸው ነው!
በደብሩ ምክትል ሊቀመንበር እና በሰበካ ጉባኤው አማካኝነት በአንድ ጀንበር የተቀጠሩት ሠራተኞች መዋቅር ሲታይ የሴራውን ስፋትና የታቀደበትን ዝረፋ ያሳያል።ከተቀጠሩት መካከል የተወሰኑት፦
- 17 የስታቲስቲክስ ሠራተኞች
-12 የሒሳብ ሠራተኞች
-12 የዕቃ ግዥ ሠራተኞች
- 9 ተላላኪዎች
- 8 ጉዳይ አስፈጻሚዎች
-6 የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዎች
- 6 የመዝገብ ቤት ሠራተኞች
ገና በቂ ገቢ ማሰባሰብ ያልጀመረ ደብር ውስጥ ይህ ሁሉ ሠራተኛ የተቀጠረው አገልግሎትን ለማፋጠን ሳይሆን የቤተ ክርስቲያኗን ሀብት ለመቦጨቅ ታስቦ የተዘረጋ የዘረፋ መዋቅር ነው።እኔ ለቤተ ክርስቲያን ብር መስጠት ካቆምሁ 4ዓመት ሆኖኛል ምናልባት በገጠር አስታዋሽ የሌላቸው ካልሆኑ በቀር ። በአባትነት በአገልጋይነት ስም ቤተ ክርስቲያንቱን የሚዘርፉ ማፊያዎችን አልቀልብም። በመዝሙር አስጨፍረው ስሜታዊ አድርገው "እልል በሉ አጨብጭቡ ያጨበጨባችሁት እጃችሁን ወደ ኪሳችሁና ቦርሳችሁ አስገቡ" እያሉ ለሚያታልሉ ዘራፊዎች ብራችሁን የምትሰጡ ኦርቶዶክሳውያን ንቁ።ሌባ መቀለብ ያስኮንናል እንጂ አያፀድቅም።

❤12🤬2👍1
Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወጣት ሳሙኤል ዋሌ
Dargaggoo Saamu'eel Waalee
በዚሁ ሁኔታ ከቀጠልን አርሲ ያለችው ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ መሰደዷ የማይቀር ነው።በየቀኑ ልጆችዋን እየተነጠቀች ነው።

🥰2😭1