Eotc Task Force
8.39K subscribers
1.92K photos
445 videos
12 files
500 links
ወቅታዊ ጉዳይ
Download Telegram
1ቀን ቀራቸው ይፈቱልን ፍትህ

እንዴት ከርመው ይሆን?
በጨለማ ዕስር ቤት 136ቀን የሆናቸው ክቡር አባታችን ቀሲስ መዝገቡ ፍትሕ ለአባታችን

ግንቦት 26የታሰሩት የፍርድቤት ቀጠሮ ጥቅምት 9 ነገ የቀጠሮ ቀኝ

አባታችንን ፍቱልን
🥰15🙏8😢5❤2
"በጎች ምን አደረጉ?"
፪.ሳሙ.፳፬፥፲፯
◈በዚህ ዘመን በምእመናን ላይ የሆነውም ሆየ የሚሆነው በሥጋዊ እና በመንፈሳዊ እረኞች ምክንያት ነው።
◈በጎች ገብሩ ቀቅሉ ሲባሉ እሺ ይላሉ፤ ስጡ መጽውቱ ሲባሉ እሺ ይላሉ።
◈በጎቹ ከእረኞቹ የተሻለ የሀገርም የሃይማኖትም ክብር አላቸው።
◈በአንጻሩ ደግሞ እረኞቹ፦ሀገር እንመራለን የሚሉት ሀገር አልባ ናቸው፤የሃይማኖት አባት ነን የሚሉት ሃይማኖት አልባ ናቸው።
◈የመከራው ዶፍ ተሸካሚዎች ደግሞ በጎች ናቸው፤በሁለቱም የሥጋና የመንፈስ መሪዎች በትረ ሥልጣን የሚያርፍባቸው በእረኞች ነው።
"ዳዊትም ሕዝቡን የሚመታውን መልአክ ባየ ጊዜ እግዚአብሔርን፦እንሆ እኔ በድያለሁ ጠማማም ሥራ እኔ አድርጌያለሁ እነዚህ በጎች ግን እነርሱ ምን አደረጉ እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ እንድትሆን እለምንሃለሁ ብሎ ተናገረው።"፪.ሳሙ.፳፬፥፲፯
❤6
😭9❤2
የብልጽግና ወንጌል ቤተ ክህነት

የብልጽግና ወንጌል (Prosperity Gospel)መነሻው በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በአሜሪካ የፕሮቴስታንት እና የጴንጤቆስጤ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በስፋት የተሰራጨ የትምህርት እና የእምነት ፍልስፍና  ሲሆን በዋናነት የሚያተኩረው በቁሳዊ ብልጽግና ላይ ነው።
​የዚህ አስተምህሮ ማዕከላዊ መልእክት እግዚአብሔር ለአማኞች የሚሰጠው በረከት በዋናነት በቁሳዊ ሀብት፣ በገንዘብ፣ በስኬት እና በምቾት (Material Prosperity & Health) ይገለጻል የሚል ነው።

የብልጽግና ወንጌል (Prosperity Gospel) በአጠቃላይ የሚለይባቸው ዋና ዋና መገለጫዎች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።

1) የመከራንና የፈተናን ትርጉም ማቃለል

በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ መከራ፣ ትዕግሥትና መስቀልን መሸከም ያላቸውን ቦታ በቂ ሳያብራራ በድልና በስኬት ላይ ብቻ ማተኮር።

2)  ሀብትን ከእምነት ጋር ማያያዝ

ሰው በቂ እምነት ካለው ባለጠጋ መሆን እንደሚችል ማስተማር።

3) ጤናን ከእምነት ጋር ማያያዝ በእምነት መጸለይ ሁሉንም ሕመም ያስወግዳል ብሎ ማቅረብ።

4) ልገሳን እንደ በረከት መንገድ ማቅረብ ገንዘብ ለሰባኪ ወይም ለእምነታዊ አገልግሎት መስጠት ብዙ ገንዘብ ለማግኘት ዋስትና እንደሆነ ማስተማር።

5)  ድህነትን ከእምነት ማነስ ጋር ማያያዝ
ድህነትን ወይም የሕይወት ችግርን የግለሰቡ መንፈሳዊ ድክመት ውጤት አድርጎ መተርጎም።

7) የምድራዊ ስኬትን ከመንፈሳዊ ስኬት ጋር ማመሳሰል ብዙ ገንዘብ፣ የቅንጦት ቤት፣ ውድ መኪናና ከፍተኛ የኑሮ ደረጃ የእግዚአብሔር ሞገስ ማስረጃ እንደሆኑ ማቅረብ።

8)ለሰባኪው ያለውን እምነት ከልክ በላይ ማጉላት የሰባኪውን ቃል ያለ ጥያቄ እንዲቀበሉ ማበረታታትና የሚቃወሙትን እንደ እምነት ደካማ ሰዎች መቁጠር።


ቤተክህነትም ዋና ትኩረቱ ቁሳዊ ብልጽግና ላይ ነው።
👉ስንት ሰው ወንጌል ተማረ?
👉ስንት ሰው ንስሐ ገባ?
👉ስንት ሰው ሥጋ ወደሙን ተቀበለ?ወዘተ...ብሎ ማሰብ እንደ ኋላ ቀርነት ነው የሚታየው።ሁሌም ብር አምጡ ነው።የሚሰበሰበው ብር ቤተ ክርስቲያንቱ በምጣኔ ሀብት ራሷን እንድትችል ማድረግ፣ለኦርቶዶክሳውያን የሥራ መፍጠሪያ ሳይሆን የሚውለው ለጳጳሳት፣ለከተሜ መነኮሳት፣ ለሙሰኛ ካህናትና በጥቅም ለተሳሰሩ ግለሰቦች ቤትና መኪና መግዣ ፎቅ መሥሪያ፣ለቁርጥ መብያ ለ ውስኪ መጠጫ ነው።

እርስበርሳቸው የሚሸላለሙትም ከድሆች ኪስና መቀነት ዘርፈው ብዙ ገንዘብ ስለሰበሰቡ እንጂ ወንጌል አስተምረው አይደለም።ስጥ ሲባል ሳይሰስት የሰጠው ምስኪኑ ሕዝብ ግን ሲገደል፣ሲታረድ፣ሲሰደድ፣ሀብት ንብረቱ ሲወድም፣የጦርነት ቤተ ሙከራ ሲሆን ዝም ጭጭ አንዳች ነገር አይተነፍሱም።ለገንዘብና ለመዋጮ ብቻ የሚፈልገኝን ስገደልና ስሰደድ ዘወር ብሎ የማያየኝን ከገዳዮቼ ጋር የሚተባበርን መዋቅር የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ነው ብዬ ልቀበለው አልችልም ።
https://t.me/Eyo21e
በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ያላችሁ ኦርቶዶክሳውያን ሌሊት የተገደሉ የኦርቶዶክሳውያንን ሙሉ መረጃ (ስም፣ፎቶና ቪድዮ)ላኩልን። ፍጠኑ።
የኦርቶዶክሳውያን መታረጃ ቄራ በሆነችው በአርሲ ምድር ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ሥርዐቱ ስንቅና ትጥቅ ሰፍሮ ባሰማራቸው በአክራሪ የእስልምና ታጣቂዎች የተገደሉ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች
😭9❤2
የእመቤታችን ስደት ዛሬም አልቆመም ይኽንን ማሰብ የሚፈልግ ግን የለም። የማኅሌት ድምቀት የወረብ ውዝዋዜ የከበሮ ሽክርክሪት ነው የእመቤታችን ኀዘን እያልን ያለነው።

ወቅቱ አዘክሪ ድንግል ... ድንግል ኾይ የደረሰብሽን ስደት ረሃብ ጥም አሳስቢ ነው የሚለው።

እኛ ግን.....
❤15
◈አንድ ሰው ከጥፋት ጋራ ከተስማማ ስራ አቁሟል ማለት ነው።

◈ከጸረ ኦርቶዶክሳውያን ጋራ የማይስማማ ከሆነ እየሠራ ነው ማለት ነው።

◈ቤተ ክርስቲያንን በሥር ነቀል እያመነመኑ ካሉ አካላት ጋራ የምትሸላለም ከሆነ የጥፋት ዱላ ሁነሀል ማለት ነው።

◈ያመኑ መስሎ መካድ፣እያስመሰሉ ማመን ይሄ ነው።
❤11👍1
ሽርካዎች እየጠበቅኋችሁ ነው
👍4
#እረኞቻችን በመጽሐፍ #ሲመዘኑ

በኦርቶዶክሳዊት​ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የዚህ ትምህርት ማዕከልና ፍጹም ማሳያ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፣ በቤተ ክርስቲያን ያሉ አባቶችና መንፈሳዊ መሪዎች  የእርሱን ፈለግ በመከተል መንጋውን እንዲጠብቁ ተጠርተዋል።

የ​እውነተኛ እረኛ መገለጫዎች፦

​1. #መንጋውን የሚወድና #ሕይወቱን አሳልፎ የሚሰጥ

​እውነተኛ እረኛ ከራሱ ጥቅም፣ ምቾትና ሕይወት ይልቅ የበጎቹን (የምእመናንን) ደህንነት ያስቀድማል።
​
“እውነተኛ እረኛ እኔ ነኝ፤ እውነተኛ እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።” (ዮሐንስ 10:11)
​
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በዮሐንስ ወንጌል ትርጓሜው ላይ እንደሚያስተምረው፡ “ክርስቶስ እውነተኛ እረኛ የተባለው መንጋውን ከነፍስ አዳኝ (ከዲያብሎስ) ታደገ፤ በገዛ ደሙም ዋጃቸው። ሞያተኛው (ቅጣሪው) አደጋና መከራ ሲመጣ በጎቹን ትቶ እንደሚሸሽ፣ እውነተኛው እረኛ ግን ስለ በጎቹ ሲል ሕይወቱን አሳልፎ ይሰጣል።”

​2. #በበሩ (በክርስቶስ) የሚገባና #በሃይማኖት የጸና

​እውነተኛ እረኛ ወደ መንጋው የሚገባው በትክክለኛው መንገድና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንጂ በቋንቋ ፣በዘር ወይም በሥልጣን ጥመኝነት አይደለም።

​“ወደ በጎቹ በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ነጣቂም ነው፤ በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው።” (ዮሐንስ 10:1-2)

ቅዱስ ቄርሎስ እንደሚያስተምረው፡ “በሩ ክርስቶስ ነው። በበሩ የሚገባ እረኛ ማለት በክርስቶስ እውነተኛ እምነት አምኖ፣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ሕግ (በካህናት እጅና በሲኖዶስ ቡራኬ) የተሾመ ነው። በሌላ መንገድ (በገንዘብ፣ በኃይል፣ በስም ወይም በራሱ ፈቃድ) የሚገባ ግን ሌባና ነጣቂ ነው፤ መንጋውን ሊያጠፋ እንጂ ሊጠብቅ አይመጣም።”

​3. #በጎቹን በስም የሚያውቅና #በፍቅር የሚያገለግል

​እውነተኛ እረኛ ከሕዝቡ ጋር የጠበቀና የቀረበ መንፈሳዊ ግንኙነት አለው፤ በሩቅ ሆኖ አይገዛም።

​ “እረኛው በጎቹን በየስማቸው ይጠራቸዋል፥ ይመራቸውማል። ... በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል።” (ዮሐንስ 10:3-4)
​
ቅዱስ ጎርጎርዮስ እረኝነትን “የጥበቦች ሁሉ ጥበብ (Art of Arts)” ብሎ ይጠራዋል። እረኛ የሰዎችን ነፍስ የሚፈውስ ሀኪም በመሆኑ በጎቹን በኃይልና በጭካኔ ሳይሆን በፍቅር፣ በትዕግሥትና በትሕትና ይመራቸዋል። አብሮአቸው ይደሰታል፣ በሕመማቸውና በኃጢአታቸውም አብሮ ይታመማል፤ በትምህርትና በንሰሐ ያክማቸዋል።

​4. #ንጹሕና ያልተበረዘ #መንፈሳዊ ምግብ የሚያቀርብ

​የእረኛ ዋና ተግባር መንጋውን በጥሩ መስክ ማሰማራትና ንጹሕ የሃይማኖት ምግብ መገበብ ነው።
​ “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝ የለም። በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል።” (መዝሙረ ዳዊት 23:1-2)

ቅዱስ አትናቴዎስ እንደሚያስተምረው እውነተኛ እረኛ ቅዱሳት መጻሕፍትንና የአበውን እምነት ሳይበርዝ፣ ሳይጨምርና ሳይቀንስ እውነተኛውን የሃይማኖት ምግብ ለምእመናን ያቀርባል። መንጋው በሐሰተኛ ትምህርትና በምንፍቅና አየር እንዳይበከል ሌሊትና ቀን ይጠብቃቸዋል።

​5. #የጠፋውን የሚፈልግና #የሚያስብ (የምሕረት እረኛ)

​እውነተኛ እረኛ የወደቁትን፣ የደከሙትንና የተሳሳቱትን አይጥላቸውም፤ ይልቁንም በፍቅር ይፈልጋቸዋል።

​“ከእናንተ መቶ በግ ያለው አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ማን ነው?” (ሉቃስ 15:4)
​
ሊቃውንቱ እንደሚያስተምሩት፣ ፍጹሙ እረኛ ክርስቶስ የጠፋችዋን አንዲቷን በግ (አዳምን/የሰው ልጅን) ፍለጋ እስከ ሲኦል ድረስ በመውረድ፣ በስጋውና በደሙ መግቦ ወደ ቀደመ ክብሩ መልሷታል። በቤተ ክርስቲያን ያሉ እረኞችም ኃጢአተኞችን በመኮነን ፈንታ በንሰሐና በፍቅር ወደ እግዚአብሔር መንጋ የመመለስ ኃላፊነት አለባቸው።

​6. #በትሕትናና በፈቃደኝነት #የሚያገለግል

​እውነተኛ እረኛ ለገንዘብ፣ ለዝና ወይም ለሥልጣን ብሎ አያገለግልም።
​

" በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ"
(1ጴጥር5:2-3)

የዚህ ዘመን #እረኞቻችን 98%  ከላይ ከተጠቀሱት #መስፈርቶች  አንዱንም እንኳ አላሟሉም።ለዚህ ነው እውነተኛ #እረኞች ሳይሆኑ #ምንደኞች ናቸው የምንለው።ምንደኞችን መከተል "እውነተኛ እረኛ እኔ ነኝ"ዮሐ (10:11) ያለንን አምላክ መካድ ነው።ከሃዲ ደግሞ በሰማይ ቦታ የለውም።

https://t.me/Eyo21e
❤4👍2
ተጠናክሮ የቀጠለው #የኦርቶዶክሳውያን ፍጅት

ላለፉት ሦስት ዓመታት የኦርቶዶክሳውያን መታረጃ ቄራ ሆና የቆየችው የአርሲ ምድር አሁንም ፍጅቱ ተባብሶ እንደቀጠለ ነው።

ትናንት ጥቅምት 7/2019ዓ.ም በሽርካ ወረዳ ሄላ ዘምባባ ቀበሌ ዘምባ ማርያም ቤተ ክርስቲያን አከባቢ ሌሊት 4:00 በተከፈተ ጥቃት፦
👉 2 ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል
👉 አንድ ካህን በጥይት ተመተው ሆስፒታል ገብተዋል
👉5 ኦርቶዶክሳውያን ታግተው ተወስደዋል
ይኽ ጥቃት ከመፈጸሙ ከአንድ ቀን በፊት (ዐርብ)ሕዝቡ አክራሪ ታጣቂዎቹ በአከባቢው ላይ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ለወረዳው ባለሥልጣናት ቢያሳውቅም ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አላደረጉም።አክራሪ ታጣቂዎቹ ቅዳሜ ሌሊት ወጥተው ጥቃት ከፈቱባቸው።

በዚሁ በወረዳ ያሉ ከተለያዩ ቀበሌዎች 20,000(20ሺ)  ኦርቶዶክሳውያን ተፈናቅለዋል (ከኦሮሚያ ክልል መዋቅር የተላኩት ሰዎች ግን 7ሺ ቀንሰው ወደ 13ሺ  አውርደውታል) ።እነዚህ ኦርቶዶክሳውያን ለከፍተኛ ረሃብ ተጋልጠዋል።ይኽ ሁሉ ግፍ በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየተፈጸመ አቡነ ኤልሳዕና የሀገረ ስብከቱ ሀላፊዎች     ዝምታን መርጠዋል።
😭19❤6