Eotc Task Force
8.54K subscribers
1.92K photos
446 videos
12 files
502 links
ወቅታዊ ጉዳይ
Download Telegram
አልተመሳሰለባችሀም ግን?

ግድሎ መሸለም
አስገድሎም መሸለም

በመመካከላቸው ያለው ልዩነት የቆብና የሱፍ ልዩነት ነው

የቁስ ቤተ መንግሥት
የቁስ ቤተ ክህነት
የቁስ ፖለቲከኞች
የቁስ ጳጳሳት
በሁለቱም ዘንድ ሰው የሚባለው ፍጡር ቦታ የለውም።
❤16🤔2
ኦርቶዶክሳዊው በሀገሩ ላይ«ተገፍቷል»

ኦርቶዶክሳዊው ማኅበረሰብ  በገዛ ሀገሩ ላይ «ተገፍቷል» ስንል፤ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚ እና በባህል መብቶቹን ተነፍጎ፣ በባለቤትነት ስሜት ፋንታ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መቆጠሩን ነው።

የመገፋቱ ማሳያዎች፦

1 ከታሪካዊ መኖሪያው ተፈናቅሏል

ከቀድሞ ጀምሮ ከኖረበት  አከባቢ በጅምላ ተፈናቅሏል

2 የዜግነት መብቶች እኩል አለመከበር

በሕግ ፊት እኩል የመሆን፣ የፍትሕ ጥበቃ የማግኘት፣ በሰላም የመኖርና የመንቀሳቀስ መብቶችን ተነፍጓል።

3 ከፖለቲካዊና ከሕዝባዊ ተሳትፎ መገለል
በአስተዳደር፣ በውሳኔ ሰጪነትና በሕዝባዊ ተቋማት ውስጥ  እንዳይሳተፍ መደረጉ።

4 ለሕይወቱና ለንብረቱ ተመጣጣኝ ጥበቃ አለማግኘቱ

ለጥቃት፣ ለግድያ፣ ለእገታ፣ ለዘረፋ ወይም ለማስፈራራት ተጋላጭ ሆኖ የሕግ ጥበቃ አለማግኘም።

5 ከሀገራዊ ሀብትና ከልማት ዕድሎች መገለል

በሃይማኖቱ ምክንያት የትምህርት፣የ ጤና፣ የሥራ፣ የመሠረተ ልማትና የኢኮኖሚ ዕድሎችን በእኩልነት ማግኘት አልቻለም።

6  ማንነቱን፣ ታሪኩንና ባህሉን ማሳነስ ወይም መካድ

ቋንቋው፣ ባህሉ፣ ሃይማኖቱ፣ ታሪካዊ ቅርሶቹ ወይም በሀገሩ ላይ ያለው ታሪካዊ አስተዋጽኦ በሥርዓት መካዱ ወይም መገፋቱ።
https://t.me/Eyo21e
👍4❤2
😭14❤1👍1
ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ያላችሁ ኦርትዶክሳውያን ምንድን ነው የተፈጠረው?እስኪ መረጃ አድርሱን።
❤9🥰1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአርሲ ዞን ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ልዩ ቦታው መጪቱ ላይ   በ05/02/2019ዓ.ም ሁለት ወንድማማች  ኦርቶዶክሳውያን የሽርኩት አረም እየረጩ ባሉበት ተገድለዋል። ትናንት 06/02/2019ዓ.ም አንድ ኦርቶዶክሳዊ ተገድሏል ።በድምሩ ሦስት(3) ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል የብዙዎች ሀብት ንብረት ተዘርፏል።
😢16❤4
1ቀን ቀራቸው ይፈቱልን ፍትህ

እንዴት ከርመው ይሆን?
በጨለማ ዕስር ቤት 136ቀን የሆናቸው ክቡር አባታችን ቀሲስ መዝገቡ ፍትሕ ለአባታችን

ግንቦት 26የታሰሩት የፍርድቤት ቀጠሮ ጥቅምት 9 ነገ የቀጠሮ ቀኝ

አባታችንን ፍቱልን
🥰15🙏8😢5❤2
"በጎች ምን አደረጉ?"
፪.ሳሙ.፳፬፥፲፯
◈በዚህ ዘመን በምእመናን ላይ የሆነውም ሆየ የሚሆነው በሥጋዊ እና በመንፈሳዊ እረኞች ምክንያት ነው።
◈በጎች ገብሩ ቀቅሉ ሲባሉ እሺ ይላሉ፤ ስጡ መጽውቱ ሲባሉ እሺ ይላሉ።
◈በጎቹ ከእረኞቹ የተሻለ የሀገርም የሃይማኖትም ክብር አላቸው።
◈በአንጻሩ ደግሞ እረኞቹ፦ሀገር እንመራለን የሚሉት ሀገር አልባ ናቸው፤የሃይማኖት አባት ነን የሚሉት ሃይማኖት አልባ ናቸው።
◈የመከራው ዶፍ ተሸካሚዎች ደግሞ በጎች ናቸው፤በሁለቱም የሥጋና የመንፈስ መሪዎች በትረ ሥልጣን የሚያርፍባቸው በእረኞች ነው።
"ዳዊትም ሕዝቡን የሚመታውን መልአክ ባየ ጊዜ እግዚአብሔርን፦እንሆ እኔ በድያለሁ ጠማማም ሥራ እኔ አድርጌያለሁ እነዚህ በጎች ግን እነርሱ ምን አደረጉ እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ እንድትሆን እለምንሃለሁ ብሎ ተናገረው።"፪.ሳሙ.፳፬፥፲፯
❤6
😭9❤2
የብልጽግና ወንጌል ቤተ ክህነት

የብልጽግና ወንጌል (Prosperity Gospel)መነሻው በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በአሜሪካ የፕሮቴስታንት እና የጴንጤቆስጤ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በስፋት የተሰራጨ የትምህርት እና የእምነት ፍልስፍና  ሲሆን በዋናነት የሚያተኩረው በቁሳዊ ብልጽግና ላይ ነው።
​የዚህ አስተምህሮ ማዕከላዊ መልእክት እግዚአብሔር ለአማኞች የሚሰጠው በረከት በዋናነት በቁሳዊ ሀብት፣ በገንዘብ፣ በስኬት እና በምቾት (Material Prosperity & Health) ይገለጻል የሚል ነው።

የብልጽግና ወንጌል (Prosperity Gospel) በአጠቃላይ የሚለይባቸው ዋና ዋና መገለጫዎች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።

1) የመከራንና የፈተናን ትርጉም ማቃለል

በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ መከራ፣ ትዕግሥትና መስቀልን መሸከም ያላቸውን ቦታ በቂ ሳያብራራ በድልና በስኬት ላይ ብቻ ማተኮር።

2)  ሀብትን ከእምነት ጋር ማያያዝ

ሰው በቂ እምነት ካለው ባለጠጋ መሆን እንደሚችል ማስተማር።

3) ጤናን ከእምነት ጋር ማያያዝ በእምነት መጸለይ ሁሉንም ሕመም ያስወግዳል ብሎ ማቅረብ።

4) ልገሳን እንደ በረከት መንገድ ማቅረብ ገንዘብ ለሰባኪ ወይም ለእምነታዊ አገልግሎት መስጠት ብዙ ገንዘብ ለማግኘት ዋስትና እንደሆነ ማስተማር።

5)  ድህነትን ከእምነት ማነስ ጋር ማያያዝ
ድህነትን ወይም የሕይወት ችግርን የግለሰቡ መንፈሳዊ ድክመት ውጤት አድርጎ መተርጎም።

7) የምድራዊ ስኬትን ከመንፈሳዊ ስኬት ጋር ማመሳሰል ብዙ ገንዘብ፣ የቅንጦት ቤት፣ ውድ መኪናና ከፍተኛ የኑሮ ደረጃ የእግዚአብሔር ሞገስ ማስረጃ እንደሆኑ ማቅረብ።

8)ለሰባኪው ያለውን እምነት ከልክ በላይ ማጉላት የሰባኪውን ቃል ያለ ጥያቄ እንዲቀበሉ ማበረታታትና የሚቃወሙትን እንደ እምነት ደካማ ሰዎች መቁጠር።


ቤተክህነትም ዋና ትኩረቱ ቁሳዊ ብልጽግና ላይ ነው።
👉ስንት ሰው ወንጌል ተማረ?
👉ስንት ሰው ንስሐ ገባ?
👉ስንት ሰው ሥጋ ወደሙን ተቀበለ?ወዘተ...ብሎ ማሰብ እንደ ኋላ ቀርነት ነው የሚታየው።ሁሌም ብር አምጡ ነው።የሚሰበሰበው ብር ቤተ ክርስቲያንቱ በምጣኔ ሀብት ራሷን እንድትችል ማድረግ፣ለኦርቶዶክሳውያን የሥራ መፍጠሪያ ሳይሆን የሚውለው ለጳጳሳት፣ለከተሜ መነኮሳት፣ ለሙሰኛ ካህናትና በጥቅም ለተሳሰሩ ግለሰቦች ቤትና መኪና መግዣ ፎቅ መሥሪያ፣ለቁርጥ መብያ ለ ውስኪ መጠጫ ነው።

እርስበርሳቸው የሚሸላለሙትም ከድሆች ኪስና መቀነት ዘርፈው ብዙ ገንዘብ ስለሰበሰቡ እንጂ ወንጌል አስተምረው አይደለም።ስጥ ሲባል ሳይሰስት የሰጠው ምስኪኑ ሕዝብ ግን ሲገደል፣ሲታረድ፣ሲሰደድ፣ሀብት ንብረቱ ሲወድም፣የጦርነት ቤተ ሙከራ ሲሆን ዝም ጭጭ አንዳች ነገር አይተነፍሱም።ለገንዘብና ለመዋጮ ብቻ የሚፈልገኝን ስገደልና ስሰደድ ዘወር ብሎ የማያየኝን ከገዳዮቼ ጋር የሚተባበርን መዋቅር የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ነው ብዬ ልቀበለው አልችልም ።
https://t.me/Eyo21e
በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ያላችሁ ኦርቶዶክሳውያን ሌሊት የተገደሉ የኦርቶዶክሳውያንን ሙሉ መረጃ (ስም፣ፎቶና ቪድዮ)ላኩልን። ፍጠኑ።
የኦርቶዶክሳውያን መታረጃ ቄራ በሆነችው በአርሲ ምድር ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ሥርዐቱ ስንቅና ትጥቅ ሰፍሮ ባሰማራቸው በአክራሪ የእስልምና ታጣቂዎች የተገደሉ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች
😭9❤2