Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
እኛና የ"አዲሲቷ ኢትዮጵያ "ፖለቲከኞች
🔏እኛ ሀገር ስንል፦ የሁሉ ለሁሉ የሆነች አባቶቻችን ዋጋ ከፍለው ያቆዩልንን ነባር ኢትዮጵያን ነው እነርሱ ሀገር ሲሉ፦የምዕራባውያንና የዐረቦች ዲቃላ የሆነች አዲሲቷን ኢትዮጵያ ነው
🔏እኛ ታሪክ ስንል የ5000ሺህ ዘመን ታሪክ ነው እነርሱ ታሪክ ሲሉ የ150 ዘመን ታሪክ ነው
🔏እኛ ሰው ስንል በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ የተፈጠረን ነው እነርሱ ሰው ሲሉ ዘርን ወይም ቡድንን ነው
🔏እኛ ሕዝብ ስንል መላ ኢትዮጵያውያንን ነው እነርሱ ሕዝብ የሚሉት ግን በቋንቋና በመንደር የተካፈሉትን ብቻ ለይተው ነው
🔏እኛ ሰላም ስንል የሰው ልጅ ሁሉ በማንነቱ በሃይማኖቱ ሳይጠቃ በገዛ ሀገሩ ላይ በሰላም ወጥቶ መግባትን ነግዶ ማትረፍን አርሶ መብላትን ነው እነርሱ ሰላም ሲሉ ሌላውን እያጠቁና እረፍት እየነሱ ተደንደላቆ መኖርን ነው
🔏እኛ ፖለቲካ ስንል ሀገር የመምራት ጥበብን ነው እነርሱ ፖለቲካ የሚሉት ቁማርን ነው
🔏እኛ እድገት ስንል የሕዝቦችን አጠቃላይ የኑሮ ደረጃ፣ የኢኮኖሚ ጥንካሬ፣ የትምህርትና የጤና ሽፋን እንዲሁም የማህበራዊና የፖለቲካ ተቋማትን አቅም በዘላቂነት ማሻሻልና ማሳደግን ነው እነርሱ እድገት የሚሉት የሚጠሉትን ክፍለ ሕዝብ በእምነቱና በማንነቱ ለይቶ ማፈናቀል ህጋዊ ደሃ ማድረግ ነው
🔏እኛ እኩልነት ስንል ሁሉም ዜጋ በሕግ ፊት አንድ ዓይነት መብትና እድል እንዲኖረው ማድረግን ልዩነቶችን አክብሮ ሰብዓዊ ክብርን እኩል መስጠት ነው እነሱ እኩልነት ሲሉ ተቃውሞ እንዳይነሳ ሰዎችን ሁሉ "እኩል" አስመስሎ ማደቀቅ/ማስገደድን ነው
🔏 እኛ አካታችነት ስንል የሁሉንም ብሔር፣ ሃይማኖት፣ ጾታና አመለካከት ድምፅ መስማትና በውሳኔ ላይ ማሳተፍ በውይይትና በስምምነት አብሮ መስራትን ነው እነሱ አካታችነት ሲሉ የይስሙላ (የስም) ውክልና መስጠትን የገዢውን ቡድን ፍላጎት የተቀበሉትን ብቻ በመምረጥ "ሁሉንም አካተናል" የሚል ፕሮፓጋንዳ መስራትን ነው
🔏እኛ ፋትሕ ስንል በሕግ አሠራር ላይ የተመሠረተ የበደለ የሚቀጣበት፣ የተበደለ የሚካስበት እውነተኛ ዳኝነት ፍርድ ቤቶች ገለልተኛ እንዲሆኑ ማድረግን ነው እነሱ ፍትሕ ሲሉ ተቃዋሚዎችንና ድምጻቸውን የሚያሰሙ ሰዎችን ማጥቂያና ማሰሪያ መሳሪያ ማድረግን ፍትሕ ማለት የመንግሥትን ፍላጎት ማስፈጸሚያን ነው።
🔏እኛ ሕገ-መንግሥት ስንል የሕዝብና የሀገር ከፍተኛ የቃል ኪዳን ሰነድ፤ የዜጎችን መብት መጠበቂያና የመንግሥትን ሥልጣን ገዳቢ እነሱ ሕገመንግሥት ሲሉ ሥልጣንን ለማራዘሚያና ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ሕጋዊ ሽፋን መስጫ መሳሪያ እንደ አስፈላጊነቱ ለገዢው አካል ይመች ዘንድ የሚቀያየር ሰነድን ነው።
🔏እኛ ሕግ ማስከበር ስንል ሰላምን፣ ደህንነትንና የዜጎችን መብት ከአመፅና ከወንጀል መጠበቅን ነው እነሱ ሕግ ማስከበር ሲሉ ሥልጣንን መቃወምን እንደ ወንጀል በመቁጠር የሚጠሉትን ሕዝብ በኃይልና በሽብር ማንበርከክ የጸጥታ አካላትን ሕዝብን ማሰቃያ ማድረግን ነው
🔏 እኛ መብት ስንል መብት የመንግሥት ስጦታ ሳይሆን፣ ሰው በመሆን ብቻ የሚገኝ ተፈጥሯዊ ሀብት መሆኑን የመንግሥት ዋና ተግባር የዜጎችን የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመደራጀት፣ የሕይወትና የንብረት መብት ማስከበርና ጥበቃ ማድረግን፣ መንግሥት የዜጎችን መብት ሲጥስ በሕግ ፊት ተጠያቂ መሆንን ነው እነሱ መብት ሲሉ መብት የተፈጥሮ እና የሰው ልጅ በመሆን ብቻ የሚገኝ ሳይሆን፣ ለገዢዎች በመታዘዝ የሚገዛ ወይም የሚቸር ስጦታ አስመስሎ ማቅረብን የፖለቲካ፣ የሃሳብ እና የፕሬስ ነፃነትን ለመጨቆን እና ጥያቄ የሚጠይቁ ሰዎችን ልማት እና ሰላም የሚቃወሙ አስመስሎ መፈረጅንየገዛ ራሳቸውን ሥልጣን ለመጠበቅ ባወጧቸው ጨቋኝ ህጎች ተጠቅመው የተቃውሞ ድምፆችን ሁሉ "ህገ-ወጥ" በማለት መብትን በሕግ ስም ማፈንን ነው።
🔏እኛ የሀገር ሉዐላዊነት ስንል ሉዓላዊነት የህዝብ መሆኑን ህዝቡ በነፃነት መምረጥ፣ መናገር እና በሀገሩ ጉዳይ ላይ የመወሰን መብት መከበርን፣እውነተኛ ሉዓላዊነት የሚገነባው ከውስጥ አቅም ማለትም በጠንካራ ኢኮኖሚ፣ በፍትሃዊ ስርአት፣ በምግብ ራስን በመቻል እና የዜጎች ሙሉ ደኅንነት ማግኘትን ነው እነሱ የሀገሬ ሉዐላዊነት ሲሉ <<እኛ ነን ሀገር>> በሚል እሳቤ፣ እነሱን መቃወም እንደ ሀገር ሉዓላዊነት መድፈር መቁጠርን፣ሉዓላዊነት በወታደራዊ ኀይል፣ በፖሊስ አፈና እና ህዝብን በፍርሃት ጠፍሮ በመያዝን ነው
.
.
.
....የቀረውን እናንተ ቀጥሉበት።
https://t.me/Eyo21e

❤11😁1
Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
አልተመሳሰለባችሀም ግን?
ግድሎ መሸለም
አስገድሎም መሸለም
በመመካከላቸው ያለው ልዩነት የቆብና የሱፍ ልዩነት ነው
የቁስ ቤተ መንግሥት
የቁስ ቤተ ክህነት
የቁስ ፖለቲከኞች
የቁስ ጳጳሳት
በሁለቱም ዘንድ ሰው የሚባለው ፍጡር ቦታ የለውም።
ግድሎ መሸለም
አስገድሎም መሸለም
በመመካከላቸው ያለው ልዩነት የቆብና የሱፍ ልዩነት ነው
የቁስ ቤተ መንግሥት
የቁስ ቤተ ክህነት
የቁስ ፖለቲከኞች
የቁስ ጳጳሳት
በሁለቱም ዘንድ ሰው የሚባለው ፍጡር ቦታ የለውም።
❤16🤔2
Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
ኦርቶዶክሳዊው በሀገሩ ላይ«ተገፍቷል»
ኦርቶዶክሳዊው ማኅበረሰብ በገዛ ሀገሩ ላይ «ተገፍቷል» ስንል፤ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚ እና በባህል መብቶቹን ተነፍጎ፣ በባለቤትነት ስሜት ፋንታ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መቆጠሩን ነው።
የመገፋቱ ማሳያዎች፦
1 ከታሪካዊ መኖሪያው ተፈናቅሏል
ከቀድሞ ጀምሮ ከኖረበት አከባቢ በጅምላ ተፈናቅሏል
2 የዜግነት መብቶች እኩል አለመከበር
በሕግ ፊት እኩል የመሆን፣ የፍትሕ ጥበቃ የማግኘት፣ በሰላም የመኖርና የመንቀሳቀስ መብቶችን ተነፍጓል።
3 ከፖለቲካዊና ከሕዝባዊ ተሳትፎ መገለል
በአስተዳደር፣ በውሳኔ ሰጪነትና በሕዝባዊ ተቋማት ውስጥ እንዳይሳተፍ መደረጉ።
4 ለሕይወቱና ለንብረቱ ተመጣጣኝ ጥበቃ አለማግኘቱ
ለጥቃት፣ ለግድያ፣ ለእገታ፣ ለዘረፋ ወይም ለማስፈራራት ተጋላጭ ሆኖ የሕግ ጥበቃ አለማግኘም።
5 ከሀገራዊ ሀብትና ከልማት ዕድሎች መገለል
በሃይማኖቱ ምክንያት የትምህርት፣የ ጤና፣ የሥራ፣ የመሠረተ ልማትና የኢኮኖሚ ዕድሎችን በእኩልነት ማግኘት አልቻለም።
6 ማንነቱን፣ ታሪኩንና ባህሉን ማሳነስ ወይም መካድ
ቋንቋው፣ ባህሉ፣ ሃይማኖቱ፣ ታሪካዊ ቅርሶቹ ወይም በሀገሩ ላይ ያለው ታሪካዊ አስተዋጽኦ በሥርዓት መካዱ ወይም መገፋቱ።

👍4❤2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአርሲ ዞን ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ልዩ ቦታው መጪቱ ላይ በ05/02/2019ዓ.ም ሁለት ወንድማማች ኦርቶዶክሳውያን የሽርኩት አረም እየረጩ ባሉበት ተገድለዋል። ትናንት 06/02/2019ዓ.ም አንድ ኦርቶዶክሳዊ ተገድሏል ።በድምሩ ሦስት(3) ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል የብዙዎች ሀብት ንብረት ተዘርፏል።
😢16❤4
❤2
Forwarded from ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
"በጎች ምን አደረጉ?"
፪.ሳሙ.፳፬፥፲፯
◈በዚህ ዘመን በምእመናን ላይ የሆነውም ሆየ የሚሆነው በሥጋዊ እና በመንፈሳዊ እረኞች ምክንያት ነው።
◈በጎች ገብሩ ቀቅሉ ሲባሉ እሺ ይላሉ፤ ስጡ መጽውቱ ሲባሉ እሺ ይላሉ።
◈በጎቹ ከእረኞቹ የተሻለ የሀገርም የሃይማኖትም ክብር አላቸው።
◈በአንጻሩ ደግሞ እረኞቹ፦ሀገር እንመራለን የሚሉት ሀገር አልባ ናቸው፤የሃይማኖት አባት ነን የሚሉት ሃይማኖት አልባ ናቸው።
◈የመከራው ዶፍ ተሸካሚዎች ደግሞ በጎች ናቸው፤በሁለቱም የሥጋና የመንፈስ መሪዎች በትረ ሥልጣን የሚያርፍባቸው በእረኞች ነው።
"ዳዊትም ሕዝቡን የሚመታውን መልአክ ባየ ጊዜ እግዚአብሔርን፦እንሆ እኔ በድያለሁ ጠማማም ሥራ እኔ አድርጌያለሁ እነዚህ በጎች ግን እነርሱ ምን አደረጉ እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ እንድትሆን እለምንሃለሁ ብሎ ተናገረው።"፪.ሳሙ.፳፬፥፲፯

❤6
Forwarded from "!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
የብልጽግና ወንጌል ቤተ ክህነት
የብልጽግና ወንጌል (Prosperity Gospel)መነሻው በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በአሜሪካ የፕሮቴስታንት እና የጴንጤቆስጤ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በስፋት የተሰራጨ የትምህርት እና የእምነት ፍልስፍና ሲሆን በዋናነት የሚያተኩረው በቁሳዊ ብልጽግና ላይ ነው።
የዚህ አስተምህሮ ማዕከላዊ መልእክት እግዚአብሔር ለአማኞች የሚሰጠው በረከት በዋናነት በቁሳዊ ሀብት፣ በገንዘብ፣ በስኬት እና በምቾት (Material Prosperity & Health) ይገለጻል የሚል ነው።
የብልጽግና ወንጌል (Prosperity Gospel) በአጠቃላይ የሚለይባቸው ዋና ዋና መገለጫዎች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።
1) የመከራንና የፈተናን ትርጉም ማቃለል
በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ መከራ፣ ትዕግሥትና መስቀልን መሸከም ያላቸውን ቦታ በቂ ሳያብራራ በድልና በስኬት ላይ ብቻ ማተኮር።
2) ሀብትን ከእምነት ጋር ማያያዝ
ሰው በቂ እምነት ካለው ባለጠጋ መሆን እንደሚችል ማስተማር።
3) ጤናን ከእምነት ጋር ማያያዝ በእምነት መጸለይ ሁሉንም ሕመም ያስወግዳል ብሎ ማቅረብ።
4) ልገሳን እንደ በረከት መንገድ ማቅረብ ገንዘብ ለሰባኪ ወይም ለእምነታዊ አገልግሎት መስጠት ብዙ ገንዘብ ለማግኘት ዋስትና እንደሆነ ማስተማር።
5) ድህነትን ከእምነት ማነስ ጋር ማያያዝ
ድህነትን ወይም የሕይወት ችግርን የግለሰቡ መንፈሳዊ ድክመት ውጤት አድርጎ መተርጎም።
7) የምድራዊ ስኬትን ከመንፈሳዊ ስኬት ጋር ማመሳሰል ብዙ ገንዘብ፣ የቅንጦት ቤት፣ ውድ መኪናና ከፍተኛ የኑሮ ደረጃ የእግዚአብሔር ሞገስ ማስረጃ እንደሆኑ ማቅረብ።
8)ለሰባኪው ያለውን እምነት ከልክ በላይ ማጉላት የሰባኪውን ቃል ያለ ጥያቄ እንዲቀበሉ ማበረታታትና የሚቃወሙትን እንደ እምነት ደካማ ሰዎች መቁጠር።
ቤተክህነትም ዋና ትኩረቱ ቁሳዊ ብልጽግና ላይ ነው።
👉ስንት ሰው ወንጌል ተማረ?
👉ስንት ሰው ንስሐ ገባ?
👉ስንት ሰው ሥጋ ወደሙን ተቀበለ?ወዘተ...ብሎ ማሰብ እንደ ኋላ ቀርነት ነው የሚታየው።ሁሌም ብር አምጡ ነው።የሚሰበሰበው ብር ቤተ ክርስቲያንቱ በምጣኔ ሀብት ራሷን እንድትችል ማድረግ፣ለኦርቶዶክሳውያን የሥራ መፍጠሪያ ሳይሆን የሚውለው ለጳጳሳት፣ለከተሜ መነኮሳት፣ ለሙሰኛ ካህናትና በጥቅም ለተሳሰሩ ግለሰቦች ቤትና መኪና መግዣ ፎቅ መሥሪያ፣ለቁርጥ መብያ ለ ውስኪ መጠጫ ነው።
እርስበርሳቸው የሚሸላለሙትም ከድሆች ኪስና መቀነት ዘርፈው ብዙ ገንዘብ ስለሰበሰቡ እንጂ ወንጌል አስተምረው አይደለም።ስጥ ሲባል ሳይሰስት የሰጠው ምስኪኑ ሕዝብ ግን ሲገደል፣ሲታረድ፣ሲሰደድ፣ሀብት ንብረቱ ሲወድም፣የጦርነት ቤተ ሙከራ ሲሆን ዝም ጭጭ አንዳች ነገር አይተነፍሱም።ለገንዘብና ለመዋጮ ብቻ የሚፈልገኝን ስገደልና ስሰደድ ዘወር ብሎ የማያየኝን ከገዳዮቼ ጋር የሚተባበርን መዋቅር የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ነው ብዬ ልቀበለው አልችልም ።