Eotc Task Force
8.43K subscribers
1.92K photos
446 videos
12 files
502 links
ወቅታዊ ጉዳይ
Download Telegram
#NoMore የ150 ዓመት ታሪክ

#ቤተ_ክርስቲያን_ዘኢትዮጵያ - አዲስ መጽሐፍ!

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ፦
1. ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
2. መምህር ግርማ ባቱ
3. መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል
4. መምህር ብርሃኑ አድማስ
5. መምህር ያረጋል አበጋዝ
6. መምህር በረከት አዝመራው የተሳተፉበት ሲኾን ጽሑፎቻቸው ራሳቸውን የቻሉ መጻሕፍት ይኾናሉ ቢባል ማጋነን አይደለም።

መጽሐፉ ከነገ ዐርብ ጥቅምት 6/ 2019 ጀምሮ በ ባኮስ መጻሕፍት መደብር - Bakos Book Store ይከፋፈላል።

#ቤተ_ክርስቲያን_ዘኢትዮጵያ - The Church of Ethiopia.
❤18👏3
አሳብን በአሳብ ከመሞገት ይልቅ ሮጦ በዘር ስር መደበቅ ድንቁርና ነው
ትኅትና"አቡነ ሳዊሮስን ተናገረችብን "ብላችሁ የምትንጫጩ ሰዎች በዘር ስር አትደበቁ ጎበዞች ከሆናችሁ  ተሰባስባችሁ ፊት ለፊት ግጠሟትና በአሳብ ሞግቷት ።አቡነ ሳዊሮስን መቃወም ከኦሮሞ ሕዝብ ጋር በምንም  አይገናኝም።እኔም ለምን አልነግራችሁም አቡነ ሳዊሮስ ቆብ ያጠለቁ  ፖለቲከኛ እንጂ የቤተ ክርስቲያን አባት አይደሉም።እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ እንደ እሳቸው ዘር የሚቆጥሩ ኦርቶዶክሳውያንን በ ዘር በቋንቋ የሚከፋፍሉ ሁሉ የቤተ ክርስቲያን አባት ሳይሆኑ የቤተ ክርስቲያን ጠላት ናቸው።የአባት ተግባሩ ፦
👉ሰዎችን ማጣላት ሳይሆን የተጣሉትን  ማስታረቅ ነው
👉የተለያዩትን አንድ ማድረግ እንጂ አንድ የሆኑትን መለያየት አይደለም
👉የተበተኑትን መሰብሰብ እንጂ የተሰበሰቡትን መበተን አይደለም
👉ከቤተ ክርስቲያን ጋር ቆሞ ጠላቶችዋን መታገል እንጂ ከጠላት ጋር ተሰልፎ ቤተ ክርስቲያንን መታገል አይደለም
👉  ፖለቲከኞችን ከቤተ ክርስቲያን መጠበቅ እንጂ ቤተ ክርስቲያንን ለፖለቲከኞች መሸጥ አይደለም
👉 ለመንጋው ራስን አሳልፎ መስጠት እንጂ መንጋውን መግደልና ማስገደል አይደለም
👉ሐዋርያዊነትን ማስቀጠል እንጂ ከሐዋርያዊነት ተቆርጦ ሌሎችንም መቁረጥ አይደለም
👉አማኞችን  ከጨለማ ወደ ብርሃን መመለስ እንጂ በብርሃን ያሉትን ወደጨለማ መመለስ አይደለም።
👉ጽድቅ እየሰሩ ራስን እንደ ኀጢአተኛ መቁጠር እንጂ እየገደሉና እያስገደሉ "ብፅዕ "ብላችሁ ጥሩኝ ማለት አይደለም።

ማንም ይሁን ማን አባት ነኝ እያለ ዘር እንዲቆጥርብን አንፈቅድለትም። የፖለቲካ ጥማት ያለበት ሰው ቆባችንና መስቀላችንን አስቀምጦ የፖለቲካ ፓርቲ መመሥረት መብቱ ነው ።አባት ነኝ እያለ የዘር ፖለቲካ ማቀንቀን ግን አይችልም።

ትኅትና እህታችን በርቺ አቋምሽ አቋማችን ነው።

@ ኢዮሳፍጥ ጌታቸው
https://t.me/Eyo21e
❤23👍13
😁😁😁ትውልዱ ግን አልተቻለም በደፈናው አባት ብሎ መከተል አቁሟል
❤22😁5
"ይኽን ያህል ሰዎችን አሳስረናል" እያሉ ሪፖርት የሚያቀርቡ ሰዎች ያሉበት ጉደኛቸው ቤተ ክህነት
❤12
"ብር ካለህ በ ቤተ ክህነት ቦታ አለህ"
❤18🤔5😱2👍1👎1
እኛና የ"አዲሲቷ ኢትዮጵያ "ፖለቲከኞች


🔏እኛ ሀገር ስንል፦ የሁሉ ለሁሉ የሆነች  አባቶቻችን ዋጋ ከፍለው ያቆዩልንን ነባር ኢትዮጵያን ነው እነርሱ ሀገር ሲሉ፦የምዕራባውያንና የዐረቦች ዲቃላ የሆነች አዲሲቷን ኢትዮጵያ ነው

🔏እኛ ታሪክ ስንል የ5000ሺህ ዘመን ታሪክ ነው እነርሱ ታሪክ ሲሉ የ150 ዘመን ታሪክ ነው

🔏እኛ ሰው ስንል በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ የተፈጠረን ነው እነርሱ ሰው ሲሉ ዘርን ወይም ቡድንን ነው

🔏እኛ ሕዝብ ስንል መላ ኢትዮጵያውያንን ነው እነርሱ ሕዝብ የሚሉት ግን በቋንቋና በመንደር የተካፈሉትን ብቻ ለይተው ነው

🔏እኛ ሰላም ስንል የሰው ልጅ ሁሉ በማንነቱ በሃይማኖቱ ሳይጠቃ በገዛ ሀገሩ ላይ በሰላም ወጥቶ መግባትን ነግዶ ማትረፍን  አርሶ መብላትን ነው እነርሱ ሰላም ሲሉ ሌላውን እያጠቁና እረፍት እየነሱ ተደንደላቆ መኖርን ነው

🔏እኛ ፖለቲካ ስንል ሀገር የመምራት ጥበብን ነው እነርሱ ፖለቲካ የሚሉት ቁማርን ነው


🔏እኛ እድገት ስንል የሕዝቦችን አጠቃላይ የኑሮ ደረጃ፣ የኢኮኖሚ ጥንካሬ፣ የትምህርትና የጤና ሽፋን እንዲሁም የማህበራዊና የፖለቲካ ተቋማትን አቅም በዘላቂነት ማሻሻልና ማሳደግን ነው እነርሱ እድገት የሚሉት የሚጠሉትን ክፍለ ሕዝብ በእምነቱና በማንነቱ ለይቶ ማፈናቀል ህጋዊ ደሃ ማድረግ ነው
🔏እኛ እኩልነት ስንል ሁሉም ዜጋ በሕግ ፊት አንድ ዓይነት መብትና እድል እንዲኖረው ማድረግን ልዩነቶችን አክብሮ ሰብዓዊ ክብርን እኩል መስጠት ነው እነሱ እኩልነት ሲሉ  ተቃውሞ እንዳይነሳ ሰዎችን ሁሉ "እኩል" አስመስሎ ማደቀቅ/ማስገደድን ነው

🔏 እኛ አካታችነት ስንል የሁሉንም ብሔር፣ ሃይማኖት፣ ጾታና አመለካከት ድምፅ መስማትና በውሳኔ ላይ ማሳተፍ በውይይትና በስምምነት አብሮ መስራትን ነው እነሱ አካታችነት ሲሉ  የይስሙላ (የስም) ውክልና መስጠትን የገዢውን ቡድን ፍላጎት የተቀበሉትን ብቻ በመምረጥ "ሁሉንም አካተናል" የሚል ፕሮፓጋንዳ መስራትን ነው
🔏እኛ ፋትሕ ስንል በሕግ አሠራር ላይ የተመሠረተ የበደለ የሚቀጣበት፣ የተበደለ የሚካስበት እውነተኛ ዳኝነት ፍርድ ቤቶች ገለልተኛ እንዲሆኑ ማድረግን ነው እነሱ ፍትሕ ሲሉ  ተቃዋሚዎችንና ድምጻቸውን የሚያሰሙ ሰዎችን ማጥቂያና ማሰሪያ መሳሪያ ማድረግን  ፍትሕ ማለት የመንግሥትን ፍላጎት ማስፈጸሚያን ነው።

🔏እኛ ሕገ-መንግሥት ስንል የሕዝብና የሀገር ከፍተኛ የቃል ኪዳን ሰነድ፤ የዜጎችን መብት መጠበቂያና የመንግሥትን ሥልጣን ገዳቢ እነሱ ሕገመንግሥት ሲሉ ሥልጣንን ለማራዘሚያና ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ሕጋዊ ሽፋን መስጫ መሳሪያ እንደ አስፈላጊነቱ ለገዢው አካል ይመች ዘንድ የሚቀያየር ሰነድን ነው።

🔏እኛ ሕግ ማስከበር ስንል ሰላምን፣ ደህንነትንና የዜጎችን መብት ከአመፅና ከወንጀል መጠበቅን ነው እነሱ ሕግ ማስከበር ሲሉ ሥልጣንን መቃወምን እንደ ወንጀል በመቁጠር የሚጠሉትን ሕዝብ በኃይልና በሽብር ማንበርከክ የጸጥታ አካላትን ሕዝብን ማሰቃያ ማድረግን ነው

🔏 እኛ መብት ስንል  መብት የመንግሥት ስጦታ ሳይሆን፣ ሰው በመሆን ብቻ የሚገኝ ተፈጥሯዊ ሀብት መሆኑን  የመንግሥት ዋና ተግባር የዜጎችን የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመደራጀት፣ የሕይወትና የንብረት መብት ማስከበርና ጥበቃ ማድረግን፣ መንግሥት የዜጎችን መብት ሲጥስ በሕግ ፊት ተጠያቂ መሆንን ነው እነሱ መብት ሲሉ መብት የተፈጥሮ እና የሰው ልጅ በመሆን ብቻ የሚገኝ ሳይሆን፣ ለገዢዎች በመታዘዝ የሚገዛ ወይም የሚቸር ስጦታ አስመስሎ ማቅረብን የፖለቲካ፣ የሃሳብ እና የፕሬስ ነፃነትን ለመጨቆን እና ጥያቄ የሚጠይቁ ሰዎችን ልማት እና ሰላም የሚቃወሙ አስመስሎ መፈረጅንየገዛ ራሳቸውን ሥልጣን ለመጠበቅ ባወጧቸው ጨቋኝ ህጎች ተጠቅመው የተቃውሞ ድምፆችን ሁሉ "ህገ-ወጥ" በማለት መብትን በሕግ ስም ማፈንን ነው።

🔏እኛ የሀገር ሉዐላዊነት ስንል ሉዓላዊነት የህዝብ   መሆኑን ህዝቡ በነፃነት መምረጥ፣ መናገር እና በሀገሩ ጉዳይ ላይ የመወሰን መብት መከበርን፣እውነተኛ ሉዓላዊነት የሚገነባው ከውስጥ አቅም  ማለትም በጠንካራ ኢኮኖሚ፣ በፍትሃዊ ስርአት፣ በምግብ ራስን በመቻል እና የዜጎች ሙሉ ደኅንነት ማግኘትን ነው እነሱ የሀገሬ ሉዐላዊነት ሲሉ <<እኛ ነን ሀገር>> በሚል እሳቤ፣ እነሱን መቃወም እንደ ሀገር ሉዓላዊነት መድፈር መቁጠርን፣ሉዓላዊነት በወታደራዊ ኀይል፣ በፖሊስ አፈና እና ህዝብን በፍርሃት ጠፍሮ በመያዝን ነው
.
.
.

....የቀረውን እናንተ ቀጥሉበት።

https://t.me/Eyo21e
❤11😁1
Eotc Task Force
https://vt.tiktok.com/ZSg2Jf6uh/
አፋጣኝ የድረሱልኝ መልክት👉❗❗❗❗❗❗👉👂👂👂👂👂
Eotc Task Force pinned a voice message
አልተመሳሰለባችሀም ግን?

ግድሎ መሸለም
አስገድሎም መሸለም

በመመካከላቸው ያለው ልዩነት የቆብና የሱፍ ልዩነት ነው

የቁስ ቤተ መንግሥት
የቁስ ቤተ ክህነት
የቁስ ፖለቲከኞች
የቁስ ጳጳሳት
በሁለቱም ዘንድ ሰው የሚባለው ፍጡር ቦታ የለውም።
❤16🤔2
ኦርቶዶክሳዊው በሀገሩ ላይ«ተገፍቷል»

ኦርቶዶክሳዊው ማኅበረሰብ  በገዛ ሀገሩ ላይ «ተገፍቷል» ስንል፤ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚ እና በባህል መብቶቹን ተነፍጎ፣ በባለቤትነት ስሜት ፋንታ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መቆጠሩን ነው።

የመገፋቱ ማሳያዎች፦

1 ከታሪካዊ መኖሪያው ተፈናቅሏል

ከቀድሞ ጀምሮ ከኖረበት  አከባቢ በጅምላ ተፈናቅሏል

2 የዜግነት መብቶች እኩል አለመከበር

በሕግ ፊት እኩል የመሆን፣ የፍትሕ ጥበቃ የማግኘት፣ በሰላም የመኖርና የመንቀሳቀስ መብቶችን ተነፍጓል።

3 ከፖለቲካዊና ከሕዝባዊ ተሳትፎ መገለል
በአስተዳደር፣ በውሳኔ ሰጪነትና በሕዝባዊ ተቋማት ውስጥ  እንዳይሳተፍ መደረጉ።

4 ለሕይወቱና ለንብረቱ ተመጣጣኝ ጥበቃ አለማግኘቱ

ለጥቃት፣ ለግድያ፣ ለእገታ፣ ለዘረፋ ወይም ለማስፈራራት ተጋላጭ ሆኖ የሕግ ጥበቃ አለማግኘም።

5 ከሀገራዊ ሀብትና ከልማት ዕድሎች መገለል

በሃይማኖቱ ምክንያት የትምህርት፣የ ጤና፣ የሥራ፣ የመሠረተ ልማትና የኢኮኖሚ ዕድሎችን በእኩልነት ማግኘት አልቻለም።

6  ማንነቱን፣ ታሪኩንና ባህሉን ማሳነስ ወይም መካድ

ቋንቋው፣ ባህሉ፣ ሃይማኖቱ፣ ታሪካዊ ቅርሶቹ ወይም በሀገሩ ላይ ያለው ታሪካዊ አስተዋጽኦ በሥርዓት መካዱ ወይም መገፋቱ።
https://t.me/Eyo21e
👍4❤2
😭14❤1👍1
ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ያላችሁ ኦርትዶክሳውያን ምንድን ነው የተፈጠረው?እስኪ መረጃ አድርሱን።
❤9🥰1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአርሲ ዞን ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ልዩ ቦታው መጪቱ ላይ   በ05/02/2019ዓ.ም ሁለት ወንድማማች  ኦርቶዶክሳውያን የሽርኩት አረም እየረጩ ባሉበት ተገድለዋል። ትናንት 06/02/2019ዓ.ም አንድ ኦርቶዶክሳዊ ተገድሏል ።በድምሩ ሦስት(3) ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል የብዙዎች ሀብት ንብረት ተዘርፏል።
😢16❤4
1ቀን ቀራቸው ይፈቱልን ፍትህ

እንዴት ከርመው ይሆን?
በጨለማ ዕስር ቤት 136ቀን የሆናቸው ክቡር አባታችን ቀሲስ መዝገቡ ፍትሕ ለአባታችን

ግንቦት 26የታሰሩት የፍርድቤት ቀጠሮ ጥቅምት 9 ነገ የቀጠሮ ቀኝ

አባታችንን ፍቱልን
🥰15🙏8😢5❤2