Eotc Task Force
7.23K subscribers
1.56K photos
349 videos
12 files
398 links
ወቅታዊ ጉዳይ
Download Telegram
እንዲህ የሚል የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ አለ እንዴ ንገረን እስኪ ወንድማችን። የትኛው ሐዋርያ ነው እንዲህ ያስተማረው? ደግሞስ መቼ ነው አባታዊ ሀላፊነታቸውን የተወጡት ሕይወት አልባ፣ማንገዳይ ማን ተገዳይ እንደሆነ እንኳ የማይለይ መግለጫ ከማውጣት ይልቅ። አሁን ዝም ብሎ በጭፍን መደገፍና መቃወም ሳይሆን ፓትርያርኩ ከተቀሱት 12 ነጥቦች ተግባራዊ የትኛቹን ተግባራዊ እንዳደረጉ መናገር ነው የሚጠበቅብህ። ሚሊየኖች እየተጨፈጨፉና እየተሰደዱ ባሉበት ዘመን ላይ "አባት አትናገር" እያሉ መናገር ራሱ አረመኔነት ነው።በየቀኑ እየተጨፈጨፈ ያለው ቲማቲም ወይም ድንች አይደለም ክርስቶስ ስጋውን የቆረሰለት ደሙን ያፈሰሰለት የሰው ልጅ ነው።
6🤬4👍2😭1
ማውገዝና ገዳም መግባት 

የሲኖዶስ ሥራ ሕንጻ ማነጽ፣ መኪና መግዛት ደሞዝ መጨመር፣ ጳጳስ ማዘዋወር አይደለም። ኹለንተናዊ የካህናትና የማእመናንን ደኽንንነት መጠበቅ ከሚያጠቃቸውም መከላከል ነው። ሲኖዶስ ያስፈለገው ለቤተክርስቲያን ችግር የኾነን ጉዳይ መፍትሔ መስጠት ነው። 

ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ተልእኮ እንጂ የደሞዝ ማስተካከያ ቅያሬ ማስፈጸሙያ የቦዝነስና አስተዳደር ጽ/ቤት አይደለም። የሕንጻ ቤተክርስቲያን መገንባት በቁጥር መብዛት የምእመናንን መብዛት የቤተክርስቲያንን ማደግ አያሳይም። 

ከቅዱስ እስጢፋኖ ሞት እስከ ታላቁ ቆስጠንጢኖስ ድረስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን አልተገነባም። ክርስቲያኖች በዋሻ በዛፍ ስር በየቋጥኙ በየግለሰብ ቤት ተደብቀው ነው ይኖሩ የነበሩት። ነገር ግን የሚያምኑ ክርስቲያኖች ቁጥር ይጨምር ዋሻዎቹ እየሞሉ በየከተማው ዐዳዲስ የአማንያን መሰብሰቦያ ይፈጠሩ ነበር። 
ከበሮ መደለቅ ማህሌት መቆም ሕንጻ ማነጽ ሰበካ ጉባኤ ማደራጀት አልነበረም። ዋና ሥራቸው ክርስቲያኑን በወንጌል ማጽናት ያላመነውን ማስመን ያመነውን አስተምሮ ማጥመቅ ማቁረብ ሕይወቱን ከዓለም ለይቶ ራሱን ለሰማዕትነት እንዲያዘጋጅ ማብቃት ነው። ይኽ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በስፋት የመዘገበው እውነታ ነው። 

 የቀደመችውን ቤተክርስቲያን ስናስብ ቤተክርስቲያን የመሩ ሊቃነ ጳጳሳት ስናይ ከዛሬዋ ቤተክርስቲያን ጋር ስናስተያይ ዓለማዊነት የበላት ቤተክርስቲያን ኾናለች። የጥንቱ አማኝ ከዓለም ወደ ቤተክርስቲያን ይመጣ ነበር። ዛሬ ካህናቱም ምእመኑም ቤተክርስቲያንን ዓለም አድርጓታል።

ሲኖዶሱ ይኽንን አማኙን የሚጨርሰውን አስቦ አቅዶ የሚያጠፋውን መንግሥት መግደል ማፍረስ አቁም ብሎ ማሳሰብ ማስጠንቀቅ ከዚያም ማውገዝና ምእመናን ሃገራችሁን ቤተክርስቲያንን በያላችሁበት ጠብቁ ብሎ በየሃገረ ስብከቱ ወደ አገልግሎት መግባት ነበረበት። 

እነርሱ ከመንግሥት ጋር ተግባብቶ መሥራት ያስፈልጋል እያሉ ሃገር አልባ ቤተክርስቲያን አልባ እያደረጉን ነው። በየአጥቦያው ካህናቱ ጉዳዩን ከምእመኖቻቸው ጋር አንሥተው አይመክሩም። በየዱር ለሚወድቁት ምንም ማድረግ አይፈልጉም። ካህናቱ የየአጥቢያው ወር ኀዊ ገቢ ነው የሚያሳስባቸው። ሞርጌጅ ፣ ዐዲስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ነው ዋና አጀንዳቸው። 

አብይን ያወገዙ አቡነ ሉቃስ ዛሬ የሚሄዱበት ቤተክርስቲያን አጥተው ቤታቸው ተቀምጠዋል። ቤተክርስቲያን እንዳይደርሱ ያደረጋቸው ደግሞ ሊቀ ጳጳሱ ፣ ካህናቱ ምእመናኑ ናቸው። በየደረጃቸው።

ምእመኑንም ለምን ብሎ አይጠይቅም፣ ካህኑም እንዴት ብሎ አያሳስብም። ተያይዞ ማለቅ ማለት ይኽ ነው። ማሰብ ያልጀመረ ሕዝብ አያሸንፍም። 

ንዋይ ካሳሁን
9
ቤቱ ልማዱ ነው

ፋሽስት ጣልያንን ካህናትን ሰብስቦ ከበሮ እያደበደበ ግራዚያኒን ዐዲስ አበባ አቀባበል ያደረገው በአቡነ አብርሃም ባንዳነት ቤተክህነት መኾኑን ታውቁ ኖሯል?

በዚኽ ድርጊት ተስፋ የቆረጡ የተቆጩ አርበኞች እነ አበበ አረጋዊ እነ በላይ ዘለቀ ወደየጫካቸው ገብተው መፋለም የጀመሩት።
😱6
የ፳፩ ዓመት የቤተ ክርስቲያን ሸክም
8👎2
እናንተስ ምን ትላላችሁ?
👍34😭3🥱1
"አርሲ የእኛ ናት?" "አርሲን ኬኛ?"

ዛሬ አርሲ ላይ ሙስሊሞቹ የሸዋ አማራና የሸዋ ኦሮሞ ኦርቶዶክሱን በጅምላ የሚያርዱትና የሚያፈናቅሉት መሬቱ የእኛ ነው  ብለው ነው።እውነታው ግን እነርሱ እንደሚሉት አይደለም።አርሲ የሙስሊሞቹም የሸዋ አማራና የሸዋ ኦሮሞ ኦርቶዶክሶችም አይደለችም።የሀዲያ ናት።ያው አሁን እሆነ እንዳለው አብዛኞቹ ተውጠው ግማሾቹ ደግሞ ተሰደው ነው የወጡት።እስካሁን ድረስ በአንዳንድ አከባቢዎች ላይ ሀዲያዎች አሉ።

"አርሲን ኬኛ " እያሉ ኦርቶዶክሳውያንን ማረድና ማፈናቀል አያዋጣም።እናንተም በወረራ ነው የያዛችሁት ኦርቶዶክሱም  በሰፋራ የመጣ ነው።የሚያዋጣው ተከባብሮ መኖር  ብቻ ነው። እናንተ ባለሀገር እኛ እንደመጤ የምንቆጠርበት አንድም ምክንያት የለም። እውነታው ልንገራችሁ ብዬ ነው።
20
እንዲህ የምታደርጉ ሰዎች ጤናኞች ናችሁ ግን ?
5
በተደጋጋሚ ተናግረናል በኦሮሚያ ያላችሁ ኦርቶዶክሳውያን ጥንቃቄ አድርጉ ። ይኽ ሰውዬ እንደ ከዚህ በፊቱ ብዙ ክርስቲያኖችን ለማስጨፍጨፍ እየሠራ ይገኛል።ከዚህ በፊት ያደረገውን እንተወውና ሰሞኑን ብቻ በወለጋ መነኮሳት፣ካህናት፣አዛውንቶችና እና ህጻናት እንዲጨፈጨፉ አቢያተ ክርስቲያናት እንዲወድሙ አድርጓል።አሁን የቀረው አርሲ ነው።በተደጋጋሚ አርሲ ላይ " ፋኖ አለ"የሚል የሐሰት መረጃዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል አሁንም እንደቀጠለበት ነው።ይኽ ብቻ አይደለም "አርሲ ላይ ኦርቶዶክሱ ተደራጅቶ ራሱን እየተከላከለ ነው"የሚሉ ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲሰራጩ እየተደረገ ነው።ሰሞኑን ከአሰኮ ወረዳ ሲናፈሱ የነበሩ ወሬዎች ለዚሁ ዓለማ የወጡ ናቸው።ኦርቶዶክሱ ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ለመፈጸም ለምን ተብለው ሲጠየቁ "ፋኖ ናቸው ተደራጅነው እየተዋጉን ነው" የሚል ማስተባበያ ለመስጠት እንዲያመቻቸው ነው። ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
43
በሁላችንም ልብ ውስጥ የማይረሳ ክፉ ታሪክ፣ የማይፈርስ ጽኑ ሐውልት ነው። የእኒህ መናኝ ካህን ሞት የብዙ ካህናትን ሞት የሚተረጉም፣ የምእመናንን እልቂት የሚመሠክር ነው።
ዓለም ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን የሚሆን ጆሮ እንደሌላት ከገባን ቆይቷል። ምእመኑ ቢያልቅ፣ ካህናት በየቦታው ቢረግፉ፣ ታቦት ከመንበሩ ቢሰደድ፣ አድባራት ቢጋዩ፣ ገዳማት ምድረ በዳ ቢሆኑ ጆሮውንም የሰብአዊነት ልቡንም የሚሰጠን አካል እንደሌለ እናውቀዋለን።
ያለን መፍትሔ አንድ ብቻ ነው። እርሱም ራስን አጠንክሮ፣ አንድነትን ገንዘብ አድርጎ፣ ትቢያ ልሶ መነሳት ብቻ። ይህንን እሥራኤላውያን አድርገውታል። እኛም እንችላለን።

በቴሌግራም ቻናሌ ያግኙኝ
👇
https://t.me/mezgebesemay

ዲ/ን ታደለ ሲሳይ
279
እየሆነ ያለውን በአግባቡ የተረዳ  አንድ ኦሮሚኛ ተናጋሪ ወንድማችን አሳቡን እንደሚከተለው አቅርቧል

   ንቁ!!!

"ሸኔ ቤተክርስቲያን ውስጥ ምን ፍለጋ ነው የገባችው? ሲጠሉህ እምነትህን እና እሴትህን (ባህልህን) ያዋርዳሉ። .አንተን እየጠሉ መሬትህን መፈለግ አይሠራም።የሸኔ ትግል መሬታችንን ከሰዎቻችን እና ከሃይማኖታችን ከባህላችን የማፅዳት ሥራ ከመሥራት ውጭ ሌላ ዓላማ የለውም። እስከ አሁን ድረስ የፕሮቴስታትቶች ቸርች አልገቡም፣ ወደ መስጊድ አልገቡም የእኛን ቤተ ክርስቲያን ግን ገብተው እያረከሱ ነው። ሕዝባችን ደግሞ ከ90% በላይ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው። ይህ በምድር ላይ ያለ እውነታ ነው። 😡 ሕዝባችን ንቃ፣ ራስህን እወቅ። ራስህን አድን። ጠላት ሁሉንተናህን  ለማጥፋት መጥቷል"።

ወንድማችን እውነታውን ነገር ነው የነገረን።ሸኔ ጨካ ከገባበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ አንድም መስጊድ አላቃጠለም፣አንድም የጴንጤ ቸርች አላቃጠለም፣አንድም የዋቄፋና ማምለኪያ ቤት አላቃጠለም።የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ግን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እያቃጠሉ እያፈረሱ ማፍረስ ያልቻሉትን ደግሞ በውስጡ እየተጸዳዱ ነው።ለምን ኦርቶዶክስን ዒላማ አደረጉ ካልን ሥሪታቸውም ኦርቶዶክስ ጠል ስለሆነ።የዘር ፖለቲካ የመሠረቱትም ጫካ  የጉቡትም  እርስዋን ለማጥፋት ነው።በኦነግ   ፖለቲካ ውስጥ ሦስት የእምነት አክራሪዎች አሉ፦

፩   ስድስት 6 ሚሊየን አይሁዶችን ዘር ያጠፉ የጀርመን ሚሽነሪዎች በወለጋ ጊምቢ  የመሠረቱት ጽንፈኛ ፕሮቴስታንቶች(Nazi Type Of Protestatisim)

፪ አክራሪ እስልምና።ሁለት ዓይነት ነው። የግራኝ አሕመድን ታሪክ ለመድገም የሚቋምጥ ሲሆን ሌለኛው  የአልሸባብ፣የአይኤስ፣የቦኮሃራምና የአልቃይዳን ርዕዮተዓለም የሚያቀነቅን ነው።

፫   የዋቄፋና እምነት ተከታይ፦ከ16መክዘ ጀምሮ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ሲያወድም ርስቶችዋን ሲወር አማኞችዋን ሲያርድ የነበረ ዛሬም ኢትዮጵያን ወደዚያ መንፈስ መመለስ የሚፈልግ ነው።

እነዚህ ሦስቱ እርሰበርሳቸው በፍጹም አይስማሙም ኦርቶዶክስን በማጥፋት ግን ይስማማሉ።
👍215
ታስረዋል
መምህረ ሞገስ ሁኒያለው
ነሐሴ 22 ትላንትና አርብ የታሰሩ ሲሆን የታሰሩበት ምክንያት በፁፍ ባላቸው ሶሻል ሚዲያ ሁሉ በሚያገኙበት አጋጣሚ ለአርሲ ድምፅ ስለሆኑ ብቻ ነው ፍትህ ለመምህራችን

በሚዲያ ስማቸው
ጠፈር ሚዲያ

ለአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ድምፅ መሆን ወንጀል አይደለም
31👍18😢14
እንዲህ ዓይነት አሳቦች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው።"አባት አትናገር" ለሚሉ አላዋቂዎች ጆሮ መስጠት አያስፈልግም።
😢19🙏5
ሰማዕታትን እንዘክር

ቄስ ንጉሤ ወልደመድኅን ይባላሉ። የኦርቶዶክሳውያን መታረጃ ቄራ በሆነችው በአርሲ ዞን ሮቤ ዲደዓ  ወረዳ ልክ የዛሬ ዓመት ነሐሴ 24/2017ዓ.ም በአክራሪ የኦሮሞ ኢስላም ታጣቂዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ። ቄስ ንጉሤ  የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ፣ በሃይማኖታቸው ጠንካራ ፣ ለኦርቶዶክሳውያን ሁሉ የሚራሩ ደግና ትኁት አባት እንደ ነበሩ የአከባቢው ነዋሪዎች ይመሰክራሉ።
😭173🙏3😢1