Eotc Task Force
7.23K subscribers
1.56K photos
349 videos
12 files
397 links
ወቅታዊ ጉዳይ
Download Telegram
የኦርቶዶክሳዊ ሀገሩ የት ነው?

ጥያቄው የጅል ጥያቄ ይመስላል አይደል? አዎ ነው። ግን መልሱ እንደ ገደል የራቀ ነው። የመጣልን አልያ የሚመስለንን መመለስ መልስ ስለማይኾን ነው። መልሱን ለማግኘት ተግባሩን መከተል አግባብ ነው። 

ኢትዮጵያ የኦርቶዶክሳዊነት ሃገር ናት። መሠረቷ የሕይወት ፍልስፍናዋ ተዋሕዶአዊነት ነው። ተከፍሎ ወይም ምንታዌነት የአውሮፓውያን የጥፋት ዘር በቅሎብን ነው። ሥጋና ነፍስን መነጣጠል፣ ሃይማኖትና ፓለቲካን ነጣጥሎ ማየት የኖረ ሳይኾን እንድንጠፋ የተዘራብን ነው። ሃገሩ የእኔ ነው። እኔ የዚኽ ሀገር ዜጋ ነኝ ካልክ በኋላ ፓለቲካው ግን አይመለከተኝም ካልኽ ደንቁረሃል ማለት ነው። ኑሮው መኖሪያው፣ መማሪያው ማምለኪያ ቦታው፣ ሥራው አይመለከተኝም ማለትኽ ነው። በጥቅሉ በገዛ እጅኽ ሃገሩን አስረክበሃል ማለት ነው። 

ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ የኦርቶዶክሳዊ ሀገሩ የት ነው? ራሱ ኦርቶዶክሳዊው ስለ ሀገሩ የሚያስበው በጠላት የማሰቢያ መነጽርነት ነው። አንገቱ እየተቀላ በጥይት እየተደበደበ የሚሞተው ሃገርኽ አይደለም ቦታኽ አይደለኽም። ወራሪ ነኽ ሰፋሪ ነኽ እየተባለ ነው። ምድሪቱ ሀገሩቱ የእርሱ ኾና ሳለ በደምና አጥንት ቆጠራ መሬት ለክተው አንተ ከዚኽ ቦታ አይደለኽም ብለው ይገሉሃል። 

ይኽንን ይዘን የጀርባ ሥነ ልቡናዊ የጥፋት ውቅሩንም እንየው።

በኦርቶዶክሳዊ መረዳት ሀገሩ የተከፋፈለው በሃገረ ስብከት እንጂ በብሔር አይደለም። ለዚኽ ነው ሃገረ ስብከት የምንለው። ስለዚኽ ፓለቲካው ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ፣… ቢል ቤተ ክርስቲያን ይኽንን የምታውቀው በክልል ሳይኾን በሃገረ ስብከትነት ነው። ለስብከት የተከለለ ማለት ነው። አንድ ጳጳስ ለወንጌል ማዳረስ ይረዳው ዘንድ የተክልለለ ቦታ ወይም ሃገር ማለት ነው። ሃገረ ስብከት ዋና ዓላማው ለነስበክ ነው። 

ኾኖም ግን የጠላት ወጥመድ ውስጥ ገብተን በትውልድ ስፍራ ላይ ጳጳስ መመደብ ጀመርን። ጎንደሬ ጎንደር፣ ሸዌ ሸዋ፣ ኦሮሞ ኦሮሚያ፣ ትግሬ ትግራይ ላይ። ይኽ አጥንትና ደም ቆጣሪ የዳርዊን ትምህርት እንጂ የኦርቶዶክሳዊ ትምህርት አይደለም። ለእኛ ክህደት ጭምር ነው። 

የጎሳ አከላለል እውቀትም እውነትም የለውም። ትውልድን ሃገርን ከመበተን ውጭ ስሜትከመፍጠር ሌላ ሙያ የለውም። የተዋሐደውን በተነው። 
ዘጠኙ ቅዱሳን ኢትዮጵያ ሃገረ ስብከታቸው ናት። ለአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ኢትዮጵያ ሀገረ ስብከታቸው ናት። ከደምና አጥንት ጋር አይያያዘም። እጨጌ እንባቆም ደብረ ሊባኖስ ሃገረ ስብከታቸው ናት። ኹሉም ፍሬ አፈሩበት። 

የእኛ ጳጳሳት ወደ ሰፈራቸው የገቡት በምን ምክንያት ነው። ለስብከት ወይስ ለወንጀል መሸፈኛቸው? በደምና አጥንት ቆጠራ የተደበቁት ለስብከት ወይስ የፓለቲካ መስፈርት? 

ዛሬ ኦርቶዶክሳዊ ኢትዮጵያ ውስጥ ሀገር የለውም። መጤ ኾኗል። ወለጋ፣  ቤኒሻንጉል፣ ኦሮሚያ፣ ሐረር፣ ሶማሌ የሱ ሃገር አይደለም ተብሏል። ሃገረ ስብከት አለኝ የሚል ሲኖዶስ የሃገረ ስብከት ሉቀ ጳጳስ የስብከት ሃገሩን ወደ ጎሳ ክልል ሰጥቶ መንጎቹ ሲያልቁ ዝም ይላል። 
በወለጋ በአርሲ የሚያልቁት ካህናት ምእመና ሃገረ ስብከታቸው ነው።

ኦርቶዶክሳዊ የሚኖረው በስብከት ሃገሩ ነው። ለዚኽ ነው ቤተ ክርስቲያን በኖረበት የሚተክለው። ዛሬ ግን ካለበት እየተነቀለ እንደ በግ እየታረደ የሚኖረው። 

ይኽንን የሚያይ ጳጳስ ፣ ቄስ፣ ምእመናን ደግሞ በግድ የለሽነት እያዩ እየሰሙ ዝም ብለዋል። እንደ ሩቅ አካል ቆጥረዋቸዋል። ሕመማቸው አይሰማቸውም። ጳጳሱም የስብከት ሃገሩ ሳትኾን የሳንቲም ሃገሩ አድርጓታል። ወደ ስብከት ሃገራችን እንመለስ። ቋንቋ መግባቢያ እንጂ ሃገር አይደለም። በሃገር መሞት እንዲያበቃ ሃገር የነጠቀንን መታገል ብቸኛው ምርጫ ነው። እመኑ የሰው ልጅ የማይተርፍባት የእልቂት ሃገር ከፊታን አለች። መኝታው በዝቷል፣ መዝለሉ ለንግሥ መደለቁ፣ ሕንጻ ግንባታው ቆሞ ስለ ሕዝብ ማትረፍ ብቻ እናስብ። 

ንዋይ ካሳሁን
23
ኦርቶዶክሱ ራሱን ለመከላከል ወስኖ ያልተነሳው " እነ እንትና እየተዋጉ ነው ከጥቂት ጊዜ በኋላ መጥተው ነጻ ያወጡናል"የሚል የተሳሳተ አሳብ ውስጥ ስለተዘፈቀነው።እኛ ቁጭ ብለን ኑሮአችንን እየቀጨን ሌላው ሞቶ ነጻ እንዲያወጣን እንፈልጋለን።ይኽ ድንቁርና ነው። ነጻ አውጪ በመጠባበቅ የሚቆም መከራ የለም እንደውም የከፋ መከራ ነው ከፊታችን ያለው።
36👍2🔥1🥰1
የጥቁር ናዚዎች ጭካኔ
😢361
የመነኮሳት ፍጅት በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በአጭሩ

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ፣ መነኮሳትና ካህናት አባቶች በብዛት የተገደሉባቸውና መከራ የተቀበሉባቸው በርካታ ዘመናት አልፈዋል። ከእነዚህም መካከል በታሪክ ጎልተው የሚታወሱት ዋነኞቹ የመነኮሳት ፍጅቶች የሚከተሉት ናቸው።

1) በግራኝ አሕመድ ዘመን በ16ኛው ክፍለ ዘመን ከ1529 እስከ 1543 ዓ.እ በነበረው ጦርነት ወቅት፣ በግራኝ በሚመራው ሠራዊት እንደ ደብረ ሊባኖስና መሰል ታሪካዊ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ወድመዋል። በወቅቱም በገዳማቱ ውስጥ የነበሩ በርካታ መነኮሳትና ሊቃውንት ለሃይማኖታቸው ሲሉ ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።

2) በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ዘመን የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት እልቂት የሚጠቀስ ታሪክ ነው። ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በመነኮሳት ላይ የተፈጸመው እጅግ ዘግናኝና የጅምላ ጭፍጨፋ ነው። ድርጊቱ የተፈጸመው ግንቦት 12 ቀን 1929 ዓ.ም ነበር። በጣሊያኑ እንደራሴ ግራዚያኒ በተወረወረበት የቦምብ ፍንዳታ ምክንያት ለመበቀል ባስተላለፈው ትእዛዝ መሠረት፣ በገዳሙ የነበሩ ብዙ መነኮሳት፣ ዲያቆናትና ንጹሐን ምእመናን በሠራዊቱ ተከበው በግፍ ተፈጅተዋል።

3) በቅርብ ዓመታት በመነኮሳት ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች መጥቀስ ይገባል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በንጹሐን መነኮሳት ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት እጅግ ዘግናኝ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል በሚገኘው በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ከአራት በላይ መነኮሳት በታጣቂዎች መገደላቸው ይታወሳል። በሌሎችም ቦታዎች ተመሳሳይ ጥቃቶች ደርሰዋል።

በምስሉ ላይ የሚታዩት የ85 ዓመቱ አዛውንት አባ አየለ አረጋ እና እማሆይ እስከዳር ገላው ይባላሉ። ሁለቱ መነኮሳት ከቀናት በፊት በወለጋ አካባቢ፣ ልክ እንደ ፋሺስት ጣሊያንና እንደ ግራኝ አሕመድ ሠራዊት ጨካኝ በሆኑ አረመኔዎች የተገደሉ ናቸው።

ዲ/ን ዬሴፍ ፍስሐ
13
እኚህ  አባት  የትኛው ሀገር ፓትርያርክ ናቸው?

  እስኪ የምታወቋቸው ንገሩኝ እኚህ አባት የ የትኛው ሀገር ፓትርያርክ ናቸው? የ አርመን? የሶሪያ?የ ህንድ? የኮፕቲክ?የኤርትራ?


መቼም የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ናቸው አትሉኝም? የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ቢሆኑ ኖሮ ፦

1)በሕገ-መንግሥት፣ በፖለቲካ ማኒፌስቶ፣ በመደበኛ ትምህርት፣በእምነት ተቋማት፣በ ባህል መሪዎች በሚዲያና መሰል መንገዶች ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮን ኦርቶዶክሳዊያንን ለጥቃት የሚጋልጡ መልዕክቶችን ሲተላለፉ ያስቆሙ ነበር

2) በኦርቶዶክሳዊያን ላይ ያነጣጠሩ የአካል፣ የሥነ-ልቦና፣ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ የፖለቲካ፣ የማፈናቀል፣ ከአገራዊ ተሳትፎ የመገለልና የፍጅት ጥቃቶችሲፈጸሙ ያስቆሙነበር

3) ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን  በቋንቋና በተለያዩ ዘውጎች   መከፋፈል የ ፖለቲካዊ ሸፍጥን፣ በጥናትና በምርምር ስም የሚደረጉ የመከፋፈል ዘመቻዎችን ያስቆሙ ነበር በዚህ የተሳተፉ   ጳጳሳትንም ሆነ ምዕመናን አውግዘው ከ ቤተ ክርስቲያን ይለዩአቸው ነበር

4) ኦርቶዶክሳውያን የሚበዙባቸው አከባቢዎች ሆን ተብሎ ታስቦበትና ታቅዶበት ከኢስላም ሀገራት ድጋፍ ሰጪነት  በህግ ማስከበር ሽፋን በጦርነት እንዲደቁ ሲደረጉ ለምን ብለው ይጠይቁ ሥርዐቱን ያወግዙ ነበር

5) ሥርዐቱ ከኦርቶዶክስ የጸዳች  አዲስ ሀገር ለመፍጠር ጨራቃ ቤት፣የወንዝ ዳር ልማት ፣የከተማ ኮሪደር ልማት፣የገጠር ኮሪደር ልማት ወዘተ... እያለ ቤታቸውን ሲያፈራርስ ከርስት ጉልታቸው አፈናቅሎ ኦርቶዶክሳውያንን ሀገር አልባ ሲያደርጋቸው ያስቆሙ ነበር

6) "ሀገራዊ ምክክር"በሚል ሽፋን ኦርቶዶክሳዊ አሻራዎች፣ዕሴቶች፣ምልክቶና ታሪኮች ሲደመሰሱ ዝም ብለው አይመለከቱም ነበር
7  ሥርዐቱ   "ገዳማትና አቢያተ ክርስቲያናት የሽፍቶች መሠልጠኛ ምሽጎች ናቸው"የሚል የማጥቂያና የማጥፊያ ኮድ ለጥፎ መነኮሳት፣ካህናትንና የአብነት ተማሪዎችን በጅምላ ሲረሽን ገዳማቱንና አቢያተ ክርስቲያናቱንም ሲያወድም ለምን? ብለው ይቆጡ ነበር

8) ኦርቶዶክሳውያን ለ ገዳይ ሥርዐት እንዳይገዙ ራሳቸውንና ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ  ጥሪ ያቀርቡ ነበር

9) ኦርቶዶክሳውያንን መጠበቅ ያልቻሉ ጳጳሳትና ካህናት ላይ ኖላዊ እርምጃ ይወስዱባቸው ነበር

10 ኦርቶዶክሳውያን ስምንት ዓመት ሙሉ 'ኧረ  የአባት ያለህ ልናልቅ ነው ልንታረድ ነው ድረሱልን"እያሉ ሲጮኹ አንድም ቀን እንኳ ቢሆን ይራሩላቸው ነበር

11) በኢትዮጵያ ምድር ሃይማኖትንና ማንነትን መሠረት ያደረገ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመ መሆኑን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፣ለአኃት አቢያተ ክርስቲያናት፣ለዓለም አቀፍ  የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ለተባበሩት መንሥታት ድርጅት፣ለዓለም ሀገራት መሪዎች ወዘተ...ደብዳቤ በመጽፍ ያሳውቁ ነበር

12) ቁጥር 11 ላይ የተጠቀሰውን ተግባራዊ ማድረግ ካልቻሉ  "ሕዝቤን አላስጨርስም" ብለው ወደ ገዳም ይገቡ ነበር

https://t.me/Eyo21e
9👍2👎1
እንዲህ የሚል የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ አለ እንዴ ንገረን እስኪ ወንድማችን። የትኛው ሐዋርያ ነው እንዲህ ያስተማረው? ደግሞስ መቼ ነው አባታዊ ሀላፊነታቸውን የተወጡት ሕይወት አልባ፣ማንገዳይ ማን ተገዳይ እንደሆነ እንኳ የማይለይ መግለጫ ከማውጣት ይልቅ። አሁን ዝም ብሎ በጭፍን መደገፍና መቃወም ሳይሆን ፓትርያርኩ ከተቀሱት 12 ነጥቦች ተግባራዊ የትኛቹን ተግባራዊ እንዳደረጉ መናገር ነው የሚጠበቅብህ። ሚሊየኖች እየተጨፈጨፉና እየተሰደዱ ባሉበት ዘመን ላይ "አባት አትናገር" እያሉ መናገር ራሱ አረመኔነት ነው።በየቀኑ እየተጨፈጨፈ ያለው ቲማቲም ወይም ድንች አይደለም ክርስቶስ ስጋውን የቆረሰለት ደሙን ያፈሰሰለት የሰው ልጅ ነው።
6🤬4👍2😭1
ማውገዝና ገዳም መግባት 

የሲኖዶስ ሥራ ሕንጻ ማነጽ፣ መኪና መግዛት ደሞዝ መጨመር፣ ጳጳስ ማዘዋወር አይደለም። ኹለንተናዊ የካህናትና የማእመናንን ደኽንንነት መጠበቅ ከሚያጠቃቸውም መከላከል ነው። ሲኖዶስ ያስፈለገው ለቤተክርስቲያን ችግር የኾነን ጉዳይ መፍትሔ መስጠት ነው። 

ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ተልእኮ እንጂ የደሞዝ ማስተካከያ ቅያሬ ማስፈጸሙያ የቦዝነስና አስተዳደር ጽ/ቤት አይደለም። የሕንጻ ቤተክርስቲያን መገንባት በቁጥር መብዛት የምእመናንን መብዛት የቤተክርስቲያንን ማደግ አያሳይም። 

ከቅዱስ እስጢፋኖ ሞት እስከ ታላቁ ቆስጠንጢኖስ ድረስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን አልተገነባም። ክርስቲያኖች በዋሻ በዛፍ ስር በየቋጥኙ በየግለሰብ ቤት ተደብቀው ነው ይኖሩ የነበሩት። ነገር ግን የሚያምኑ ክርስቲያኖች ቁጥር ይጨምር ዋሻዎቹ እየሞሉ በየከተማው ዐዳዲስ የአማንያን መሰብሰቦያ ይፈጠሩ ነበር። 
ከበሮ መደለቅ ማህሌት መቆም ሕንጻ ማነጽ ሰበካ ጉባኤ ማደራጀት አልነበረም። ዋና ሥራቸው ክርስቲያኑን በወንጌል ማጽናት ያላመነውን ማስመን ያመነውን አስተምሮ ማጥመቅ ማቁረብ ሕይወቱን ከዓለም ለይቶ ራሱን ለሰማዕትነት እንዲያዘጋጅ ማብቃት ነው። ይኽ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በስፋት የመዘገበው እውነታ ነው። 

 የቀደመችውን ቤተክርስቲያን ስናስብ ቤተክርስቲያን የመሩ ሊቃነ ጳጳሳት ስናይ ከዛሬዋ ቤተክርስቲያን ጋር ስናስተያይ ዓለማዊነት የበላት ቤተክርስቲያን ኾናለች። የጥንቱ አማኝ ከዓለም ወደ ቤተክርስቲያን ይመጣ ነበር። ዛሬ ካህናቱም ምእመኑም ቤተክርስቲያንን ዓለም አድርጓታል።

ሲኖዶሱ ይኽንን አማኙን የሚጨርሰውን አስቦ አቅዶ የሚያጠፋውን መንግሥት መግደል ማፍረስ አቁም ብሎ ማሳሰብ ማስጠንቀቅ ከዚያም ማውገዝና ምእመናን ሃገራችሁን ቤተክርስቲያንን በያላችሁበት ጠብቁ ብሎ በየሃገረ ስብከቱ ወደ አገልግሎት መግባት ነበረበት። 

እነርሱ ከመንግሥት ጋር ተግባብቶ መሥራት ያስፈልጋል እያሉ ሃገር አልባ ቤተክርስቲያን አልባ እያደረጉን ነው። በየአጥቦያው ካህናቱ ጉዳዩን ከምእመኖቻቸው ጋር አንሥተው አይመክሩም። በየዱር ለሚወድቁት ምንም ማድረግ አይፈልጉም። ካህናቱ የየአጥቢያው ወር ኀዊ ገቢ ነው የሚያሳስባቸው። ሞርጌጅ ፣ ዐዲስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ነው ዋና አጀንዳቸው። 

አብይን ያወገዙ አቡነ ሉቃስ ዛሬ የሚሄዱበት ቤተክርስቲያን አጥተው ቤታቸው ተቀምጠዋል። ቤተክርስቲያን እንዳይደርሱ ያደረጋቸው ደግሞ ሊቀ ጳጳሱ ፣ ካህናቱ ምእመናኑ ናቸው። በየደረጃቸው።

ምእመኑንም ለምን ብሎ አይጠይቅም፣ ካህኑም እንዴት ብሎ አያሳስብም። ተያይዞ ማለቅ ማለት ይኽ ነው። ማሰብ ያልጀመረ ሕዝብ አያሸንፍም። 

ንዋይ ካሳሁን
9
ቤቱ ልማዱ ነው

ፋሽስት ጣልያንን ካህናትን ሰብስቦ ከበሮ እያደበደበ ግራዚያኒን ዐዲስ አበባ አቀባበል ያደረገው በአቡነ አብርሃም ባንዳነት ቤተክህነት መኾኑን ታውቁ ኖሯል?

በዚኽ ድርጊት ተስፋ የቆረጡ የተቆጩ አርበኞች እነ አበበ አረጋዊ እነ በላይ ዘለቀ ወደየጫካቸው ገብተው መፋለም የጀመሩት።
😱6
የ፳፩ ዓመት የቤተ ክርስቲያን ሸክም
8👎2