Eotc Task Force
7.23K subscribers
1.56K photos
349 videos
12 files
397 links
ወቅታዊ ጉዳይ
Download Telegram
ቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት ተፈጸመ

በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ጀዊ ዋጬ ቀበሌ ትናንት 19/12/2018ዓ.ም የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በአክራሪ የእስልምና ታጣቂዎች ጥቃት ተፈጽሞታል።ታጣቂዎቹ የቤተ ክርስቲያኑን በር ሰብሮ በመግባት በውስጡ ያሉትን ንዋያተ ቅዱሳት ከዘረፉ በኋላ በውስጡ ተጸዳድተዋል።ይህ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ዓይነት ጥቃት ሲፈጸምበት ለሁለተኛ ጊዜው ነው።በወርኃ የካቲት ላይ ሰብረው ገብተው በውስጡ ከጨፈሩ በኋላ ተጸዳድተውበት ነበር ወጥተው የሄዱት። አከባቢው ሙሉ በሙሉ ከኦርቶዶክስ ጸድቷል።እዚሁ ቀበሌ ላይ ከወርኃ የካቲት ጀምሮ በተፈጸመ ጥቃት 32 ኦርቶዶክሳውያን የተገደሉ ሲሆን 50 ቤቶች ተቃጥለዋል ከ40 በላይ የሚሆኑት ፈራርሰዋል ከ2000 በላይ የሚሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ተሰደዋል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለ በሚታና ሰኬ  ቀበሌ ኦርቶዶክሳውያኑ ሙሉ በሙሉ የተሰደዱ ሲሆኑ የእርሻ መሬታቸው በሙስሊሞች ተወርሷል።በሚታና ጋዶ ቀበሌ ከመስከረም ጀምሮ የተሰደዱት ወደ 2000 የሚጠጉ ኦርቶዶክሳውያን እስካሁን ወደ ቦታቸው እንዳልተመለሱ ከቦታው የደረሱ መረጃዎች ያመላክታሉ።

በዚሁ ወረዳ በ13/12/2018ዓ.ም የደብረ ታቦርን በዓል አክብረው ሲመለሱ   አካላቸው በሜንጫ የተቆራረጠ ኦርቶዶክሳውያን  ወደ ዞኑ ከተማ ሪፈር ቢጻፍላቸውም የከፋ ጉዳት ስለደረሰባቸው ከፍተኛ  የህክምና ወጪ ተጠይቀው ለመክፈል መቸገራቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል።

በዚህ ተጠያቂው ማን ነው?

፩ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ፈዴራል ድረስ ያለው የሥርዐቱ መዋቅር
፪ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ፣ጠቅላይ ቤተ ክህነት እና ፓትርያርኩ
፫ መጅሊስ
፬ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
፭ የሲቪክ ማኅበራት

ፎቶና ቪድ፦በጃዊ ዋጬ ቀበሌ የተቃጠለ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የእህል መጋዘንና የኦርቶዶክሳውያን ቤት
4😱3🤬2
🔥6
2
The Church Attacked By Muslim Militiants

Yesterday, on 19/12/2018 E.C., Abune Gebre Menfes Kidus Church in Jawi Wache Kebele, Shirka Woreda, Arsi Zone, was attacked by extremist Islamic militants. The militants broke down the church door, looted the sacred relics inside, and then defiled the premises. This is the second time this church has suffered such an attack. In the month of February, they broke in, danced inside, defiled it, and left. The area has been completely cleared of Orthodox Christians. In this same kebele, attacks since the month of February have resulted in the killing of 32 Orthodox Christians, 50 houses burned down, over 40 destroyed, and more than 2,000 Orthodox Christians displaced.
Meanwhile, in Mitana Seke Kebele, the Orthodox Christians have been completely displaced, and their farmland has been seized by Muslims. Reports coming from Mitana Gado Kebele indicate that around 2,000 Orthodox Christians who were displaced since Meskerem have not yet returned to their land.
In the same woreda, on 13/12/2018 E.C., Orthodox Christians returning from celebrating the Debre Tabor festival were attacked with machetes, severing their limbs. Although they were referred to the zonal city hospital, eye-witnesses reported that due to the severity of their injuries, high medical expenses were requested, which they are struggling to pay.
Who is responsible for this?
The government structure from the kebele up to the federal level
The Archbishop of the Diocese, the Patriarchate, and the Patriarch
The Majlis (Islamic Affairs Council)
The Council of Religious Institutions
Civic Organizations
Photo & Video: The burned grain storehouse of Abune Gebre Menfes Kidus Church and houses of Orthodox Christians in Jawi Wache Kebele.
🥰4
የኦርቶዶክሳዊ ሀገሩ የት ነው?

ጥያቄው የጅል ጥያቄ ይመስላል አይደል? አዎ ነው። ግን መልሱ እንደ ገደል የራቀ ነው። የመጣልን አልያ የሚመስለንን መመለስ መልስ ስለማይኾን ነው። መልሱን ለማግኘት ተግባሩን መከተል አግባብ ነው። 

ኢትዮጵያ የኦርቶዶክሳዊነት ሃገር ናት። መሠረቷ የሕይወት ፍልስፍናዋ ተዋሕዶአዊነት ነው። ተከፍሎ ወይም ምንታዌነት የአውሮፓውያን የጥፋት ዘር በቅሎብን ነው። ሥጋና ነፍስን መነጣጠል፣ ሃይማኖትና ፓለቲካን ነጣጥሎ ማየት የኖረ ሳይኾን እንድንጠፋ የተዘራብን ነው። ሃገሩ የእኔ ነው። እኔ የዚኽ ሀገር ዜጋ ነኝ ካልክ በኋላ ፓለቲካው ግን አይመለከተኝም ካልኽ ደንቁረሃል ማለት ነው። ኑሮው መኖሪያው፣ መማሪያው ማምለኪያ ቦታው፣ ሥራው አይመለከተኝም ማለትኽ ነው። በጥቅሉ በገዛ እጅኽ ሃገሩን አስረክበሃል ማለት ነው። 

ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ የኦርቶዶክሳዊ ሀገሩ የት ነው? ራሱ ኦርቶዶክሳዊው ስለ ሀገሩ የሚያስበው በጠላት የማሰቢያ መነጽርነት ነው። አንገቱ እየተቀላ በጥይት እየተደበደበ የሚሞተው ሃገርኽ አይደለም ቦታኽ አይደለኽም። ወራሪ ነኽ ሰፋሪ ነኽ እየተባለ ነው። ምድሪቱ ሀገሩቱ የእርሱ ኾና ሳለ በደምና አጥንት ቆጠራ መሬት ለክተው አንተ ከዚኽ ቦታ አይደለኽም ብለው ይገሉሃል። 

ይኽንን ይዘን የጀርባ ሥነ ልቡናዊ የጥፋት ውቅሩንም እንየው።

በኦርቶዶክሳዊ መረዳት ሀገሩ የተከፋፈለው በሃገረ ስብከት እንጂ በብሔር አይደለም። ለዚኽ ነው ሃገረ ስብከት የምንለው። ስለዚኽ ፓለቲካው ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ፣… ቢል ቤተ ክርስቲያን ይኽንን የምታውቀው በክልል ሳይኾን በሃገረ ስብከትነት ነው። ለስብከት የተከለለ ማለት ነው። አንድ ጳጳስ ለወንጌል ማዳረስ ይረዳው ዘንድ የተክልለለ ቦታ ወይም ሃገር ማለት ነው። ሃገረ ስብከት ዋና ዓላማው ለነስበክ ነው። 

ኾኖም ግን የጠላት ወጥመድ ውስጥ ገብተን በትውልድ ስፍራ ላይ ጳጳስ መመደብ ጀመርን። ጎንደሬ ጎንደር፣ ሸዌ ሸዋ፣ ኦሮሞ ኦሮሚያ፣ ትግሬ ትግራይ ላይ። ይኽ አጥንትና ደም ቆጣሪ የዳርዊን ትምህርት እንጂ የኦርቶዶክሳዊ ትምህርት አይደለም። ለእኛ ክህደት ጭምር ነው። 

የጎሳ አከላለል እውቀትም እውነትም የለውም። ትውልድን ሃገርን ከመበተን ውጭ ስሜትከመፍጠር ሌላ ሙያ የለውም። የተዋሐደውን በተነው። 
ዘጠኙ ቅዱሳን ኢትዮጵያ ሃገረ ስብከታቸው ናት። ለአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ኢትዮጵያ ሀገረ ስብከታቸው ናት። ከደምና አጥንት ጋር አይያያዘም። እጨጌ እንባቆም ደብረ ሊባኖስ ሃገረ ስብከታቸው ናት። ኹሉም ፍሬ አፈሩበት። 

የእኛ ጳጳሳት ወደ ሰፈራቸው የገቡት በምን ምክንያት ነው። ለስብከት ወይስ ለወንጀል መሸፈኛቸው? በደምና አጥንት ቆጠራ የተደበቁት ለስብከት ወይስ የፓለቲካ መስፈርት? 

ዛሬ ኦርቶዶክሳዊ ኢትዮጵያ ውስጥ ሀገር የለውም። መጤ ኾኗል። ወለጋ፣  ቤኒሻንጉል፣ ኦሮሚያ፣ ሐረር፣ ሶማሌ የሱ ሃገር አይደለም ተብሏል። ሃገረ ስብከት አለኝ የሚል ሲኖዶስ የሃገረ ስብከት ሉቀ ጳጳስ የስብከት ሃገሩን ወደ ጎሳ ክልል ሰጥቶ መንጎቹ ሲያልቁ ዝም ይላል። 
በወለጋ በአርሲ የሚያልቁት ካህናት ምእመና ሃገረ ስብከታቸው ነው።

ኦርቶዶክሳዊ የሚኖረው በስብከት ሃገሩ ነው። ለዚኽ ነው ቤተ ክርስቲያን በኖረበት የሚተክለው። ዛሬ ግን ካለበት እየተነቀለ እንደ በግ እየታረደ የሚኖረው። 

ይኽንን የሚያይ ጳጳስ ፣ ቄስ፣ ምእመናን ደግሞ በግድ የለሽነት እያዩ እየሰሙ ዝም ብለዋል። እንደ ሩቅ አካል ቆጥረዋቸዋል። ሕመማቸው አይሰማቸውም። ጳጳሱም የስብከት ሃገሩ ሳትኾን የሳንቲም ሃገሩ አድርጓታል። ወደ ስብከት ሃገራችን እንመለስ። ቋንቋ መግባቢያ እንጂ ሃገር አይደለም። በሃገር መሞት እንዲያበቃ ሃገር የነጠቀንን መታገል ብቸኛው ምርጫ ነው። እመኑ የሰው ልጅ የማይተርፍባት የእልቂት ሃገር ከፊታን አለች። መኝታው በዝቷል፣ መዝለሉ ለንግሥ መደለቁ፣ ሕንጻ ግንባታው ቆሞ ስለ ሕዝብ ማትረፍ ብቻ እናስብ። 

ንዋይ ካሳሁን
23
ኦርቶዶክሱ ራሱን ለመከላከል ወስኖ ያልተነሳው " እነ እንትና እየተዋጉ ነው ከጥቂት ጊዜ በኋላ መጥተው ነጻ ያወጡናል"የሚል የተሳሳተ አሳብ ውስጥ ስለተዘፈቀነው።እኛ ቁጭ ብለን ኑሮአችንን እየቀጨን ሌላው ሞቶ ነጻ እንዲያወጣን እንፈልጋለን።ይኽ ድንቁርና ነው። ነጻ አውጪ በመጠባበቅ የሚቆም መከራ የለም እንደውም የከፋ መከራ ነው ከፊታችን ያለው።
36👍2🔥1🥰1
የጥቁር ናዚዎች ጭካኔ
😢361
የመነኮሳት ፍጅት በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በአጭሩ

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ፣ መነኮሳትና ካህናት አባቶች በብዛት የተገደሉባቸውና መከራ የተቀበሉባቸው በርካታ ዘመናት አልፈዋል። ከእነዚህም መካከል በታሪክ ጎልተው የሚታወሱት ዋነኞቹ የመነኮሳት ፍጅቶች የሚከተሉት ናቸው።

1) በግራኝ አሕመድ ዘመን በ16ኛው ክፍለ ዘመን ከ1529 እስከ 1543 ዓ.እ በነበረው ጦርነት ወቅት፣ በግራኝ በሚመራው ሠራዊት እንደ ደብረ ሊባኖስና መሰል ታሪካዊ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ወድመዋል። በወቅቱም በገዳማቱ ውስጥ የነበሩ በርካታ መነኮሳትና ሊቃውንት ለሃይማኖታቸው ሲሉ ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።

2) በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ዘመን የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት እልቂት የሚጠቀስ ታሪክ ነው። ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በመነኮሳት ላይ የተፈጸመው እጅግ ዘግናኝና የጅምላ ጭፍጨፋ ነው። ድርጊቱ የተፈጸመው ግንቦት 12 ቀን 1929 ዓ.ም ነበር። በጣሊያኑ እንደራሴ ግራዚያኒ በተወረወረበት የቦምብ ፍንዳታ ምክንያት ለመበቀል ባስተላለፈው ትእዛዝ መሠረት፣ በገዳሙ የነበሩ ብዙ መነኮሳት፣ ዲያቆናትና ንጹሐን ምእመናን በሠራዊቱ ተከበው በግፍ ተፈጅተዋል።

3) በቅርብ ዓመታት በመነኮሳት ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች መጥቀስ ይገባል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በንጹሐን መነኮሳት ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት እጅግ ዘግናኝ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል በሚገኘው በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ከአራት በላይ መነኮሳት በታጣቂዎች መገደላቸው ይታወሳል። በሌሎችም ቦታዎች ተመሳሳይ ጥቃቶች ደርሰዋል።

በምስሉ ላይ የሚታዩት የ85 ዓመቱ አዛውንት አባ አየለ አረጋ እና እማሆይ እስከዳር ገላው ይባላሉ። ሁለቱ መነኮሳት ከቀናት በፊት በወለጋ አካባቢ፣ ልክ እንደ ፋሺስት ጣሊያንና እንደ ግራኝ አሕመድ ሠራዊት ጨካኝ በሆኑ አረመኔዎች የተገደሉ ናቸው።

ዲ/ን ዬሴፍ ፍስሐ
13