Eotc Task Force
7.25K subscribers
1.55K photos
348 videos
12 files
392 links
ወቅታዊ ጉዳይ
Download Telegram
አጀንዳችን አርሲ ናት ሼር አርጉት በደንብ
61👍7
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ልብ በሉ ይኽን ግፍ የሚፈጽመው ጫካ ያለው ሸኔ ወይም የ አክራሪ እስልምና ታጣቂ ቡድን አይምሰላችሁ። የኦሮሚያ ክልል መዋቅር የሚያዘው ነው።
😭34🤬3💔2
እንኳን አደረሳችሁ
17🙏10🥰6
ነሐሴ ፲፮ /16/

በዚችም ዕለት ዳግመኛ የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋው ከፋርስ አገር ወደ አገሩ ልዳ በክብር የፈለሰበት ነው።

የሥጋውም ፍልሰት ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋ ፍልሰት ጋር አንድ ሁኗል ስለዚህም እርሷን መውደዱን የሚያወቁ ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ በስሙ ለሚማፀኑ የድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በኃያሉ ተጋዳይ በጊዮርጊስም ጸሎት በእኛ ላይምሕረት ይቅርታ ቸርነት ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
17👏3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ልጆቻቸው የታፈሱባቸው እናቶች ዋይታ
😭17💔21
ሽርካ ላይ ምን ተፈጠረ?

[እውነታው ሲገለጥ]

በሽርካ ወረዳ ሶሌ ዲገሉ ቀበሌ ላይ ዘግናኝ የሆኑ ጭፍጨፋዎች በመፈጸማቸው ኦርቶዶክሳውያውን አከባቢውን ለቀው ይሰደዳሉ።በዚህ ምክንያት ከ2016ዓ.ም ጀምሮ ያ ሰፊ የኦርቶዶክሳውያን የእርሻ መሬቶች አልታረሱም። ራሳቸውን  ከአክራሪ የእስልምና  ታጣቂ ቡድን እና ጀሌዎቹ ለጠበቅ የተሰባሰቡ ገበሬዎች በዚህኛው ክረምት መሬቱን ማረስ ይጀምራሉ።መሬቱን ጠቅልሎ የመውሰድ ፍላጎት  ያደበት የአከባቢው ሙስሊም ማኅበረሰብ በተደጋጋሚ ትንኮሳ ይፈጽሚባቸዋል።ሆነ ብለው  ነገር ፍለጋና ለጠብ አጫሪነት ከብቶቻቸውን ሰብስበው በኦርቶዶክሳውያን የእርሻ መሬት ላይ ይለቃሉ ኦርቶዶክሳውያን መሬታቸውን ሲከላከሉ ደግሞ  ተሰብሰበው መጥተው ያጠቋቸዋል።ሰሞኑንም የሆነው ይኽው ነው። በ13/12/2018ዓ.ም እንደለመዱት ከብቶችን ሰብስበው በኦርቶዶክሳውያን የእርሻ መሬት ላይ ይለቃሉ።  እነዚህ ተሰባስበው አከባቢያቸውን የሚጠብቁ  ኦርቶዶክሳውያን  ገበሬዎች ከብቶቹን ለማስወጣት ሲሞክሩ ሙስሊም ማኅበረሰብ ወንድ ሴት ወጣት አዛውንት ሳይል ገጀራ(ቆንጨራ)፣ቢለዋ፣፣ጦር፣ድንጋይ ይዞ ወጥቶ ጥቃት ይከፍትባቸዋል ፣ታጥቆ ጫካ የገባው አክራሪው ቡድንም ከበባ ፈጽሞ መተኮስ ይጀምራል።ነገሩ እንደ ከበደ የተረዱት ኦርቶዶክሳውያኑም ራሳቸውን መከላከል ጀመሩ።በሁለቱም መካከል ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጥ ተደረገ።በመሃል ከብቶቹን ሰብስበው በኦርቶዶክሳውያን የእርሻ መሬት ላይ ሲያሰማሩ ከነበሩት አንዱ የጥቃቱ ሰለባ ይሆናል ።ብዙም ሳይቆዩ ሞተ ተባለ።ሬሳው ይመርመር ብለው ወዲያውኑ ወደ ጎቤሣ ሆስፒታል ይወስዱታል።ሬሳው ሲታይ ሰውዬው የተመታው እጅና እግሩ ላይ ነው ሙስሊሞቹ ግን ሀኪሞቹን አስገድደው "በጥይት ነው የተመታው ብላችሁ ጻፉልን"ይሉአቸዋል እነርሱም ሰውዬ በጥይት አልተመታም እንዲህ ብለንማ አንጽፍም የሚል ምላሽ ሲሰጧቸው እሬሳውን አዲስ አበባ ምንሊክ ሆስፒታል ወሰዱት።

ልብ በሉ !!! ይኽ የሞተው ሰውዬ ሀለት ወንድሞቹ ታጥቀው ጫካ የገቡና ኦርቶዶክሳውያንን የሚያርዱ ናቸው እሱም ተሳታፊ ነው።እንደውም በዚሁ ምክንያት ለዘጠኝ (9) ወራት ታስሮ ጉቦ ከፍሎ ነው የተፈታው።ብዙም ሳይቆይ ወደ ቀደመ ጥፋቱ በመመለሱ ለእስር የሚፈለግ ሰው ነው እነርሱ እንደሚሉት ንጹህ ሰው አይደለም።

በዚሁ ዕለት ማለትም በ13/12/2018ዓ.ም ኮነ እግዚአብሔር አብ በዓል አክብረው የሚመለሱ ኦርቶዶክሳውያን መንገድ ላይ ጠብቀው በሜንጫ(በሰይፍ)በድንጋይ አጥቅተዋል።ስድስት ኦርቶዶክሳውያን ተጎድተዋል።ሁለት እጃቸው ከጥቅም ውጭ የሆነ አሉ።

ይኽን ሁሉ ግፍ የሚፈጽሙት እነርሱ አደባባይ ወጥተው "እናጠፋችኋለን" እያሉ የሚፎክሩም እነርሱ ናቸው። ሴት ወንድ ወጣት ሽማግሌ ሳይሉ ሆ!ብለው ወጥተው ሆስፒታል የገቡ ኦርቶዶክሳውያንን ካላረድናቸው ብለው እስከመፎከር ደርሰዋል።

ጅራፍ ራሷ ገርፋ ራሷ ትጮኻለች እንደሚባለው እነርሱም ራሳቸው ጥቃት ፈጽመው የተጎዱ ለመምሰል አደባባይ ወጥተው ይጮኻሉ።"መንግሥት ይፈቀድልንና ኦርቶዶክሱን በጥቂት ቀናት ውስጥ የገደልነውን ገድለን የቀረውን እናስወጠዋለን "እያሉ እስከመናገር ደርሰዋል።ይኽ ብቻ አይደለም "ፋኖ ሙስሊሞችን አረደ" ብለው ነው በሐሰት ሕዝቡን ሲቀሰቅሱ የነበሩት።ፋኖ የሚሉት ኦርቶዶክሱን ነው።ለማጥፋት ያመቻቸው ዘንድ ነው "ፋኖ" የሚለውን ታርጋ የለጠፉት።ይኽንን ነው እንግዲህ እነ ጀዋር ባለሜንጫው በየሚዲያው የሚያራግቡት።

መልእክት ለሽርካ ሙስሊሞች

201 ኦርቶዶክሳውያንን አርዳችኋል ሺዎችን አፈናቅላችኋል አቢያተ ክርስቲያናትን አፍርሳችኋል።በዚህ አረመኔያዊ ተግባራችሁ ማፈር ሲገባችሁ  "አንድ ሰው ሞተ" ብላችሁ ለዚያዚውም በራሳችሁ ችግር ፈጥራችሁ በእኛ ላይ ጅሃድ ማወጃችሁ አብሮ አያኗኑረንምና ቆም ብላችሁ ብታስቡ። ዛሬ የተደገፋችሁበት ሥርዐት ነገ ይወድቃል ዋጋ የምትከፍሉት እናንተ ናችሁ።
👍53
10
ጥንቃቄ⚠️⚠️⚠️

በአርሲ ዞን በየ መስጊዶቹ  በኦርቶዶክስና በአማራ ላይ የጭፍጨፋ ቅስቀሳ እየተደረገ ነው። ሕዝበ ሙስሊሙ በገጀራም(በሜንጫ) ፣በጦርና በቢለዋ  ባገኘው ሁሉ ጥቃት እንዲፈጽም ጥሪ ተላልፎለታል።እንዲህ ዓይነት የጥፋት ቅስቀሳዎች በሁሉም የዞኑ ክፍሎች ቢደረጉም በሽርካ ላይ እየተደረገ ያለው ግን ከሁሉም የከፋ ነው።ሴቶች ሳይቀር "ነፍጠኛን አጥፉ"እያሉ ባሎቻቸውን እያነሳሷቸው ነው።
😢74💔1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ የአንዶዴ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ቄስ አባሆይ ታደሰ ይባላሉ።የሽመልስ አብዲሣ ገዳ ልዩ ኮማንዶ እያሰቃያቸው ይገኛል ።
😢24😭8🤬43
በአርሲ ምድር አክራሪ የኦሮሞ እስልምና ታጣቂ ቡድን ያደራጀው ጀዋር መሐመድ ነው። ይኽንን የዞኑ ባለሥልጣናት ጭምር በአደባባይ ተናግረዉታል።ለመጀመሪያ ጊዜ የተደራጀው በሽርካ ምድር ነው።ከዚያ በኋላ ነው ወደ ሌሎች ወረዳዎች የተስፋፋው። እርሱ መሠረቱን ጣለ ሥርዐቱ ስንቅና ትጥቅ አሟልቶ አጠነከራቸው።እስካሁን  ለታረዱትና ለተፈናቀሉት ሁሉ ግንባር ቀደም ተጠያቂው ይኽው ሰው ነው።ይኽን የጥፋት ቡድኑን ለመታደግ ሲል ነው "አርሲ ላይ ፋኖ እንዲህ አደረገ እንዲያ አደረገ"እያለ ሲቀጥፍ የሚውለው።ፋኖ እያለ የሚወነጅለው ኦርቶዶክሱን ሁሉ ነው።
👍15😢32
በዚህ እንዳትታሉ ለ አንድ ወር ቀልበው ይለቋቸዋል ።ነገ ሪጴ ሎላ ተብለው እንደሚሾሙባችሁ አትጠራጠሩ።ሳይገባችሁ በደመ ነፍስ ከበሮ የምትደልቁ አደብ ግዙ። የእኛ ብቸኛው መዳኛችን መደራጀትና ራስን ማስከበር ነው።ይኽን የአልሸባብ ተላላኪ ማሸነፍ የምንችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው።
👍30
አሳዛኝ መረጃ‼️

ተባብሶ የቀጠለው  የአገልጋዮች ጅምላ አፈሳ


የኦርቶዶክሳውያን መታረጃ ቄራ በሆነችው በሽርካ ምድር  በዲያቆናት በሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ነጠላ ለብሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን በሚሄዱ አገልጋዮች ላይ የሚደረገው  አፈሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል።ትናንት ነሐሴ 16/2018ዓ.ም የወረዳው ዋና መቀመጫ በሆነችው በጎቤሣ ከተማ የጎቤሣ ቅድስት ኪዳነምሕረት በዓል አክብረው በሚመለሱ  ዲያቆናት እና የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት  ላይ ከቤተ ክርስቲያኑ በር 200ሜ ርቀት  ላይ የጅምላ አፈሳ ተፈጽሞባቸዋል።ከ2 ሁለት ቅጥቅጥ ያላነሱ ኦርቶዶክሳውያን የታፈሱ ሲሆን ወዲያውኑ ነው ከወረዳው አውጥተው ወደ ዞኑ የወሰዷቸው።የልጆቹ ቤተሰብ ጠዋት ተሰብስቦ ሲያለቅስ ነው ያረፈደው ነገር ግን አንድም ምላሽ የሰጣቸው አካል የለም።

ይኽ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ ወረዳ  በሚታና ጋዶ ቀበሌ የጋዶ ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ዲያቆን ኀይሌ በላይ እና ዲ/ን አስቻለው ጸጋ ከፍተኛ ከ ቤተ ክርስቲያን ሲወጡ ጠብቀው ከፍተኛ ድብደባ ካደረሱባቸው በኋላ አፍሰው ወደ ዞኑ ዋና ከተማ አሰላ ወስደዋቸዋል። እነዚህ ዲያቆናት ይህንኑ አፈሳ በመፍራት ከቤተ ሰብቻቸው ሳይገናኙ  ቤተ ክርስቲያን ሳይወጡ ሲያገለግሉ ሰንብተው  ጾማቸውን ለመፍታት በወጡበት ቅጽበት ነው ጠብቀው ያፈሷቸው።የዚሁ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የነበሩ ሁለት ዲያቆናት ከሱባኤው በፊት ታፍሰው ከፍተኛ ብር ከፍለው የተለቀቁ ሲሆን አሁንም እንታፈሳለን የሚል ስጋት ስላደረባቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደው ማገልገል አልቻሉም።በዚህ ምክንያት  የጋዶ ማርያም ቤተ ክርስቲያን በአገልጋይ እጥረት ልትዘጋ ነው።

ይኽን የወንብድና ሥራ የሚሠራው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጣሂር አማኖ ነው።እስካሁን በኦርቶዶክሳውያን ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት በመረጃና በማስረጃ ስለተጋለጠበት ያንን ነው እየተበቀለ ያለው።

የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አባ ኤልሳዕና የሀገረ ስብከቱ ሥራ እስኪያጅ ይኽን ጸረ ኦርቶዶክሳዊ አካሄድ እንዲያስቆሙ  በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ለጉዳይ ትኩረት ሊሰጡት አልቻሉም።በዚህ ከቀጠልን ሽርካ ላይ አቢያተ ክርስቲያናት ሙሉ በሙሉ የዘጋታቸው አይቀሬ ነው።
😭147🤬4
ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ሌለኛው አፈሳ

በሽርካ ወረዳ ዋጂ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን 23 ኦርቶዶክሳውያን የታፈሱ ሲሆን 3 አምልጠው 20 ተወሰደዋል። ፖሊስ ያመለጡ ልጆች ቤተሰቦችን በድብደባ እያሰቃያቸው ይገኛል።
💔10😭41
"ፍኖተ ጽድቅ ማኅበር" የእመቤታችንን አማላጅነት የማይቀበል የተሐድሶ ፕሮቴስታንት ማኅበር ነው።ይኽንን ነው እነ ሳዊሮስ የሚያቆለጳጵሱት።
💔174😱3
የእርድ ዜና‼️

በአርሲ ዞን ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመው ጭፍጨፋ ተባብሶ እንደ ቀጠለ ነው። ነሐሴ 15 /2018ዓ.ም ዐርብ ለቅዳሜ አጥቢያ በ መጪቱ ቀበሌ ልዩ ቦታው "በቀቅሳ "  በአክራሪ የእስልምና ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ከአንድ ቤተሰብ  ሦስት ኦርቶዶክሳውያን ታርደዋል።የታረዱት የኦርቶዶክሳውያን ስም ዝርዝር ፦
1) ፍቃዱ አየለ(አባት)
2) ኀይሉ ፈቃዱ
3) ንጉሤ ፍቃዱ

ይኽን ጭፍጨፋ የሚመራው የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሐሰን መሐመድ ነው።ይኽ ሰው በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጽመውን ጭፍጨፋ በተደጋጋሚ  በመካድ የሚታወቅ ሰው ነው።ይኽ ብቻ አይደለም በማኅበራዊ ሚዲያ ለሙስሊም ወጣቶች፦

ሉዲያቹን(ገጀራችሁን ) ሳሉ በምትይዙበት ያዙ
ሜንጫችሁን ምዘዙ ከላችሁበት ጨፍጭፉ
ቄሮዎች ተነሱ እባካችሁ
ስለምን ቁጭ ብላችሁ ታያላችሁ
ስማችን ጠፋ እኮ
እንደ አንበሣ እያገሣችሁ
እንደ ነብር እያጉረመረማችሁ
እንደ ንብ ተናደፉ
እንዋጋለን የምንለው ባርነትን ጠልተን ነው
ባርነትን ፈልገህ ነው ወይ የማትነሳው?
ለምንስ ነው የማትወጣው?
የሚል የጅሃድ ሽለላ ሲያስተጋባ የነበረ ሰው ነው።
7👍4😡3💔2