Eotc Task Force
7.25K subscribers
1.55K photos
348 videos
12 files
394 links
ወቅታዊ ጉዳይ
Download Telegram
አርሲ ላይ እየሆነ ያለውን በትኩረት እየተከታተልሁ ነው። ወለጋ ላይ እነ ቄስ ዱጉማ ኡፋና ቄስ ደሲለኝ ነሞምሳን በኦነግ ሸኔ ያስገደለው ፣ቢሾፍቱ ላይ የወልዳ ዳንዲ አቦቲ(ፍኖተ አበው ማኅበር) ሰብሳቢ አቶ ንጉሤን አሳግቶ ደብዛው እንዲጠፋ ያደረገው ማፊያ ቡድን በአርሲም ያንኑ ታሪክ እንዳይደግም ያሰጋል።አሳቦቻችንና አይደግፉም የሚሉአቸውን ካህናትና ዲያቆናት ላይ በየሚዲያው "የግደለው ፍለጠው ቁርጠው" ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ናቸው።ቁጥራቸው ቀላል አይደለም ይኽን የጥፋት አጀንዳ የሚመራ ቡድን አለ።አርሲ ላይ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ላይ የሆነ ችግር ቢደርስ እነዚህም ልጆች ተጠያቂዎች ናቸው።በአዳማና በአሰላ ሆነው ይኽን የጥፋት ሴራ የሚመሩ ግለሰቦችን ከእነ ፎቶአቸው አጋልጣለሁ።
6👍63
እኔ የምለው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት "የጠለታ ቅዱስ ገብርኤልን እንሠራለን" እያለ ጥሩምባ ሲነፋ አልነበረም ወይ? "ከቁልቡ ገብርኤል ለጠለታ ገብርኤል" እየተባለ የሕዝቡ ኪስ ሲታጠብ አልነበረም ወይ?
19🤔2
"የባሰ አታምጣ" እያሉ ሃይማኖታዊ ጭቆናዎችን መታገስ መንፈሳዊነት ነው?
እርስዎስ መቼ ነው ከሥራዎ የሚታገዱት?ቀድሶ የሚያቆርብ እጅዎ በደም ቆሽሿልና።
😢28💯14🙈53😱2
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ አደረሰን አደረሳችሁ!!!
👏2726
የቤተ ክርስቲያን ችግር የሚስተካከለው መዋቅሩ ከላይ እስከታች ሲታከም ብቻ ነው።ጳጳሳቱና የከተማ መነኮሳቱ ቤተ ክርስቲያንቱን እያስተዳደሯት ሳይሆን እየጠቧት ነው።ቢቆጠሩ አምስት እንኳ የማይሞሉ ጳጳሳት ካልሆኑ በቀር አራት አምስት ፎቅ ያለሠራ የቤተ ክርስስቲያንቱን ካዝና ያላራቆተ ጳጳስ የለም።በቃ እውነት እውነቱን እንነጋገር ሌባ ሌባን ማገድ አይችልም።እነ አቡን ሳዊሮስ እነ አቡን ዲዮስቆሮስ በሌሎች ላይ እርምጃ መውሰዳቸው የሚበረታታ ቢሆንም እነርሱም ግን ከሁሉ የከፋ ጥፋት በ ቤተ ክርስቲያን ላይ ሲያደርሱ ኖረዋል አሁንም እያደረሱባት ነው።አቡነ ሳዊሮስ ከወሀቢያ ጋር ተሰልፈው ኦርቶዶክሳውያንን አስጨፍጭፈዋል እጃቸው በደም ተጨማልቋል ለብዙዎች አካል መጉደል ምክንያት ሆነዋል ከፖለቲከኞች በከፋ መልኩ በኦርቶዶክሳውያን መካከል ልዩነትን ተክለዋል ቤተ ክርስቲያንቱ የሥርዐቱ ሁለተኛው ጽ/ቤት አድርገውታል።አቡን ዲዮስቆሮስ በዘመነ ኢሕአዴግ የኢሕዴግ ሰው የነበሩ አሁን ደግሞ ተገልብጠው አሁን ያለውን ኦርቶዶክስ ጠል ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክስ በል ሥርዐት በካድሬነት በማገልገል ላይ ናቸው ይኽ ብቻ አይደለም ሀገረ ስብከታቸው ራያን ዘወር ብለው እንኳ አላዩትም ።አዎ ! ለውጥ እንዲመጣ ከተፈለገ ጳጳሳቱ በአደባባይ የበደሏትን ቤተ ክርስቲያን በአደባባይ ይቅርታ ይጠይቁ።ሳዊሮስም እስከ ጥቅምት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ይዘርፉታል የራሳቸውን ሰው በየመዋቅሩ ይሰገስጋሉ ከጥቅምት በኋላ ደግሞ እንደ እርሳቸው ቤተ ክርስቲያንቱን ለሥርዐቱ የሚያስገብር ጳጳስ ያስቀምጣሉ።እንደውም ከወዲሁ "ማርያ ቤዛ አትባልም፣የቤተ ክርስቲያን አዋልድ መጽሐፍት ተረትተረት ናቸው"በሚል የምንፍቅና ትምህርት የሚታወቁት አባ ገብርኤል እንዲሾሙ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጀምሯል።
😭2013👍6
የገጽታ ግንባታ አገልግሎት መሆኑ ነው። የምንገደለው በ ቤተ መንግሥትና ቤተ ክህነትና ትብብር ነው የምንለው ለዚህ ነው።በአጭር ቃል ቤተ ክህነቱ በልጽጓል ።
24😁5👍2😭2
   
◈የወንጌል ለምምዳችን በተቃራኒው ሁኗል።
በስሁት ልምምድ እነዚህን አፍርተናል👇
◈1.)የእግዚአብሔርን ቃል እንደተራ ቃል መለማመድ፤
◈2.)ወንጌልን ሙያና መብያ ማድረግ፤
◈3.)የማንኖረውን ቃል ለሌላው መስበክ፤
◈4.)ሳይታወቁ በማስመሰል ሲታወቁ በመቃረን መኖር፤
◈5.)ሞትንና ትንሣኤ ሙታንን፣ፍትሐ እግዚአብሔርን መርሳት፤
◈6.)እግዚአብሔር አጎታችን እስኪመስለን ድረስ መዳፈር፤
◈7.)አምላካዊ አደራን ከቁስ አደራ በታች አድርጎ ማየት፤
◈8.)ፌዝን ቧልትን እንደ ቁም ነገር ማዘውተር፤
◈9.)ሲጠቀለል፦ምረረ ገሀነመ እሳትን ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን መዘንጋት ይስተዋልብናል።
◈10.)መፍትሄው ከእነዚህ ጉዳዮች በተቃራኒ መሆን ነው።
"ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማል
እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።
ይህ ቃል የታመነ ሁሉም እንዲቀበሉት የተገባ ነው
ይህን ለማግኘት እንደክማለንና ስለዚህም እንሰደባለን ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።"፩.ጢሞ.፬፥፰-፲
🙏14👍11
ሰውን በሚናገረው ቋንቋ በማንነቱና በሃይማኖቱ ለይቶ ዘሩን ማጥፋት እንደ እድገት የምትቆጥር "አዲሲቷ ኢትዮጵያ"
😭32💔133
ፆማችን ሱባዔያችን ዋጋ እንዲኖረው እነዚህን ሰማዕታትና በመከራ ውስጥ ያሉ ኦርቶዶክሳውያንን በማሰብ ይሁን።
👍129