7) የጨቦ መካነ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ዋሻ (ገዳም)
ይኽ ዋሻ የሚገኘው በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥር፣ በወንጪ ወረዳ፣ ወራቡ ገበያ በተባለ ቦታ ነው፡፡ የተመሠረተውም በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (በዐፄ ካሌብ ዘመነ መንግሥት) መኾኑ በትውፊት (ከአከባቢው አረጋውያን) ከመነገሩ በቀር ተጨባጭ የጽሑፍ ማስረጃዎችን ለማግኘት ባይቻልም በግራኝ አህመድ ጥፋት ወቅት ግን ለበርካታ ንዋያተ ቅድሳት መሸሸጊያ ኾኖ በአደራነት መጠበቁ ይነገራል፡፡ በቦታው ስውራን ቅዱሳን እንዳሉ ማሳያው ደግሞ በተለይ ሌሊት ላይ በዋሻው ውስጥ በከበሮና ጸናጽል የታጀበ ስብሐተ እግዚአብሔር ሲደርስ መስማታቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች መመስከራቸው ነው፡፡
8) የዝዋይ ደሴቶች ገዳማት
የዝዋይ ደሴት በውስጡ ሌሎች አምስት ደሴቶች ያሉት ሲኾን በምሥራቅ ሸዋና አርሲ አኅጉረ ስብከቶች መካከል (አዋሳኝ) ላይ ይገኛል፡፡ ዮዲት ጉዲት በሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል የነበሩ ገዳማትን ከነ ንዋያተ ቅዱሳቱና ሊቃውንቱ ማውደም በጀመረች በ9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወቅት ታቦተ ጽዮንን ጨምሮ ሌሎችም ታቦታት ወደዚህ ቦታ (ዝዋይ ሐይቅ ላይ) እንዲያርፉ ተደርጎ እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ ታቦተ ጽዮንም ለ40 ዘመናት የተጠለለችበት፣ የበርካታ ሊቃውንትም አሻራ ያረፈባት ቦታ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ዝዋይ ደሴት ከዚያን ወቅት ጀምሮ የበርካታ ገዳማት መናኸርያ ለመኾን በቅታለች፡፡[2]
9) ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም
Photo
ይህ በጥንት ታሪኩ በዘመነ ዮዲት ጉዲት ወደ ዝዋይ ደሴት ከመጡት ታቦታት መካከል ኾኖ ከ40 ዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ ሌሎች ታቦታት ወደየመጡበት ሲመለሱ ታቦተ ገብኤል ተረስቶ መቅረቱ በመታወቁ፣ ፈቃደ እግዚአብሔርም ኾኖ ወደዚኽ ቦታ መጥቶ ሊተከል እንደቻለ ለማወቅ ተችሏል፡፡[3] ከዚያ በኋላ ግን ለረጅም ዘመናት በዚያው ተሠውሮ ቆይቶ በልዑል ራስ መኮንን አማካይነት (1884 ዓ.ም) በዐዲስ መልኩ ተሠርቶ ታቦቱ ሊገባ፣ አገልግሎቱም ተጠናክሮ ሊቀጥል ችሏል፡፡ አስቀድሞ ከተጠቆመው ታሪኩ በመነሣት ታዲያ የክርስትናው አሻራ ቁልቢ አከባቢ የደረሰው በ9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መኾኑን ልብ ይሏል፡፡
ምንጭ፡- ‹‹ግንጊልቻ›› መጽሐፍ፤ ገጽ.404-406)

❤8👍1
👆👆ልብ በሉ ከኦሮሞ እንቅስቃሴ (ኦሮሞ ክርስትናንንም እስልምናንም ሳይቀበል)
በፊት ዛሬ "ኦሮሚያ" ተብሎ በተከከለ መሬት ክርስቲያኖች ነበሩ ታላላቅ ገዳማትና አቢያተ ክርስቲያናት ነበሩ።ታሪክ እንደሚነግረን የኦሮሞ እንቅስቃሴ የጀመረው ከግራኝ አሕመድ ወረራ በኋላ(በ16መክዘ) ነው ክርስትና ደግሞ ከአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት በዚህ ምድር ነበረ ።ቤተ ክርስቲያን መሬታችንን ወረረች የሚለው የውሸት ትርክት ውኃ በላው።

❤20👍2
<<330ዓ.ም ኢትዮጵያ የኤጵስ ቆጶስ መንበር የጀመረችበት እንጂ ክርስትናን የተቀበለችበት አይደለም >>የኔታ ኀይለማርያም ዘውዱ
❤17
የከተማ መነኩሴ ሲነካ የሚንጫጩት እነ ማን ናቸው?
፩ ራሳቸው የከተማ መነኮሳት
፪ የምንኩስና መስፈርቱ ምን እንደሆነ የማያውቁ የግሪክ ልብስ የለበሰውን ሁሉ አባ የሚሉ ምዕመናን
፫ ፍትፍት ይዘው ወደ ከተማ መነኮሳት ቤት የሚንጦለጦሉ ሴቶች
፬ ከመነኮሳቱ ጋር ጥቅም የሚጋሩ
፭ የከተማ መነኮሳቱ ቤተ ክርስቲያንቱን እያዳከሙ መሆኑን የተረዱ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን

❤16👍6💯2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሁን ደግሞ "የወንጌል" ሰዓት ነው።መነኮሳቱና ካህናቱ እየተሰበኩ ነው። ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚንስትሩ ጳጳሳቱን ሰብስበው ከመጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሰ ሲሰብካቸው ነበር።ቤተ ክርስቲያናችን ከባድ ፈተና ውስጥ ናት።
😭26❤9🔥3
ከቀሲስ ዶ/ር መንግሥቱ ጎበዜ
«ሞዐ ተዋሕዶ» የማነው?
ከወቅታዊ የሀገርና የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ጎልተው ከሚነሱ አጀንዳዎች መካከል አንዱ «ሞዐ ተዋሕዶ» ነው። ስለ ንቅናቄው ግልጽና የጠራ ግንዛቤ ይኖረን ዘንድ በተረዳሁት መጠን የሚከተለውን ምልከታ ማጋራት ወደድሁ።
«ሞዐ ተዋሕዶን» በተመለከተ ብዙ ግራ መጋባቶች ይስተዋላሉ። አንዳንዶች ሆን ብለው በሚመስል ሁኔታ ከዐውዱና ከዓላማው ውጭ የሆነ መረጃ በማሰራጨት፣ ንቅናቄው የፖለቲካ ዓላማ እንዳለው አድርገው በመሳል ብዙዎችን ያሳስታሉ። እንዲያውም «ሞዐ ተዋሕዶ» በአንዳንድ የመንግሥት አካላትም ሆነ በሌሎች የቤተ ክርስቲያን ተቃዋሚዎች በኩል የሚለጠፍበት አሉታዊ ስም፣ በተግባር ከሚሠራው በጎ ሥራ ጋር በፍጹም የሚገናኝ አይደለም። ከዚያም አልፎ ስሙን የመምቻ ዱላ በማድረግ፣ ኦርቶዶክሳውያንን ለማሳቀቅ፣ ለማሰር፣ ለማሳደድና ለማጥቃት እንደ ምክንያት ሲጠቀሙበት ይስተዋላል።
ሆኖም «ሞዐ ተዋሕዶ» ምንም ዓይነት የፖለቲካ ወገንተኝነት የሌለውና ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ሊጋሩት የሚችሉትን ዓላማ ሰንቆ የሚጓዝ ግብረ-ኃይል ነው። ዋና ግቡም ቤተ ክርስቲያንን ከጥቃት፣ ከስደትና ከጥፋት መከላከል ብቻ ነው። አንዳንዶች ሞዐ ተዋሕዶን ከ«ሞአ አንበሳ» ጋር በማመሳሰል ንቅናቄውን ከንጉሣዊ ሥርዓት መመለስ ጋር ለማያያዝ የሚያደርጉት ጥረት ፈጽሞ መሠረት የለውም። የግብረ-ኃይሉን ርእይ፣ ተልዕኮ፣ ግብና ተግባር ከግለሰቦች ማንነት ጋር ማያያዝም ትክክል እንዳልሆነ ተገንዝቤአለሁ።
የ«ሞዐ ተዋሕዶ» መነሻ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት 2013 ዓ.ም. የምልዓተ ጉባኤው ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ያደረገውን ጥሪ መሠረት ያደረገ ነው። ሲኖዶሱ በምእመናንና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በመመልከት፣ ምእመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የካቲት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በይፋ ተመሠረተ።
ሞዐ ተዋሕዶ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ የሚሰነዘሩ መዋቅራዊ፣ አስተዳደራዊና ርዕዮተ-ዓለማዊ ጥቃቶችን ለመመከት የሚሠራ የጥብቅና ንቅናቄ (Advocacy Movement) ነው ማለት ይቻላል። ግብረ-ኃይሉ ለዘመናት የነበረውን «የዝምታ ስልት» በመስበር፣ የቤተ ክርስቲያኗን መብትና ድምፅ በግልጽ የሚያሰማበትን ሰላማዊ መንገድ ቀይሷል። ይህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከዝምተኛ ተከታይነት ወደ «ንቁ ተሟጋችነት» የተሸጋገሩበትን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ያመላክታል።
«ሞዐ ተዋሕዶ» ከምሥረታው ዕለት ጀምሮ ለኢትዮጵያ መንግሥትና ለሚመለከታቸው አካላት ያቀረባቸው ሰባት ዋና ዋና ጥያቄዎችን በማስተጋባት ላይ ይገኛል። እነዚህም በትምህርት፣ በሚዲያና በልማት ስም የሚሰራጩ ጸረ-ኦርቶዶክስ ትረካዎች እንዲቆሙ፣ በመንግሥት መዋቅርና በኢኮኖሚ ላይ የሚፈጸም መዋቅራዊ ማግለል እንዲያበቃ፣ ቤተ ክርስቲያንን በብሔርና በቋንቋ የመከፋፈል ፖለቲካዊ ሴራዎች እንዲገቱ፣ በምእመናን ላይ የሚፈጸሙ አካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ጥቃቶች እንዲቆሙ፣ በጥፋተኞች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ተወስዶ ለተጎጂዎች ካሳ እንዲሰጥ፣ የተፈናቀሉ ምእመናን ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ፣ እንዲሁም «አዲሲቷን ኢትዮጵያ» በመገንባት ሰበብ የሚካሄዱ ኦርቶዶክሳዊ አሻራዎችን የማጥፋት ዘመቻዎች እንዲቆሙና መንግሥት ይፋዊ የይቅርታ መግለጫ እንዲሰጥ የሚጠይቁ ናቸው።
በአጠቃላይ፣ መገንዘብ እንደቻልሁት ሞዐ ተዋሕዶ በየትኛውም ዓይነት የፖለቲካ አሰላለፍ ያልወገነ፣ ዋና ዓላማውና ትኩረቱ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻና ብቻ የሆነ ንቅናቄ ነው። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ የታሪክ እውነታ ሀገርና ቤተ ክርስቲያን ተነጣጥለው ስለማይቆሙ፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አወንታዊ አስተዋጽኦ ከማበርከት ወደ ኋላ አይልም። ሁሉም ኢትዮጵያውያን በፍቅርና በመከባበር የሚኖሩባት፣ ፍትሕ፣ እኩልነትና ነጻነት የሰፈነባት ሀገር እንድትገነባ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል።
እንደ እኔ መረዳት፣ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ እየደረሰ ያለውን ዘርፈ-ብዙ ጥቃት ለመከላከል ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ የሚያበረክቱበት የትብብር መረብ በመሆኑ «ሞዐ ተዋሕዶ» የማንም ሳይሆን የሁሉም ነው። በአሁኑ ወቅት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በህልውና አደጋ ውስጥ የምትገኝ በመሆኗና ይህንን ሰፊና መዋቅራዊ ፈተና ለመመከት ይመጥናል ተብሎ የሚታመን ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት ባለመኖሩ፣ የጎደለውን ሞልቶና የጎበጠውን አቃንቶ እንደ «ሞዐ ተዋሕዶ» ያሉ ንቅናቄዎችን መደገፍ፣ ማበረታትና ማሳደግ ከመላው ኦርቶዶክሳውያን የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው የሚል ጽኑ እምነት አለኝ።

❤20👍8
አርሲ ላይ እየሆነ ያለውን በትኩረት እየተከታተልሁ ነው። ወለጋ ላይ እነ ቄስ ዱጉማ ኡፋና ቄስ ደሲለኝ ነሞምሳን በኦነግ ሸኔ ያስገደለው ፣ቢሾፍቱ ላይ የወልዳ ዳንዲ አቦቲ(ፍኖተ አበው ማኅበር) ሰብሳቢ አቶ ንጉሤን አሳግቶ ደብዛው እንዲጠፋ ያደረገው ማፊያ ቡድን በአርሲም ያንኑ ታሪክ እንዳይደግም ያሰጋል።አሳቦቻችንና አይደግፉም የሚሉአቸውን ካህናትና ዲያቆናት ላይ በየሚዲያው "የግደለው ፍለጠው ቁርጠው" ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ናቸው።ቁጥራቸው ቀላል አይደለም ይኽን የጥፋት አጀንዳ የሚመራ ቡድን አለ።አርሲ ላይ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ላይ የሆነ ችግር ቢደርስ እነዚህም ልጆች ተጠያቂዎች ናቸው።በአዳማና በአሰላ ሆነው ይኽን የጥፋት ሴራ የሚመሩ ግለሰቦችን ከእነ ፎቶአቸው አጋልጣለሁ።
✍6👍6❤3
እኔ የምለው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት "የጠለታ ቅዱስ ገብርኤልን እንሠራለን" እያለ ጥሩምባ ሲነፋ አልነበረም ወይ? "ከቁልቡ ገብርኤል ለጠለታ ገብርኤል" እየተባለ የሕዝቡ ኪስ ሲታጠብ አልነበረም ወይ?
❤19🤔2