ዘግይቶ የደረሰኝ መረጃ(አርሲ በአክራሪ የእስልምና ታጣቂዎች ስለተገደሉ ኦርቶዶክሳውያን)
፩ በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ሰንጎ ያያ ቀበሌ በ24/11/2018ዓ.ም አባቱ ተገድሎ የነበረው አቡሌ ክፍሌ ከታገተበት ተገድሎ ተጥሎ ትናንት በ27/11/2018ዓ.ም ሥርዓተ ቀብሩ በጋዶ ማርያም ቤተክርስቲያን ተፈጽሞአል
፪ ትናንት ሐምሌ 27/2018ዓ.ም በጉና ወረዳ ገበያ ውለው ሲመለሱ የነበሩ ኦርቶዶክሳውያን " መሶ" የሚባል ቦታ ላይ ሲደርሱ ጥቃት ተከፍቶባቸው 3 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን 30 ሴቶችም ታግተው ተወስደዋል
፫ በመርቲ ወረዳ ላይ ሰሞኑን አንድ ኦርቶዶክሳዊ ተገድሏል

💔24😢18🔥3
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የኦሮሞን መሬት ወራለች፣ኦርቶዶክስን በኦሮሞ ላይ የጫነው ሚንሊክ ነው የሚለውን የሐሰት ትርክት የሚያከሽፍ ጽሑፍ ነውና አንብቡት።ጸሐፊው የኦሮሞ ተወላጅ ፉፋ ኦላና ኩማ ነው።የመጽሐፉ ስም <<ግንግልቻ>>ይባላል።
👇👇
👇👇
ከ4ኛው እስከ 9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኦሮሚያ ከነበሩት ጥንታውያን ቅዱሳት መካናት መካከል ጥቂቶቹ
===========================================
‹‹ኦርቶዶክስ ቅድመ ምኒልክ በኦሮሚያ ምድር አልነበረችም!›› ለሚሉት አካላት ተጨባጭ የታሪክ ማስረጃዎች አሉ፤ ከ4ኛው እስከ 9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዚሁ አከባቢ ከነበሩት ቅዱሳት መካናት መካከል ጥቂቶቹን ብቻ እነኾ፡-[1]
1) ዋሻ ቅዱስ ሚካኤል
ይኽ ገዳም የሚገኘው በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሥር፣ ወራ ጃርሶ ወረዳ ውስጥ ሲኾን የተመሠረተውም በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት (4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን) ነው፡፡ ነገሥታቱ ዓባይን ተሻግረው የሸዋን ምድር እንደረገጡ መጀመሪያ የመሠረቱት ገዳምና በአባ ሰላማ ተባርኮ ጽላተ ሚካኤል እንደገባበትም ይነገራል፡፡ ኾኖም ግን በሀገራችን እንደነበሩት ሌሎች ጥንታውያን ገዳማት ኹሉ ይኽ ም ቅዱስ ሥፍራ በግራኝ አህመድ ተቃጥሎ ነበር፤ በዐፄ ገላውዴዎስ ዘመነ መንግሥት ግን በአቅራቢያው ከሚገኙትና ለተመሳሳይ ጥቃት ተጋልጠው ከነበሩት የደብረ ሊባኖስ ገዳምና ጎሐ ጽዮን ማርያም ጋር አብሮ እንዲታደስ ተደርጓል፡፡
2) ጎሐ ጽዮን ቅድስት ማርያም
በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሥር፣ በወራ ጃርሶ ወረዳ ውስጥ፣ በዓባይ በረሃ አፋፍ ላይ የምትገኝ የምትገኝ ጥንታዊት ደብር ናት፤ ከዋሻ ቅዱስ ሚካኤል ጋር በአብርሃ ወአጽብሃ (4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን) እንደተመሠረተችም ነው የሚታመነው፡፡ አስቀድሞ እንደተጠቆመው በግራኝ አህመድ ተቃጥላ ከጠፋች ከበርካታ ሺሕ ዘመናት በኋላ በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ታድሳ አገልግሎቷን ቀጥላለች፡፡
3) ፍቼ አራተ ማርያም
ይኽ ችም አስቀድመው እንደተገለጹቱ ሁለቱ በተመሳሳይ ጊዜና በተመሳሳይ ነገሥታት (በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፣ በአጽብሃ) የተመሠረተች ናት፡፡ የምትገኘውም በተመሳሳይ ቦታ (ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ውስጥ) ነው፡፡ ‹‹አራተ ማርያም›› በግእዙ ‹‹የማርያም አልጋ/መንበር›› የሚል ትርጉም ያለው ነው፡፡ በሌላ መልኩ ‹‹አራተ›› የሚለውን ‹‹አርባዕተ›› ብለው ‹‹አራተኛዋ ማርያም›› የሚሉም አሉ (ከአኵሱም ጽዮን ጀምሮ ሲቆጠሩ ከተተከሉና በእመቤታችን ስም ከተሰየሙ አብያተ ክርስቲያናት፣ ከተድባበ ማርያም፣ መርጡለ ማርያም እና ጎሐ ጽዮን ማርያም ቀጥላ አራተኛዋ እንደማለት)፡፡
4) ኤረር በዓታ ለማርያም ገዳም
አብርሃና አጽብሃ ይባሉ የነበሩ ወንድማማች ነገሥታት ሀገሪቱን በኹለት ተካፍለው እንዲያስተዳድሩ ባደረጉበት ወቅት የአጽብሃ መንበረ መንግሥት በኤረር እንዲኾንተደርጎ ነበር፡፡ እናም፥ ይኽ ች ገዳም የተመሠረተችው በዚኹ ንጉሥ አማካይነት፣ በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነበር ማለት ነው፡፡ ከመጀመሪያ ጀምሮ የተተከለውና ዛሬም በቦታው ላይ የሚገኘው የቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ ቤተ ክርስቲያን ሲኾን ከዚያው ጋር የነበሩ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ግን በግራኝ አማካይነት መቃጠላቸው ይነገራል (ዛሬ ግን ይበልጥ የሚታወቀው በእግረ ደብረ በተተከለችው ‹‹ኤረር በዓታ ለማርያም ገዳም›› ስያሜው ነው)፡፡ እጅግ ምሥጢራዊ ስለኾነው ስለዚህ ተራራና በዙርያው ያሉ ገዳማት በብዛት በድርሳነ ዑራኤልና በታሪከ ነገሥት አብርሃ ወአጽብሃ ማግኘት ይቻላል፡፡
5) ኤካ ሚካኤል ዋሻ
ይኽ ከዛሬው የካ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን (ዐዲስ አበባ) ከፍ ብሎ በተራራው ላይ ይገኝ የነበረ፣ ከአለት ተፈልፍሎ የተሠራ ውቅር ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ አጽብሐ መንበረ መንግሥቱን ወደ ሸዋ ‹‹ኤረር›› ባዛወረበት ወቅት (372 ዓ.ም አከባቢ) በየረር ተራራ ላይ ቤተ መንግሥቱን ከመሠረተ በኋላ ታቦተ ሚካኤልን በዋሻው እንዲገባ ማድረጉን ውቅሮ አብርሃ ወአጽብሃ ገዳም የሚገኘው የነገሥታቱ ገድል ያስረዳል፡፡ በእርግጥ ስለ ዋሻው የሚነገሩት የተለያዩ ታሪኮች ናቸው፡- ተጀምሮ ሳይጠናቀቅ እንደቀረ፣ ተጠናቅቆ አገልግሎት ሲሰጥ ከቆየ በኋላ በግራኝ አህመድ እንደወደመ፣ ጣልያን በመድፍ እንደመታው፣ ወዘተ. የሚሉ ይገኝበታል፡፡ በትልቅነቱ ግን በሀገራችን ካሉት ፍልፍል ዋሻዎች ሁለተኛውን ሥፍራ እንደሚይዝ ይነገራል፡፡
6) ዘጋመል ቅድስት ማርያም
ይኽ ች ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት፣ ደብረ ሊባኖስ ወረዳ ውስጥ፣ በጀማ ወንዝ ሸለቆ የምትገኝ የዋሻ (ከአለት የተፈለፈለች) ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ የተመሠረተችውም በ450 ዓ.ም እንደኾነም ከቤተ ክርስቲያኒቱ የተገኘ የታሪክ መረጃ ያመለክታል፡፡

❤6👍2
7) የጨቦ መካነ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ዋሻ (ገዳም)
ይኽ ዋሻ የሚገኘው በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥር፣ በወንጪ ወረዳ፣ ወራቡ ገበያ በተባለ ቦታ ነው፡፡ የተመሠረተውም በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (በዐፄ ካሌብ ዘመነ መንግሥት) መኾኑ በትውፊት (ከአከባቢው አረጋውያን) ከመነገሩ በቀር ተጨባጭ የጽሑፍ ማስረጃዎችን ለማግኘት ባይቻልም በግራኝ አህመድ ጥፋት ወቅት ግን ለበርካታ ንዋያተ ቅድሳት መሸሸጊያ ኾኖ በአደራነት መጠበቁ ይነገራል፡፡ በቦታው ስውራን ቅዱሳን እንዳሉ ማሳያው ደግሞ በተለይ ሌሊት ላይ በዋሻው ውስጥ በከበሮና ጸናጽል የታጀበ ስብሐተ እግዚአብሔር ሲደርስ መስማታቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች መመስከራቸው ነው፡፡
8) የዝዋይ ደሴቶች ገዳማት
የዝዋይ ደሴት በውስጡ ሌሎች አምስት ደሴቶች ያሉት ሲኾን በምሥራቅ ሸዋና አርሲ አኅጉረ ስብከቶች መካከል (አዋሳኝ) ላይ ይገኛል፡፡ ዮዲት ጉዲት በሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል የነበሩ ገዳማትን ከነ ንዋያተ ቅዱሳቱና ሊቃውንቱ ማውደም በጀመረች በ9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወቅት ታቦተ ጽዮንን ጨምሮ ሌሎችም ታቦታት ወደዚህ ቦታ (ዝዋይ ሐይቅ ላይ) እንዲያርፉ ተደርጎ እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ ታቦተ ጽዮንም ለ40 ዘመናት የተጠለለችበት፣ የበርካታ ሊቃውንትም አሻራ ያረፈባት ቦታ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ዝዋይ ደሴት ከዚያን ወቅት ጀምሮ የበርካታ ገዳማት መናኸርያ ለመኾን በቅታለች፡፡[2]
9) ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም
Photo
ይህ በጥንት ታሪኩ በዘመነ ዮዲት ጉዲት ወደ ዝዋይ ደሴት ከመጡት ታቦታት መካከል ኾኖ ከ40 ዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ ሌሎች ታቦታት ወደየመጡበት ሲመለሱ ታቦተ ገብኤል ተረስቶ መቅረቱ በመታወቁ፣ ፈቃደ እግዚአብሔርም ኾኖ ወደዚኽ ቦታ መጥቶ ሊተከል እንደቻለ ለማወቅ ተችሏል፡፡[3] ከዚያ በኋላ ግን ለረጅም ዘመናት በዚያው ተሠውሮ ቆይቶ በልዑል ራስ መኮንን አማካይነት (1884 ዓ.ም) በዐዲስ መልኩ ተሠርቶ ታቦቱ ሊገባ፣ አገልግሎቱም ተጠናክሮ ሊቀጥል ችሏል፡፡ አስቀድሞ ከተጠቆመው ታሪኩ በመነሣት ታዲያ የክርስትናው አሻራ ቁልቢ አከባቢ የደረሰው በ9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መኾኑን ልብ ይሏል፡፡
ምንጭ፡- ‹‹ግንጊልቻ›› መጽሐፍ፤ ገጽ.404-406)

❤8👍1
👆👆ልብ በሉ ከኦሮሞ እንቅስቃሴ (ኦሮሞ ክርስትናንንም እስልምናንም ሳይቀበል)
በፊት ዛሬ "ኦሮሚያ" ተብሎ በተከከለ መሬት ክርስቲያኖች ነበሩ ታላላቅ ገዳማትና አቢያተ ክርስቲያናት ነበሩ።ታሪክ እንደሚነግረን የኦሮሞ እንቅስቃሴ የጀመረው ከግራኝ አሕመድ ወረራ በኋላ(በ16መክዘ) ነው ክርስትና ደግሞ ከአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት በዚህ ምድር ነበረ ።ቤተ ክርስቲያን መሬታችንን ወረረች የሚለው የውሸት ትርክት ውኃ በላው።

❤20👍2
<<330ዓ.ም ኢትዮጵያ የኤጵስ ቆጶስ መንበር የጀመረችበት እንጂ ክርስትናን የተቀበለችበት አይደለም >>የኔታ ኀይለማርያም ዘውዱ
❤17
የከተማ መነኩሴ ሲነካ የሚንጫጩት እነ ማን ናቸው?
፩ ራሳቸው የከተማ መነኮሳት
፪ የምንኩስና መስፈርቱ ምን እንደሆነ የማያውቁ የግሪክ ልብስ የለበሰውን ሁሉ አባ የሚሉ ምዕመናን
፫ ፍትፍት ይዘው ወደ ከተማ መነኮሳት ቤት የሚንጦለጦሉ ሴቶች
፬ ከመነኮሳቱ ጋር ጥቅም የሚጋሩ
፭ የከተማ መነኮሳቱ ቤተ ክርስቲያንቱን እያዳከሙ መሆኑን የተረዱ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን

❤16👍6💯2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሁን ደግሞ "የወንጌል" ሰዓት ነው።መነኮሳቱና ካህናቱ እየተሰበኩ ነው። ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚንስትሩ ጳጳሳቱን ሰብስበው ከመጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሰ ሲሰብካቸው ነበር።ቤተ ክርስቲያናችን ከባድ ፈተና ውስጥ ናት።
😭26❤9🔥3
ከቀሲስ ዶ/ር መንግሥቱ ጎበዜ
«ሞዐ ተዋሕዶ» የማነው?
ከወቅታዊ የሀገርና የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ጎልተው ከሚነሱ አጀንዳዎች መካከል አንዱ «ሞዐ ተዋሕዶ» ነው። ስለ ንቅናቄው ግልጽና የጠራ ግንዛቤ ይኖረን ዘንድ በተረዳሁት መጠን የሚከተለውን ምልከታ ማጋራት ወደድሁ።
«ሞዐ ተዋሕዶን» በተመለከተ ብዙ ግራ መጋባቶች ይስተዋላሉ። አንዳንዶች ሆን ብለው በሚመስል ሁኔታ ከዐውዱና ከዓላማው ውጭ የሆነ መረጃ በማሰራጨት፣ ንቅናቄው የፖለቲካ ዓላማ እንዳለው አድርገው በመሳል ብዙዎችን ያሳስታሉ። እንዲያውም «ሞዐ ተዋሕዶ» በአንዳንድ የመንግሥት አካላትም ሆነ በሌሎች የቤተ ክርስቲያን ተቃዋሚዎች በኩል የሚለጠፍበት አሉታዊ ስም፣ በተግባር ከሚሠራው በጎ ሥራ ጋር በፍጹም የሚገናኝ አይደለም። ከዚያም አልፎ ስሙን የመምቻ ዱላ በማድረግ፣ ኦርቶዶክሳውያንን ለማሳቀቅ፣ ለማሰር፣ ለማሳደድና ለማጥቃት እንደ ምክንያት ሲጠቀሙበት ይስተዋላል።
ሆኖም «ሞዐ ተዋሕዶ» ምንም ዓይነት የፖለቲካ ወገንተኝነት የሌለውና ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ሊጋሩት የሚችሉትን ዓላማ ሰንቆ የሚጓዝ ግብረ-ኃይል ነው። ዋና ግቡም ቤተ ክርስቲያንን ከጥቃት፣ ከስደትና ከጥፋት መከላከል ብቻ ነው። አንዳንዶች ሞዐ ተዋሕዶን ከ«ሞአ አንበሳ» ጋር በማመሳሰል ንቅናቄውን ከንጉሣዊ ሥርዓት መመለስ ጋር ለማያያዝ የሚያደርጉት ጥረት ፈጽሞ መሠረት የለውም። የግብረ-ኃይሉን ርእይ፣ ተልዕኮ፣ ግብና ተግባር ከግለሰቦች ማንነት ጋር ማያያዝም ትክክል እንዳልሆነ ተገንዝቤአለሁ።
የ«ሞዐ ተዋሕዶ» መነሻ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት 2013 ዓ.ም. የምልዓተ ጉባኤው ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ያደረገውን ጥሪ መሠረት ያደረገ ነው። ሲኖዶሱ በምእመናንና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በመመልከት፣ ምእመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የካቲት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በይፋ ተመሠረተ።
ሞዐ ተዋሕዶ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ የሚሰነዘሩ መዋቅራዊ፣ አስተዳደራዊና ርዕዮተ-ዓለማዊ ጥቃቶችን ለመመከት የሚሠራ የጥብቅና ንቅናቄ (Advocacy Movement) ነው ማለት ይቻላል። ግብረ-ኃይሉ ለዘመናት የነበረውን «የዝምታ ስልት» በመስበር፣ የቤተ ክርስቲያኗን መብትና ድምፅ በግልጽ የሚያሰማበትን ሰላማዊ መንገድ ቀይሷል። ይህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከዝምተኛ ተከታይነት ወደ «ንቁ ተሟጋችነት» የተሸጋገሩበትን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ያመላክታል።
«ሞዐ ተዋሕዶ» ከምሥረታው ዕለት ጀምሮ ለኢትዮጵያ መንግሥትና ለሚመለከታቸው አካላት ያቀረባቸው ሰባት ዋና ዋና ጥያቄዎችን በማስተጋባት ላይ ይገኛል። እነዚህም በትምህርት፣ በሚዲያና በልማት ስም የሚሰራጩ ጸረ-ኦርቶዶክስ ትረካዎች እንዲቆሙ፣ በመንግሥት መዋቅርና በኢኮኖሚ ላይ የሚፈጸም መዋቅራዊ ማግለል እንዲያበቃ፣ ቤተ ክርስቲያንን በብሔርና በቋንቋ የመከፋፈል ፖለቲካዊ ሴራዎች እንዲገቱ፣ በምእመናን ላይ የሚፈጸሙ አካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ጥቃቶች እንዲቆሙ፣ በጥፋተኞች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ተወስዶ ለተጎጂዎች ካሳ እንዲሰጥ፣ የተፈናቀሉ ምእመናን ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ፣ እንዲሁም «አዲሲቷን ኢትዮጵያ» በመገንባት ሰበብ የሚካሄዱ ኦርቶዶክሳዊ አሻራዎችን የማጥፋት ዘመቻዎች እንዲቆሙና መንግሥት ይፋዊ የይቅርታ መግለጫ እንዲሰጥ የሚጠይቁ ናቸው።
በአጠቃላይ፣ መገንዘብ እንደቻልሁት ሞዐ ተዋሕዶ በየትኛውም ዓይነት የፖለቲካ አሰላለፍ ያልወገነ፣ ዋና ዓላማውና ትኩረቱ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻና ብቻ የሆነ ንቅናቄ ነው። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ የታሪክ እውነታ ሀገርና ቤተ ክርስቲያን ተነጣጥለው ስለማይቆሙ፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አወንታዊ አስተዋጽኦ ከማበርከት ወደ ኋላ አይልም። ሁሉም ኢትዮጵያውያን በፍቅርና በመከባበር የሚኖሩባት፣ ፍትሕ፣ እኩልነትና ነጻነት የሰፈነባት ሀገር እንድትገነባ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል።
እንደ እኔ መረዳት፣ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ እየደረሰ ያለውን ዘርፈ-ብዙ ጥቃት ለመከላከል ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ የሚያበረክቱበት የትብብር መረብ በመሆኑ «ሞዐ ተዋሕዶ» የማንም ሳይሆን የሁሉም ነው። በአሁኑ ወቅት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በህልውና አደጋ ውስጥ የምትገኝ በመሆኗና ይህንን ሰፊና መዋቅራዊ ፈተና ለመመከት ይመጥናል ተብሎ የሚታመን ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት ባለመኖሩ፣ የጎደለውን ሞልቶና የጎበጠውን አቃንቶ እንደ «ሞዐ ተዋሕዶ» ያሉ ንቅናቄዎችን መደገፍ፣ ማበረታትና ማሳደግ ከመላው ኦርቶዶክሳውያን የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው የሚል ጽኑ እምነት አለኝ።

❤20👍8
አርሲ ላይ እየሆነ ያለውን በትኩረት እየተከታተልሁ ነው። ወለጋ ላይ እነ ቄስ ዱጉማ ኡፋና ቄስ ደሲለኝ ነሞምሳን በኦነግ ሸኔ ያስገደለው ፣ቢሾፍቱ ላይ የወልዳ ዳንዲ አቦቲ(ፍኖተ አበው ማኅበር) ሰብሳቢ አቶ ንጉሤን አሳግቶ ደብዛው እንዲጠፋ ያደረገው ማፊያ ቡድን በአርሲም ያንኑ ታሪክ እንዳይደግም ያሰጋል።አሳቦቻችንና አይደግፉም የሚሉአቸውን ካህናትና ዲያቆናት ላይ በየሚዲያው "የግደለው ፍለጠው ቁርጠው" ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ናቸው።ቁጥራቸው ቀላል አይደለም ይኽን የጥፋት አጀንዳ የሚመራ ቡድን አለ።አርሲ ላይ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ላይ የሆነ ችግር ቢደርስ እነዚህም ልጆች ተጠያቂዎች ናቸው።በአዳማና በአሰላ ሆነው ይኽን የጥፋት ሴራ የሚመሩ ግለሰቦችን ከእነ ፎቶአቸው አጋልጣለሁ።
✍6👍6❤3