Eotc Task Force
7.25K subscribers
1.55K photos
348 videos
12 files
392 links
ወቅታዊ ጉዳይ
Download Telegram
Forwarded from እሷ ታማ እሱ ታማ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Ethiopia: Drone Strike on Christian Monastery Raises Questions for Abiy Ahmed | Firstpost Africa

Firstpost examines the growing fears among Ethiopia's Orthodox Christian community after a deadly drone strike reportedly hit the historic Abbay Giyorgis St. Arsema Unity Monastery in the Amhara region. Reports say the strike killed members of the monastic community and injured several others during a religious gathering. Ethiopian government sources have alleged that Fano fighters were using the monastery as a shelter, while church leaders strongly deny that any armed group was present and insist only priests, nuns and worshippers were targeted. The incident has drawn international condemnation, with the World Council of Churches calling for an independent investigation. It also comes amid broader concerns over attacks...
Alyson Le Grange explains why this incident is resonating far beyond Ethiopia, raising questions about the protection of Africa's oldest Christian heritage during war, on Firstpost Africa.
13👍3
Eotc Task Force
Photo
ኑ ለራሳችን እናልቅስ!!🥹🥹😢😢

እናታችን ቤተክርስቲያን መከራ በበዛባት ጊዜ ልጆቼ ብላ ስትጠራን መድረስ ላልቻልነው ለራሳችን እናልቅስ።

የእናት ጡት ነካሾች በዝተውባት የሚያስጥላት ፍለጋ ስትጮህ አልሰማም ብለን ዳባ ልበስ ላልነው ለራሳችን እናልቅስ። ቤተክርስቲያን ለተደቀነባት ፈተና መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ በየቀኑ አጀንዳ እየተቀበልን መከራዋን ላፀናንባት ለራሳችን እናልቅስ። አወ ለራሳችን እናልቅስ የታሪክ ተወቃሾች ለሆነው ከራሳችን ይልቅ ቤተክርስቲያን እና ክርስቶስን ማስቀደም ላቃተን ከወሬ በዘለለ ምንም ማድረግ ላልቻልነው ለራሳችን እናልቅስ!!

ቤተክርስቲያን ወላድ ዘተጽናስኪ ፈድፈደ
የሀብኪ እግዚአብሔር ዘይናዝዝ (ዘያጸንዕ) ወልደ።

©ሄሬኔዎስ ሚዲያ
😭415
የከተማ መነኮሳት( አባ  ለከርሴ) ኦርቶዶክሳዊነትን ለማጥፋት ከሚሠራ የወሀቢያና የብልጽግና ወንጌል ስብስብ  ለሆነው ኮሚሽን እየተላላኩ ነው።
7👍6😁1
ህንጻ በመደርደር፣በዓል በማድመቅ፣ነጭ ለብሶ አደባባይ ሞልቶ በመዘመር፣ማኅበር በመፈልፈል ፣በዘርና በሰፈር በመቧደን፣ተመሳስሎ በመኖር፣ከገዳዮች ጋር እየተሻሹ በመኖር፣የገዳዮችን የጥፋት ፕሮጄክት እያደነቁ በመኖር ቤተ ክርስቲያንን መታደግ አይቻልም።ቤተ ክርስቲያንን የምንታደግበት ብቸኛው መንገድ ሰማዕትነት ነው ይኽውም እውነትን መናገር ነው።
"እውነት አርነት ያወጣችኋል" ዮሐ ፰፡፴፪
👍2813
ዘግይቶ የደረሰኝ መረጃ

በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ቢርቦና ጮሌ ቀበሌ  ኪኖ የሚባል ቦታ ላይ በ24/11/2018ዓ.ም በተከፈተው ጥቃት አንድ ኦርቶዶክሳዊ በአክራሪ ሙስሊም ታጣቂዎች የተገደለ ሲሆን ትናንት በ25/11/2018ዓ.ም ጠዋት ላይ ሬሳው  ተገኝቶ ሥርዐተ ቀብሩ ተፈጽሟል።የቀበሌው ባለሥልጣናት መረጃው እንዳይወጣ ምንም ዓይነት የቪድዮና የፎቶ ቀረጻ እንዳይደረግ ክትትል ሲያደርጉ ነበር።
😭17😢61
ቤተ ክህነቱ የሥርዐቱ ሁለተኛው ጽ/ቤት ነው  የምንለው በምክንያት ነው። የከተማ አባ ኩብኩባዎች ከወሀቢያ የከፉ ናቸውና ቤተ ክርስቲያንን ከእነዚህ ማጽዳት ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም።
👍35😁95🔥2
ቤተ ክህነቱን የምተችበት 15 ምክንያቶቼ

አንባቢው  ያስተውል
👉 እኔ የምተቸው ቤተ ክህነቱን እንጂ ቤተ ክርስቲያንን አይደለም
👉ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም  የተመሠረተች ናት ፣ቤተ ክህነት ግን በሰው የተመሠረተ ነው
👉ቤተ ክርስቲያን በምድር ላይ ያለች የእግዚአብሔር መንግሥት ናት ፣ቤተ ክህነት ግን አስተዳደራዊ ሥርዐት ነው
👉ቤተ ክርስቲያን አትሳሳትም ቤተ ክህነት ግን ይሳሳታል
👉 ይኽ ጽሑፍ  ጥቂት እውነተኛ አባቶችን፣ለዓለም የሚጸልዩ ገዳማውያንን ፣በገጠር ያሉ የቤተ ክህነት መዋቅራትን አያካትትም

  የምተችበት ምክንያቶቼ፦

1) ሲኖዶሱ ከሐዋርያት ሰንሰለት ተቆርጦ  መለካዊና (ንጉሥ የወደደውን ዘመን የወለደውን የሚፈጽም)ሲሞናዊ(በእጅ መንሻ የሚሾም) ሆኗል።
2) የሲኖዶሱ መሪ መንፈስ ቅዱስ ቢሆንም አሁን ግን በትክክል  በፖለቲካ ነው እየተመራ ያለው።ቤተ ክህነቱ ሁለተኛው የሥርዐቱ ጽ/ቤት ሆኗል።
3) ስሑት ሥርዐት በተቀያየረ ቁጥር አብሮ የሚቀያየርና ነውራቸውን ገንዘቡ እያደረገ የሚኖር ስለሆነ ነው ።ደርግ ሲመጣ ማደሪያው ሆኖ ፣ኢሕዴግ ሲመጣ  ማደሪያው ሆኖ፣ ብልጽግና ሲመጣ ማደሪያው ሆኖ ቤተ ክርስቲያንን ያሳድዳታል ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን እንዳትወጣ እንቅፋት ይሆንባታል
4) የሲኖዶሱ አባላት በዘር ኮታ የተሾሙ፣ጸረ ኦርቶዶክስ  ፖለቲከኞች ቤተ ክርስቲያንቱን ያድክሙልናል በማለት በባትሪ ተፈልገው ያሾሙአቸው ናቸው።
5) የሲኖዶሱ አባላት ሀብት ማፍራት፣እንደ ኢንቬስተር በየከተማው  ፎቅ መገንባት፣በየባንኩ ብር ማከማቸት፣ስለ ደሞዝ ጭማሪ፣ስለ ሀገረ ስብከት ቅያሪ  መጨነቅ፣አውሮፓና አሜሪካ ሄዶ ዶላር  ከመሰብሰብ ውጭ ስለ ቤተ ክርስቲያን ስደት ስለ ኦርቶዶክሳውያን እልቂት  የማይገዳቸው ፈጽሞ አባታዊ ርህራሄ የማይታይባቸው ናቸው።
6)ሲኖዶሱ ነፍስ የገደሉና ያስገደሉ፣ምዕመናን በዘርና በቋንቋ የሚከፋፍሉ፣ በቅርስና ታቦት ስርቆት ሙዳየ ምፅዋት ግልበጣ ላይ የተሰማሩ ጳጳሳትን ብፅዕ ብሎ በአባልነት አቅፎ ስለያዘ
7) በኢትዮጵያ ምድር የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጸም፣ሚሊየኖች ሲሰደዱ፣ወጣቱ የቀይ ባሕር እራት የበረሃ አሞሮች ሲሳይ ሲሆን ቤተ ክህነቱ ጨውነቱንና ብርሃንነቱን አላሳየም መሪዎችን አልገሰጸም
8) ቤተ ክህነቱ  እንደ ምዕራባውያኑ ሁለመናው ቁሳዊ ሆኗል።ሚሊየኖች እየተገደሉ፣እየተፈናቀሉና እየተራቡ ፣ሚሊየኖች ከእምነት እየወጡ ስለ ህንጻ ያወራል።
9) ቤተ ክህነቱ ቅድስና ጠል፣እውነት ጠል ፣ሊቃውንት ጠል ነው። ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት የማይታይባቸው፣እውነትን የሚያሳድዱ፣ እውነተኛ ሊቃውንትን የሚያሳድዱ  አቅመቢስ ሰዎች የተሰበሰቡት ነው።ወይ አይጠይቁ ወይ አይጠየቁ፣ወይ አያውቁ ወይ አያሳውቁ፣ወይ አይማሩ ወይ አያስተምሩ፣ወይ አይረዱ ወይ አያስረዱ....።ግራ የገባው ነገር።
10)  የቤተ ክርስቲያን ገንዘቧና ፍትፍቷ ስለሚመች፣ምዕመናንም እንደ ፈረንጅ ላም ለመታለብ ስለሚመቹ በውስጧ ይኖራሉ እንጂ መዋቅሯን የተቆጣጠሩ አብዛኞቹ  ኢአማንያን ናቸው።

11)  ቤተ ክህነቱ ደሃ ጠል ነው።
    👉 ቅድስና እና እውቀት ኖሮት ገንዘብ የሌለው  መነኩሴ ለጵጵስና አይታጭም
👉  የፈለገ ሊቅ ቢሆን ገንዘብ ወይም ዘመድ ከሌለው አይቀርጠም።አዲስ አባባ ሎቶሪ የሚያዞር፣ውዳሴ ማርያም የሚሸጥውን ሊቅ ቤት ይቁጠረው።
👉 ገንዘብ ወይም ዘመድ የሌለው ካህን ዲያቆን አይቀጠርም።
👉ድሃ ሰው ወደ አገልግሎት አይቀርብም
👉 ድሃ ሰው፦ ልጁን ክርስትና ለማስነሳት ይቸገራል፣ቢሞትም የመቃብር ቦታ ለማግኘት መከራ ነው። 👉ክብረ ንጽህናቸውን ጠብቀው በተክሊል ለማግባት የሚፈልጉ ነገር ግን  ገንዘብ የሌላቸው ወጣቶች ይገፋሉ ማንም ዞር ብሎ የሚያያቸው ሰው የለም።በጓደኞቼ ላይ የሆነውን እኔ ራሴው ምስክር ነኝ።
👉 በ ቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ላይ የሚቀመጡ ነዳያንን እንደ ሰው ቆጥሮአቸው ፣መምህርና የንስሐ አባት የሚመድብላቸው የለም።መንግሥተ ሰማያት ለእነርሱ የማትገባ ሆኖ ነው?  የተሻለ ሥጋዊ ኑሮ እንዲኖራቸው አይሠሩም ለይስሙላ በዓላት ሲመጡ ሕዝብ አስጨንቀው ጥቂት ነገር ይሰጣቸዋል ።ይህንን እምነት የሌሉውም ያደርገዋል።
13) ሁሉንም የግል ባንኮችን ሳይጨምር ንግድ ባንክ ያለው ገንዘብ40% የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደሆነ ይነገራል።በዚህ ገንዘብ ፋብሪካዎችን ከፍቶ
👉 ተመርቆ ሥራ አጥቶ የሚሰቃየውን ወጣት፣በኢኮኖሚ እጥረት ትዳር መመሥረት  ያልቻለውን ወጣት ማገዝ ሲገባቸው፣በችግር ምክንያት እምነቱን የሚቀይር እንዳይኖር መሥራት ሲገባቸው ገንዘቡን ግን እንዳሻቸው የሚጫወቱበት ጥቂት ግለሰቦች ናቸው፣የሚለወጡበት ጸረ ኦርቶዶክስ ተቋማት ናቸው።ንግድ ባንክ ሌሎች ቤተ እምነቶችን የሚረዳ ኦርቶዶክስን ግን የሚጠላ ነው።ከደሃው ሕዝብ ኪስና መቀነት የተሰበሰበን ገንዘብ ለእንደዚህ ዓይነት ተቋማት መበልጸጊያ ማድረግ ማድረግ ከስህተትም በላይ ስሕተት ነው።አሁንማ መንግሥትም ማንንም ማስፈቀድ ሳይጠበቅበት እየዘረፈ ይገኛል

14) ፖለቲከኞች ቤተ ክርስቲያንቱን ለመምታት እንደ መዶሻ የሚጠቀሙበት "የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ"የሚባል ጸረ ኦርቶዶክስ  ተቋም  አባል ሆኖ ቤተ ክርስቲያንቱን እየበደላት ይገኛል።
15)አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ቤተ ክህነቱ ቤተ ክርስቲያንቱን ማሻገር አይችልም።በተግባር ከገዳይ ጎን ተሰልፎ በኦርቶዶክሳውያን እልቂት እየተሳለቀ ይገኛል።

መፍትሔ ምንድን ነው?
👉ቤተ ክህነቱ በሁለቱ በሁለት ማለያ መጫወቱን አቁሞ ሚናውን መለየት አለበት ።ወይ የቤተ ክርስቲያን መሆን ወይ ደግሞ ሀብቶቿን ምልክቶቿን አስቀምጦ ወደዚያው መቀላቀል።
👉 ኦርቶዶክሳዊው ማኅበረሰብ በጭፍን መንጋነት ከመነዳት ወጥቶ ቤተ ክህነቱ ወደ መስመር እንዲመለስ የራሱን ተፅዕና ማድረግ አለበት
👉የኦርቶዶክሳውያን መከራ የማይገዳቸው ምንደኞችን አባት ብሎ አለመከተል
👉 ጧፍ እጣን ለሌላቸው ፣በሴቶች ቀሚስ ለሚቀደስባቸው ለገጠር አቢያተ ክርስቲያናት ካልሆነ በቀር እንደ ካፒታሊስት ለሚያደርጋቸው  ለከተሜዎች ምንም ዓይነት ገንዘብ አለመስጠት
👉እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሊቃውንትን ወደ ፊት ማምጣትና የቤተ ክርስቲያን ልዕልና እንዲጠበቅ በጋራ ተጋድሎ ማድረግ

ኢዮሳፍጥ ጌታቸው
https://t.me/Eyo21e
19👍4
Forwarded from ኢዮሳፍጥ (ኀይለሚካኤል)
clergy.pdf
88.3 KB
Forwarded from ኢዮሳፍጥ (ኀይለሚካኤል)
1
ኦርቶዶክሳዊነትን ማስቀጠል የምንችለው ኦርቶዶክሳዊ ልቡና ሲኖርን ብቻ ነው።ቁማርተኛ፣ዘረኛ፣ጎጠኛ ፣ባዕድ ናፋቂ እና ጥቅም ፈላጊ ነጻ ሊያወጣን አይችልም።
👍37👏1
😭በጻድቃኔ ማርያም ገዳም እግዚአብሔርን ደጅ እየጠኑ ያሉ እመቤታችንን እየተማጸኑ የነበሩ ምዕመናን በደረሰው አደጋ ከ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉን እየሰማን ነው

ነገሩ ሁሉ በጨለማ ላይ የገደል የዛፍ ጥላ ሁኖብናል

በዱር በገደሉ በመላው የኢትዮጵያ ምድር የሚወድቀው በጦርነት የሚያልቀው ህዝብ ሰሞኑን በድሮን በተጨፈጨፉ መነኮሳት ገዳማውያን በየቀኑ እያስለቀሰን

ዛሬ ደግሞ በጻድቃኔ ገዳም ይህን ስንሰማ አዕምሯችን ተጨነቀ በጨለማ ላይ የገደል ጥላ ሆነብን 😭

እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማርልን 😭
😢24😭222
አሳዛኝ ዜና !

በ ደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም ድንገት በተከሰተ ርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰው ሕይወት ሲያልፍ በ5 ሰው ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ መሪር ኀዘን ተሰምቶናል።
__

በጌታ የሚሞቱ ብፁዓን ናቸው ። ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ሥራቸው ይከተላቸዋልና። ራዕ ፲፫ ÷ ፲፬

ከክረምቱ መግባት ጋር ተያይዞ በተከሰተው ከፍተኛ የዝናብ መዝነብና የመባርቅት ድምፅ በታላቋ ገዳማችን በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት አደጋ በድንገት በመከሰቱ ለጸበል ፣ ለሱባኤና ለመሳለም ከአራቱም አቅጣጫ በተሰበሰቡ በጻድቃኔ ማርያም ልጆችና ወዳጆች ላይ እጅግ አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ ኀዘን በመድረሱ ከፍተኛ ኀዘን ተሰምቶናል ።

በዚህ አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ ድንገተኛ አደጋም የ14 ወገኖቻችን ሕይወት ሲያልፍ በ3 ወገኖቻችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት በሁለት ወገኖቻችን ላይ መለስተኛ ጉዳት ደርሶብን በከፍተኛ የመርዶ ኀዘን ውስጥ እንገኛለን ።

በዚህ ሰኣት የሀገረ ስብከታችን ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሌምንጦስ በስፍራው በመገኘት ለሞቱ ወገኖቻችን ጸሎተ ፍትሐት ለተጎዱት ጸሎት ላዘኑ ወገኖቻችን የማጽናኛ ትምህርተ ወንጌልና አባታዊ ቃለ በረከት በመስጠት ላይ ይገኛሉ ።

በዚህ አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ መርዶ ሀገረ ስብከታችን የተሰማውን ጥልቅና መሪር ኀዘን እየገለጽን እግዚአብሔር አምላክ ለሞቱ ወገኖቻችን እረፍተ ነፍስን ለተጎዱት ፈውስን ላዘኑት መጽናናትን ይሰጥልን ዘንድ ከዕንባ ጭምር ጋር ከልባችን እንመኛለን።

© ነቅዐ ጥበብ ነቅዐ ጥበብ
💔3113😭5😢3😁1
👉👂👂👂👂👂
👍326
👉👂👂👂👂👂
👍289
Eotc Task Force pinned a voice message
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፖለቲከኞችን መቃወም  ይቻላል ሕዝብን እንደ ሕዝብ መሳደብ  ግን ከኀጢአት ሁሉ የከፋ ኀጢአት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ኦርቶዶክሳዊውን ማኅበረሰብ ማዋረድ የተለመደ ሆኑአል።ይኽን ጥፋት የሚመራው ደግሞ ሥርዐቱ ነው። ወጣቶቹ የሚሉትን ልተርጉምላችሁ፦
"ትግሬ  ሸ*ር*ሙ*ጣ ትውልድ"
"ትግሬ  የእናትህ እንትን"
"ትግሬ የአህያ ፔሬድ"

እንዲህ ዓይነት  መረን የለቀቀ የድንቁርና አካሄድ ነገ ብዙ ዋጋ ያስከፍላልና ቆም ብሎ ማሳቡ ይሻላል።
😢20😱41🥰1
👆"ሀገረ ትግራይ" የተሰኘ መጽሐፍ ነገር

ቅዳሜ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ጠዋት፣ "ሆሄ ምዕራፍ" ባዘጋጀው የመጽሐፍ ውይይት መርሐ ግብር ላይ ታድሜ ነበር። ስለ መጽሐፉ ጠቀሜታ መነጋገር የሚፈልግ ሰው በየቤቱ መወያየት ይችላል፤ እኔ ግን በውይይቱ ወቅት የመጽሐፉን ጠቀሜታ ለማስረዳት የተሰጠኝ ጊዜ አይበቃኝም ብዬ በማሰቤ፣ በቀጥታ ቢስተካከል የምላቸውን አስተያየት ሰጥቻለሁ። የሰጠሁት አስተያየት በከፊል የሚከተለው ነበር።

"ሀገረ ትግራይ" የተባለው መጽሐፍ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ሃይማኖትና ታሪክ ያዛባ መጽሐፍ ነው።

1) መጽሐፉ "የደቂቀ እስጢፋኖስ እንቅስቃሴ ማርያምን ጨምሮ ጻድቃንንም ማምለክ የሚያወግዝ ነበር" ይላል።

የደቂቀ እስጢፋኖስ እንቅስቃሴ ማርያምን ጨምሮ ጻድቃንን ማምለክን የሚያወግዝ አልነበረም። አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ አምልኮ ለሥላሴ ብቻ እንደሚገባ ጠንቅቀው ያውቁ ነበር። ቅድስት ድንግል ማርያምን አያመልኩም ነበር፤ ነገር ግን እንደ ማናቸውም የኦርቶዶክስ አማኝ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናት መሆኗንና አማላጅነቷን ያምኑ፣ ያከብሯትም ነበር። ይሁን እንጂ "ለቅዱሳት ሥዕላት እና ለመስቀል አንሰግድም" የሚል አቋም ነበራቸው። "ዘመናዊ ነበሩ" በሚል እሳቤ ስለ ሴቶች መብት ይሟገቱ ነበር ተብሎ በመጽሐፉ የተጠቀሰውም ሐሰት ነው። በተጨማሪም እንቅስቃሴው በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ:(1426-1460 ዓ.ም.) ዘመን የተጀመረ ሳይሆን፣ ከዚያ በፊት የነበረና ከዘርዐ ያዕቆብ የሚቀድም ነው።

2) የቤተክርስቲያናችን እምነት "ተዋሕዶ" እያለ ግን መጽሐፉ "ሞኖፊሳይት" ወይም "አውጣኪያዊ" ያደርገናል።

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የ"ተዋሕዶ" ትምህርትን የምትከተል በመሆኗ፣ Miaphysite የሚለው ነገረ መለኮታዊ ቃል ይገልጻታል። ይህም ማለት ከሁለት ባሕርይ የተዋሐደ "አንድ" ማለት ነው፤ ለምሳሌ ሰው አንድ ቢባልም፣ አንድነቱ ነጠላ ሳይሆን ከነፍስና ከሥጋ ተዋሕዶ የተገኘ አንድነት (Mia) እንደሆነ ማለት ነው። አብዛኞቹ የውጭ አገር ጸሐፊያን እምነታችንን በስህተት "ሞኖፊዛይት" (Monophysite) ይሉታል። "Monophysite" ማለት ግን ነጠላ አንድ ባሕርይ ማለት ሲሆን፣ ይህም የአውጣኪ ክህደት አስተሳሰብ ነው። ስለዚህ ተዋሕዶን ለመግለጽ "Monophysite" የሚለውን ቃል መጠቀም የለብንም። በ"ሀገረ ትግራይ" መጽሐፍ ላይ ያለው መሠረታዊ ችግር፣ የቤተክርስቲያናችንን እምነት እንደ አውጣኪ አስተሳሰብ አስመስሎ መጻፉ ነው።

3)"ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ክብረ ነገሥት ቅዱስ ነው" እያለ በጽሑፉ ሐሰት አስፍሯል።

ይህ አባባል ፍጹም ስህተት ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍት የምትላቸው በግልጽ የታወቁ ናቸው፤ «ክብረ ነገሥት» የተባለውን መጽሐፍ ግን ፈጽሞ እንደ ቅዱስ መጽሐፍ አትቆጥረውም። ቅዱሳት መጻሕፍት የሃይማኖት ትምህርት መሠረቶች ናቸው። «ክብረ ነገሥት» ግን በይዘቱ አገራዊ ትርክትን፣ ትውፊትንና ማኅበራዊ እሳቤዎችን የያዘ መጽሐፍ ነው። ቤተክርስቲያኗ የራሷ የሆነና 81 መጻሕፍትን ያካተተ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ቀኖና አላት። «ክብረ ነገሥት» በዚህ በ81ዱ ቅዱሳት መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥም ሆነ በአዋልድ መጻሕፍት ምድብ ውስጥ አይካተትም።

4) "ዐፄ ዮሐንስ በቦሩ ሜዳ ጉባኤ የቅባት እምነት አወጁ"

የቦሩ ሜዳ ጉባኤ በኢትዮጵያ የታሪክና የሃይማኖት ጉዞ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠውና በግንቦት 1870 ዓ.ም. የተካሄደ ታሪካዊ ክንውን ነው። የጉባኤው አስተባባሪና መሪ ዐፄ ዮሐንስ አራተኛ ነበሩ። በዚህ ጉባኤ ላይ ሰፊ ክርክር ከተደረገ በኋላ ንጉሡ ያወጁት የ«ተዋሕዶ» እምነትን እንጂ የ«ቅባት» እምነትን አልነበረም። ይህ ጉባኤ "ክርስቶስ ሦስት ልደት አሉት፤ ይኸውም ከአብ ቅድመ ዓለም፣ ከድንግል ማርያም በሥጋ፣ እና በማኅፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ መቀባት የጸጋ ልጅ ሆኗል" የሚለውንና «የጸጋ ልጅ» ወይም «ሦስት ልደት» ተብሎ የሚጠራውን ትምህርት ውድቅ የተደረገበት ነበር።

5) "የሲሶ መንግስት/መሬት ለቤተክርስቲያን ተሰጥቷት ነበር"

ይህ እሳቤ በታሪክ እውነትነት የሌለው ነው። ከፈጠራ ትርክት የመነጨ ነው። በታሪክ ሂደት ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመንግሥት ጋር የጠበቀ ቁርኝት የነበራት ቢሆንም፣ የሀገሪቱን አንድ ሦስተኛ (ሲሶ) የፖለቲካ ሥልጣን ወይም መሬት በይፋ ተረክባ የምታስተዳድርበት ሕጋዊ መዋቅር በታሪክ አልነበረም። ይህንን ለመረዳት ቢያንስ የቅርብ ጊዜ ጥናት የሆነውን «ኢትዮጵያዊ ሱራፊ» የተሰኘውን መጽሐፍ መመልከት በቂ ነው። በቂ ማስረጃ በሌለው ሐሰተኛ ትርክት ላይ ተቸንክሮ ዕድሜ ልክን መጻፍ ተገቢ አይደለም።

6) "ክርስትና በፍሬምናጦስ ወደ ኢትዮጵያ ገባ።"

ብዙ ጸሐፊያን ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው በ4ኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ አድርገው ያቀርባሉ። ሆኖም ግን ክርስትና በ1ኛው ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ አማካኝነት በአገሪቱ መሰበኩንና መጀመሩን ማወቅ ያስፈልጋል። የመጽሐፍ ቅዱስ አካል የሆነው የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የተመዘገበውን ታሪክ ማስተባበል ካልተቻለ በቀር፣ ክርስትና በኢትዮጵያ የጀመረው በኢዛና ዘመን በ4ኛው ክፍለ ዘመን ነበር ማለት ስህተት ነው።

7) "አል ነጃሽ የሰለመ የአክሱም ንጉሥ ነበር"

በቂና አሳማኝ ማስረጃ ሳይቀርብ ንጉሡ "ሰልመዋል" የሚል ፍርደ ገምድል ብያኔ መስጠት ተገቢ አይደለም። ታሪክ ተመራማሪዎች ንጉሡ ሙሉ በሙሉ ወደ እስልምና መለወጣቸውን የሚያሳይ ገለልተኛ የታሪክም ሆነ የአርኪኦሎጂ ማስረጃ የለም እያሉ ነው። በተጨማሪም የአክሱም ነገሥታት ሳንቲሞች በሙሉ የክርስትና ምልክት መስቀል ያረፈባቸው እንጂ የእስልምና ምልክት የሌለባቸው በመሆኑ፣ ንጉሡ እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ የክርስቲያን መንግሥት መሪ ነበሩ ተብሎ በታሪክ ተመራማሪዎች ዘንድ ይታመናል።

8)ፕ/ር ታደሰ ታምራት "በአክሱም ሥልጣኔ ዘመን የነበሩት ሰዎች የትግረ እና የትግርኛ ተናጋሪዎች ነበሩ" ብለዋል መባሉ ሐሰት ነው። በተጠቀሰው "Church and State in Ethiopia" መጽሐፋቸው ላይ ይህንን አላሉም። እንዲያውም የ"አክሱም" የቃል ትርጉም ራሱ የሚያስረዳው የራሱ የሆነ የታሪክ ሐሳብ አለው። ስለዚህ የዘመናችንን የሕዝብ አሰፋፈር በመመልከት ብቻ በአክሱም ሥልጣኔ ዘመን የነበረው ሕዝብና ቋንቋ፣ አሁን ቦታውን የያዘው ሕዝብና ቋንቋ ተናጋሪ ነው ማለት አይቻልም።

መሰል መጻሕፍት እንደ ዋና ማጣቀሻ እየቀረቡ ሐሰተኛ ትርክቶችን ከመፍጠራቸው በፊት፣ አስቀድሞ በቂ ግምገማና አስተያየት ቢሰጥባቸው መልካም ነው። ትንሽ መስላ የምትታየን ስህተት ውሎ አድሮ በተሳሳተ እሳቤ ሥር ትሰዳለችና።

ዲ/ን ዮሴፍ ፍስሐ
28👍1🥰1
8👎4
ዘግይቶ የደረሰኝ መረጃ(አርሲ በአክራሪ የእስልምና ታጣቂዎች ስለተገደሉ ኦርቶዶክሳውያን)

፩   በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ሰንጎ ያያ ቀበሌ  በ24/11/2018ዓ.ም አባቱ ተገድሎ  የነበረው አቡሌ ክፍሌ ከታገተበት ተገድሎ ተጥሎ ትናንት በ27/11/2018ዓ.ም ሥርዓተ ቀብሩ በጋዶ ማርያም ቤተክርስቲያን ተፈጽሞአል

፪ ትናንት ሐምሌ 27/2018ዓ.ም  በጉና ወረዳ ገበያ ውለው  ሲመለሱ የነበሩ ኦርቶዶክሳውያን " መሶ" የሚባል ቦታ ላይ ሲደርሱ ጥቃት ተከፍቶባቸው 3 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን 30   ሴቶችም ታግተው ተወስደዋል

፫ በመርቲ ወረዳ  ላይ ሰሞኑን  አንድ ኦርቶዶክሳዊ  ተገድሏል
💔24😢18🔥3
ሕዝባችን ሞትን ስደትን፣መገፋትን ተለማምዶታል።ይኽ ደግሞ ገና ብዙ ዋጋ ያስከፍለናል።
💔23😢64