Eotc Task Force
7.25K subscribers
1.55K photos
348 videos
12 files
392 links
ወቅታዊ ጉዳይ
Download Telegram
Forwarded from እሷ ታማ እሱ ታማ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Ethiopia: Drone Strike on Christian Monastery Raises Questions for Abiy Ahmed | Firstpost Africa

Firstpost examines the growing fears among Ethiopia's Orthodox Christian community after a deadly drone strike reportedly hit the historic Abbay Giyorgis St. Arsema Unity Monastery in the Amhara region. Reports say the strike killed members of the monastic community and injured several others during a religious gathering. Ethiopian government sources have alleged that Fano fighters were using the monastery as a shelter, while church leaders strongly deny that any armed group was present and insist only priests, nuns and worshippers were targeted. The incident has drawn international condemnation, with the World Council of Churches calling for an independent investigation. It also comes amid broader concerns over attacks...
Alyson Le Grange explains why this incident is resonating far beyond Ethiopia, raising questions about the protection of Africa's oldest Christian heritage during war, on Firstpost Africa.
13👍3
Eotc Task Force
Photo
ኑ ለራሳችን እናልቅስ!!🥹🥹😢😢

እናታችን ቤተክርስቲያን መከራ በበዛባት ጊዜ ልጆቼ ብላ ስትጠራን መድረስ ላልቻልነው ለራሳችን እናልቅስ።

የእናት ጡት ነካሾች በዝተውባት የሚያስጥላት ፍለጋ ስትጮህ አልሰማም ብለን ዳባ ልበስ ላልነው ለራሳችን እናልቅስ። ቤተክርስቲያን ለተደቀነባት ፈተና መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ በየቀኑ አጀንዳ እየተቀበልን መከራዋን ላፀናንባት ለራሳችን እናልቅስ። አወ ለራሳችን እናልቅስ የታሪክ ተወቃሾች ለሆነው ከራሳችን ይልቅ ቤተክርስቲያን እና ክርስቶስን ማስቀደም ላቃተን ከወሬ በዘለለ ምንም ማድረግ ላልቻልነው ለራሳችን እናልቅስ!!

ቤተክርስቲያን ወላድ ዘተጽናስኪ ፈድፈደ
የሀብኪ እግዚአብሔር ዘይናዝዝ (ዘያጸንዕ) ወልደ።

©ሄሬኔዎስ ሚዲያ
😭415
የከተማ መነኮሳት( አባ  ለከርሴ) ኦርቶዶክሳዊነትን ለማጥፋት ከሚሠራ የወሀቢያና የብልጽግና ወንጌል ስብስብ  ለሆነው ኮሚሽን እየተላላኩ ነው።
7👍6😁1
ህንጻ በመደርደር፣በዓል በማድመቅ፣ነጭ ለብሶ አደባባይ ሞልቶ በመዘመር፣ማኅበር በመፈልፈል ፣በዘርና በሰፈር በመቧደን፣ተመሳስሎ በመኖር፣ከገዳዮች ጋር እየተሻሹ በመኖር፣የገዳዮችን የጥፋት ፕሮጄክት እያደነቁ በመኖር ቤተ ክርስቲያንን መታደግ አይቻልም።ቤተ ክርስቲያንን የምንታደግበት ብቸኛው መንገድ ሰማዕትነት ነው ይኽውም እውነትን መናገር ነው።
"እውነት አርነት ያወጣችኋል" ዮሐ ፰፡፴፪
👍2813
ዘግይቶ የደረሰኝ መረጃ

በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ቢርቦና ጮሌ ቀበሌ  ኪኖ የሚባል ቦታ ላይ በ24/11/2018ዓ.ም በተከፈተው ጥቃት አንድ ኦርቶዶክሳዊ በአክራሪ ሙስሊም ታጣቂዎች የተገደለ ሲሆን ትናንት በ25/11/2018ዓ.ም ጠዋት ላይ ሬሳው  ተገኝቶ ሥርዐተ ቀብሩ ተፈጽሟል።የቀበሌው ባለሥልጣናት መረጃው እንዳይወጣ ምንም ዓይነት የቪድዮና የፎቶ ቀረጻ እንዳይደረግ ክትትል ሲያደርጉ ነበር።
😭17😢61
ቤተ ክህነቱ የሥርዐቱ ሁለተኛው ጽ/ቤት ነው  የምንለው በምክንያት ነው። የከተማ አባ ኩብኩባዎች ከወሀቢያ የከፉ ናቸውና ቤተ ክርስቲያንን ከእነዚህ ማጽዳት ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም።
👍35😁95🔥2
ቤተ ክህነቱን የምተችበት 15 ምክንያቶቼ

አንባቢው  ያስተውል
👉 እኔ የምተቸው ቤተ ክህነቱን እንጂ ቤተ ክርስቲያንን አይደለም
👉ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም  የተመሠረተች ናት ፣ቤተ ክህነት ግን በሰው የተመሠረተ ነው
👉ቤተ ክርስቲያን በምድር ላይ ያለች የእግዚአብሔር መንግሥት ናት ፣ቤተ ክህነት ግን አስተዳደራዊ ሥርዐት ነው
👉ቤተ ክርስቲያን አትሳሳትም ቤተ ክህነት ግን ይሳሳታል
👉 ይኽ ጽሑፍ  ጥቂት እውነተኛ አባቶችን፣ለዓለም የሚጸልዩ ገዳማውያንን ፣በገጠር ያሉ የቤተ ክህነት መዋቅራትን አያካትትም

  የምተችበት ምክንያቶቼ፦

1) ሲኖዶሱ ከሐዋርያት ሰንሰለት ተቆርጦ  መለካዊና (ንጉሥ የወደደውን ዘመን የወለደውን የሚፈጽም)ሲሞናዊ(በእጅ መንሻ የሚሾም) ሆኗል።
2) የሲኖዶሱ መሪ መንፈስ ቅዱስ ቢሆንም አሁን ግን በትክክል  በፖለቲካ ነው እየተመራ ያለው።ቤተ ክህነቱ ሁለተኛው የሥርዐቱ ጽ/ቤት ሆኗል።
3) ስሑት ሥርዐት በተቀያየረ ቁጥር አብሮ የሚቀያየርና ነውራቸውን ገንዘቡ እያደረገ የሚኖር ስለሆነ ነው ።ደርግ ሲመጣ ማደሪያው ሆኖ ፣ኢሕዴግ ሲመጣ  ማደሪያው ሆኖ፣ ብልጽግና ሲመጣ ማደሪያው ሆኖ ቤተ ክርስቲያንን ያሳድዳታል ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን እንዳትወጣ እንቅፋት ይሆንባታል
4) የሲኖዶሱ አባላት በዘር ኮታ የተሾሙ፣ጸረ ኦርቶዶክስ  ፖለቲከኞች ቤተ ክርስቲያንቱን ያድክሙልናል በማለት በባትሪ ተፈልገው ያሾሙአቸው ናቸው።
5) የሲኖዶሱ አባላት ሀብት ማፍራት፣እንደ ኢንቬስተር በየከተማው  ፎቅ መገንባት፣በየባንኩ ብር ማከማቸት፣ስለ ደሞዝ ጭማሪ፣ስለ ሀገረ ስብከት ቅያሪ  መጨነቅ፣አውሮፓና አሜሪካ ሄዶ ዶላር  ከመሰብሰብ ውጭ ስለ ቤተ ክርስቲያን ስደት ስለ ኦርቶዶክሳውያን እልቂት  የማይገዳቸው ፈጽሞ አባታዊ ርህራሄ የማይታይባቸው ናቸው።
6)ሲኖዶሱ ነፍስ የገደሉና ያስገደሉ፣ምዕመናን በዘርና በቋንቋ የሚከፋፍሉ፣ በቅርስና ታቦት ስርቆት ሙዳየ ምፅዋት ግልበጣ ላይ የተሰማሩ ጳጳሳትን ብፅዕ ብሎ በአባልነት አቅፎ ስለያዘ
7) በኢትዮጵያ ምድር የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጸም፣ሚሊየኖች ሲሰደዱ፣ወጣቱ የቀይ ባሕር እራት የበረሃ አሞሮች ሲሳይ ሲሆን ቤተ ክህነቱ ጨውነቱንና ብርሃንነቱን አላሳየም መሪዎችን አልገሰጸም
8) ቤተ ክህነቱ  እንደ ምዕራባውያኑ ሁለመናው ቁሳዊ ሆኗል።ሚሊየኖች እየተገደሉ፣እየተፈናቀሉና እየተራቡ ፣ሚሊየኖች ከእምነት እየወጡ ስለ ህንጻ ያወራል።
9) ቤተ ክህነቱ ቅድስና ጠል፣እውነት ጠል ፣ሊቃውንት ጠል ነው። ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት የማይታይባቸው፣እውነትን የሚያሳድዱ፣ እውነተኛ ሊቃውንትን የሚያሳድዱ  አቅመቢስ ሰዎች የተሰበሰቡት ነው።ወይ አይጠይቁ ወይ አይጠየቁ፣ወይ አያውቁ ወይ አያሳውቁ፣ወይ አይማሩ ወይ አያስተምሩ፣ወይ አይረዱ ወይ አያስረዱ....።ግራ የገባው ነገር።
10)  የቤተ ክርስቲያን ገንዘቧና ፍትፍቷ ስለሚመች፣ምዕመናንም እንደ ፈረንጅ ላም ለመታለብ ስለሚመቹ በውስጧ ይኖራሉ እንጂ መዋቅሯን የተቆጣጠሩ አብዛኞቹ  ኢአማንያን ናቸው።

11)  ቤተ ክህነቱ ደሃ ጠል ነው።
    👉 ቅድስና እና እውቀት ኖሮት ገንዘብ የሌለው  መነኩሴ ለጵጵስና አይታጭም
👉  የፈለገ ሊቅ ቢሆን ገንዘብ ወይም ዘመድ ከሌለው አይቀርጠም።አዲስ አባባ ሎቶሪ የሚያዞር፣ውዳሴ ማርያም የሚሸጥውን ሊቅ ቤት ይቁጠረው።
👉 ገንዘብ ወይም ዘመድ የሌለው ካህን ዲያቆን አይቀጠርም።
👉ድሃ ሰው ወደ አገልግሎት አይቀርብም
👉 ድሃ ሰው፦ ልጁን ክርስትና ለማስነሳት ይቸገራል፣ቢሞትም የመቃብር ቦታ ለማግኘት መከራ ነው። 👉ክብረ ንጽህናቸውን ጠብቀው በተክሊል ለማግባት የሚፈልጉ ነገር ግን  ገንዘብ የሌላቸው ወጣቶች ይገፋሉ ማንም ዞር ብሎ የሚያያቸው ሰው የለም።በጓደኞቼ ላይ የሆነውን እኔ ራሴው ምስክር ነኝ።
👉 በ ቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ላይ የሚቀመጡ ነዳያንን እንደ ሰው ቆጥሮአቸው ፣መምህርና የንስሐ አባት የሚመድብላቸው የለም።መንግሥተ ሰማያት ለእነርሱ የማትገባ ሆኖ ነው?  የተሻለ ሥጋዊ ኑሮ እንዲኖራቸው አይሠሩም ለይስሙላ በዓላት ሲመጡ ሕዝብ አስጨንቀው ጥቂት ነገር ይሰጣቸዋል ።ይህንን እምነት የሌሉውም ያደርገዋል።
13) ሁሉንም የግል ባንኮችን ሳይጨምር ንግድ ባንክ ያለው ገንዘብ40% የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደሆነ ይነገራል።በዚህ ገንዘብ ፋብሪካዎችን ከፍቶ
👉 ተመርቆ ሥራ አጥቶ የሚሰቃየውን ወጣት፣በኢኮኖሚ እጥረት ትዳር መመሥረት  ያልቻለውን ወጣት ማገዝ ሲገባቸው፣በችግር ምክንያት እምነቱን የሚቀይር እንዳይኖር መሥራት ሲገባቸው ገንዘቡን ግን እንዳሻቸው የሚጫወቱበት ጥቂት ግለሰቦች ናቸው፣የሚለወጡበት ጸረ ኦርቶዶክስ ተቋማት ናቸው።ንግድ ባንክ ሌሎች ቤተ እምነቶችን የሚረዳ ኦርቶዶክስን ግን የሚጠላ ነው።ከደሃው ሕዝብ ኪስና መቀነት የተሰበሰበን ገንዘብ ለእንደዚህ ዓይነት ተቋማት መበልጸጊያ ማድረግ ማድረግ ከስህተትም በላይ ስሕተት ነው።አሁንማ መንግሥትም ማንንም ማስፈቀድ ሳይጠበቅበት እየዘረፈ ይገኛል

14) ፖለቲከኞች ቤተ ክርስቲያንቱን ለመምታት እንደ መዶሻ የሚጠቀሙበት "የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ"የሚባል ጸረ ኦርቶዶክስ  ተቋም  አባል ሆኖ ቤተ ክርስቲያንቱን እየበደላት ይገኛል።
15)አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ቤተ ክህነቱ ቤተ ክርስቲያንቱን ማሻገር አይችልም።በተግባር ከገዳይ ጎን ተሰልፎ በኦርቶዶክሳውያን እልቂት እየተሳለቀ ይገኛል።

መፍትሔ ምንድን ነው?
👉ቤተ ክህነቱ በሁለቱ በሁለት ማለያ መጫወቱን አቁሞ ሚናውን መለየት አለበት ።ወይ የቤተ ክርስቲያን መሆን ወይ ደግሞ ሀብቶቿን ምልክቶቿን አስቀምጦ ወደዚያው መቀላቀል።
👉 ኦርቶዶክሳዊው ማኅበረሰብ በጭፍን መንጋነት ከመነዳት ወጥቶ ቤተ ክህነቱ ወደ መስመር እንዲመለስ የራሱን ተፅዕና ማድረግ አለበት
👉የኦርቶዶክሳውያን መከራ የማይገዳቸው ምንደኞችን አባት ብሎ አለመከተል
👉 ጧፍ እጣን ለሌላቸው ፣በሴቶች ቀሚስ ለሚቀደስባቸው ለገጠር አቢያተ ክርስቲያናት ካልሆነ በቀር እንደ ካፒታሊስት ለሚያደርጋቸው  ለከተሜዎች ምንም ዓይነት ገንዘብ አለመስጠት
👉እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሊቃውንትን ወደ ፊት ማምጣትና የቤተ ክርስቲያን ልዕልና እንዲጠበቅ በጋራ ተጋድሎ ማድረግ

ኢዮሳፍጥ ጌታቸው
https://t.me/Eyo21e
19👍4
Forwarded from ኢዮሳፍጥ (ኀይለሚካኤል)
clergy.pdf
88.3 KB
Forwarded from ኢዮሳፍጥ (ኀይለሚካኤል)
1
ኦርቶዶክሳዊነትን ማስቀጠል የምንችለው ኦርቶዶክሳዊ ልቡና ሲኖርን ብቻ ነው።ቁማርተኛ፣ዘረኛ፣ጎጠኛ ፣ባዕድ ናፋቂ እና ጥቅም ፈላጊ ነጻ ሊያወጣን አይችልም።
👍37👏1
😭በጻድቃኔ ማርያም ገዳም እግዚአብሔርን ደጅ እየጠኑ ያሉ እመቤታችንን እየተማጸኑ የነበሩ ምዕመናን በደረሰው አደጋ ከ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉን እየሰማን ነው

ነገሩ ሁሉ በጨለማ ላይ የገደል የዛፍ ጥላ ሁኖብናል

በዱር በገደሉ በመላው የኢትዮጵያ ምድር የሚወድቀው በጦርነት የሚያልቀው ህዝብ ሰሞኑን በድሮን በተጨፈጨፉ መነኮሳት ገዳማውያን በየቀኑ እያስለቀሰን

ዛሬ ደግሞ በጻድቃኔ ገዳም ይህን ስንሰማ አዕምሯችን ተጨነቀ በጨለማ ላይ የገደል ጥላ ሆነብን 😭

እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማርልን 😭
😢24😭222
አሳዛኝ ዜና !

በ ደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም ድንገት በተከሰተ ርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰው ሕይወት ሲያልፍ በ5 ሰው ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ መሪር ኀዘን ተሰምቶናል።
__

በጌታ የሚሞቱ ብፁዓን ናቸው ። ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ሥራቸው ይከተላቸዋልና። ራዕ ፲፫ ÷ ፲፬

ከክረምቱ መግባት ጋር ተያይዞ በተከሰተው ከፍተኛ የዝናብ መዝነብና የመባርቅት ድምፅ በታላቋ ገዳማችን በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት አደጋ በድንገት በመከሰቱ ለጸበል ፣ ለሱባኤና ለመሳለም ከአራቱም አቅጣጫ በተሰበሰቡ በጻድቃኔ ማርያም ልጆችና ወዳጆች ላይ እጅግ አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ ኀዘን በመድረሱ ከፍተኛ ኀዘን ተሰምቶናል ።

በዚህ አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ ድንገተኛ አደጋም የ14 ወገኖቻችን ሕይወት ሲያልፍ በ3 ወገኖቻችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት በሁለት ወገኖቻችን ላይ መለስተኛ ጉዳት ደርሶብን በከፍተኛ የመርዶ ኀዘን ውስጥ እንገኛለን ።

በዚህ ሰኣት የሀገረ ስብከታችን ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሌምንጦስ በስፍራው በመገኘት ለሞቱ ወገኖቻችን ጸሎተ ፍትሐት ለተጎዱት ጸሎት ላዘኑ ወገኖቻችን የማጽናኛ ትምህርተ ወንጌልና አባታዊ ቃለ በረከት በመስጠት ላይ ይገኛሉ ።

በዚህ አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ መርዶ ሀገረ ስብከታችን የተሰማውን ጥልቅና መሪር ኀዘን እየገለጽን እግዚአብሔር አምላክ ለሞቱ ወገኖቻችን እረፍተ ነፍስን ለተጎዱት ፈውስን ላዘኑት መጽናናትን ይሰጥልን ዘንድ ከዕንባ ጭምር ጋር ከልባችን እንመኛለን።

© ነቅዐ ጥበብ ነቅዐ ጥበብ
💔3113😭5😢3😁1
👉👂👂👂👂👂
👍326
👉👂👂👂👂👂
👍289