Eotc Task Force
7.23K subscribers
1.56K photos
349 videos
12 files
397 links
ወቅታዊ ጉዳይ
Download Telegram
https://vt.tiktok.com/ZSXoQd9Ph/ናትያል አካውንቷ ተዘግቷል ሁላቹም ፎሎ አርጓት
👍8
በአራጆች የሚመራው የምክክር ኮሚሽን
🙉25😢5👍3😭3
ወንድሜ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም ኋይለሚካኤል ብላችሁ በፀሎት አስቡት ድጋሜ ወንድሙን በሞት አቷል

አፅናኝ መንፈስ ቅዱስ ያበርታህ

እዚህ ቴሌግራም ላይ አይን ሆኖ የሚያገለግለን ወንድማችን ከባድ ሀዘን ገጥሞታል
😢4015🙏11💔10😭9
መዝግባችሁ ያዙ

በሀዲያ  ዞን አመካ ወረዳ  ጽንፈኛ ፕሮቴስታንቶችን  አሰማርተው የቡታራ ኢስጢናፋኖስ ቤተ ክርስቲያንን ያስፈረሱና ኦርቶዶክሳውያንን ያስጨፈጨፉ የብልጽግና ወንጌል(የፕሮቴስታንት ) ባለሥልጣናት፦
፩  አቶ ደገፈ ሞላንጎ (የአመካ ወረዳ አስተዳዳሪ)
2)ኢ/ር እሸቱ አዳነ አሼቦ( የአመካ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ)
3)፶ አለቃ ጡምሲዶ ሞላጎ(የወረዳው ሰላምና ጸጥታ ሀላፊ)

የጊዜ ጉዳይ ነው ሁሉም የዘራውን ነው የሚያጭደው

አሁን ስልጣን ላይ ሆኖ ክርስቲያኖችን የሚያሳርደው
💔193
👍61
ዝኾኑን የመጣል ዘመቻ

አንድ የኮሌጅ ጓደኛችን ነበር። በጣም ጥሩ አመለ ሸጋ አስተዋይ ጓደኛ ነበረን። ኹላችንም ታናናሾቹ ብንኾንም በመቀለድም፣ በምንም የምንመታው የምንቀልድበት ወንድማችን ነው። አይናደድ አይበሳጭ እንደውም አንድ አባባል ጣል አድርጎ ይበልጥ ያበሳጨን ነበር።

ታድያ ኹላችንም አቅማችንን ስለማናሳይበት "በእኔና በጥምቀት የማይጨፍር የለም" ይል ነበር። እውነቱን ነው። አኹንም በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የማይጨፍር የለም።

አቡበከርም፣ አሕመዲንም፣ ኢዩጩፋም፣ አስቴር በዳኔም ይኽ ታዬ ቦጋለም ቤተ ክርስቲያን ላይ እየጨፈሩ ናቸው።ይኽ ኹሉ ርብርብ ዝኾኑን (ውርዝው ነጌ) ለመጣል ነው። 

ታዬ ቦጋለ እንደምንም ብሎ እስልምናም ኦርቶዶክስም ከውጭ ነው የመጡት ለማለት የገባበት ገደል መውጭ የለውም። 

ከመደበኛ እውቀት ማለትም በትምህርት ቤት ከመምህራን ከመጽሐፍት የሚገኝ እውቀት ስትወድቅ የምታርፈው የፕሮፓጋንዳ እውቀት ላይ ነው።

የፕሮፓጋንዳ እውቀት ምንጭ የለውም፣ ጫፍ ይዞ መሄድ ብቻ ነው። ግን አየሩን የሚሞላው እሱ ነው። ብዙዎቻችን የፕሮፓጋንዳ እውቀት ሰለባ ነን። ምንጩን መነሻውን ታሪኩንና የታሪኩን ምንነት አንድረዋው። ተንትነን አንገነዘብም። እንደ አብይ "አጼ ዮሐንስ በጎጃም ላይ ያደረጉትን አትረሱትም" ያለው ፕሮፓጋንዳ ነው። የኾነ ክስተት ተደርጓል። ግን ለውጦ ለሚፈልገው ማዋል ፈለገ። አደገኛ ነው። 

ታዬ ኦርቶዶክስ በአምስተኛው ክፍለ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ ዘጠኙ ቅዱሳን ጋር የኦርቶዶክስ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ተናገረ። ይገርማል።

ጃንደረባው ባኮስ ከዲያቆኑ ፊሊጶስ ጋዛ ተጠምቆ መምጣቱን አያውቅም። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በበዓለ ሃምሳ ኢትዮጵያውያን መኖራቸውን መጻፉን አያውቅም። ሐዋ.8

የመጀመሪያዎቹ ነገሥታት ኢዛናና ሳይዛና በክርስትና ስማቸው  አብርሃና አጽብሃ ስማቸው ክርስትናን መቀበላቸውን አያውቅም።

ተስዓቱ ቅዱሳን ወንጌል አስፋፉ፣ ምንኩስናን አስፋፉ እንጂ ክርስትና ይዘው አልመጡም። የመጡትኮ በኬልቄዶን ጉባኤ ስደት ሲደርስባቸው የምትመስለን ሰላማዊ ክርስቲያን ሃገር አለች እዚያ እንጠለል ብለው ነው።

ከነርሱ ቀድሞ እነ ቅዱስ ያሬድ ድርሰት ደርሰዋል። ክርስትና እየሰፋ መጥቷል ሰሜኑን አዳርሷል። ፍሬምናጦን የመጀመሪያው ጳጳስ እንጂ የመጀመሪያው ክርስቲያን አይደለም። በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ክርስቲያን ባኮስ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን አክሱም ጽዮን፣ የመጀመሪያው ፣ ኤጲስ ቆጶስ ሕዝበ ቀድስ (እንበረም)፣ የመጀመርያው ጳጳስ ፍሬምናጦስ (ሰላማ) ነው። መቼ ከተባለ ከጰራቅሊጦስ በወረድ ማግሥት፣ በሠላሳ አራተኛው ዓመት። 

ንዋይ ካሳሁን
14
የመጀመሪያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

+ የመጀመሪያው ጳጳስ:- አባ ሰላማ
+የመጀመሪያው ኤጲስ ቆጶስ:- ሕዝበ ቀድስ (በኦሪት ስሙ እንበረም)
+ የመጀመሪያው ቄስ:- ቄስ ተክለ ሃይማኖት ( በኦሪት ስሙ ፊንሐስ)
+ የመጀመሪያ ምእመን:- ባኮስ (ጃንደረባው)
+ የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን:- አክሱም ጽዮን
+ የመጀመሪያው ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ

ንዋይ ካሳሁን
👍2519