Eotc Task Force
7.23K subscribers
1.56K photos
349 videos
12 files
397 links
ወቅታዊ ጉዳይ
Download Telegram
11
ይኽን መልእክቱ የፌስቡክም በቲክቶኩም በማጋራት እንተባበር
17
10
#ቅዱስ_ቂርቆስና_እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ (#ሐምሌ_19)

ሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ። ይህም ሕፃን ዕድሜው ሦስት ዓመት ሲሆነው ከሮሜ አገር ወደሌላ ሀገር እናቱ ይዛው ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኰንን አገኘችው። 

ሰዎችም ነገር ሠሩባት ወደርሱ አስቀረባትና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኰንን ሆይ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው። 

ሕፃኑም ወደአለበት ጭፍራውን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው። ሕፃኑም መልሶ አዎ ለእኔ ደስታ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኀዘንና ልቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው መጽሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና አለው እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስከ አስደነገጣቸው ድረስ ንጉሡን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሣ አደነቁ። 

መኰንኑም በአፈረ ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው እናቱንም ከርሱ ጋር እንደ እርሱ አሠቃያት እግዚአብሔርም ያለምንም ጉዳት ያነሣቸው ነበር። ብዙዎች አሕዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ። 

በሕፃኑ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት። ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው።

ከዚህም በኋላ መኰንኑ በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውኃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ሆነ ያን ጊዜም ፍርሀትና የሃይማኖት ጉድለት በእናቱ ላይ ደረሰባት ሕፃኑም ስለ እናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። 

ያን ጊዜ ጌታችን ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አየች ከዚህም በኋላ ጸናች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው ልጅዋንም ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አንተ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ አለችው። 

ያቺ ከኔ የተወለድክባትም ቀን የተባረከች ናት አለች ወደዚያ ወደ ጋኑ ውስጥ በገቡ ጊዜም የውኃው ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና። 

ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው እንዲጐትቷቸው አዘዘ ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ አዳናቸው መኰንኑም በታላቅ ሥቃይ ያሠቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው። 

ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕፃኑ ቂርቆስ ወርዶ አጽናናው አረጋጋውም። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ ➛ስንክሳር ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ)
🥰132
የእኛ ትልቁ ችግር ወይ አንሠራም ወይ ደግሞ የሚሠሩትን አናግዝም።እርግጠኛ ሆኜ የምናግራችሁ ሁላችንም በአንድ ቃል ቅዱስ ፓትርያርኩ ላይ ጫና ብናሳድርባቸው ለውጥ ማምጣት እንችላለን ።አንፍራ አናስመስል እውነትን በፍቅር እንናገር ።መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ እናጋራው።
ሳር አምባ፣ፍኖተ አበው፣ፍኖተ ርቱዓን ሬድዮ እና ሞዐ ተዋሕዶ እናመሰግናለን።እንደነዚህ ዓይነት ሚዲያዎችን ማበረታታት ማሳደግ ያስፈልጋል።
33
"ሃይማኖትህን ስትቀይር መጤ ትሆናለህ! "
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
በ Ahmedin Jebel-አሕመዲን ጀበል

አምስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ጓደኞሞች ነበሩ።በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በአንድ ትምህርት ቤት አብረው ተምረዋል።ሆኖም ወደ ተለያዩ ዩኒቪርሲቲዎች ተመደቡና ተለያዩ።ከረጅም ዓመታት ተጠፋፍተው በማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት ተገናኙ። ተነፋፍቀው ነበርና በአካል ሊገናኙ ተቀጣጥረው ተገናኙ።

በቆይታቸው በህይወታቸው የተለያዩ ለውጦች ተስናግደዋል። አራቱ እምነታቸው ቀይረዋል።አንዱ ሙስሊም፣ ሌላው ካቶሊክ፣ሌላኛው ፕሮቴስታንት ሲሆን አንዱ ደግሞ የጆቫ እምነት ተከታይ ሆነዋል። እምነቱን ከኦርቶዶክስ ያልቀየተው ጓደኛቸው የኦርቶዶክስን እምነትን በመቀየራቸው ክፉኛ አዘነ። ዉስጡንም ንዴት ሞላው።

ሻይቡና ካሉ በኋላ ስለኢትዮጵያና ስለእኩልነት ሲወያዩ የኦርቶዶክሱ ጋር የሀሳብ ልዩነት ተፈጠረ።
በአንድ ሀገር ተወልደው አድገው፣ከአንድ ህዝብ ወጥተው፣ አንድ የኦርቶዶክስ እምነትን ሲከተሉ እንዳልነበር ዛሬ ላይ እምነታቸው ቀይረው ስላገኛቸው በቁጣ ተሞልቶ "እናንተ መጤዎች! ከኛ ከነባሩ ሕዝብ ጋር ሀገርን በእኩልነት እንጋራ ለማለት ደረሳችሁ? ይህ ድፍረት ነው! ኦርቶዶክስ ሀገር ያቆመች።ፊደል ቀርጻ ትውልድ ያስተማረች። እናንተ ተሰዳችሁ ስትመጡ የተቀበለች ነች።" እያለ ተናገራቸው። በሁኔታው አዘኑ። አንደኛው "እምነት መቀየር መጤ የሚያደርግ ከሆነ፣ሁላችንም መጤ ነና?"።

የካቶሊክ እምነት ተካዩ ደግሞ "እምነትን ከኦርቶዶክስ ወደ ሌላ መቀየር መጤ የሚያደርግ ከሆነ፣እናንተ ኦርቶዶክስን የኢትዮጵያዊነት ብያኔ ማዕከል አደርጋችኋል ማለት ነው።

ኦርቶዶክስ ከሌላው በተለየ የሀገር ባለውለታ ከሆናች ያንን ዉለታ ማን ላይ የምትቆጥረው? እኛም ዉለታ የተባለው ነገርን ኦርቶዶክስ እያለን አብረን ያበረከት ነው።" አለ።

ሙስሊሙ ወንድም አከለ"ኦርቶዶክስ በ7ኛ ክፍለ ዘመን የነቢዩ ሙሐመድ(ሰ. ዐ. ወ) ተከታዮች ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት አለኝ ብላ በምትቆጠረው ታሪክና ስልጣኔ ሁሉ የብቻዋ አይደለም። ኦርቶዶክስ የነበሩና እምነታቸውን ወደ ኢስላም የቀየሩ ኢትዮጵያውያን ጭምር ነው።" አሉ።

ፕሮቴስታንቱም ቀጠለ "ለእኛ የወንጌላውያንም እንደዚሁ ነው።ከ19ኛ ክፍለ ዘመን ወንጌላውያን እምነቱን ወደ ኢትዮጵያ ከማምጣታቸው በፊት ኦርቶዶክስም፣ሙስሊሞችም ሆኑ ካቶሊካውያን በኢትዮጵያ የሠሩት ታሪክ፣ገድል፣ስልጣኔና አሻራ ሁሉ እኛ ወንጌላውያን እነዚያን እምነቶችን በምንከተልበት ጊዜ አብረን የሠራናቸው ናቸው። እንደ ግል ደግሞ የዛሬ 5 ዓመት ወንጌላዊ ከመሆኔ በፊት ኦርቶዶክስ አለኝ በምትለው ነገር ሁሉ አለሁበት።ያኔ የነበረኝ አስተዋፅኦና ስፍራ እምነቴን ስለቀየርኩ ብቻ የትናንት ድርሻዬ አይሻርም።" አለ።

ሙስሊም በማስከተል እንዲህ በማለት ሀሳቡን ማብራራት ቀጠለ "ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን መስሊሞች በመሆናቸው ብቻ መጤ አድርጎ የሚፈርጀው ይህ የደናቁርት ርዕዮተ ዓለም እያለ ያለው ዐማራ ሙስሊሞች እምነታቸው ኢስላም ስለሆነ ብቻ መጤ ናቸው፥ ክርስቲያን አማሮች ግን ኢትዮጵያዊ ናቸው፤

ትግራዋይ ክርስቲያኖች ኢትዮጵያዊ ናቸው፤ ሙስሊም ትግራዋይ ግን መጤ ናቸው፤ ሲዳማ ክርስቲያኖች ኢትዮጵያዊ ናቸው፤ ሙስሊም ሲዳማዎች ግን መጤ ናቸው፤ ክርስቲያን ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ነው፤ ሙስሊም ኦሮሞ ግን መጤ ነው፤ እያላችሁ መሆኑን አስተውላችኋልን?"

የጆቫ እምነት ተከታዩም ቀጠለ "አንድ የትግሬ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ ወይም የሌላ ብሔር አባል የሆነ ሰው ሃይማኖቱን ሲቀይር የዉስጥ ማንነቱ መገለጫ «ዲ ኤን ኤው» (DNA) ወይም የዘር ግንዱ አይቀየርም። ሃይማኖቱ ተቀየረ እንጂ የብሄር ወይም የዘር ማንነቱ አይቀየርም።" በማለት አብራራ።

ማጠቃለያ
🌺🌺🌺🌺

ሀ) ኢትዮጵያዊነት የጋራ ቤት እንጂ የአንድ ክፍለ ዘመን ዉርስ አይደለም።
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥

አንድ ሰው እምነቱን ሲቀይር የቀደሙ አባቶቹ (እርሱ) ከጥንት ጀምሮ የገነቡትን ሀገር አያጣም።አይሁድ፣ኦርቶዶክስ አልያም ሌላ እምነት ተከታይ እያለ የከፈለው መስዋዕትነት፣ የሠራው ታሪክ እና ያቆየው ቅርስ እምነቱን ሥለቀየረ ብቻ ባለቤትነቱ አይነፈግም። "የኔ አይደለም" ብሎም አይጥለውም።ሌላውም ሊገፋበት አይችልም።

ለ) ታሪክን በሃይማኖት ብቻ መመዘን ታሪካዊ ስህተት ነው!
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

የኢትዮጵያ ታሪክ የሃይማኖት ታሪክ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ፣የግብርና፣የቋንቋ፣የክነ ሕንጻ፣የእውቀት ስርጭት፣የሀገር ግንባታ፣የሥልጣኔ፣የሉዓላዊነት፣ የንግድ፣የባህል፣ወዘተ ታሪክ ድምር ነው። በነዚህ ሁሉ የተሳተፊት ከሁሉም ኢትዮጵያውያን የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን እንጂ የአንድ ሃይማኖት ተከታዮች ብቻ አይደሉም።

ሐ)ዜግነት በሕግ፣ሃይማኖት በነጻነት!
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
ዜግነትና ሀገራዊ መብት የሚወረሱት ወይም የሚገኙት በደም(በወላጆች) እና በሕግ እንጂ በሃይማኖት ምዝገባ አይደለም። ሃይማኖት የምርጫ ጉዳይ እንጂ የሀገር ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ አይደለም።

መ)መጤነት በሃይማኖት ከሆነ ኦርቶዶክሶችም መጤዎች ናቸው።

.
.
#የአህመዲን ጀበል ማደንዘዣ እና እስልምናን የሀገር ባለውለታ ማድረግ እና ኦርቶዶክስን ጨቋኝ ለማለት እንዲሁም ቤተክርስቲያን ምንም የኢትዮጵያ አሻራ እንደሌላት የማሳየት ዘዴ
👍84
ኃላፊው የፕሮቴስታንት እምነት ተከተይ ስለሆኑ ከፍተኛ የኦርቶዶክስ ጥላቻ አለባቸው - የወረዳው ቤተ ክህነት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የአመካ ወረዳ ቤተ-ክህነት ጽሕፈት ቤት ጉዳዩን አስመልክቶ ይፋዊ አቤቱታውን ባቀረበበት ደብዳቤ ላይ  በቦታው የሚኖሩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከተዮች ለዘመናት  አስከሬን ተሸክመው ከ20 ኪሎ ሜትር በላይ አቋርጠው በመጓዝ ለብዙ ዓመታት መቆየታቸውን አስታውሷል።

አሁን ግን ቁጥራቸው ከ300 በላይ የሆነ ምዕመናን በአካባቢያቸው የቤተክርስቲያን መስሪያና የመቃብር ቦታ ከግለሰብ በስጦታ ማግኘታቸውን ገልጿል።

ቦታው  ከሌሎች የእምነት ተቋማት ጋር የድምጽ መረባበሽ እንዳይኖር ህጋዊና  ርቀቱን ጠብቀው በስጦታ ባገኙት ቦታ ላይ የተገነባ መሆኑን ገልፆ ይሁን እንጂ የሌሎች እምነት ተከታዮች ለወረዳው ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ተቃውሟቸውን አቅርበዋል ብሏል።

ቤተክህነቱ በአካባቢው የሚኖሩ የልዩ ልዩ ሃይማኖት ተከተዮች እርስ በእርስ በመከባበርና በሰላም አብረው የሚኖሩ ቢሆንም፣ የአመካ ወረዳ የሰላምና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የፕሮቴስታንት እምነት ተከተይ በመሆናቸው እና ከፍተኛ የሃይማኖት ጥላቻን በሚገልጽ መልኩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጥር እንድታፈርስና በአካባቢው ምንም ዓይነት ልማት እንዳይካሄድበት በማድረግ ከፍርድ ቤት አሰራር ውጪ እና ያለ አግባብ ሥልጣናቸውን  በመጠቀም ፍትሕ እንዳናገኝ አድርገዋል ሲል አስታውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ላይ የተደራጁ የፕሮቴስታንት እምነት ተከተዮች ይዞታውንና ንብረቱን ይጠብቁ በነበሩ 6 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከተዮች ላይ ድገተኛ ጥቃት በመሰንዘር ከፍተኛ አካላዊ ድብደባ’ ፈጽመውባቸዋል ሲል ገልጿል።

በተጨማሪም ድምጽ በሌለው መሣሪያ አማካይነት ከፍተኛ ጉዳት  አድርሰዋል ያለ ሲሆን፣ በቦታው ላይ የነበረውን ሕንፃ በማፍረስና ንብረቱንም ሙሉ በሙሉ በማፍረስ ከፍተኛ ውድመት አድርሰዋል ብሏል።

በመሆኑም የወረዳው አስተዳደር ጽሕፈት ቤት በድርጊቱ ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ወንጀለኞችን በፍጥነት ለሕግ እንዲያቀርብና ተገቢው አስተማሪ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ይገባል ሲል ጠይቋል።

አክሎም ጉዳት የደረሰባቸው ምዕመናን አስፈላጊውን ሕክምና እንዲያገኙና ለወደመው ንብረት ተመጣጣኝ ካሣ በሕግ አግባብ እንዲከፈላቸው እንዲሁም በፈረሰው ቤት ምትክ ሌላ ቤት ተገንብቶ ለአገልግሎት እንዲበቃ ቤተ-ክህነቱ  ጠይቋል።

የሃይማኖት እኩልነትና ነፃነት እንዲረጋገጥ፣ የሕግ የበላይነት እንዲከበርና ለቤተ ክርስቲያኗና ለምዕመናን ተገቢው የሕግ ከለላ እንዲሰጥ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ይህ አቤቱታውንም ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ ለክልሉ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ ለሀዲያ ዞን ሰላም እና ጸጥታ መመሪያ፣ ለዞኑ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እንዲሁም ለሀዲያ እና ስልጤ ሀገረስብከት ግልባጭ እንደላከ በደብዳቤው ጠቅሷል።

‌‎   #ቦርከና_ዜና
👍103
እነዚህን በመጨፍጨፍ የሚጸናውን መንግሥት አብረን እናየዋለን፡፡ ቤተ ክርስቲያንን በማሰደድ የሚጸናው ሀገር የሚጠቀም አንድም የማኅበረሰው ክፍል የለም፡፡

ጠላት በንጹሐን ሞት የዚህን ያህል መቦረቁ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም ነው፡፡ ይኸንን የማይረዳው ሕዝባች አሁን ይነቃል፡፡ ሕዝብ ከነቃ ደግሞ መፍትሔው ቀላል ነው፡፡ አማራጩን መጥፋት ወይም በመኖር መካከል መሆኑ መታወቁ የሚያተርፈው ለቤተ ክርስቲያን ነው፡፡

ይኸው ነው፡፡

ዶ/ር አረጋ አባተ
👍22
ዳግም የድሮን ጥቃት ይፈፀምብናል በሚል የገዳሟ ተማሪዎች እየተሰደዱ መሆኑ ተነገረ!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ወሎ ሐገረ ስብከት ከመካነሰላም ከተማ በቅርብ ርቀት ዓባይ ድልድይ አከባቢ በምትገኘው የዓባይ ቅድስት አርሴማ ገዳም በድሮን መደብደቧን ተከትሎ በገዳሟ ውስጥ ይማሩ የነበሩ የአብነት ተማሪዎች ገዳሟን ለቀው እየተሰደዱ መሆናቸው ታወቀ።

ፅረ ሕዝቡና ሃገር አውዳሚው የብልፅግና አገዛዝ ሐምሌ 15/2018 ዓ/ም ማርፈጃውን በገዳሟ ላይ የድሮን ድብደባ መፈፀሙ ይታወቃል።

ጥቃቱን ተከትሎ በገዳሟ ውስጥ መንፈሳዊ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ የአብነት ተማሪዎችና አንዳንድ አበው መምህራን ልባቸው እጅጉን በመሰበሩ አካባቢውን እና ገዳሟን ጥለው ለመሰደድ መገደዳቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

የብልፅግናው አገዛዝ ስለ ሀገር አንድነትና ሰላም በሚፀልዩ መናንያን መነኮሳትና ገዳማት እንዲሁም አብያተክርስቲያናት ላይ በሰው አልባ አውሮፕላንና በሜካናይዝድ መሣሪያዎች ታግዞ የሚፈፀመው እልቂትና ውድመት ተባብሶ ቀጥሏል።

ሀገር እያስተዳደርኩ ነው የሚለው ይሄው ኦህዴድ መሩ የብልፅግናው አገዛዝ፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ወሎ ሐገረ ስብከት ከመካነሰላም ከተማ በቅርብ ርቀት ዓባይ ድልድይ አከባቢ በምትገኘው ዓባይ ቅድስት አርሴማ ገዳም ውስጥ ታቅበው ስለ ነፍሳቸው መዳን፣ ስለ ሀገር አንድነትና ሰላም፣ ስለ ሰው ልጆች ሁሉ  በሚፀልዩ መናንያን መነኮሳት ላይ ሐምሌ 15 /2018 ዓ/ም በፈፀመው ዘግናኝ የድሮን ጥቃት ሁለት መናንያን መነኮሳት ለሕይወተ ሕልፈት ሲዳረጉ በርካቶች ደግሞ ለከባድ የአካል ጉዳት መጋለጣቸውን መረብ ሚዲያ በእለቱ መዘገቡ አይዘነጋም።

በጥቃቱ በመነኮሳቱ ላይ ከደረሰው እልቂት በተጨማሪ፡ የገዳማውያኑ የዓመት ቀለብ እህልና ጥራጥሬ፣ ተግባር ቤት፣ ማብሰያ እቃዎች፣ የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከር ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተረጋግጧል።

በዚህም መናኒያኑ የለት ቀለባቸውና በዛ በርሃ ውስጥ የመጠጥ ውሃ የሚያጠራቅሙበት የውሃ ታንከር በመውደሙ ምክኒያት ለረሃብና ለከባድ የውሃ ጥም ተጋልጠዋል።

በዚህ ምክኒያት እና ዳግም ጥቃት ይፈፀምብናል በሚል ስጋት በገዳሟ ውስጥ ይማሩ የነበሩ የአብነት ተማሪዎችና አንዳንድ አበው መምህራን ገዳሟን ለቀው እየተሰደዱ ስለመሆናቸው ነው መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው።

በዚኸው ሃገረ ስብከት በመኃል ሳይንት ወረዳ በታሪካዊቷ ታዕካ ነገስት አትሮንስ ማርያም ቤተክርስቲያን ላይ የካቲት 28/2018 ዓ/ም ማርፈጃውን በተፈፀመ የከባድ መሣሪያ ጥቃት፡ ሁለት ካህናትና ሦስት ዲያቆናት እንዲሁም አንዲት የቤተክርስቲያኗ አቃቢ በድምሩ ስድስት ንፁኋኖች ሲገደሉ ከ20 በላይ ንፁኋኖች ደግሞ ለከባድ የአካል ጉዳት መጋለጣቸውን በእለቱ ጣቢያችን መረብ ሚዲያ የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ መዘገቡ አይዘነጋም።

በአብርሃ አፅብሃ ዘመነ መንግስት እንደተመሠረተች የሚነገርላት ታሪካዊቷ ታዕካ ነገስት አትሮንሰ ቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን፡ በርካታ ነገስታት ንግስናቸውን የተቀበሉባትና ከበርካታ ነገስታት በስጦታ መልክ የተሰጠችውን ልዩ ልዩ ታሪካዊ ቅርሶችን በውስጧ የያዘች ከሐይማኖታዊ ስፍራነቷ ባሻገር በአከባቢው እንደሙዝየም የምታገለግል ደብር ናት።

በዚች ታሪካዊትና እድሜ ጠገብ ቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ የካቲት 28/2018 ዓ/ም ማርፈጃውን በጄነራል ዘውዱ ሰጣርጌ የሚመራው የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት  ተከታታይ የመድፍ ድብደባ ተፈፅሟል።

በጥቃቱ የአትሮንስ ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ሞገስ ፍስሃ፣ የቤተክርስቲያኗ አቃቢ እማሆይ ድንቄ ታከለን ጨምሮ ሌሎች ስድስት የቤተክርስቲያኗ አገልጋይ ቀሳውስትና ዲያቆናት ሲገደሉ ከ20 ፡ብላይ ንፁኋኖች ነቁሰላቸውን ነው በእለቱ ጣቢያችን ዘግቦ የነበረው።

መረብ ሚዲያዳግም የድሮን ጥቃት ይፈፀምብናል በሚል የገዳሟ ተማሪዎች እየተሰደዱ መሆኑ ተነገረ!

😢121🥰1
በጥቃቱ የአትሮንስ ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ሞገስ ፍስሃ፣ የቤተክርስቲያኗ አቃቢ እማሆይ ድንቄ ታከለን ጨምሮ ሌሎች ስድስት የቤተክርስቲያኗ አገልጋይ ቀሳውስትና ዲያቆናት ሲገደሉ ከ20 ፡ብላይ ንፁኋኖች ነቁሰላቸውን ነው በእለቱ ጣቢያችን ዘግቦ የነበረው።

መረብ ሚዲያ
💔9😱2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እነዚህ ናቸው የሀገርን ችግር የሚፈቱት? ቸርች ላይ እንደፈለገ መናገር የለመደ አፍ ሥልጣን ሲመጸወትለትም የመጣለትን ይናገራል
😁6
መዝግባችሁ ያዙ

በሀዲያ  ዞን አመካ ወረዳ  ጽንፈኛ ፕሮቴስታንቶችን  አሰማርተው የቡታራ ኢስጢናፋኖስ ቤተ ክርስቲያንን ያስፈረሱና ኦርቶዶክሳውያንን ያስጨፈጨፉ የብልጽግና ወንጌል(የፕሮቴስታንት ) ባለሥልጣናት፦
፩  አቶ ደገፈ ሞላንጎ (የአመካ ወረዳ አስተዳዳሪ)
2)ኢ/ር እሸቱ አዳነ አሼቦ( የአመካ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ)
3)፶ አለቃ ጡምሲዶ ሞላጎ(የወረዳው ሰላምና ጸጥታ ሀላፊ)

የጊዜ ጉዳይ ነው ሁሉም የዘራውን ነው የሚያጭደው
👍388🕊21
https://vt.tiktok.com/ZSXoQd9Ph/ናትያል አካውንቷ ተዘግቷል ሁላቹም ፎሎ አርጓት
👍8
በአራጆች የሚመራው የምክክር ኮሚሽን
🙉25😢5👍3😭3