Eotc Task Force
7.23K subscribers
1.57K photos
349 videos
12 files
398 links
ወቅታዊ ጉዳይ
Download Telegram
ራሱን" የምክክር ኮሚሽን "ብሎ የሚጠራው ስብስብ፦
👉ሥርዐቱ ኦርቶዶክስን ለማጥፋት የሚጠቀምበት በትር ነው
👉መሪዎቹ አክራራ የብልጽግና ወንጌል አማኞችና ኢትዮጵያን አስልመን በሸሪዓ ህግ እናስተዳድራለን የሚሉ ወሀቢያዎች ናቸው  እንደ ካምፓስ ዜርፎር ለይስሙላ ጣል  ጣል የተደረጉ ሆድ እንጂ ጭንቅላት የሌላቸው ጥቂት የከተሜ አባ ኩብኩባዎች  እንዳሉ ሆኖ
👉የሚመክረው ኦርቶዶክሳውያንን ለማስጠፋት እንጂ ለመታደግ አይደለም
💯14😢65
በሀዲያ ዞን በአንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይዞታ እና ተከታዮች ላይ በሌላ ሀይማኖት ተከታዮች ጥቃትንና ውድመት መድረሱን ተከትሎ የአመካ ወረዳ ቤተክህነት  የሕግ የበላይነት ይከበር ሲል ጥሪ አቀረበ

ዓርብ፣ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የአመካ ወረዳ ቤተ-ክህነት ጽሕፈት ቤት በ ወረዳው “የታኛኛው በታራ” በተባለ ልዩ ቦታ በሚገኝ የቤተ ክርስቲያን ይዞታ ላይ ጥቃትና የንብረት ውድመት “በፕሮቴስታንት አማኞች” ደርሷል ሲል አስታወቀ።

ጉዳዩን አስመልክቶ ይፋዊ አቤቱታው በደብዳቤ  ለተለያዩ ተቋማት ልኳል።  የወረዳው ቤተክህነት በደብዳቤው ላይ እንደገለጸው በቦታው የሚኖሩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከተዮች ለዘመናት ሲጠቀሙበት የነበረውንና በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው ከ300 በላይ ለሚሆኑ ምዕመናን አገልግሎት የሚሰጠውን የጸሎት፣ የመሰብሰቢያና የመቃብር ስፍራ በሕጋዊ መንገድ አጥር በማጠርና ለበጎ አድራጎት ሥራዎች በማዋል ሰላማዊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ቦታው  ከሌሎች የእምነት ተቋማት ጋር የድምጽ መረባበሽ እንዳይኖር ርቀቱን ጠብቀው በስጦታ ባገኙት ቦታ ላይ የተገነባ መሆኑን ገልፆ ይሁን እንጂ የሌሎች እምነት ተከታዮች ለወረዳው ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ተቃውሟቸውን አቅርበዋል ብሏል።

አክሎም በአካባቢው የሚኖሩ የልዩ ልዩ ሃይማኖት ተከተዮች እርስ በእርስ በመከባበርና በሰላም አብረው የሚኖሩ ቢሆንም፣ የአመካ ወረዳ የሰላምና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የፕሮቴስታንት እምነት ተከተይ በመሆናቸው እና “ከፍተኛ የሃይማኖት ጥላቻን” በሚገልጽ መልኩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጥር እንድታፈርስና በአካባቢው ምንም ዓይነት ልማት እንዳይካሄድበት በማድረግ ከፍርድ ቤት አሰራር ውጪ እና ያለ አግባብ ሥልጣናቸውን  በመጠቀም ፍትሕ እንዳናገኝ አድርገዋል ሲል አስታውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ላይ የተደራጁ ‛‛የፕሮቴስታንት እምነት ተከተዮች ይዞታውንና ንብረቱን ይጠብቁ በነበሩ 6 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከተዮች ላይ ድገተኛ ጥቃት በመሰንዘር "ከፍተኛ አካላዊ ድብደባ’’ ፈጽመውባቸዋል ሲል ገልጿል።

በተጨማሪም “ድምጽ በሌለው መሣሪያ” አማካይነት ከፍተኛ ጉዳት  አድርሰዋል ያለ ሲሆን፣ በቦታው ላይ የነበረውን ሕንፃ በማፍረስና ንብረቱንም “ሙሉ በሙሉ” በማፍረስ ከፍተኛ ውድመት አድርሰዋል ብሏል።

በመሆኑም የወረዳው አስተዳደር ጽሕፈት ቤት በድርጊቱ ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ወንጀለኞችን በፍጥነት ለሕግ እንዲያቀርብና ተገቢው አስተማሪ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ይገባል ሲል ጠይቋል።

አክሎም ጉዳት የደረሰባቸው ምዕመናን አስፈላጊውን ሕክምና እንዲያገኙና ለወደመው ንብረት ተመጣጣኝ ካሣ በሕግ አግባብ እንዲከፈላቸው እንዲሁም በፈረሰው ቤት ምትክ ሌላ ቤት ተገንብቶ ለአገልግሎት እንዲበቃ ቤተ-ክህነቱ  ጠይቋል።

በመጨረሻም የሃይማኖት እኩልነትና ነፃነት እንዲረጋገጥ፣ የሕግ የበላይነት እንዲከበርና ለቤተ ክርስቲያኗና ለምዕመናን ተገቢው የሕግ ከለላ እንዲሰጥ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ይህ አቤቱታውንም ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ ለክልሉ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ ለሀዲያ ዞን ሰላም እና ጸጥታ መመሪያ፣ ለዞኑ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እንዲሁም ለሀዲያ እና ስልጤ ሀገረስብከት ግልባጭ እንደላከ በደብዳቤው ጠቅሷል።


ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦

YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
6👍1
👆👆👆አንዳንድ የፕሮቴስታንት ዲኖሚኔሽኖች ጨንብላቸውን ገልጠው ጅሃድ ጀምረዋል!
"ኢየሱስ" እያሉ ክርሰቲያን እየመሰሉ የማጭበርበር ዘመን እያበቃ መሆኑ ነው!
3
ይድረስ ለሀዲያ ስልጤ ሀገረስብከት፣ለአመካ ወረዳ ኦርቶዶክሳውያን

ምንም እንኳ የሚፈጸምብን ጥቃት ከፌዴራል መንግሥት ትእዛዝ ሰጪነት የሚፈጸም ቢሆንም የአጥፊዎችን ስም ማወቅ ያስፈልጋልና፦
👉ጥቃቱን የፈጸሙ አካላት መሉ መረጃ(ስም፣ፎቶ ግራፍ፣ስልክ ቁጥር አድራሻ)
👉 አከባቢው ላይ ያለው ቸርች ከእነ ፓስተሮቹ
👉ጥቃቱን ማስቆም ሲገባቸው ዝም ያሉ የፕሮቴስታንት  ሽማግሌዎች ስምና ፎቶ ግራፍ ቢቻል ስልክ ቁጥርም ቢታከልበት
👉 የወረዳው አስተዳዳሪ፣የወረዳው ፖሊስ መምሪያ፣የቀበሌው አስተዳዳሪ ሙሉ መረጃ(ስም፣ፎቶ ግራፍና ስልክ ቁጥር)

እንድትሰጡን እናሳስባለን።

https://t.me/EotcTaskForce
3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የጊዜ ጉዳይ ነው ወገኖቹ ላይ በሚፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ውስጡ ያረረ ወጣት አንድ ቀን መነሳቱ አይቀሬ ነው።ደግሜ እናገራለሁ የጊዜ ጉዳይ ነው ወጣቱ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ ቃል ተናጋሪ ሆኖ ይነሳል በዓይን ጥቅሻ በከንፈር ንክሻ ይግባባል።የተገፋ ወተት ቅቤ ይወጠዋል። ተገፍተናል በገዛ ሀገራችን ላይ ከ11ቀን ህጻን ጀምሮ እስከ 90 ዓመት አዛውንት በጅምላ ተጭፍጭፈናል፣ተገድለን እንኳ እሬሳችን ማረፍ አልቻለም በእሳት ተቃጥሏል፣ዓለምን የናቁ ገዳማውያን በእስላም ሀገራት ድሮኖች ተጨፍጭፈዋል፣ሆን ተብሎ ታስቦበት በኢኮኖሚ እንድንደቅ ተደርጓል ሕዝባችን በየቦታው ለልመና ተዳርጓል።አዎ በተገው አጋጣሚ ሁሉ ወጣቱን ማንቃት ማበራታት ማጀገን ያስፈልጋል።እግዚአብሔር ሁሌም ከተገፉት ጋር ነው እንደሚረዳን አንጠራጠርም።ብቻ እኛ እንንቃ ከልባችን እንሥራ እንደጋገፍ፣ከመለያየት ይልቅ ኅብሩትን፣ከማስመሰል ይልቅ እውነትን ገንዘብ እናድርግ።ያኔ እግዚአብሔር በመካከላችን ይገኛል።
https://t.me/EotcTaskForce
35
ኦርቶዶክሳውያንን ከአርሲ ምድር የማጽዳት መንግሥታዊ ፕሮጄክት ግቡን እየመታ ነው።ይህ የምሥራቅ አርሲ ዞን ጉና ወረዳ ኮሚንኬሽን ቢሮ ዘገባ ነው። በጉና ወረዳ በጃዊ ናኖ ቀበሌ ከማኅበረሰቡ ጋር "ስለ ሰላምና ልማት ተወያየን "ነው የሚሉት። በስብሰባው ላይ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ውጭ ሌላ እምነት የለም።ከማን ጋር ነው ሰለ ሰላም የሚወያዩት? ገዳዮቹ እነርሱ የሚገደሉት ኦርቶዶክሳውያን ሆነው ሳሉ።ናኖ ጃዊ ቀበሌ ማለት በወርኃ ጥቅምት በአንድ ቀን 14 ኦርቶዶክሳውያን የተጨፈጨፉበት እነዚያ ሁለቱ ህጻናት አካላቸው በገጀራ የተቆራረጠበት ቦታ ነው።ታርዶም ሆነ ተሰዶ ኦርቶዶክሱ ከአርሲ ምድር እየተጸዳ ነው።አብዛኛው የገጠሩ ክፍል ከኦርቶዶክስ ጸድቷል።የሃገረ ስብኩቱ ሊቀ ጳጳስ ይኽን ደፍረው አይናገሩም ሁለት ቀን አለቀሱ በዝያው ዝም አሉ።እየሆነ ያለው ይኽ ነው።
13🤬9😢1
ኦርቶዶክሳውያን ሆይ፦
👉ትናንት የሆነብን የልብ ሙቀት መለኪያ(የሥነ ልቡና) ነው
👉ዛሬ እየሆነብን ያለው መግቢያ(የመከራ ማለማመጃ) ነው
👉ነገ ይሆንብን ዘንድ ያለው ግን ይከብዳል

መፍትሔው፦በቃን ብሎ በኅብረት መነሳት
👍247
"ትውልዱ ኦርቶዶክስና አማራን እየተበቀለው ነው"~አስቴር በዳኔ

በኢትዮጵያ ምድር ኦርቶዶክስና አማራ ጠልነት የተራ ግለሰቦች ሳይሆን ፦
👉ህገ መንግሥታዊ ነው
👉 እንደ አንድ ወሳኝ ማኅበረሰባዊ ሕይወት መስተጋብር ይቆጠራል
👉 እምነታዊ ነው
👉 ሕዝባዊ ነው

ይኽች በኦርቶዶክስ ጠልነት ያበደች ሴት ስልክ ቁጥሯ +251947428444 ነው መደወል የሚፈልግ ካለ
👍253
ሀገርና ቤተ ክርስቲያን ምን ዓይነት መከራ ውስጥ እንዳሉ የተረዳን አይመስለኝም
10
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መሬት ላይ እየኖሩ እየበሉ እየጠጡ "እኔ መንፈሳዊ ነኝ ስለ ፖለቲካ አታውሩብኝ"ለሚሉ ዝንጉዑን አድርሱልኝ።ሲጀመር "ሃይማኖት እና ፖለቲካ ይለያያል" የሚለውን እሳቤ ያመጡት ምዕራባውያን ናቸው ሰውን ከእግዚአብሔር ለይተው ቂሳዊ ለማድረግ።እኛ ኦርቶዶክሳውያን እንጸልያለን ፣እንጾማለን፣እንቆርባለን፣እናስቀድሳለን ስለ ሀገራችንም እናወራለን ሀገራችን እንድትኖር እንሡራለን።ሀገር ከሌለች የት ሆነን የጽድቅ ሥራ እንሠራለን? በምድር ላይ የጽድቅ ሥራ ከላልሠራን ደግሞ በሰማይ ቦታ አይኖረንም።አዎ " እኔ መንፈሳዊ ነኝ ስለ ፖለቲካ አታውሩብኝ" የሚሉ ሰዎች እዚህ እኛን ማጣቡብ የለባቸውም ወደ ሰማይ ሄደው እዚያ ይኑሩ።
👍379💯5
በዚህ ጉዳይ ደጋግመን ተናግረናል ማንነቱን የ ማታውቁት ሰው "ኑ እንደራጅ" ቢላችሁ በፍጹም መቀበል የለባችሁም። እምነቱ ሙስሊም የሆነ ሰው ስሙን ኀይለገብርኤል ብሎ ቀይሮ ከሆነ በምን እናውቃለን? የሚያወራን ሰው የመንግሥት ደኅንነት ቢሆንስ ?መሥራት የሚፈልግ በአከባባው ከሚያውቃቸው ሰዎች ጋር ይሥራ።ትክክለኛ ኦርቶዶክሳውያን ሊያወሩን ይችላሉ በሚዲያ ማን ምን እንደሆነ መለየት ይከብዳል።አንዳንዶች ፎቶና መታወቂያ ይላላካሉ የሌላ ሰው ተልኮልን ቢሆንስ?
👍2113👏1
የእስልምና አጀማመር

ከእስልምና በፊት ያለው የአረብ ማህበረሰብ (ጃህሊያ)  በጎሳ የተዋቀረ ነበር።
ብዙዎቹ ጣዖታዊ እምነት ይከተሉ ነበር።
👉መካ የንግድና የሃይማኖት ማዕከል ነበረች።

👉እስልምና በ Muhammad (570–632) ተጀመረ።
👉610 ቁራን ወርዶ የተጠቃለለበት ነው ብለው ያምናሉ
👉ከእስልምና በፊት የነበረው የአረብ ማህበረሰብ (ጃህሊያ) በጎሳ የተዋቀረ ነበር።
👉ብዙዎቹ ጣዖታዊ እምነት ይከተሉ ነበር
👉ሙሐመድ ሲመጣ ግን ወደ እስልምናው ተጠቃቀሉ
👉622 ዓ.ም (ሂጅራ) በመዲና የመጀመሪያው እስላማዊ ማህበረሰብ ተቋቋመ። ይህ የፖለቲካ እና የሀይማኖት አንድነት መሠረት ሆነ።
👉ከዚያን ጊዜ በኋላ ባሉት ዓመታት እስልምና ባሳየው መስፋፋፋት የዓለምን ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ይዞታ ለውጦታል።በሳዑዲ ዓረቢያ የተጀመረው ኢስላማዊ መንግሥት በአንድ ክፍለ ዘመን ውስጥ ይዞታውን በማስፋፋት በምዕራብ ከአትላንቲክ ጀምሮ በምሥራቅ እስከ መካከለኛው እስያ ደርሷል።
ሙሐመድ እምነቱን ይጀምሩት እንጂ ያስፋፉት ተከታዮቻቸው ናቸው።መሐመድ ከሞቱ በኋላ እስልምና እንዴት ይመራ በሚለው ጥያቄ ክርክር ተነሳ። ከእርሱ በኋላ ተከታዮቹ መሪነትን ማን እንደሚወስድ በሚለው ጉዳይ ልዩነት ተፈጠረ። በዚህ ምክንያት በእስልምና ታሪክ “ፍትና (Fitna)” ተብሎ የሚጠራ የውስጥ ግጭት ተከሰተ።
ከዚያ በኋላ የኡማያድ መንግሥት ተመሠረተ፤ በኋላም የአባሲድ መንግሥት ተተካ። የኡማያድ መንግሥት እስልምናን በሰፊው አስፋፋ፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ድረስ ብዙ አገሮች ተካተቱ።
በአባሲድ ዘመን ደግሞ ባግዳድ የእውቀት እና የሳይንስ ማዕከል ሆነች። ብዙ መጻሕፍት ተተርጎሙ፤ ፍልስፍና፣ ሕክምና፣ ሳይንስ እና ሌሎች ዕውቀቶች ተስፋፉ።እንዲያና እንዲህ እያ እስልምና እስልምና እየተስፋፋ ሄደ።
  እስልምና ወደ ኢትዮጵያ  መቼ እና እንዴት ገባ?
እስልምና ወደ ኢትዮጵያ በ7ኛው ክፍለ ዘመን ገባ።
በ615 ዓ.ም በመካ ላይ የነበረው እስላሞችና የማሳደድ ዘመቻ እየጠነከረ ሲመጣ ነቢዩ Muhammad  ተከታዮቹን ወደ አቢሲኒያ (የዚህ ዘመን ኢትዮጵያ) እንዲሄዱ አደረገ።
በዚያን ጊዜ ኢትዮጵያን ይመራ የነበረው ንጉሥ አርማሕ ነበር። እርሱ ሙስሊሞቹን በእንግድነት ተቀበላቸው። ይህ ክስተት በእስላማዊ ታሪክ “የመጀመሪያው ሂጅራ” ተብሎ ይጠራል።
ይህ እስልምናና ኢትዮጵያ መካከል ያለው የመጀመሪያ ሰላማዊ ግንኙነት ነበር።

እስልምና በኢትዮጵያእንዴት ተስፋፋ?

1)  በንግድ መንገድ  (8ኛ–12ኛ ክፍለ ዘመን)
የቀይ ባሕር እና የህንድ ውቅያኖስ ንግድ መንገዶች እስልምናን ወደ ምሥራቅ ኢትዮጵያ አስገቡ።
©ዘይላ
©ባርበራ
©ሐረር
ነጋዴዎች በሰላማዊ መንገድ እስልምናን አስፋፉ። ይህ ስፋት በተለይ በአፋር፣ በሶማሌ እና በሐረርጌ ክልሎች ታይቷል።
2 የእስላማዊ ስልጣናት (12ኛ–16ኛ ክፍለ ዘመን)
1 የኢፋት ስልጣን(Ifat Sultanate)
2የአዳል ስልጣናት(Adal Sultanate)

ይቀጥላል....
👏82👍2
 
ወሀቢያ ምንድን ነው ? ከየት መጣ?

ወሀቢያ በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መሐመድ ኢብን አብደል ዋሂብ /1703-1792 ዓ.ም./ በተባለ ሰው የተመሠረተ የእስልምና ርእዮተ ዓለም ነው። ኢብን አብደል ዋሂብ ከ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የብዙ እስላሞችን ቀልብ የሳበውን አዲሱን አክራሪ እስልምና መሠረት የጣለ ነው። ተከታዮቹ ራሳቸውን ዋሂዲኖች ብለው ይጠራሉ። ትርጉሙም “በተውሂድ የሚያምኑ” ማለት ነው።
መሐመድ ኢብን አብደል ዋሂብ የተወለደው በማዕከላዊው ዐረቢያ ከሪያድ በስተ ስሜን ዑያናህ በተባለ ሥፍራ ከሃንባሊ የእስልምና ት/ቤት ጋር ግኑኝነት ከነበራቸው ቤተሰቦች ነው። አብዛኞቹ ቤተዘመዶች ከዚህ ት/ቤት የወጡ መምህራን ናቸው። በልጅነቱ በወግ አጥባቂው የሱኒ እስልምና ትምህርት ተኮትኩቶ አደገ፡ ከዚያም ለበለጠ ዕውቀት ወደ መካ እና መዲና ተጓዘ። በሃራማየን ት/ቤት በዘመኑ ዋና የአክራሪ እስልምና አቀንቃኞች ከነበሩት ከመሐመድ ሐያት አል ሲንዲ ከፍተኛ ዕውቀት አግኝቷል። በዚያም በተለይም ሃዲትን በተመለከተ በቂ የሆነ ዕውቀት ለመጨበጥ ችሏል። አብደል ዋሂብ በሃዲት በተገለጠው የጥንቱ እስልምና አሁን በሚያየው እስልምና መካከል ያለው ልዩነት ያሳስበው ነበር።
በልዩ ልዩ ቦታዎች ተዘዋውሮ ዕውቀቱን ካጎለመሰ በኋላ ወደ ሀገሩ ወደ ናጅድ ከተማ ተመለሰ። በዚያም ሕዝቡ የያዘውን የተለመደ ዓይነት እስልምና በመተው ቃል በቃል ቁራዓንን በሱኒ የእስልምና መርህ መሠረት እንዲከተል ማስተማር ጀመረ። ምንም እንኳን መጀመርያ ላይ ብዙዎች ቢቃወሙትም የዳሪያው ገዥ ሙሀመድ ኢብን ሳዑድ ጥሪውን በመቀበል የሃሳቡ ደጋፊ ሆነ። በአክራሪው የእስልምና መምህርና በጦረኛው መሪ መካከል የተጀመረው ወዳጅነት ወታደራዊ የሆነ እስላማዊ መንግሥት ለመመሥረት በቃ። ይህ እስላማዊ ወታደራዊ መንግሥት በአጭር ጊዜ ውስጥ ግዛቱን ወደ ሌላው የዐረቢያ ልሳነ ምድር ማስፋፋት ቻለ።
ይህ ኃይል በ1802 ዓ.ም. በደቡብ ኢራቅ የነበሩትን የሺአቶች ቦታዎች አስለቀቀ፡ በ1803 ዓ.ም. ደግሞ መካን ተቆጣጠረ። በዚያም የመጀመርያው ጠንካራ የሳዑዲ መንግሥት ተመሠረተ። በወቅቱ የእስልምናውን ዓለም አንድ አድርገን እንገዛለን ብለው የተነሱት ኦቶማን ቱርኮች ሁኔታው ስላሰጋቸው በግብጽ የነበረውን ጦር ወደ ሳዑዲ ላኩት። በዚህ ምዕራባዊውን አሠራር ይዞ የነበረው የኦቶማን ቱርክና አዲስ በመነሳሳት ላይ በነበረው ዐረባዊው አክራሪነት መካከል በተደረገው ጦርነት የሳዑዲ ወሀቢያዎች ለጊዜው ተሸነፉ። በ1818 ዓ.ም. የመጀመሪያው የሳዑዲ መንግሥት ተጠናቀቀ።
ወሀቢዝም ማናቸውንም ዓይነት የሱፊ እስልምና አካሄዶችን አይቀበልም። የተቀደሱ ሰዎች የሚባል ነገርን አያውቅም፡ በዚህ ዓይነት አምልኮ የተስፋፉ ስዎችም ከእስልምና ያፈነገጡ በመሆናቸው ሞት ይገባቸዋል ይላል። ከቁርዓንና ከሱና በስተቀር ሌላ የእስልምና መጽሐፍ አይቀበልም። እስልምና ብቸኛ የድኅነት መንገድ ነው ይህንን ደግሞ ሰዎች በውድም ሆነ በግድ መቀበል አለባቸው፡ ስለዚህም የተቀደሰ ጦርነትን ማካሄድ አስፈላጊ ነው ይላል። /ሱረቱ 8:65/
ይህ የወሀቢዝም አስተሳሰብ በሶማልያ ከሚገኘው የአልሸባብ ቡድን እስከ አል ቃኢዳ ድረስ ያሉ የዘመናችን አሸባሪዎች የሚመሩበት አስተሳሰብ ነው። የሀገራችን እና የቤተ ክርስቲያናችን የዘመኑ ፈተናም ይህ ነው። ወሃቢዝም በየሀገሩ በተለያየ ስም ይጠራ እንጂ አሠራሩ ተመሳሳይ ነው፡ እስልምናን አክራሪ በሆነ መንገድ ኃይል ቀላቅሎ መጠቀም ነው። የወሀቢዝም መነሻም መስፋፊያውም ሳዑዲ ዐረቢያ ነው። በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደረገው የአክራሪ እስልምና እንቅስቃሴ ዋናው ድጋፍ የሚገኘው ከሳዑዲ ነው።


   የ20 መክዘ የወሀቢያ መስፋፋት

1. የመንግሥት መመስረት (1932)

ዘመናዊ ሳዑዲ አረቢያ በIbn Saud ተመሠረተ። ከዚህ በኋላ ወሀቢዝም የመንግሥት ዋና ሀይማኖታዊ መርህ ሆነ። ይህ ማለት፦
የእምነት ትምህርት በመንግሥት ቁጥጥር ውስጥ ገባ
የእስልምናተቋማት በመንግሥት ድጋፍ ተጠናከሩ
የወሀቢ ትምህርት በአገር ውስጥ ተስፋፋ
2. የነዳጅ ድፍድፍ  (1970ኛው ዘመን)

1970ኛው ዘመን የነዳጅ ዋጋ  እየጨመረ ሲሄድ ሳዑዲ አረቢያ እጅግ ታላቅ ገቢ አገኘች። ይህ ገቢ የወሀቢ አስተሳሰብን ዓለም አቀፍ ለማስፋፋት ተጠቃሚ ሆነ።

   በዚህ ምክንያት፦
በአፍሪካ፣ እስያ እና አውሮፓ መስጂዶች ተገነቡ
ኢስላማዊ ማዕከላት እና ትምህርት ቤቶች ተመሠረቱ
ወሀቢዝምን የሚያቀነቅኑ መጽሐፍት ታተሙ ወደ ተለያዩ  ቋንቋዎች ተተረጎሙ
ለውጭ ተማሪዎች የትምህርት እድል (Scholarship) መስጠት
3. የትምህርትና  ተቋማት መስፋፋት

Islamic University of Medina
Muslim World League
እነዚህ ተቋማት ከዓለም አቀፍ ተማሪዎችን በመቀበል የወሀቢያን አስተሳሰብ

ይዘው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አደረጉ።

4.

አፍጋኒስታን ጦርነት (1979–1989)

በ1979 ሶቪየት ሀገር አፍጋኒስታንን በወረረች ጊዜ፣ ሳዑዲ አረቢያ ከአሜሪካ ጋር በመተባበር የሙጃሂዲን ኀይሎችን ደገፈች።
ይህ ሁኔታ፦
የጂሃድ አስተሳሰብ እንዲስፋፋ አደረገ
ዓለም አቀፍ እስላማዊ ኔትዎርኮች እንዲፈጠሩ በር ከፈተ።

ይቀጥላል....
https://t.me/EotcTaskForce
👍43👏1
ወሀቢዝም በዓለም ላይ የተስፋፋባቸው መንገዶች

20ኛው ክፍለ ዘመን ወሀቢዝም ከክልላዊ እንቅስቃሴ ወደ ዓለም አቀፍ ተፅእኖ እንዲደርስ ያገለገሉ ዋና መንገዶች እነዚህ ናቸው።
1. የመንግሥት ድጋፍ
1932 ከዘመናዊ ሳዑዲ አረቢያ መመስረት በኋላ፣ ወሀቢዝም የመንግሥት ዋና ሀይማኖታዊ መርህ ሆነ።
የአክራሪ እስልምና ሚኒስቴሮች ተመሰረቱ
መስጂዶች በመንግሥት ድጋፍ ተገነቡ
ክልላዊ ባለስልጣኖች ተጠናከሩ
የነዳጅ ገቢ ይህን ድጋፍ እጅግ አጠናከረው።
2. የትምህርት ተቋማት
ወሀቢዝም  በጣም ከተስፋፋባቸው ዋነኛው  መንገድ አንዱ  ትምህርት ነበር።
Islamic University of Medina
Muslim World League
ለውጭ ተማሪዎች የነፃ ትምህርት እድል
ስኮላርሺፕ (Scholarship)
ይሰጣቸውና 
መድረሳዎችን ኢማሞችንና መምህራንን አሰለጠኗቸው እነርሱም ወደ ሀገራቸው
ወደ አገራቸው ተመልሰው "አዲስ" የሀይማኖት አመራሮች ሆኑ።
3. መስጂድ ግንባታ እና መሠረተ ልማት
በአፍሪካ፣ እስያ እና አውሮፓ መስጂዶች ተገነቡ
ኢስላማዊ ማዕከላት ተመሰረቱ
ቁርአንና መጻሕፍት ተሰራጩ
መስጂዶች የትምህርቱ ማስፋፊያ ማዕከላት ሆኑ።
4. በህትመት እና በሚዲያ
ብዙ ሚሊዮን ቁርአን ታተመ
የሐንባሊ እና የማሻሻያ መጻሕፍት ተተረጎሙ
ቢድዓን (መውሊድን(የነብዩን ልደት ማክበርን)፣እነርሱ ቅዱሳን ብሎ የሚያምኑ ሰዎችን መቃብር መሳለምን)የሚቃወሙ ጽሑፎች ተሰራጩ
በኋላ ሳተላይት ቲቪና ዲጂታል ሚዲያን ወሀቢዝምን ለማስፋፊያነት ተጠቅመውበታል።
5. በጎ አድራጎት ድርጅቶች
ኢስላማዊ በጎ አድራጎት ድርጅቶች፦
ትምህርት ቤቶች መገንባት
የእርዳታ ፕሮግራሞች
የማህበራዊ ድጋፍ መስጠት
6. የቀዝቃዛ ጦርነት (Cold War) አውድ
ሳዑዲ አረቢያ ኮሚዩኒዝምን ለመቃወም ራሷን የሱኒ እስልምና ጠባቂ አደረገች
አፍጋኒስታን ጦርነት ዓለም አቀፍ የእስላማዊ ኔትዎርኮችን(ትስስሮችን) አጠናከረ
7. ስደት እና የሥራ እንቅስቃሴ
የሥራ ስደት ወደ ሳዑዲ አረቢያ
   ለሥራ የሄዱ ሰዎች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ከነባሩ የእስልምና የሚቃረን ጽንፍ ረገጥና አዲስ የእልልምና አስተሳሰብ ይዘው ይገባሉ
ዓለም አቀፍ ኢስላማዊ የማህበራዊ ኔትዎርክ(ትስስር)


ይቀጥላል....
https://t.me/EotcTaskForce
9👍1