🦋Öfficial Ęķű§ĥą🦋❤️💖
492 subscribers
4.03K photos
1.07K videos
14 files
691 links
Víđęø 💯💯
Pîç💝💝
Cóûplęŝ
Mŭžíç🎶🎶
Çòvêr mūźič🎤🎤
Đáñćê
Pøęm vóîĉé😜😜
Tłktòk øf Kóręâ😉😉
ßF^ Płç😂😂
Çŭpl pîć💑
👇👇l👇👇👇👇
ąñy prøblêm àñđ çrøśš
@Tinaye_22
@Birabiroye_123
Join join join
@Ekushaye_22
Download Telegram
ካንቺ የበለጡ ቆንጆዎች
እንዳሉ አውቃለሁ ...
⇨ ነገር ግን የወደድኩሽ
በአይኔ ሳይሆን በልቤ ነው ።
❤️ጣፋጭ የፍቅር ቃላት❤️   
                                                                                                                                          
💘የትኛውም የህይወት ፈተና ባጋጠመኝ ጊዜ ባንተ መፈቀሬን ሳስብ 
ልበ ሙሉነት ይሰማኛል።    
                                                       
                                                                                                   💘ከማያቸው ሚሊዮን ከዋክብቶች በልቤ ውስጥ ምታንፀባርቀው
አንተ ብቻ ነክ።                                                                                                                                                                                       
                                                                                                   💘ካንተ ጋር ማሳልፈው እያንዳንዱ ቅስበት ነብሴን በደስታ ትሞላለች።  
                                                                                                                  
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አደይ ምዕራፍ 2 ክፍል 1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አደይ ምዕራፍ 2 ክፍል 2
​​​​. ♥️✿የማይፋቅ ስህተት✿♥️

♥️ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

●▬ተከታታይ ልቦለድ▬●

#ክፍል_6

...🖍እሷም እየሳቀች "አሁን በደንብ ገብቶሀል!" አለችኝ። ልጅቷን አተኩሬ አየኋት! ሙሉ ለሙሉ ጥቁር ናት። የሆነ ናይጄሪያዊ ነዉ የምትመስለዉ። ግን ደስ የሚል ነገር አላት። የፌቪ ጓደኛ ባትሆን አሰምጣት ነበር።
እዉነት ለመናገር እኔ ከፌቪ ጋር ለመተኛት ብዬ ሆቴል በሉት ወላ ሪዞርት መሄድ አልፈልግም ነበር። የተስማማሁት ጓደኛዋ ስለገንዘቡ አትጨነቅ እሷ ጋር አለ ስላለችኝ ነዉ።
.
ማታ ማታ አምስት ሰዓት ድረስ ፌቪንናየአረብ ሀገሮቹን ሴቶች በአንድነት እያዋራሁ አመሻለሁ። እናቴ እንዳትሰማኝ በፅሁፍ ብቻ ነዉ የማስተናግዳቸዉ። ሰሞኑን ከሪሜ የሚያወራት ልጅ ደሞዜን ባንክ አስቀምጥልኝ ብላ ስለላከችለት ብር በብር ሆነናል። ወር ሙሉ የለፉበትን እንዲህ ለኛ ሲያስረክቡ በጣም ነዉ የሚገርሙኝ! እንዴት ለማንም አንስተዉ የለፉበትን ይልካሉ? የሚያስቅ የዋህነት!
ማታዉን እየተጀናጀንኩ እማዬ ስታቃስት ሰማሁ። እየሮጥኩ ወደሷ ክፍል ሄድኩኝ። "ምነዉ እማ?" አልኳት። ጉበቷን አንዳንዴ ያማት ነበር። አሁንም እሱ እንደሆነ በእጇ ጠቆመችኝ። ሀኪም ቤት እንዳንሄድ በጣም መሽቷል። እማዬን ሳያት ግን በጣም ያመማት ስለመሰለኝ የአምሪያን አባት መኪና ለማስቸገር አሰብኩ። ወዲያዉ ግን እማዬ እንደመሻል አላት። እስክትተኛ ድረስ አጠገቧ ተቀምጬ ጠበቅ
ኳት። እንቅልፍ ሲወስዳት ወደ ምተኛበት ክፍል ሄጄ መጀናጀኔን ቀጠልኩ።
.
ጠዋቱን እማዬ እንደተለመደዉ ጉድ ጉድ ስትል ሰማሁ። ማታ የታመመች ሴትዮ አሁን ጤነኛ ሆናለች። ይገርማል! እንጀራዉን ይሀ የፈረደበት የላስቲክ ምግብ ቤት አድርሼላት ከሚኪ ጋር ወደ ትምህርት ለመሄድ ተገናኘን። ሚኪ ፈገግ ብሎ "ዛሬ ኦፊሱ የኔናየሄለን ግዛት ነዉ ድርሽ እንዳትሉ!" አለኝ። ከኔ ቀድሞ ማስማማቱ ገረመኝ። ያዉ ሄለንን ዛሬ ሊተኛት መሆኑ ነዉ። ስለኔዋ ስነግረዉ "በሷ ወጪ ከሆነ ለምን ሆቴል አይደለም ቤተ መንግስት አትልህም ምን ቸገረህ?!" አለኝ።
.
ጠዋቱን ከከሪም እና አብነት ጋር ሆነን ባወጣነዉ እቅድ መሰረት ክላስ ቀጥተን ሚኪናሄለን እስኪመጡ የተከራየናትን ኦፊስ አፀዳድተን ጠበቅናቸዉ። አምስት ሰዓት አካባቢ ሚኪ ሄለንን የሆነ ቦታ ደህና ምግብ ጋብዟት ይመስለኛል መጡ። ሄለን የኛ ትምህርት ቤት ልጅ ስለሆነች ሁላችንም በደንብ እናዉቃታለን። አጠር ያለች ጠይም ልጅ ናት።
እንደመጡ ሰላም ብለናቸዉ ቤቱን ለቀን ወጣን። ስወጣ እየሳቅኩ ሚኪን በጆሮዉ "በል እንግዲህ ያላየኸዉን አዲስ ሀገር እየዉ!" አልኩት። እየሳቀ ገፍትሮ አስወጥቶኝ በሩን ዘጋዉ። እኛ እንዳማረብን ወደ ፑል ቤት ሄደን ስንጫወት ቆየን።
.
በግምት ከነሚኪ ጋር ከተለያየን ከአራት ሰዓታት በኋላ ይመስለኛል ሚኪ ደወለልኝ። እየሳቅኩኝ "ወዬ ክቡርነትዎ!" አልኩት። "የት ናችሁ? ተከሰቱ!" አለኝ። ከአብነት እና ከሪሜ ጋር ሆነን ወደ ኦፊስ ሄድን። ስንገባ ሄለን የሚኪያስን ሹራብ ለብሳ ተቀምጣለች። እሱ በቦዲ ነዉ። ቤቱ የሆነ የሞት ሽረት ትግል እንደነበረበት ያስታዉቃል። ከሪሜ ከቤት ያመጣት አንሶላ በደንብ ተንገላታለች። ትንሽ ተቀምጠን ካወራን በኋላ የኔዋ ጉድ ፌቨን ከትምህርት የምትለቀቅበት ሰዓት ስለደረሰ ለመሄድ ተነሳሁ። ሚኪም ሄለንን ሊሸኛት ልብሷን ቀያይራ አብረን ወጣን። ሄለንን ሸኝቶ ፑል ቤት እንደሚጠብቀኝ ነግሮኝ ተለያየን። የሚገርመዉ ግን ሄለን ድንግል አልነበረችም። ከሚኪ በፊት ከሌላ ወንድ ጋር ፍቅቅሮሽ ዉስጥ ገብታ ነበር።
.
ፌቪን እንዳገኘኋት በጣም ከማፈሯ የተነሳ ቀና ብላ እንኳ አላየችኝም። ሲመስለኝ ጓደኛዋ እንዳናገረችኝ ነግራታለች።
እየተሽኮረመመች "እኔ አልነበርኩም የላኳት! ራሷ ነች።" አለችኝ። ፈገግ ብዬ "እቅድሽን ንገሪኝ!" አልኳት። በጓደኛዋ ልደት አሳበን ሶደሬ ለመዝናናት እንድንሄድ ቤተሰቧን አስፈቅዳ ቅዳሜ ሄደን እሁድ ማታ እንድንመለስ ነዉ ያቀደችዉ። ለገንዘቡ አታስብ ጓደኞቼም አብረዉን ስለሚመጡ ችግር የለዉም ስላለች እቅዷን ሙሉ ለሙሉ ተቀበልኩት። እኔ ከሴት ጋር ለመተኛት ብዙ ብር አወጣ ብለዉ እነሚኪ እንዳይፎግሩኝ ብዬ ነዉ እንጂ ከአረብ ሀገር ሚስኪን ታላቢዎቻችን የተላከ ገንዘብ ነበረኝ።...

#ይቀጥላል...

❥..................🍃🍃...................❥

🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አደይ ምዕራፍ 2 ክፍል 3
Forwarded from Cross bot
📌ተማሪ ነህ/ነሽ አሁኑኑ ምረጡ?
​​​​. ♥️✿የማይፋቅ ስህተት✿♥️

♥️ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

●▬ተከታታይ ልቦለድ▬●

#ክፍል_7

...🖍ከማክሰኞ እስከ አርብ አስራሁለተኛ ክፍሎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ስለሚፈተኑ ትምህርት አልነበረንም። ለሙድ ብለን እሮብ ተገናኝተን ቃምን። ለነገሩ ትንሽ ቅጠል ስለነበር የጎረስኩት አልመረቀንኩም። ከሪሜ ግን አይኑ ቦግ ብሏል። ጥርሴን እየፋቅኩኝ ቅዳሜ እና እሁድን ሶደሬ ስለማሳልፍ ሚኪ ቅዳሜ በጠዋት እኛ ቤት ሄዶ ለእማዬ እንጀራዉን ወደ ምግብ ቤት እንዲያደርስላት አደራ አልኩት። አርብን እዚሁ የተከራየነዉ ቤት አድሬ በለሊት ለመሄድ ነዉ ያሰብኩት።
የጎፈረ ፀጉሩን እየፈተለ "ስታይል ሀቢቤ ደሞ ለዚህ አንሳለሁ እንዴ?" አለኝ። እንዳያረፍድባት ደጋግሜ አደራ አልኩት።
አብነት የመጨረሻዋን ቅጠል እየጎረሰ "ስማ ሀቢቤ ያቺ የጎረቤታችሁ ልጅ አስራሁለተኛ ክፍል ናት ምናምን ያልከዉ ፈተና እንዴት ነዉ አለችህ? ሰርተዉታል?" አለኝ። እዉነት ለመናገር አምሪያ ተፈታኝ መሆኗን በራሱ ረስቼዉ ነበር።
.
ማታ ከእማዬ ጋር ወደ ቤት ስንገባ አምሪያ በራቸዉ ላይ እንጨት አጋድማ ለመፍለጥ ስትሞክር ደረስን። ሲጀመር መፍለጥ አይደለም መጥረቢያ መያዝ ራሱ አትችልም። እናቴ ሂድ አግዛት ማለቷ አይቀርም ብዬ ቀድሜ "እንኪ ሰፌዱን ላግዛት!" አልኳት።
እማዬ ፈገግ ብላ "ተወዉ ደክሞሀል!" አለችኝ። በጣም ደስ አለኝ! ግልግል አልኩ በልቤ። ወዲያዉ እናቴ ሳቀችና "አመዳም ሂድና ፍለጥላት! ሴት ልጅ የጉልበት ስራ ስትሰራ ይሰማህ!" አለችኝ። እየተበሳጨሁ ወደነአምሪያ ቤት በር ሄድኩና መጥረቢያዉን እየተቀበልኳት "አምሪ ግቢያችሁ ዉስጥ አትፈልጪም ነበር? ዉስጥ አይሻልም?" አልኳት። እዉነት ለመናገር ምርር ብሎኛል።
አምሪ ጥርሷን ያጠረዉ ሽቦ እስኪታይ ድረስ ፈገግ እያለች "ቴራዞ ነዉ ሙሉ ግቢዉ! እንጨት ቢፈለጥበት ይሰበራል።" አለችኝ። ቴራዞዉ አየር ላይ አልቆመ የሚሰበረዉ! የሆነች ብሽቅ።
በመጥረቢያዉ የሰነጠቅኩትን እንጨት በእጆቼ ለመለያየት እየሞከርኩ "ፈተና እንዴት ይዞሻል?" አልኳት።
"ምንም አይልም! ያዉ ዉጤት ሲመጣ ነዉ እንዴት እንደነበረ የሚታወቀዉ።" አለችኝ። እኔ እየፈለጥኩ አምሪያ ቆማ እያወራችኝ አባቷ ከቤት ወጡ። እንጨቱን እያዩ "ይሄ ደግሞ ለምንድነዉ?" አሉ።
አምሪያ እየተሽቆጠቆጠች "ለማንደጃ ፈልገነዉ ነዉ።" አለች። አባቷ ለቤቱ እንጨት ሲያስፈልግ አለማወቃቸዉ ገረመኝ። ለነገሩ እሳቸዉ ኩሽና አይገቡ! አባቷ መኪናቸዉ ዉስጥ ገብተዉ እንደሄዱ "ቆይ አባትሽ ወዴት ነዉ ሁሌ በዚህ ሰዓት የሚሄዱት?" አልኳት።
"ትልቅ የሀይማኖት ትምህርት ቤት አለዉ። ቀን ንግድ ላይ ስለሚዉል አይመቸዉም ፤ አሁን ነዉ ሄዶ ያለዉን ነገር የሚያየዉና ለአስተማሪዎቹ የሚያስፈልገዉን ነገር የሚያሟላላቸዉ።" አለችኝ።
ፈልጬላት ስጨርስ ወደ ግቢያቸዉ እንጨቱን እያስገባሁላት "መልካም ፈተና!" አልኳት።
እሷም መልሳ "መልካም ፈተና!" አለችኝ። እኔ ተፈታኝ አልነበርኩም። የሆነች ቀዉስ ነገር።
.
ቅዳሜ አይደርስ የለ ደረሰ። እነፌቪ ቀደም ብለዉ ሚኒባስ ኮንትራት አናግረዉ ስለነበር ከያለንበት ለቃቀመን። እማዬ የምታዉቀዉ ከሪሜ ቤተሰቦቹ ለቅሶ ለመድረስ ክፍለሀገር ስለሚሄዱ ከሱ ጋር ለመሆን መሄዴን ነዉ። በነገራችን ላይ ከፌቪ ዉጪ ሌሎች አራት ልጆች አብረዉን አሉ። አንዷ ፍቅር ናት የፌቪ ጓደኛ! ባለፈዉ ካፌ ያገኘኋት! ስገምት እሷም ከፍቅረኛዋ ጋር ናት። አብሯት የተቀመጠ ቀላ ያለ ልጅ አለ። ሁለቱ የቀሩትም ፍቅረኞች ናቸዉ። ሶስት ወንድ ሶስት ሴት ነን። ደብረዘይትን እንዳለፍን እማዬ ጋር ደዉዬ ሚኪ መጥቶ እንጀራዉን እንዳደረሰላት አረጋገጥኩ። ሶደሬ እንደደረስን ፌቨን እና አንድ ፍራኦል ነኝ ብሎ የተዋወቀኝ ልጅ አልጋ ለመያዝ ተሯሯጡ። ሶስት አልጋ ያዝን። እቃችንን አስተካክለን ፈታ ማለት ጀመርን። ቅዳሜ መሽቶ የቁርጡ ሰዓት ደረሰና ከፌቪ ጋር ከአዲስ አበባ አዳማ ድረስ ያስመጣንን ጉዳይ ተገበርነዉ። ማንም ያልነካት ልጃገረድ ነበረች። እኔ የመጀመሪያዋ ሆንኩኝ። አብረን አደርን።
.
እሁድ ጠዋቱን እኔ እየዋኘሁ ፌቪ ገንዳዉ አጠገብ ተቀምጣ እያየችኝ እያለ ትልቁ መዋኛ ፊትለፊት በፍፁም ያልጠበቅኩትን ሰዉ አየሁ። አምሪያ ነበረች። ረዥም ቀሚሷን እንደለበሰች ከዋና ገንዳዉ ፊት ለፊት ቆማለች። ምን ልትሰራ መጣች? ደሞ አይታኛለች። ፌቪን ትቼ ወደ ትልቁ መዋኛ ብረቱን ዘልዬ ገባሁ። እየዋኘሁ አምሪያ ወደ ቆመችበት ጥግ ሄድኩ። ዉሀዉ ዉስጥ እንደሆንኩ ቀና ብዬ እያየኋት "እንዴት መጣሽ?" አልኳት።
ትልቁ ገንዳ ዉስጥ የሚዋኙትን ልጆች እያሳየችኝ "ፈተና ስለጨረስን ዘና ለማለት ከጓደኞቼ ጋር መጥተን ነዉ። አንተ እዚህ ምን ትሰራለህ?" አለችኝ።
እነፍራኦልን እያሳየኋት "አንዳንዴ ዋና ጥሩ ነዉ ብዬ ከጓደኞቼ ጋር መጥቼ ነዉ።" አልኳት።
በሽቦ የታጠረዉ ጥርሷ እስኪታይ ሳቀችና በከንፈሮቿ ሽቦዉን ለመሸፈን እየሞከረች "ደስ ይላል! በርታበት። ለማንኛዉም ቤት ሌላ ቦታ እንጂ እዚህ እንደምዝናና ስለማያዉቁ እዚህ እንደተገናኘን እንዳታወራ!" አለችኝ።
እየሳቅኩ "አላወራም! ባይሆን ክፍያዉን አስቢበት!" አልኳትና ወደነፌቪ ተመለስኩ። ለፌቪ ማንነቷን በደንብ አስረዳኋት...

#ይቀጥላል...

❥..................🍃🍃...................❥

🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አደይ ምዕራፍ 2 ክፍል 4
😭😭ዛሬ በጣም ከፍቶኛል

🥀💊 ሰላም እንዴት ዋላቹ ውድ የከፍቶኛል ቤተሰቦች🥺 Telegram Account warning⚠️ ሰቶኛል እናም Acc ዛሬ ማታ BAN/Delete ይደረጋል❗️❗️

እዚ ቻናል ላይ መስራት አልችልም ስለዚህ አዲስ ቻናል ከስር ከፍቻለሁ Join በማድረግ የኔን ስሜት ጥቅስ ፎቶዎች ማግኘት ትችላላችሁ😔😞

🍁
https://t.me/+2W-HsxabBMNjMTM8🍁
🍁
https://t.me/+2W-HsxabBMNjMTM8
🍁
https://t.me/+2W-HsxabBMNjMTM8
Forwarded from Cross bot
📌ተማሪ ነህ/ነሽ አሁኑኑ ምረጡ?
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አደይ ምዕራፍ 2 ክፍል 5
ልቤን ሰጣለው
Buju Star ft Gildo
*ከሴት ጋር እግር ኳስ ማየት በጣም ያስጨንቃል*🤣

👩🏾‍🦰"የትኞቹ ቡድኖች እየተጫወቱ ነው?"
👨🏽‍🦱"ማን ሲቲ vs ሊቨርፑል"
👩🏾‍🦰"ሊቨርፑልን እወዳለሁ"
👨🏽‍🦱"ጥሩ ቡድን ነው"
👩🏾‍🦰"ሮናልዶ እየተጫወተ ነው?"
👨🏽‍🦱"ለእነዚህ ቡድኖች አይጫወትም"
👩🏾‍🦰"እሺ ጣፋጭ......... ያ ክሪስ ብራውን ነው?"
👨🏽‍🦱😒"አይ....ማኔ ነው😕"
👩🏾‍🦰"እሺ ...ግን አንድ አይነት ናቸው.....ያ ቢጫ ካርድ ለምንድነው?"
👨🏽‍🦱"ለተጫዋቹ ማስጠንቀቂያ ነው"
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ስተርሊንግ አስቆጥሯል።
👩🏾‍🦰💃🏼💃🏼💃🏼💃🏼"ያ ማኔ ነው ጎል ያስቆጠረ?"
👨🏽‍🦱[በጸጥታ] አይ ለማን ሲቲ ስተርሊንግ ነው"
👩🏾‍🦰"እንዴት ነው ማስቆጠር የነበረበት ሊቨርፑል ነው"😡😡😡
👨🏽‍🦱🤐🤐🤐
👩🏾‍🦰"ያ ቀይ ካርድ ምንድነው?"
👨🏽‍🦱"ተጫዋቹ ለተሳሳተ ባህሪ ከሜዳው መውጣት አለበት ማለት ነው😥😓
👩🏾‍🦰"ታዲያ አሰልጣኝ ይሆናል"
👨🏽‍🦱😳😠😖😩😫"አaaaaah ኑኡ"
👩🏾‍🦰"ከትራፊክ መብራቶች ጋር ተመሳሳይ ነው፣ ቢጫ ማስጠንቀቂያ ቀይ አደጋ"
👨🏽‍🦱" በትክክል ውዴ"
👩🏾‍🦰"አረንጓዴ ካርዱስ?"
👨🏽‍🦱"በጨዋታው መስክ እንደዚህ ያለ ነገር የለም"
👩🏾‍🦰"ሊቨርፑል የአለም ዋንጫን እንዲያሸንፍ እፈልጋለሁ"
👨🏽‍🦱🤐🤐🤐🤐
👩🏾‍🦰"ሚስተር ቢን የሚመስለው ማን ነው የቆመው?"

👨🏽‍🦱🥺😰😓"የማን ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ነው"
👩🏾‍🦰"ለምን አይጫወትም?"
👨🏽‍🦱: