EdMap Community
3.29K subscribers
910 photos
8 videos
40 files
596 links
EdMap, Powered by PiSpace Inc.
A one-stop destination platform for Ethiopian students.

For further information @contact_edmap

Our website:
🌐 www.edmap.et
Download Telegram
👨‍🎓የ Feynman የጥናት ቴክኒክ

የ Feynman የጥናት ቴክኒክ ጠጠር ያሉ ሃሳቦችን ለመረዳት የሚያስችለን ነው። ይሄ ቴክኒክ ለመረዳት 4 ደረጃዎች አሉት

1. ለመረዳት የሚፈልጉትን ከባድ ሀሳብ ይምረጡ

2. የመረጡትን ሀሳብ ለህፃን ልጅ እንደሚያስረዱ በማሰብ ለማስረዳ መሞከር

3. ይሄን ከባድ ያለ ሀሳብ በሚያስረዱበት ጊዜ የትኛውን ሀሳብ ለማስረዳት አስቸገረዎት

4. የሚያጠኑት መፅሀፍ ጋር በመሄድ ለማስረዳት የከበድዎት ሀሳብ በድጋሚ ያንብቡና ለመረዳት ይሞክሩ።

"The Feynman Technique" በመባል የሚታወቀው ይህ የጥናት ዘዴ በአጭሩ አንድ ሀሳብ ቀለል ባለ ሁኔታ ማስረዳት ካልቻላችሁ በደምብ አልተረዳችሁትም የሚል እሳቤን የያዘ ነው።

TikTok | Facebook | Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔥8👍3
🎓Mastercard Foundation እጅግ አስደናቂ የሆነ የማስተርስ ዲግሪ ስኮላርሺፕ እድል አዘጋጅቶላችኋል።

የሚሰጡት የማስተርስ ስኮላርሺፕ ፕሮግራሞች የሚከተሉት ናቸው።

- Health Informatics
- Health Administration
- Occupational and Environmental Health
- Social and Behavioral Health Sciences
- Financial Insurance
- Engineering (Biomedical)
- Biotechnology (starting in 2025).

እጅግ አስደሳች የሚያደርገው ደግሞ ሙሉ ወጪዎ መሸነፉ እንዲሁም በተለያዩ የካናዳ ዩንቨርስቲዎች መማር እና ልምድ መቅሰምዎ ነው።

ማመልከቻ ማስገቢያ የሚገባደድበት ቀን November 15, 2023!

ይህ እድል እንዳይመልጥዎ

ማመልከቻ ሊንክ

TikTok | Facebook | Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍7
ፎቶዎችን በማገጣጠም ሆነ እንደ Flowcharts ፣ Diagrams እና ሌሎችንም ነገሮች እንድትሰሩ የሚያግዛችሁ ድረገፅ እንዳለ ታውቃላችሁ?

"Draw" ከላይ የዘረዘርናቸውን ጥቅሞችና ሌሎችንም የምታገኙበት ድረ ገፅ ነው።

ሊንክ: www.draw.io

TikTok | Facebook | Telegram
👍6
ስራ እና ትምህርትን አንድላይ ማስኬድ ከብድዎታል?

እነዚህን ጥያቄና መልሶች ተከታተሏቸው! ይጠቅምዎታል!

ጥያቄ፡ እጅጉን ሳልጨናነቅ ስራና ትምህርትን አንድላይ ማስኬድ እችላለሁ?

መልስ፡ በሚገባ! ለትምህርትዎ ፣ ለስራ ፣ ለጥናት እንዲሁም ራስን ለመንከባከብ ስሜታዊ እቅዶችን ያቅዱ እንዲሁም ተግባራዊ ያድርጓቸው።

ያለብዎትን ሀላፊነቶች ለመምህርዎ እንዲሁም ለስራ አለቃዎ ማስረዳት ነገሮችን ቀለል ለማድረግ ይጠቀማል።

ጥያቄ፡ በዚህ ግርግር በበዛበት ሁኔታ ውስጥ እንዴት ድካምንና መዛልን መከላከል እችላለሁ?

መልስ፡ ያለ ድርድር ራስዎን ለመንከባከብ ዝግጁ ይሁኑ! ለእረፍት፣ ለመዝናናት እና ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር ጊዜ ማሳለፍዎን አይዘንጉ።

እርዳታ ሲያስፈልግዎ ደግሞ ከጎደኞች ወይም ቤተሰብዎ ጋር ይማከሩ!

ጥያቄ፡ ኤድማፕ፤ ይህን ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ ምን ትመክሩኛላችሁ?

መልስ፡ የስራ ሀላፊዎ እንዲሁም መምህራንዎ ትልቁን ሚና ይጫወታሉ። ያሉበትን ሁኔታ እንዲረዱ በደምብ ያግባቧቸው፣ ያሳውቋቸው።

ተጨማሪ ሀላፊነቶች እና ስራዎችን ለሌላ ሰው ሃላፊነት መስጠት የምትችሉ ከህነ እንደ አማራጭ ይጠቀሙ።


TikTok | Facebook | Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍4
Study in the U.S. Virtual Fair 2023 ያዘጋጀውን የOnline ዝግጅት ሐሙስ፣ ጥቅምት15 እንድትሳተፉ ይጋብዛል!

ተሳታፊዎች ከተለያዩ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ተወካዮች ጋር የመወያየት እድል ይኖራቸዋል።

ዝግጅቱ ለአፍሪካ ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ከክፍያም ነፃ ነው።

መመዝገቢያ ሊንክ: https://bit.ly/usvirtualfair23
👍21
🎁አዳዲስ ቋንቋ ለመማር እነዚህን ነፃ ድህረ ገፆች ይጠቀሙ።

1. Duolingo
🔗ሊንክ: duolingo.com
2. Babbel
🔗ሊንክ: babbel.com
3. FluentU
🔗ሊንክ: fluentu.com
4. Anki
🔗ሊንክ: apps.ankiweb.net
5. Tandem
🔗ሊንክ: tandem.net

TikTok | Facebook | Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍7
Anna's surprise birthday party was a delightful __________ that left her speechless.
Anonymous Quiz
24%
Conundrum
41%
Revelation
12%
Vehemence
24%
Extravaganza
👍51
🧳 ኤድማፕ የስራ ጥቆማ ለ ተማሪዎች እና ለ አዲስ ተመራቂዎች

📌እነዚህ ክፍት የስራ ቦታዎች የኤድማፕ አይደሉም፣ ለማመልከት ሊንኩን ይጫኑ!

1. Content and Marketing Assistant
2. Marketing and Social Media Manager
3. Indoor sales person
4. Data Base coordinator
5. Supervisor
6. Reception and Librarian
7. Web data scraper
8. Accountant
9. Junior one on one assistant
10. Product Manager

TikTok | Facebook | Telegram

#Job_Post #Career #EdMap_Eth
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5
💡 የሳምንቱ ፈሊጥ: "Break the ice"

💡 ትርጉም:
ሰው ተሰብሰቦ ያለበት ቦታ ላይ መስተጋብርን ማስጀመር

ምሳሌ:
His joke really helped to break the ice at the business meeting.

💡 ፀጥ ብሎ የነበረው ስብሰባ ላይ መቀለዱ ቀለል ያለ ስሜት በሰዎቹ መሃል እንዲኖር አድርጓል።

TikTok | Facebook | Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍8
ማር በጭራሽ አይበላሽም!

በአሁን ሰዕት በጥንቷ ግብፅ መቃብሮች ውስጥ የሚገኘው ማር ከሺህ አመታት በኋላ እስከዛሬ ድረስ ለምግብነት የሚውል ነው።

ተፈጥሯዊ ስብጥሩ ፣ አነስተኛ የውሃ ይዘቱ እና አሲዳማ ፒኤች ባህሪው ለባክቴሪያዎችን እና ረቂቅ ተሕዋስያን ምቹ ያልሆነ አካባቢ ስለሚፈጥር ለመበላሸት እድል አይሰጠውም።

TikTok | Facebook | Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍3
ሰንበት መጥቷል!

ዘና ይበሉ፤ ለመጪው ፈታኝ ሳምንት ይዘጋጁ!
5
👨🏽‍⚕️የአንጀት_ተስቦ/ታይፎይድ / Typhoid Fever

🔔ይህ የ Edmap የጤና አምድ ነው!

⤵️  የታይፎይድ ህመም ምንድ ነው?
⤵️ ታይፎይድና ታይፈስ አንድ ናቸው?
⤵️ ለምን አብዛኛው ሰው ታይፎይድና ታይፈስ አለብኝ ይላል?
⤵️ ህክምናውስ?

በዚህ ሳምንት የ Edmap የጤና አምድ   በጣም ስለተለመደውና ሁሉም ሰው "አለብኝ" ስለሚለው  የታይፎይድ ህመም በሁለት ክፍል አዘጋጅቶ ለEdmap ቤተሰቦች ያቀርባል።

በክፍል አንድ
       - ስለ ታይፎይድ ህመም ምንነት
       - ስለ መተላለፊያ መንገዶቹ
       - ስለ ምልክቶቹ ና ከታይፈስ ጋ ስላላቸው ቁርኝት እናነሳለን
 
መልካም ቆይታ

🔔 ክፍል_አንድ

🔘ታይፎይድ  - የአንጀት ንዳድ በመባል ይታወቃል።
🔘Salmonella Typhi በሚባል ባክቴሪያ ምክንያት የሚመጣ የአንጀት ኢንፌክሽን ነው።
🔘ከንፅህና ጉድለት ጋ ተያይዞ እንደ ሀገራችን ባሉ ታዳጊ ሀገራት ዘንድ በሽታው የተንሰራፋ ነው።
🔘በዓለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ ከ10 እስከ 20 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች በዚህ በሽታ ይለከፋሉ።

መተላለፊያ_መንገዶቹ

🔘 የታይፎይድ በሽታ ከሰው ወደሰው የሚተላለፊው በዋነኝነት በንፅህና ጉድለት ነው።
🔘 በ Salmonella Typhi ባክቴሪያ ከታማሚው ዓይነ ምድር ወጥቶ ለምግብነት የሚያገለግል ውሀን ሲበክል፣
በታይፎይ የተጠቃ ሰው ከሽንት መልስ እጁን በአግባቡ ሳይታጠብ ምግብ ሲያዘጋጅ-  ከዚያ የተመገቡ ሁሉ በዚህ ባክቴሪያ የመለከፍ እድላቸው ከፍ ያለ ነው።
🔘ንፅህና የጎደላቸው የጋራ መፀዳጃ ቤቶችን መጠቀም እጁን ከሽንት ቤት መልስ በአግባቡ ለማይታጠብ ሰው የዚህ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች ይሆናሉ።

/የአንጀት ንዳድ/ታይፎይድ_ምልክቶች

🔘 በበሽታው የተጠቃ ሰው ምልክቶቹን የሚያሳይበት ደረጃዎች አሉት
🔘 በመጀመሪያው ሳምንት ባክቴሪያው በደም ውስጥ የሚቆይቀት ጊዜ ሲሆን የመጀመሪያው ምልክት ከስሙ እደምንረዳው ከምልክቶቹ ሁሉ ጎላ ብሎ የሚወጣውና ንዳድ የሚለውን ስያሜ ያገኘበት በየቀኑ እየጨመረ የሚሄድ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት ነው ።
🔘 ከትኩሳቱ ጋ ተያይዞ ከፍተኛ ራስምታት ብርድ ብርድ ማለት ፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ ቁርጥማት ይከሰታል።

🔘 በሀለተኛው ሳምንት ባክቴሪያው በሆድ ውስጥ መራባት ይጀምራል በዚህም ምክንያት
የሆድ ህመም፣ የሆድ ድርቀት (አንዳንዴ ተቅማጥ) ይናራል ከዚህም በተጨማሪ ቆዳ ላይ የሚታይ ቀላ ያለ/የሮዝ ቀለም አይነት/  ሽፍታ ሊታይ ይችላል። ይህም ሮዝ ስፖት ይባላል።

🔘 በሶስተኛው ሳምንት ካልታከመ ባክቴሪያው በሰፊው በመሰራጨት በሽታው መወሳሰብ የሚጀምርበት ጊዜ ነው ።
🔘 ከዚህ ጋ ተያይዞ
- የአንጀት መድማት /enteric bleeding/
- የአንጀት ግድግዳ መሸንቆር/ bowel perforation/
- ጠቅላላ የሆድ ብግነት/generalized peritonitis/
- የጉበት ማበጥ
- የአንጎል ብግነት  ራስን መሳትና እስከሞት ሊያበቃ ይችላል።
-  በመጨረሻው ደረጃ እድለኛ የሆኑ ሰዎችና ከላይ ያሉትን አስከፊ የህመም ደረጃዎች ሁሉ አልፈው በራሳቸው በሽታ የመከላከል አቅማቸው ልክ ከህመሙ ሊያገግሙ ይችላሉ።

ከታይፈስ_ጋ_አንድ_ናቸውን?
🔘በፍፁም የስማቸው መመሳሰል ሰዎችን ቢያደናግርም በአንድ ላይ አንድ ሰው ላይ የመከሰት እድላቸው እንኳ እጅግ አናሳ ነው( ሰው ታይፎይድ ናታይፈስ አሉኝ የሚለው በልምድ ነው)።
🔘ከታይፈስ ጋ በሁለት ነገሮች ብቻ ይመሳሰላሉ !
    - የደሀ ሀገራት በሽታ መሆናቸው ና
    - አንዳንድ የጋራ የሆኑ ምልክቶች አሏቸው
ከዛ ውጪ መንስኤያቸው፣ መተላለፊያ፣ መንገዳቸው ህክምናቸው ሁሉ የተለያዩ ናቸው።

የታከሙ_ሰዎች_ህመሙን_ያስተላልፋሉ?
- በሚያዛዝን ሁኔታ መልሱ አዎ ነው!
- እስከ 5% የሚሆኑ ከበሽታው ያገገሙ/የታከሙ/ ሰዎች እስከ አንድ ዓመት ድረስ ባክቴሪያው ከሰገራቸው አይጠፋም ስለዚህ ምንም የህመም ምልክት ሳይኖራቸው ወደ ሰው ማስተላለፋቸውን ይቀጥላሉ ማለት ነው።

በክፍል_ሁለት
🔘ስለ ምርመራዎቹ
🔘 ስለ ህክምናው
🔘 ስለ መከላከያ መንገዶች እናነሳለን!

🤝#ዋናው_ነገር_ጤና!!
በየጊዜው ጤና ነክ ጉዳዎችን በማንበብ እውቀቶን ያዳብሩ!!!

💬ሀሳብ ፣ጥያቄና አስታየት ካላችሁና ስለ ጤናችሁ ማወቅ የምትፈልጉት ነገር ካለ በነፃነት ላኩልን -በደስታ እንቀበላለን።
@Contact_EdMap

© ዶ/ር ሀብቴ ገብረሚካኤል

ጥያቄ ፣ሀሳብ አስታየት ላኩልን

ቤተሰብ ይሁኑ!!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5
👣"የስኬት ጉዞዎ በአንድ እርምጃ ይጀምራል። ዛሬ ይጀምሩት!"
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
7👍2
Audio
🎙የ2015 የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ከወሰደው የEdMap ቤተሰብ ጋር ያደረግነውን ክፍል 1 ቆይታ ያድምጡ፤ ብዙ ቁምነገር ያገኙበታል!

መልካም ቆይታ!

TikTok | Facebook | Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
5
👨‍💻በራሴ ኦንላይን ኮዲንግ ለመማር ከየት ልጀምር?

ክፍል አንድ

1. ፍላጎትዎን ይወቁ
- ለምን ኮድ ማድረግ መማር እንደፈለጉ ይለዩ። ለ web development፣ ዳታ ሳይንስ ወይስ አፕልኬሽን ለመስራት?
- ፍላጎትዎን መረዳት መንገድዎን ቀለል ያደርግልዎታል።

2. Programming Language ይምረጡ
- ለጀማሪ ቀላል በሆነ ፕሮግራሚንግ ቋንቋ ይጀምሩ። Phyton ለጀማሪዎች ብዙ ጊዜ ይመከራል።
- Java Script ለWeb Development ተመራጭ ነው፣ ሩቢ ደግሞ በቀላልነቱ ይታወቃል።

3. የመማሪያ መንገድዎን ይወስኑ
- የኮዲንግ ኮርሶችን የሚያቀርቡ የተለያዩ Online መድረኮች አሉ። Codecademy, freeCodeCamp, Udacity, ወይም Coursera ለምሳሌነት ይጠቀሳሉ።

4. በመሰረታዊ ነገሮች ይጀምሩ
- የኮዲንግ እውቀትዎን መሰረት ለማስያዝ እንደ variables ፣ data types ፣ control structures (if statements, loops), እና functions ካሉት ይጀምሩ።

5. ዘወትር ይለማመዱ
- ኮድ ማድረግ በመለማመድ የሚሻሻል ችሎታ ነው። የተማሩትን ለማጠናከር በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ይስሩ።
- እንደ HackerRank እና LeetCode ያሉ ድህረ ገፆች ለተለያዩ የክህሎት ደረጃዎች የኮድ ፈተናዎችን ያቀርባሉ። እዛ ላይም ራስዎን ይገምግሙ፣ ያዳብሩ።

ይቀጥላል...

⚡️ TikTok | Facebook | Telegram ⚡️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍531
🚫 4 በመጀመሪያ ሥራዎ ላይ ማስወገድ ያለብዎ  ስህተቶች

1. ጥያቄ አለመጠየቅ፡-
አንዳንድ ሰዎች ልምድ የሌላቸው እንዳይመስሉ በመፍራት ጥያቄዎችን ከመጠየቅ ወደኋላ ይላሉ።

2. ከመጠን በላይ በራስ መተማመን፡- በራስ መተማመን ጥሩ ቢሆንም ከመጠን በላይ በራስ መተማመን ግን ወደኋላ ይገፋልl።

3. ራስን ማግለል፡-  ከስራ ባልደረቦችዎ ጋር በሙያዊ እና በማህበራዊ ግንኙነት ለመሳተፍ ይሞክሩ።

4. አስተያየቶችን ችላ ማለት፡- አወንታዊም ሆነ ገንቢ የሆነ አስተያየት ከተቀበሉ ራስዎን ለማሻሻል ይጠቀሙበት።

TikTok | Facebook | Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍6
The sunrise over the mountains painted the sky with vibrant hues, creating a breathtaking _____________.
Anonymous Quiz
75%
Panorama
11%
Maelstrom
6%
Quandary
8%
Connotation
4
☀️ 5 በጠዋት የመነሳት ልምድ ማዳበሪያ መንገዶች

1. ጊዚያዊ ለውጥ
- እንበልና 2 ሰዓት ከሆነ አዘውትረው የሜነሱት ነገ 1፡45 በሚቀጥለው ቀን 1፡30 ከዛም 1፡15 እያሉ በየዕለቱ 15 ደቂቃ በማሻሻል እስከ ግብዎ ድረስ እየቀነሱ መሄድ

2. የመኝታ ሰዓትዎን ማስታወስ
- የመኝታ ሰዓት ሲሆን ለማስታወስ ማንቂያ/ Alarm ይጠቀሙ። ለመተኛት ጊዜው አሁን መሆኑን ለአዕምሮዎ እንዲጠቁም ይረዳል።

3. አስደሳች የጠዋት ልምዶች
- ለጠዋትዎ የሚወዱትን ነገር ያቅዱ፣ ጣፋጭ ቁርስ ወይም ንባብ ሊሆን ይችላል። ከአልጋ መነሳትን የበለጠ አስደሳች ያደርገዋል።

4. የምሽት ዝግጅቶች
- ሲነሱ የሚለብሱትን ልብሶች አስቀምጡ፣ ቁርስ እና ቡና/ሻይ ያዘጋጁ፣ ጠዋት ላይ የሚሰሩትን ስራ ይቀንስልዎታል።

5. የቡና አፍቃሪ ነዎት?
- ቡና ወይም ሻይ ከወደዱ የጠዋት ልምድዎ ውስጥ ያካቱት። የሚወዱትን ቡና ወይም ሻይ ማሰብ ከአልጋዎ ለመውጣት 1 ምክንያት ይሰጥዎታል።

TikTok | Facebook | Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍11
📖የመፅሀፍ ጥቆማ

"It Ends with Us" በ Colleen Hoover

📌የመፅሀፉ ትኩረት፡ ስለ ውስብስብ የፍቅር ግንኙነቶች የሚያስተምት ሲሆን ነገሮች አስቸጋሪ ሲሆኑ ሰዎች ስለሚያደርጉት ከባድ ውሳኔዎች ያሳያል።

🏳️ቁልፍ ሀሳቦች፡
- በፍቅር ግኑኝነት ውስጥ ስለሚኖሩ ፈተናዎች፣ እድገቶች እንዲሁም እንዴት አዕምሯዊ ጥንካሬን ማዳበር እንደሚቻል ያስተምራል።

⤵️ምን እንማር?
በህይወት ጎዳና ውስጥ ፍቅር እና ምርጫ የማይነጣጠሉ የግግላዊ እድገት ዋና መሰረቶች እንደሆኑ ነው።

🕔በቀን 1 ሰዓትዎ ለዚህ መፅሀፍ ቢሰጡ በሁለት ሳምንታት ውስጥ አንብበው ይጨርሱታል።

TikTok | Facebook | Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
6👍1