EdMap Community
3.29K subscribers
910 photos
8 videos
40 files
596 links
EdMap, Powered by PiSpace Inc.
A one-stop destination platform for Ethiopian students.

For further information @contact_edmap

Our website:
🌐 www.edmap.et
Download Telegram
ሁሌም በየሳምንቱ ቅዳሜ በማራኪ የአፃፃፍ ዘዴ እውቀቶችን በማካፈል የሚታወቀው የጋዜጠኛ ወንድዬ እንግዳ ፅሁፎችን እንድታነቡ ጋበዝን።

ነገ ስለ ቀድሞው የሊቢያ ፕሬዝዳንት መሃመድ ጋዳፊ ሞት፣ ከሞቱስ በስተርጀባ ማን እንዳለ፣ ወዘተ ርዕሰ ጉዳዮች እያነሳ ያዘጋጀውን ጣፋጭ ፅሁፍ እነሆ ወደ እናንተ እናቀርባለን።
ይጠብቁን!

@EdMap_Community | @EdMap_Eth

#የቅዳሜቀደዳ #ወንድዬእንግዳ #WendiyeEngida
👍19
ባለ ጥቁሩ እግር ድመት በዓለም ላይ በጣም ገዳይ ከሚባሉት የድመት ዝርያ ነው።
ክብደቱ ከ2-6 ኪሎ ግራም ብቻ ቢሆንም፣ ነብር በ6 ወራት ውስጥ ከሚያድነው የበለጠ  በአንድ ሌሊት ባለ  ጥቁር እግር ድመት ያድናል።

#EdMap #FunFact
👍8😁1
አና ካሬኒና እንደ ፍቅር፣ ቤተሰብ፣ ማህበራዊ ህይወት ያሉ የተለያዩ ጭብጦችን የሚዳስስ ውስብስብ ልቦለድ ነው። ሴራው የሁለት ጥንዶችን ታሪክ ይከተላል::

ልብ ወለዱ በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ባሉ የሩስያ ማህበረሰብ ላይ ያውጠነጥናል።

ደራሲው የተለያዩ የስልጣን ደረጃዎችን እና የሩስያ መኳንንትን የአምልኮ ሥርዓቶች እና ስምምነቶችን ይመረምራል። በተጨማሪም የህብረተሰቡን ግብዝነት፣ ሙስና እና ኢ-እኩልነት በመተቸት ስለ ሰው ልጅ ስነ-ልቦና እና ባህሪ ጥልቅ ትንታኔ ይሰጣል።

#EdMap #Book_Review
@EdMap_Community | @EdMap_Eth
👍6
ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምርቶች ላይ ለኤድማፕ ቤተሰቦች ልዩ ቅናሽ ማድረጋችንም፣ በዛም በርካታ ቤተሰቦቻችን መደሰታቸው ይታወሳል። EdDiscount ሁሌም ከጎንዎ አለ!

በቅርቡም ተመሳሳይ አስደሳች ቅናሾችን እነሆም እንላለን። እስካዛው ድረስ እነዚህን ቅናሾች ይጠቀሙ።

1. Sinerline Exercise Book (50 page)
ገበያ ላይ = 820 ብር በደርዘን
EdDiscount ላይ = 620 ብር ብቻ!

2. Hp Laptop (Core i5, 1TB HDD, 8Gb Ram, 6th gen, 5hrs Battery Life)

ገበያ ላይ : 27,500 ብር
EdDiscount ላይ በ25,500 ብር ብቻ!

3. Saachhi 3 in 1 Blender:
ገበያ ላይ : 3700 ብር
EdDiscount ላይ በ3200 ብር ብቻ!

ይፍጠኑ! በተወሰነ ቁጥር ብቻ የቀረቡትን ቶሎ ይሸምቱ።

አዲስ አበባ ለምትኖሩ በሙሉ ባሉበት ይደርሳችኋል!

በቅርቡ መተግበሪያ (Application) ይፋ ሲሆን ደግሞ ወደ የተለያዩ ከተማዎች አድማሳችንን እናሰፋለን።

ለማዘዝ @Contact_EdMap ላይ አልያም በስራ ሰዓት 011- 639-5500 ይደውሉ።

ለተጨማሪ ዲልስ እና ቅናሽ @edmapdeals ይጎብኙ።
👍9
"..ወቅቱ እ.ኤ.አ 1986 ላይ ነው! የአሜሪካ ደህንነት ተቋም የሆነው "CIA" ከሰሜን አፍሪካዋ ሃገር ሊብያ ከሳተላይት እና ኤሌክትሮኒክ ሰርቪላንስ የሚሰበሰቡ የተለያዩ ሚስጥራዊ መልእክቶችን እየቃረመ ነው። ከነዚህ ሚስጥራዊ መልእክቶች ውስጥ ለአሜሪካ የደህንነት ስጋት የሚሆን ነገር ከተገኘ ይመረመራል። የዛን ቀን "CIA" 397 የተለያዩ ሚስጥራዊ መልእክቶችን አዳምጦ ምንም የደህንነት ስጋት የሚሆን ነገር አላገኘም! ነገር ግን ጠልፈው ከሚሰሟቸው መልእክቶች ውስጥ 398ኛው መልእክት ለአሜሪካ ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት ሆኖ ተገኘ።  መልእክቱ "...stand by and be ready to attack American targets and Execute the plan..." የሚል ነበር! ይህ መልዕክት የደህንነት ተቋሙ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጠረ። ከሊቢያ ተጠልፎ የተሰማው መልእክት "Muammar Gaddafi" ከሚመራው መንግስት እንደሆነ ማወቅ ቢችሉም ጥቃት እንዲደርስባቸው የተባሉት አሜሪካውያን የት እና መቼ እንደሆነ ግን ማወቅ አልተቻለም። ማጣራታቸውን ቀጠሉ!..."

በጋዜጠኛ ወንድዬ እንግዳ የተፃፈው ይህ ማራኪ ፅሁፍ ሙሉውን በኤድማፕ ድህረገፅ ላይ ያገኙታል። እንዲያነቡት ጋበዝን!

በዚህ ያግኙት ፡ https://www.edmap.et/the-story-behind-muammar-gaddafi/
👍201😁1
#Get_to_know_your_degree

የንግድ ሥራ አስተዳደር (ቢዝነስ ማኔጅመንት) በመባል የሚታወቀው የጥናት ዘርፍ የንግድ ድርጅትን የሚያስተዳድር ነው።

የማኔጅመንት፣ የፋይናንስ አስተዳደር፣ የጥራት ማረጋገጫ አስተዳደር፣ የመረጃ ትንተና፣ የሽያጭ፣ የፕሮጀክት አስተዳደር፣ የኢንፎርሜሽን-ቴክኖሎጂ አስተዳደር እና የመሳሰሉትን ያካተቱ መስኮችንም በውስጡ ይዞ አገልግሎት ይሰጣል።

በቢዝነስ አስተዳደር እውቅና ያለው ሰው በሚፈለገው መስክ በማንኛውም ኩባንያ ውስጥ መሥራት ይችላል። በሚከተሉት ቦታዎች ላይ መስራት ይችላል:-

- በማርኬቲንግ አስተዳደር
- በሂሳብ ባለሙያ እና ፋይናንስ
- በኦፕሬሽን አስተዳደር
- በሰው ሀብት ስፔሻሊስት
- በሽያጭ ሃላፊ
- በምክር አገልግሎት ዘርፍ

#EdMap #Business_Administartion #Get_to_know_your_degree

@EdMap_Community | @EdMap_Eth
👍8
😁😭
#MedSchool #Medlife #meme

How many med students have we got here?
😁16👎1
በግቢ ቆይታዎ ለማጥናት ተስማሚ ቦታ የት ነው ብለው ያስባሉ?

ኤድማፕ ባዘጋጀው አምድ (Blog) የንባብ ፍላጎትዎን በመጨመር የፈተና ውጤትዎ የተሻለ እንዲሆን ሊያድርጉ የሚችሉ የማንበቢያ ስፍራዎችን ለማሳየት ሞክሯል። መነሳሳት ሊፈጥሩ የሚችሉ ቤተመፅሀፍትና ማራኪ ቦታዎች የት እንደሆኑ በተዘጋጀው አምድ (Blog) ማወቅ ይችላሉ።

https://www.edmap.et/best-study-spots-on-campus/
1
Forwarded from SkillMatch
Forwarded from SkillMatch
EdMap is Hiring!

Join our team at EdMap as a Marketing Communications Specialist in Addis Ababa, Ethiopia!

Responsibilities:
- Create engaging content for various marketing channels
- Coordinate marketing campaigns and develop promotional materials
- Execute strategies aligned with company objectives
- Collaborate with the creative team for high-quality visuals
- Monitor and optimize campaign performance
- Manage social media accounts and engagement
- Act as a spokesperson and prepare communications

Qualifications:
- Bachelor's degree in Marketing, Communications, or related field
- Experience in developing marketing strategies and content creation for social media platforms
- Strong writing and editing skills
- Understanding of digital media trends and best practices
- Proficiency in social media management tools and analytics
- Familiarity with video production and editing is a plus
- Excellent interpersonal skills and ability to work in a team
- Highly organized with a creative mindset

If you're passionate about marketing communications and possess strong strategic thinking skills, don't miss this opportunity! Apply now at https://skillmatchjobs.com/qsm_quiz/marketing-communications-specialist/.

Join our dynamic team and make an impact.

#MarketingJobs #JoinUs #EdMap #AddisAbaba
👍6
የኤድማፕ የስራ ጥቆማ

❗️እነዚህ ክፍት የስራ ቦታዎች የኤድማፕ አይደሉም፣ ለማመልከት ሊንኩን ይጫኑ!

1. Business plan and Proposal Writer

2. Logo and Brand Identity Designer

3. Waiter and Hed Waiter

4. Receptionist

5. Personal Assistant/ Social Media Manager

6. Graphics Designer

#Job_Post #Career #EdMap_Ethiopia
👍3
#ይህን_ያውቁ_ኖሯል

ከተለያዩ የአለም ክፍሎች ከተውጣጡ ሰዎች እና ባለሙያዎች ጋር በፕሮጀክታችሁ ላይ በአንድነት ለመስራት የሚረዳዎ ድህረ ገጽ እንዳለ ያውቃሉ?

ማንኛውም ኘሮጀክቶች እና ስራዎች ላይ ደረጃ በደረጃ እንድትሰሩ የሚረዳው ይህ ድህረ ገፅ፣ ከመነሻ ሀሳብ  እስከ አውደ ጥናቱ ድረስ በየቀኑ በመተንተን በሚጋሩት ወይም ድህረ ገፁ ላይ በሚያገኙት ግሩም ፕሮጀክቶች የተለያዩ ሀሳብና እውቀትን ይገነባሉ።

በዚህ ያግኙት:  instructables

@EdMap_Community | @EdMap_Eth
👍61
Quiz time:)
_______ spent time abroad when I was a student, I found it easier to get used to ______ in another country.
Anonymous Quiz
20%
Having, living
48%
Having, live
9%
To have, living
22%
Have, live
👍51
በዚህ ሳምንት በአዲስ አበባ የሚሄዱ ዝግጅቶች እና ኤግዚቢሽንኖች

1. Summer ግራፊክ ዲዛይን ኮርስ

📅 ሐምሌ 3 2015
📍 አዲስ አበባ፣ ሜክሲኮ፣ ፈጠራ ማዕከል ከሸበሌ ሆቴል ፊት ለፊት
🙏 @nibred_01

2.የክረምት መዝናኛ ለልጆች
📅 ሰኔ 26 2015
📍 በጀርመን ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ (ካዛንቺስ አዋሬ)

@EdMap_Community | @EdMap_Eth
😃ለ2015 አዲስ አመት ያለዎት እቅድ ምን ነበር? ስፖርት መጀመር፣ ጤናማ አመጋገብ መከተል፣ በትምህርትዎ የተሻለ ውጤት ማምጣት ወይስ ተጨማሪ ገንዘብ ማግኘት?

ግን ለማሰብ ትንሽ ጊዜ እንውሰድና እቅዶቻችንን አሳክተናል ወይ ብለን ራሳችንን እንጠይቅ።

ዓመቱ ሊያልቅ 76 ቀናት ይቀሩታል፣ ቀጣዩን አዲስ አመት ከመጠበቅ ይልቅ ቢያንስ አንዱን ግባችንን ለማሳካት ቀሪዎን ቀናቶችን ብንጠቀምስ?

አሪፍ ሀሳብ ነው አይደል? እና ራስዎትን በነፃ በማሰልጠት ለመጪው አመት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ብንነግርዎስ?

በዚህ ክረምት ቢማሩት ብለን የምንመክርዎ ሁለት ኮርሶችን እነሆ።

በጎግል ተዘጋጅተው በነፃ የቀረቡት ከዛም ሲያጠናቅቁ ሰርተፍኬት የሚሰጥዎት ኮርሶች፡
1. "Introduction to AI": የ AI አለም ምን ይመስላል የሚለውን የሚያስቀኝና ውስብስብ ሂሳባዊ ትምህርት እንዲሁም ምንም የፕሮግራሚንግ እውቀት የማይፈልግ ትምህርት ነው።
በዚህ ያግኙት ፡ https://course.elementsofai.com/

2. "Building AI": AI ከመገንባት በስተጀርባ ያሉት ሂደቶች ምንድን ናቸው የሚለውን ሲያስቃኝ መሰረታዊ የPython programming እውቀት ቢኖርዎ ይመከራል።
በዚህ ያግኙት ፡ https://buildingai.elementsofai.com/


@EdMap_Community | @EdMap_Eth
8👍5
ደስታና ሰላም የበዛበት የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል እንዲሆን ኤድማፕ ከልብ ይመኛል።

ይህ በዓል ይበልጥ የሚያስተሳስረን፣ የሚያፋቅረን እና ህብረት የሚያመጣልን ይሁንልን!

እንኳን አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

@EdMap_Community | @EdMap_Eth
12👍1
በተማሪና ወላጆች ጥያቄ መሰረት የተዘጋጀው የEdMap ጥቅል!

የEdMap Scholarlink አዲስ ተጨማሪ ጥቅል (Package) በውስጡ አካቶ መጥቷል!
"EdMap Package" ተብሎ የተሰየመው ይህ ለወላጆችና ለተማሪዎች እፎይታን የሚሰጥ ጥቅል የሚከተሉትን የመፍታት አቅም አለው።

- ተማሪዎች የትኛውን የትምህርት መስክ (Field) ብማር ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ይስማማል? ወላጆችም ልጄ የቱ መስክ ላይ እውቀቱን ቢያዳብር ይጠቀማል የሚለውን ጭንቀትዎን መፍትሄ ይሰጥዋል።

- ምን ላይ ጎበዝና ተሰጥዖ እንዳልዎት ግራ ከገባዎም "EdMap Package" በትምህርት ቆይታዎ ከጎንዎ አለ።

የ"EdMap Package" አገልግሎት ከብዙ በጥቂቱ:
-አጠቃላይ የአካዳሚክ Performance ምዘና/ትንተና
- የተሟላ ስኮላርሺፕ መረጃ
- የስራ/ሙያ አቅጣጫ ማማከር
- ዲፓርትመንት መረጣ
- በስልክና በ ኦንላይን ከ ባለሙያዎች ጋር ምክክር

እነዚህን ሁሉ ለማግኘትና ለመመዝገብ እንዲሁም ተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ @Contact_EdMap አልያም በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥራችን 0116 - 39 55 - 00 ሀሎ ይበሉን!

የ"EdMap Package" ዋጋ 500 ብር ነው! ሌሆቹንም የ EdMap ፓኬጆች (Basic, Premium & Dreamer) ለማግኘት ይሄን ሊንክ ይጠቀሙ

በትምህርት ጉዞዎ ላይ ብልህ ውሳኔ በመወሰን የተሳካ ህይወት እንዲኖርዎ አለኝታ መሆናችን ይቀጥላል።
10👍3
#History_Photographed
እ.ኤ.አ በ1920 የተጀመረውና ተወዳጅነትን ያፈራው Swing Dance በሃርለም እና በጃዝ ሙዚቃ በመታጀብ የሚደረግ የዳንስ እንቅስቃሴ ነው።

የነፃነት፣ ደስታ እና የመሰባሰቢያ ምልክት ተደረጎ የሚቆጠረው ይህ የዳንስ ስልት በመላ ሀገሪቱ ተወዳጅነትን ያፈራ ነበር።

#History_Photographed #EdMap
1
☀️ፍቅር፣ ደስታ እና ስኬት ይገባሀል!
4👍1