EdMap Community
3.29K subscribers
910 photos
8 videos
40 files
596 links
EdMap, Powered by PiSpace Inc.
A one-stop destination platform for Ethiopian students.

For further information @contact_edmap

Our website:
🌐 www.edmap.et
Download Telegram
የኮምፒዩተር ቴክኒሻን የኮምፒዩተር ስርዓቶችን የመጠበቅ, ስህተቶችን የመፍታት እና የድርጅቱን ሃርድዌር የመጠገን ኃላፊነት ያለው ባለሙያ ነው።

ከታች የተቀመጡትን ሊንኮች በመንካት ለዚሁ ስራ ሊጠቅሟችሁ የሚችሉትን የዩቱዩብ ገፆች ተመልከቱ።

1. Brandon Cox

2. GabakUSA Free Computer Training

3. Carey Holzman

4. Business Letters

5. Ricks Tech Repairs


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍6
1 ሚሊዮን ብር በሚያሸልመው የ Solve IT 2023 የፈጠራ ውድድር ይሳተፉ።

የፈጠራ ሃሳብ ያላችሁ ወጣቶች ከታች በተቀመጡት አማራጮች መመዝገብ ትችላላችሁ።

የውድድሩ ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን 1 ሚሊዮን ብር የሥራ መነሻ (Seed Funding) ተሸላሚ ያደርጋል።

ለመመዝገብ ➭ https://solveit-et.com

@EdMap_Community l @EdMap_Eth
👍6
#Get_to_know_your_degree

የኪነጥበብ እና የንድፍ ዲግሪ እንደ ስዕል፣ ቅርፃቅርፅ እና ግራፊክ ዲዛይን ያሉ የተለያዩ ምስላዊ ሚዲያዎችን ያጠናል።

የጥበብ እና የንድፍ ዋና ባለሙያዎች መሰረታዊ የንድፍ መርሆችን፣ የቀለም ንድፈ ሃሳብ፣ ሂሳዊ አስተሳሰብ እና ጥበባዊ ቴክኒኮችን ይማራሉ።

በሥነ ጥበብ እና ዲዛይን የተካነ ሰው በሚከተሉት የስራ መስክ ውስጥ ሊሰራ ይችላል:-

- ፋሽን ኢንዱስትሪ
- የጨዋታ Desgin እና አኒሜሽን ኢንዱስትሪ
- ኢሉስትሬሽን እና ግራፊክስ Desgin
- የፊልም ኢንዱስትሪ
- ኢንቴሪየር ዲዛይን
-የሙዚቃ ኢንዱስትሪ

#EdMap #Art_And_Desgin #Get_to_know_your_degree
👍5
😁12👎1
IELTS
EdMap Community
ስኮላርሺፕ ላይ ብዙ ጊዜ የሚታየው IELTS ምንድን ነው? IELTS ፈተና መውሰድ ለስኮላርሺፕ ዕድል ምን ይጠቅማል? ኢትዮጵያ ውስጥ ይሄን ፈተና እንዴት መውሰድ ይቻላል እንዲሁም ፈተናው በውስጡ ምን ያካትታል የሚሉና ሌሎች ኤድማፕ ያጠናቀረውን መረጃዎች በዚህ የድምፅ ቅጂ ማዳመጥ ይችላሉ።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍7
ይህን ያውቁ ኖሯል?

ትኩረትን ለመሰብሰብ የሚረዳ መተግበሪያ (Application) እንዳለ ያውቁ ኖሯል?

Keep me Out: ስልክዎን በመቆለፍ ሃሳባችሁ ሳይሰረቅ መፈፀም ያቀዳችሁትን በተገቢው መልኩ እንድትፈፅሙ የሚረዳ ነው።

በጥናትዎ ላይ ለማተኮር፣ ዘና ለማለት ወይም የእንቅልፍ ሰዓትዎን ለማሻሻል ሊያግዝዎ ይችላል።

ሊንክ: https://play.google.com/store/apps/details?id=vikesh.dass.lockmeout
👍12
5 በነፃ "ፕሮፌሽናል" የሆነ ሲቪ እንዲሰሩ የሚያግዝዎት ድህረገፆች።

1. Canva
2. Zety
3. Resume
4. Novoresume
5. VisualCV

@EdMap_Community l @EdMap_Eth
👍8
በዚህ ሳምንት በአዲስ አበባ የሚሄዱ ዝግጅቶች እና ኤግዚቢሽንኖች

1.የጥበብ ስራዎች

📍: እንጦጦ የኪነጥበብ ማዕከል

📅: እስከ ሐምሌ 30 2015

2. የፎቶ ኤግዚቢሽን

📍: አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሲስ

📅: ሰኔ 14 2015 12.30L.T

- የአለባበስ ኮድ: መደበኛ አለባበስ

3. አርተፊሻል ኢንተሊጀንስ ፡ የሰው እና የማሽን ፍጥጫ

📍፡ በኤረር የተፈጥሮ ደን ውስጥ

📅 ሰኔ 18 2015

- ትራንስፖርት፣ ምሳ እና ቡና፣ የጫካ ውስጥ ሽርሽር
መግቢያ ብር 650
🙏 Eskender

EdMap English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍10
🌙 ጨረቃ ከባቢ አየር እንዲሁም ነፋስ ስለሌላት በጨረቃ ላይ ያሉ ማንኛውም የእግር አሻራዎች በጨረቃ ላይ ለዘላለም ይቆያሉ!

@EdMap_Community l @EdMap_Eth
👍8
📚የአመቱ ማጠቃለያ ፈተናዎች እንደደረሱ ይታወቃል ፤ በዚህ ሰዐት የተማሪ ጭንቀት ከሌላው ጊዜ ከፍ ይላል። ይህንን ጫና ለመቋቋም ጤናማ መንገዶችን መፈለግ በጣም አስፈላጊ ነው።

በጥናት መካከል አጭር እረፍት ማድረግ፣ ጥልቅ የአተነፋፈስ ልምምድ ማድረግ እና በቂ እንቅልፍ መተኛት የጭንቀት ደረጃዎችን በመቆጣጠር ላይ ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ።

በርቱ!🎓

@EdMap_Community l @EdMap_Eth
👍11
የኤድማፕ የስራ ጥቆማ

❗️እነዚህ ክፍት የስራ ቦታዎች የኤድማፕ አይደሉም፣ ለማመልከት ሊንኩን ይጫኑ!

1. Sales Person

2. Fashion Photographer

3. Betting Cashier

4. Interior Designer/ Intern Unpaid

5. Reception for language and Computer Training Centre

6. Customer Service

#Job_Post #Career #EdMap_Eth
👍8😁2
የካዛኪስታን መንግስት ለአለማቀፍ ተማሪዎች ያቀረበው ስኮላርሺፕ 2023

ይህ የስኮላርሺፕ ፕሮግራም በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ደረጃዎች ላሉ ዓለምአቀፍ ተማሪዎች በካዛኪስታን እንዲማሩ እድል የሚሰጥ ነው። ሙሉ የትምህርት ክፍያዎችም ከመሸፈናቸው በተጨማሪ ወርሃዊ አበል ይሰጣል።

የባችለር ዲግሪ ስኮላርሺፕ (490)
የማስተርስ ስኮላርሺፕ (50)
የፒኤችዲ ስኪላርሺፕ (10).

በሁሉም የዲግሪ ደረጃዎች ላሉ ዓለምአቀፍ ተማሪዎች ክፍት የሆነው ይህ እድል አመልካቹ ለተፈለገው ፕሮግራም (ባችለርስ፣ ማስተርስ ወይም ፒኤችዲ) የብቃት መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅበታል።

የማመልከቻ ማጠናቀቂያ ቀን : June 30 , 2023

ለሌሎች መስፈርቶችና ለማመልከት ይሄን ይጠቀሙ : https://www.edmap.et/kazakhstan-government-scholarships-for-international-students-2023/

@EdMap_Community l @EdMap_Eth
👍7
200 ወጣቶች ወደ አውሮፓ ትሄዳላችሁ ተብለው ከፍተኛ ገንዘብ መጭበርበራቸውን ገለጹ።

መቀመጫውን አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ደንበል ያደረገው “ኤክስሉሲቭ ትራቭል” ወደ አወሮፓ እና ወደ ተለያዩ አገራት አልካችኋለሁ በማለት ከ200 የሚጠጉ ወጣቶች ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ከሰበሰበ በኋላ አድራሻውን አጥፍቶ እንደጠፋ አዲስ ማለዳ ዘግቧል።

የዜና ምንጭ: Tikvah Magazine
ሙሉውን ያንብቡ

እንደዚህ አይነት ዜናዎች በተደጋጋሚ እየሰማን እንገኛለን። ስለ ስኮላርሺፕ፣ ስለ ውጭ ሀገር የስራና የትምህርት እድል በቂ መረጃ እየተሰጠ አለመሆኑ መሰል የማጭበርበር መንገዶች እንዲሰፉ ሆኗል።

ኤድማፕ፣ እንዴት የውጪ ሀገር የትምህርትና የስራ ዕድል ማግኘት እንደሚቻል መረጃዎችን በግልፅ እየሰጠ ነበር፣ አሁንም እየሰጠ ይገኛል። ScholarLink በማለት በሰየምነው ዝግጅትም ለእርስዎ እርዳታና እገዛ በመስጠትም ከጎንዎ ነን።

አስቀድመን፣ ለተወሰኑ የኤድማፕ ቤተሰቦች ብቻ ስናቀርበው የነበረውን ይሄን እገዛ በእናንተ ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ለብዙ የኤድማፕ ቤተሰቦች ለማድረስ እየተዘጋጀን እንገኛለን።

በScholarLink የምንሰጣቸውን አዳዲስ መረጃዎችና አገልግሎቶች እንዲከታተሉ ጋበዝን።
👍111
ዋናው ምን ያህል ጊዜ ወደቅክ ሳይሆን ለምን ያህል ጊዜ ደግመህ ተነሳህ ነው

@EdMap_Eth l @EdMap_Community
👍10
የቅድመ ሽያጭ ፕሮግራማችን ላይ እቃዎችን በማዘዝ ላደረጉት ተሳትፎ እናመሰግናለን!

ከዚህ ቀደም የነበሩት ብቻ አይደለም ፤ በዚህ ሳምንትም አዲስ የልዩ ቅናሽ ዋጋ ያላቸውን እቃዎች ለእርስዎ እናቀርባለን። ይሄንንም እያደረግን እፎይታ ስለምንሰጥዎ ደስተኞች ነን።

እቃዎቹ በፍጠነት በመሸጣቸው ምክንያት እድሉን ላላገኙ በሙሉ ይቅርታ እየጠየቅን የእቃዎች ውስንነት እንዳይከሰትም ጠንክረን እየሰራን እንገኛለን።

በድጋሚ የኤድማፕ ቤተሰብ በመሆንዎ እናመሰግናለን፣ ምንግዜም የዋጋ እፎይታ የሚሰጡ ልዩ ቅናሽ ያለባቸውን ምርቶችና አገልግሎቶች ለእርስዎ ለማቅረብ ቆርጠን ተነስተናል። 💙


ለተጨማሪ Deal እና Discount ይከታተሉን!

@EdMap_Eth
@Edmapdeals
@EdMap_Community
👍6
የምግብ ዝግጅት (Catering) ለተለያዩ ፕሮግራሞች ምግብ በማዘጋጀት እና በማቅረብ ገንዘብ ማግኘት የሚችሉበት አዋጭ ስራ ነው።

እንዴት ምግብ ማብሰል እንደሚችሉ፣ ያበሰሉትን እንዴት ማስተናገድና ማቅረብ እንደሚችሉ ሙያውን በመማር ማወቅ ይችላሉ። ይሄንን ሙያ ወደ ንግድ ስራ ለመቀየር መጀመሪያ የተወሰነ ዓይንነት ምግብ/ዝግጅት ይምረጡ፣ በመቀጠል ጠንካራ የንግድ መለያዎን በመፍጠር ከጥሩ አቅራቢዎች ጋር አብረው ይስሩ።

ዋጋዎን በማስቀመጥ ጥሩ አገልግሎት ለመስጠት ሀ ብለው ይጀምሩ። የምግብ ስራ ዝግጅት (Catering) በፈጠራ ችሎታና በትጋት ከታገዘ የተሳካ የንግድ ስራ የመሆን እድሉ ላቅ ያለ ነው።

ይሄንን ስራ በመስራት ተጨማሪ ገንዘብ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ለዚህ ስራ ሊረዷችሁ የሚችሉ የዩቲዩብ ቻናሎችን በመጎብኘት ራስዎን ማስተማር ይችላሉ።

1. Kostas Lazanas

2. Young Entrepreneurs Forum

3. Kef Tube

4. New Business Ideas

5. Foxtails Catering Service & Training Videos

#Ed_Map #Self_Made #Catering_Service
👍8
የህክምና ተማሪዎች እና ባለሙያዎች ምን ምን የሙያ አማራጭ መንገዶች አሏቸው?

1. የህክምና ፅሁፎች መፃፍ: የህክምና እውታችሁን እና የመፃግ ችሎታዎችሁን በመጠቀም ለድህረ ገፆች የፋርማሲዩቲካል ኩባንያዎች ወይም የጤና አጠባበቅ ድርጅቶች የሚሆኑ ፅሁፎችን ማዘጋጀት።

2. የህክምና Sales and Marketing: ይሄ ሙያ የህክምና እውቀታችሁን ከንግግር ችሎታችሁ ጋር በማዋሃድ የህክምና እቃዎችን መሸጥ መቻል ማለት ነው።

3. Medical Entrepreneurship (የህክምና ስራ ፈጠራ): የራሳችሁ ከጤና አጠባበቅ ጋር የተያያዘ ስራ በመጀመር የህክምና እውቀታችሁን ከስራ ፈጣሪነት ጋር በማጣመር የተሳካለት መሆን ትችላላችሁ።

@EdMap_Community | @EdMap_Eth

#Medical #EdMap #Health
👍11
ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምርቶች ላይ ለኤድማፕ ቤተሰቦች ልዩ ቅናሽ ማድረጋችንም፣ በዛም በርካታ ቤተሰቦቻችን መደሰታቸው ይታወሳል። EdDiscount ሁሌም ከጎንዎ አለ!

በቅርቡም ተመሳሳይ አስደሳች ቅናሾችን እነሆም እንላለን። እስካዛው ድረስ እነዚህን ቅናሾች ይጠቀሙ።

1. Sinerline Exercise Book (50 page)
ገበያ ላይ = 820 ብር በደርዘን
EdDiscount ላይ = 620 ብር ብቻ!

2. Hp Laptop (Core i5, 1TB HDD, 8Gb Ram, 6th gen, 5hrs Battery Life)

ገበያ ላይ : 27,500 ብር
EdDiscount ላይ በ25,500 ብር ብቻ!

3. Saachhi 3 in 1 Blender:
ገበያ ላይ : 3700 ብር
EdDiscount ላይ በ3200 ብር ብቻ!

ይፍጠኑ! በተወሰነ ቁጥር ብቻ የቀረቡትን ቶሎ ይሸምቱ።

አዲስ አበባ ለምትኖሩ በሙሉ ባሉበት ይደርሳችኋል!

በቅርቡ መተግበሪያ (Application) ይፋ ሲሆን ደግሞ ወደ የተለያዩ ከተማዎች አድማሳችንን እናሰፋለን።

ለማዘዝ @Contact_EdMap ላይ አልያም በስራ ሰዓት 011- 639-5500 ይደውሉ።

ለተጨማሪ ዲልስ እና ቅናሽ @edmapdeals ይጎብኙ።
👍8
በአለም አቀፍ ደረጃ፣ በ2023፣ ስንት ሰዎች ከ100 ዓመት በላይ ናቸው?
Anonymous Quiz
21%
8,000
29%
102,000
26%
950
24%
316,000
😁7
ላይተር የተፈጠረው ከክብሪት በፊት መሆኑ ታውቃላችሁ?

እ.ኤ.አ በ1823 "Döbereuner's lamp" የሚል ስያሜ የተሰጠው ላይተር ሲሰራ ከ3 አመታት በኋላ በ1826 ክብሪቶች መመረት ጀመሩ።

#EdMap #FunFact
👍1
የሂሳብን ትምህርት በቀላሉ እንድትረዱ የሚያደርግ መተግበሪያ (Application) እንዳለ ያውቃሉ?

Photomath በተጠቃሚ ቁጥር ከፍ ያለ ሂሳባዊ መተግበሪያ ሲሆን በAI-Powered የተዘጋጁ አጋዥ ስልጠናዎች፣ ጥልቅ ማብራሪያዎች እንዲሁም ለሌሎች መፍትሄዎችን አካቶ ይዟል።

በዚህ ያግኙት: Photomath

@EdMap_Community | @EdMap_Eth