EdMap Community
3.29K subscribers
910 photos
8 videos
40 files
596 links
EdMap, Powered by PiSpace Inc.
A one-stop destination platform for Ethiopian students.

For further information @contact_edmap

Our website:
🌐 www.edmap.et
Download Telegram
#Get_to_know_your_degree

ባዮቴክኖሎጂ
የተፈጥሮ ሳይንስ እና የምህንድስና ሳይንሶች ውህደትን የሚያካትት ሁለገብ መስክ ሲሆን ፍጥረታትን ፣ ህዋሶችን ፣ ክፍሎቹን እና ሞለኪውላዊ አናሎግዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዳ የስራ መስክ ነው።

ባዮቴክኖሎጂ ከህክምናና ግብርና ጀምሮ እስከ አካባቢያችን ድረስ በብዙ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድርም ነው።

በባዮቴክኖሎጂ ውስጥ ጥቅም ላይ ከሚውሉት ቁልፍ ቴክኒኮች ውስጥ አንዱ የጄኔቲክ ምህንድስና ሲሆን ይህም ሳይንቲስቶች የተፈለገውን ውጤት ለማግኘት የኦርጋኒክ ዘረመል (genetic makeup) እንዲቀይሩ ያስችላቸዋል።

የባዮቴክኖሎጂ ባለሙያ በሚከተሉት የስራ መስክ ውስጥ ሊሰራ ይችላል:-

- ላቦራቶሪዎች እና ቢሮዎች
- የምርምር ተቋማት
- የመንግስት ላቦራቶሪዎች
- ሆስፒታሎች
- የትምህርት ተቋማት

#EdMap #Bio_Tech #Get_to_know_your_degree
👍8
#ይህን_ያውቁ_ኖሯል

ስኮላርፔዲያ የሚባል አስደናቂ ኢንሳይክሎፔዲያ እንዳለ ያውቃሉ? ስኮላርፔዲያ ልክ እንደ ዊኪፔዲያ ነው ነገር ግን እጅግ ለአጠቃቀም አመቺ እንዲሁም በባለሙያዎች የተፃፈ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል !

ስኮላርፔዲያ ከባዮሎጂካል ሳይንስ እስከ ማህበራዊ ሳይንስን የሚሸፍን የእውቀት ክምችት ነው! 📚💡


ሊንክ: Scholarpedia

@EdMap_Eth | @EdMap_Community
👍4
በትምህርት መገልገያ ውጤቶች ላይ ልዩ ቅናሽ በማድረግ የአካዳሚክ ስኬትዎ የተቃና እንዲሆን EdDiscount ሁሌም ከጎንዎ አለ! በቅርቡ አስደሳች ቅናሾችን እነሆ እንላለን። እስከዛው ድረስ እነዚህን ቅናሾች ይጠቀሙ።

1. AirPod Pro
ገበያ ላይ = 2000 ብር
EdDiscount ላይ = 1550 ብር ብቻ!

2. Casio Scientific Calculator
ገበያ ላይ : ከ800 - 1000 ብር
EdDiscount ላይ በ550 ብር ብቻ!

3. Ruga's Neckband Headset:
ገበያ ላይ : 1500 ብር
EdDiscount ላይ በ1050 ብር ብቻ!

ይፍጠኑ! በተወሰነ ቁጥር ብቻ የቀረቡትን ቶሎ ይሸምቱ።

አዲስ አበባ ለምትኖሩ በሙሉ ባሉበት ይደርሳችኋል!

በቅርቡ መተግበሪያ (Application) ይፋ ሲሆን ደግሞ ወደ የተለያዩ ከተማዎች አድማሳችንን እናሰፋለን።

ለማዘዝ @Contact_EdMap ላይ አልያም በስራ ሰዓት 011- 639-5500 ይደውሉ።

ለተጨማሪ ዲልስ እና ቅናሽ @edmapdeals ይጎብኙ።
👍7
ከላይ የምትመለከቱት ፎቶግራፍ የ ህንፃ ሰራተኞች ምሳቸውን ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ላይ ሲመገቡ የሚያሳይ ምስል ነው ። ለተመልካች ግራ ያጋባ ነበረው ይህ ፎቶ የሮክፌለር ማእከልን የሚገነቡ ሰራተኞችን አደገኛ ተግባራቸው ትኩረትን አሰጥቷቸዋል።

በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ የተለያዩ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች በሚገነቡበት ወቅት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰራተኞች ለሞት ይዳረጉ እንደነበርም ማስታወሻ ነው።

#History_Photogarphed #EdMap
ከሚከተሉት ውስጥ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በወቅቱ የነበረውን መንግስት የክርስትና እምነትን እንዲቀበል የፈቀደው/የተቀበለው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የትኛው ነው?
Anonymous Quiz
4%
ዳግማዊ ምኒልክ
3%
ኃይለ ሥላሴ
88%
ኢዛና
5%
ዮሐንስ
👍11😁1
በኮሎምቢያ የአማዞን ጫካ ውስጥ ከአውሮፕላን የመከስከስ አደጋ የተረፉና እዛው ቦታም ለ40 ቀናት ያክል ቀናት የቆዩ ቁጥራቸው አራት የሚደርሱ ህጻናት በህይወት ተገኙ። እድሜቸው 4 ፣ 9 ፣ 11 እና 13 አመት እንደሆነ የተገለፁት ህፃናት እናታቸው እና ሁለቱም የአውሮፕላን አብራሪዎች (Pilots) ወዲያውኑ ህይወታቸው እንዳረፈም ተነግሯል።

የልጆቹ አያት "ፋጢማ ቫለንሲያ" "እጅግ በጣም አመስጋኝ ነኝ" ካሉ በኋላም "ከአራቱ ልጆች መካከል በእድሜ ታላቅ የሆነቺው እናታቸው በሥራ ላይ በነበረችበት ጊዜ ሌሎቹን መንከባከብ ከዚህ ቀደም የምታደርገው በመሆኑ አሁንም ጫካ ውስጥ በሕይወት እንዲተርፉ ረድቷቸዋል" ብለዋል።

ዱቄት እና ዳቦን እንዲሁም በጫካ ውስጥ ያለውን ማንኛውንም ፍሬ እየበሉ እንደቆዩ ተገልጿል።

#EdMapNews #Trending #Planecrush
👍12
😁10
ለመጪው የክረምት ጊዜ ኤድማፕ ዲልስ በየትኛው ላይ ከጎንዎ እንዲሆን ይፈልጋሉ?
Anonymous Poll
34%
የጂም/ ፊትነስ ዲስካውንት
18%
የፎቶ ሞዴሊንግ ስልጠና ዲስካውንት
48%
የግራፊክስ ዲዛይን ኮርስ ዲስካውንት
👍9
እንቅልፍ የማጣት/የመተኛት ችግር በኮሌጅና ዩንቨርስቲ ተማሪዎች የተለመደ ነው።

ለዚህም ጭንቀት፣ መደበኛ ያልሆነ የጊዜ ሰሌዳ እንዲሁም ከቀድሞ የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ መምጣት እንደ ምክንያት ይጠቀሳሉ።

ለዚህም አንዳንድ መፍትሄዎች አሉ። እነሱም:

1. የእንቅልፍ መርሃግብርዎን (Program) ይጠብቁ:-  ወደ መኝታ የሚያመሩበት ሰዓት ተመሳሳይ ያድርጉት።

2. አካባቢዎን ያስተካክሉ: መኝታ ክፍልዎ ንፁህ፣ ፀጥ ያለና ጨለማ ቢሆን ይመረጣል።

3. ለመዝናናት ይሞክሩ: ከመተኛትዎ በፊት ሰውነትዎን ለማዝናናት ይሞክሩ፣ ለስለስ ያለ ሙዚቃም ያዳምጡ።

4. ጭንቀትን ይቆጣጠሩ: የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ወይም ከሚወዱት አንድ ሰው ጋር መነጋገር ውጤታማ ሊሆን ይችላል።

5. እርዳታ ይጠይቁ: እንቅልፍ ማጣትዎ ከቀጠለና በእለት ተእለት ህይወትዎ ላይ ተፅዕኖ ካሳደረ የጤና ባለሙያ ያማክሩ።

@EdMap_Eth | @EdMap_Community
👍21👎2
"የሚያስቁህ፣ በሚቸግርህ ጊዜ አለሁልህ የሚሉ፣ ከልብ የሚያስቡልህን አይነት ሰዎች በህይወትህ ውስጥ ልጠብቃቸው የሚገባቸው ሰዎች ናቸው። ራስህን ደስተኛ በሚያደርጉህ ሰዎች ክበብ ፤ ሌላው ሁሉም ሰው ያልፋል"

-ካርል ማርክስ
👍20
በዚህ ሳምንት በአዲስ አበባ የሚሄዱ ዝግጅቶች እና ኤግዚቢሽንኖች

1. 3 በ 1 ስልጠና (ዲጂታል ግብይት፣ ግራፊክ ዲዛይን እና ቪዲዮ አርትዖት)
📍: አዲስ አበባ
📅: ሰኔ 10፣ 2015
🙏 @Hayugashaw


2. ከተማ ትርኢት
📍: አምባሳደር ሞል (ሎቢ) 4ኪሎ
📅: ሰኔ 10፣2015 10:00 ሰአት
🙏 +251 91 148 1466
👍5
የሪል እስቴት ወኪል ንብረቶችን ለመግዛት፣ ለመሸጥ እና ለመከራየት የሚያመቻች ባለሙያ ነው።

ደንበኞቻቸው ተስማሚ ንብረቶችን እንዲያገኙ፣ ለገበያ እና ለሽያጭ የሚሸጡ ንብረቶችን እንዲያቀርቡ፣ ግብይቶችን እንዲደራደሩ እና አስፈላጊውን ውሎች እንዲዋዋሉ ይረዷቸዋል። ስኬታማ የሪል እስቴት ግብይቶች ለማካሄድ ወሳግኝ ሚና አላቸው።

ስለለሪል እስቴት ወኪሎች ጠቃሚ ግንዛቤዎችን ለማግኘት እና ችሎታዎትን ለማሻሻል እነዚህን የዩቲዩብ ቻናሎችን ይመልከቱ።

1. Broker Bob

2. Tom Ferry

3.
Ryan Serhant

4.
Chloe De Verrier

5. Carys Eccleshall

@EdMap_Community l @EdMap_Eth
👍7
#GymDiscount

💪🏾ጂም ለመጀመር ላሰባቹ ተማሪዎች ESIC Card በማሳየት 20% ቅናሽ ያግኙ

🪪ለ ESIC Card ባለቤቶች ብቻ የተዘጋጀ ቅናሽ

🗓ቅናሹ ቀድሞ ለሚመዘገቡ 10 ተማሪዎች ብቻ

📍ቦታ ገርጂ ሰንሻይን Daily Fitness

🪪ይህን ቅናሽ የምትፈልጉ ለ @contact_edmap "Gym " ብላቹ ቴክስት አድርጉ

ለተጨማሪ Deals እና Discount @EdMapDeals Join ያርጉ

#GymDiscount #EdDeal #EdMapDeals #EdMap
👍7
በቅርቡ የምትመረቁም ሆነ አዲስ ተማሪዎች ስለ ስራው አለማ ማወቅ የሚገቧችሁ ነጥቦች!

1. ተከታታይ ትምህርት ተምራችሁ ስለተመረቃችሁ ብቻ የመማር ሂደቱን ጨርሳችኋል ማለት አይደለም። እንደውም ገና ጅምር ነው። የስራው አለም በየጊዜው እያደገ የሚሄድና ቀጣይነት ያለው እንዲሁም የግል እድገት አስተሳሰብን የምናሻሽልበት ወቅት ነው።

2. ግኑኝነትን ማጠናከር ያስፈልጋል። ብዙ የስራ ችሎች የሚመጡት ከሰዎች ጋር በሚኖረን የግል ተግባቦት/ግኑኝነት ነው። በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ እየተገኛችሁ አዳዲስ ሰው ተዋወቁ። ኤድማፕ፣ ነፃ ዝግጅቶችን በየጊዜው በቴሌግራም ይፋዊ ገፁ እንደሚለጥፍ ይታወቃል።

3. ሙያዊ ችሎታ/ክህሎት አስፈላጊ ቢሆንም ቀጣሪዎች እንደ ተግባቦት፣ የቡድን ስራ፣ ችግር አፈታት ዘዴ፣ የአመራር ጥበብን የመሳሰሉ ክህሎቶችን እንድታዳብሩና እንዲኖራችሁ ይፈልጋሉ። እነዚህ ላይ ትኩረት ማድረግ ለወደፊታችሁ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
👍13
ላይተር የተፈጠረው ከክብሪት በፊት መሆኑ ታውቃላችሁ?

እ.ኤ.አ በ1823 "Döbereuner's lamp" የሚል ስያሜ የተሰጠው ላይተር ሲሰራ ከ3 አመታት በኋላ በ1826 ክብሪቶች መመረት ጀመሩ።

#EdMap #FunFact
👍9😁2
የኤድማፕ የስራ ጥቆማ

❗️እነዚህ ክፍት የስራ ቦታዎች የኤድማፕ አይደሉም፣ ለማመልከት ሊንኩን ይጫኑ!

1. Online Teacher

2. Motion Graphics Editor

3. Graphics Designer

4. Sales Woman Part-Time

5. Office Assistant

6.Software Engineer Internship Opportunity

#Job_Post #Career #EdMap_Eth
👍1
ለ7 ቀናት የሚቆይ መሰረታዊ የBackend Web Development (JavaScript , Node.js and Express) ስልጠና!

ለጀማሪዎችም የሚሆን!

1. Introduction to JavaScript

2. Node Js for backend

3. Learn expressjs

4. Create a project in back end web development

ሰርተፍኬት በDevTown, Google እና Microsoft አማካኝነት መጨረሻ ላይ ይሰጣል።

አሁኑኑ ይመዝገቡ : https://forms.gle/FAkxLqnpZqB4axY4A

@EdMap_Community
👍10
He spends all his time avoiding me, because he _______ me money.
Anonymous Quiz
30%
owned
19%
owe
48%
owes
3%
owing
👍6
እንግሊዝኛን በነፃ ኦንላይን እንማር!
1. Duolingo
ይህ ድህረገፅ ሰርተፍኬት ባይሰጥም ቀለል ባሉ ጥያቄዎችና ጨዋታዎች እንግሊዝኛን ያስተምራል።
ሊንክ : www.duolingo.com

2. British Council
ይህ የብሪቲሽ ካውንስል ድህረገፅ በድምፅ እና በቪዲዮ የታገዘ ሲሆን ቀለል ያሉ ጥያቄዎችንም አካቶ ይዟል። ከዛም በተጨማሪ ሰርተፍኬት ይሰጣል።
ሊንክ : learnenglish.britishcouncil.org

3. Memerise
አዳዲስ ቃላቶችን በማይረሱና አዝናኝ በሆኑ መንገዶች የሚያስተምር ድህረገፅ ነው። ሰርተፍኬት ባይሰጥም የVocabulary እውቃታችንን ለማስፋት አሪፍ መድረክ ነው።
ሊንክ : www.memrise.com

@EdMapCommunity l @EdMap_Eth
👍12
#እናስተዋውቆ

ገሊላ በቀለ፣ ኢትዮጵያዊት ሞዴል ስትሆን በግብረሰናይ ስራዎችና በምትሰራቸው ዘጋቢ ፊልሞች ተፅዕኖ መፍጠር የቻለች ሴት ነች።

ገሊላ በአብዛኛው ስራዎቿ የሚቀርቡት በአውሮፓና በዩናይትድ ስቴትስ ነው። እንደ Levi's, Diesel, Tory Burch, Anna Sui, Michael Kors, H&M, Pinko, Nespresson, Pantene and L'Oreal ለመሳሰሉ አለማቀፍ ብራንዶች ሞዴል በመሆን በብዙ መፅሄቶችና አለማቀፍ ታዋቂ ህትመቶች ላይ ለመታየትም ችላለች።

ከዚህ በተጨማሪ የዶክመንተሪ ፊልም የምትሰራ ሲሆን "Mai: Life is not Honey" በሚለው ስራ በመሳተፍ እንዲሁም በ2019 "Anbessa" በሚል ስያሜ ያዘጋጀችውና በበርሊን ዓለምአቀፍ ፊልም ፌስቲቫል ላይ የቀረበው ከስራዎቿ መካከል ይጠቀሳሉ።

ለንፁህ ውሃ ፕሮጀክቶች የሚሰራው Glimmer of Hope Foundation የተሰኘውን ተቋም የምትደግፈው ገሊላ በአለም ዙሪያ ላሉ ችግረኛ ማህበረሰቦች እርዳታ ከሚሰጡት ጋርም መሪ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች።

#EdMap #Meet #Gelila_Bekele
👍18