EdMap Community
3.29K subscribers
910 photos
8 videos
40 files
596 links
EdMap, Powered by PiSpace Inc.
A one-stop destination platform for Ethiopian students.

For further information @contact_edmap

Our website:
🌐 www.edmap.et
Download Telegram
የ2023 የEdinburgh Global Online Masters ስኮላርሺፕ

ይህ ስኮላርሺፕ በመላው አለም የሚገኙ ተማሪዎች የማስተርስ ዲግሪያቸው በEdinburgh University በኦንላይን መማር ለሚፈልጉ በመሉ የቀረበ እድል ነው።

ከአለም ዙሪያ የተወጣጡ ግለሰቦችን በማገናኘት መልካም የመማር ማስተማር ሂደት እንዲፈጠር የሚያደርገው ይህ እድል በርቀት ትምህርት የማስተርስ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት ያደርጋል።

ምን አይነት ጥቅሞች ያገኛሉ?

1. ለኦንላይን የማስተርስ ፕሮግራም ሙሉ የትምህርት ክፍያ ሽፋን
2. ምንም አይነት ቪዛ አለማስፈለጉ
3. ተማሪዎች ለመማር ወደ UK መሄድ አይጠበቅባቸውም
4. በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት የሚመጡ ተማሪዎች ከUK አሪፍ የትምህርት ተቋም በመልካም ሁኔታ መማራቸው

የማመልከቻ ማጠናቀቂያው ቀን : June 5, 2023

ዝርዝር መረጃዎችና የማመልከቻው አድራሻ በኤድማፕ ድህረገፅ ይገኛል።

በዚህ ያመልክቱ : https://www.edmap.et/edinburgh-global-online-learning-masters-scholarships-2023/

EdMap English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍6
📣ESIC Card ምንድን ነው?

ESIC Card (EdMap Student Identity Card) የኤድማፕ ቤተሰብ አባል መሆንዎን የሚያሳይ ይሄም በትምህርት ጉዞዎ ደጋፊ/አጋዥ በመሆን የሚያገለግልዎ የመታወቂያ ካርድ ነው።

በማንኛውም የትምህርት መንገድ ላይ ያሉ:
- የሀይስኩል
- የመሰናዶ
- የዩንቨርስቲ/ኮሌጅ
- የዲስታንስ/ኤክስቴንሽን ተማሪዎች በሙሉ መውሰድ ይችላሉ።

ESIC ካርድ ምን አይነት ጠቀሜታ ማግኘት ይችላሉ?

- የተለያዩ ዝግጅቶች፣ ስልጠናዎችንና መከታተል
- በተለያዩ ኮርሶች፣ መፅሀፍት እና የትምህርት መሳሪያ ቁሳቁሶች ላይ ልዩ ቅናሽ ማግኘት
- የትራንስፖርት፣ የምግብ፣ የመዋቢያና የመዝናኛ ዝግጅቶች ላይ የዋጋ ቅናሽ ማግኘት

ይሄን የESIC ካርድ ለማግኘት ምን ያስፈልግዎታል?

1. የትምህርት ቤት፣ የኮሌጅ ወይም የትምህርት ቤት መታወቂያዎ
2. በጥራት የተነሳ እርስዎን የሚገልፅ ፎቶግራፍ

በኤድማፕ ድህረገፅ በ https://www.edmap.et/ESIC ካርዱን ማግኘት ይችላሉ፣ አልያም ከላይ የተጠቀሱትን በሟሟላት ወደ @Contact_edmap ቢልኩልን እኛ እንመዘግብዎታለን።
👍231
ሜሰን ኩሌይ በስቴተን አይላንድ ኮሌጅ የፈረንሳይ ሥነ ጽሑፍ ፕሮፌሰር፣ ደራሲ እና አሜሪካዊ ነበር።

እንደ "The inner life of middle class" እና "The Columbia Dictionary of Quotations" የመሳሰሉ በርካታ መጽሃፎችን ጽፏል::

ሌላኛው የርሱ መጽሃፍ "Perspectives on Success and Failure" ስለ ስኬት እና ውድቀት ፅንሰ-ሀሳቦች አዲስ እይታን የሚሰጥ ሀሳብን ቀስቃሽ መጽሃፍ ነው።

ስለ ስኬት የራሳቸውን ልምድ እና አመለካከት በተሻለ ለመረዳት ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ጠቃሚ ግብአት ነው፣ እና አንባቢዎች የእራሳቸውን የስኬት እና የውድቀት ፍቺዎች እንደገና እንዲያስቡ ያነሳሳል።

#Mason_Cooley #Motivation #EdMap #ለተማሪዎች
👍4
ውሾች ልክ እንደ ሰው ልጆች ህልም እንደሚያዩ ታውቃላችሁ?

ተመሳሳይ የእንቅልፍ ሁኔታ ከሰዎች ጋር እንደሚጋሩ የሚነገርላቸው ውሾች፣ በእንቅልፍ ወቅት ሊንቀጠቀጡ፣ መዳፋቸውን ሊያንቀሳቅሱ እና ድምፅ ሊያሰሙ ይችላሉ። ይህም ህልም እያዩ መሆናቸውን ያሳያል።

#Funfact #EdMap #Dogs
😁8👍2
ኪሩቤል አቡዬ የ19 አመት ታዳጊ ሲሆን በUniversity of Canada የስኮላርሺፕ እድል አግኝቷል።

እንዴት?

የሶሻል ሚዲያን ጥቅም የተረዳው ኪሩቤል ያለመሰልቸት ለ161 ቀናት ያክል ቲዊተር በተሰኘው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ "የስኮላርሺፕ ድጋፍ" እንደሚያስፈልገው በተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረብ ጀመረ።

ጥያቄው ወደ ካናዳዊው ባለሀብትና ኢንቨስተር Chamath Palihapitiy ይደረሳል ብሎ ግን ማንም አልጠበቀም ነበር። የኪሩቤልን ብርታትና ትዕግስት ያደነቁት ባለሀብቱ ስኮላርሺፕ ከደረሰው በራሳቸው ወጪ ሸፍነው እንደሚያስተምሩት ቃል ይገቡለታል።

ከብዙ ጊዜያት በኋላ ስኮላርሺፑ ሲሳካለት ካናዳዊው ባለሀብትም ለኪሩቤል ቃል የገቡለትን ነገር በApril 2023 አድርገውለታል።

ሙሉውን ታሪክ በዚህ ያግኙት : https://www.edmap.et/from-tweets-to-university-ethiopian-high-schoolers-journey-to-a-canadian-scholarship/

EdMap English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍23
💡በedX የሚሰጡትን ነፃ የኦንላይን ኮርሶችን ይውሰዱ!

ምን አይነት ኮርሶች ይሰጣሉ?
- Spanish
- Python
- Software Engineering
- Computer Programming
- Project Management
- Business Admin እንዲሁም ሌሎች

በብቁ ባለሙያ የተዘጋጁት እነዚህ ኮርሶች ሙሉ በሙሉ ነፃ ሲሆኑ ኮርሱን ሲያጠናቅቁም ሰርተፍኬት ይሰጥዎታል።

ኮርሶቹን በዚህ ማግኘት ይችላሉ : https://www.edx.org/school/stanfordonline


EdMap English :
@EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍9
📚ለመፅሀፍት ወዳጆች በሙሉ!

EdMap ከMexico Book Corner ጋር በመሆን ESIC ካርድ ላላቸው ለኤድማፕ ቤተሰቦች 50% ቅናሽ አድርገናል።

የጥንት እና ዘመኑን የዋጁ መፅሀፍትን ያንብቡ!

ይሄንን ልዩ እድል ለመጠቀም @Contact_EdMap በመግባት ብቻ "የመፅሀፍ ቅናሽ ማግኘት እፈልጋለሁ" ብለው ይፃፉልን! የ50% ቅናሽም ያግኙ።

📍ሜክሲኮ አምደ መፅሀፍት ዋቢሸበሌ ጎን ይገኛል።

በመፅሀፍት መደበሩ የድሮ መፅሀፍት ይገኛሉ።

ESIC ካርድ ያውጡ ፣ 50% ቅናሽ ያግኙ።

🌟መሰል ኤድማፕ ESIC ካርድ ላወጡ ቤተሰቡ የሚያዘጋጃቸውን ታላላቅ ቅናሾችን የምታገኙበት የቴሌግራም ገፅ አዘጋጅተናል።

በዚህ በመግባት ያግኙት : @EdMapDeals
👍10
የሰውን አካል በአኒሜሽን እና በ3D ሞዴሎች በመቅረፅ በተሻለ መልኩ ሊያስረዳን የሚችል website እንዳለ ያውቃሉ?

ይህ website Visible body ሲባል የሰው ልጅን አናቶሚ እና ፊዚዮሎጂ ከዝርዝር ማብራሪያዎች ጋር አጠቃላይ ግንዛቤን ይሰጣል።

በዚህ ሊንክ ማግኘት ይችላሉ: www.visiblebody.com

EdMap English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍7
በዚህ ሳምንት በአዲስ አበባ የሚሄዱ ነጻ ዝግጅቶች እና ኤግዚቢሽንኖች

1. የስነ-ህንፃ ንድፍ ኤግዚቢሽን
ቦታ፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ - EiABC ካምፓስ
ቀን፡ እስከ ግንቦት 19, 2015

2. የአ.አ.ዩ ፕሬስ የመጽሐፍት ዓውደ ርዕይ እና ሽያጭ
ቦታ፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ቀን፡ እስከ ግንቦት 13፣ 2015

3. የትምህርት እና የቴክኖሎጂ ፌስቲቫል
ቦታ፡ መስቀል አደባባይ
ቀን፡ ከግንቦት 11 - 13/2015

EdMap English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍9
የጋዜጠኝነት እና የሚዲያ ክህሎትን ከፍ ለማድረግ የሚረዱ የ YouTube ቻናሎች እነሆ

1. TEDx Talks - አነቃቂ ንግግሮችን እና ግንዛቤዎችን ከጋዜጠኛ እና ሚዲያ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ያቀርባል።
ሊንክ: TEDx Talks

2. Columbia Journalism School -2. የጥናታዊ ዘገባዎችን፣ የመልቲሚዲያ ታሪኮችን ከሚዝግቡ ታዋቂ ጋዜጠኞች ጋር የተደረጉ ቃለመጠይቆች እንዲሁም የፓናል ውይይች ይቀርቡበታል።
ሊንክ: Columbia Journalism School

3. Mediabistro - ለጋዜጠኝነት፣ ለብሮድካስቲንግ፣ ለዲጂታል ሚዲያ እና ለContent Creation አጋዥ ሊሆኑ የሚችሉ ስልጠናዎች እና ቃለመጠይቆች ይቀርቡበታል።
ሊንክ: Mediabistro

EdMap English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍9
ተመራቂዎች የመመረቂያ ወረቀት ሲያዘጋጁ በብዛት ሲሰሯቸው የሚስተዋሉ ስህተቶች:

1. በቂ ያልሆነ ጥናት/ምርምር
2. ደካማ የቴሲስ መግለጫ መጠቀም
3. እርማት የመስጠት እጥረት
4. ማጭበርበር / የሌላ ሰው የምርምር ውጤት የራስ አድርጎ ማቅረብ
5. ወጥነት የሌለው ማጣቀሻ/Reference/ ማስገባት

ከላይ የተዘረዘሩትን ስህተቶች ሊያስወግድባቸው የሚችሏቸውን ድህረገፆች እንጠቁምዎ!

1. EasyBib : ለመመረቂያ ወረቀትዎ ትክክለኛ ጥቅሶችን በቀላሉ እንድታዘጋጁ ይረዳል።
አድራሻ : www.easybib.com

2. Researchgate : እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ መጣጥፎችና የጥናት ወረቀቶችን የምታገኙበት ድህረገፅ ነው።
አድራሻ : www.researchgate.net

3. Plagiarism detector. net : የሰራችሁት ሪሰርች ኦርጂናልነቱን ለማረጋገጥ የምትጠቀሙበት ድህረገፅ ነው።
አድራሻ: plagiarismdetector.net


EdMap English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍9
ዶ/ር ቃልኪዳን ላቀው በገጠር ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል የህክምና ዶክተር ነች። በህክምና ጣቢያው ስር የሚካሄዱትን በበላይነት በመቆጣጠር ረገድም ልዩ እገዛ ታደርጋለች።

በኢትዮጵያ የህክምና ተማሪዎች ማህበር ውስጥ የህብረተሰብ ጤና ዳይሬክተር የሆነቺው ዶ/ር ቃልኪዳን በሌሎች ድርጅቶች ዘንዳ ንቁ የበሆ ፈቃድ አገልግሎት ልምድም አካብታለች።

ዶ/ር ቃልኪዳን በመላ ሀገሪቷ ሴቶችን በማብቃት ብሎም በፆታዊ ስነተዋልዶ ጤናና መብቶች ዙሪያ አስተዋጽኦ እያደረገች ትገኛለች።

#Meet #DrKalkidan_Lakew #EdMap
👍20
ይሄንን ያውቃሉ?

የኤድማፕ ድህረገፅ ላይ በሀገራችን ዩንቨርስቲዎች የሚሰጡ የትምህርት ፕሮግራሞችን እንዲሁም በነዚህም የትምህርት መስኮች የተማረ ግለሰብ የት ተቋማት ላይ መቀጠር እንደሚችል ይገልፃል።

በዚህ ያግኙት ፡ www.edmap.et/programs/


EdMap English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍7
ማስታወሻ በክፍል ውስጥ መውሰድ ትምህርቱ ላይ ያላችሁን ግንዛቤ የሚያሻሽል እንዲሁም ሃሳባችሁን ለማደራጀት የሚጠቅም መንገድ ነው።

ማስታወሻዎችን እንዴት ነው የምትወስዱት?

እነዚህን 2 ዘዴዎች ግምት ውስጥ በማስገባት የተሻለ ስራ መስራት ይቻላል።

Cornell Method : ይህ የማስታወሻ አወሳሰድ ዘዴ ገፅዎን በሶስት ክፍሎች እንድትከፍሉ እድል ይሰጣል። በቀኝ በኩል ለዋና ማስታወሻዎች፣ በግራ ረድፍ ለቁልፍ ቃላትና ጥያቄዎች፣ ከታች ደግሞ የማጠቃለያ ቃላትን እንድትጠቀሙ ያስችላል።

Outline Method:ይህ ዘዴ ዋና ርዕሶችን እና ንዑስ ርዕሶችን በተዋረድ በመከፋፈል ቁልፍ ነጥቦችን ለመለየት የሚያስችል የማስታወሻ መንገድ ነው።

ለተሻለ ግንዛቤ የተያያዙትን ምስሎች ይመልከቱ።

EdMap English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍81
ኤድማፕ፣ ለሚከተሉት ስራዎች ብቁ ከሆኑ እንዲያመለክቱ ይጋብዛል።

1. Social media host - unpaid internship
2. Online sales - Remote
3. Digital Marketing and Graphic Design
4. Female Video Host/Model for Brand Advertising
5. Virtual Assistant

❗️እነዚህ ክፍት የስራ ቦታዎች የኤድማፕ አይደሉም፣ ለማመልከት ሊንኩን ይጫኑ!
👍7
Atomic Habits ራስን ለመገንባት የሚረዳ በደራሲ James Clear የተፃፈ መፅሀፍ ነው። መልካም ልምድን ለማስቀጠል፣ እኩዮችን ደግሞ ለማስወገድ የሚረዱ ምክረሀሳቦችን የሚያሳየው መፅሀፉ በአፃፃፍ ዘይቤው ማራኪነትም ደራሲው ሙገሳ እንዲያገኝ አስችሎታል።

በፅሁፉም ጥቃቅን ነገሮች እንዴት ትልቅ ምስሎችን እንደሚገነቡም ያሳያል። ሀሳቡን ለመደገፍም ዕለት ተዕለት ከሚያጋጥሙን የህይወትና ሳይንሳዊ መንገዶች ጋር በማስተሳሰር ያሳያል።

ራስን ለማነፅ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው Atomic Habits ማንበብ አለበት። አንባቢዎች ትንሽ ጅማሮዎች ትልቅ መድረሻዎችን እንዴት እንደሚፈጥሩ እንዲረዱ ያድርጋል።

በህይወታቸው ትልቅ ተስፋንና መልካም ተሞክሮ ያለው እይታ ለሚፈልጉ በሙሉ ይሄን መፅሀፍ ጋበዝን!

EdMap English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍14
እናስታውስዎ!

1. UNESCO World Heritage Young Professionals Forum 2023 in Saudi Arabia


የማመልከቻ የመጨረሻ ቀን:June 04
እዚህ ያመልክቱ

2.Google Analytics Course
የመማሪያ አድራሻ

3.Hubspot's marketing and sales Course
የመማሪያ አድራሻ


EdMap English l @EdMap_Eth
www.edmap.et l @EdMap_Community
👍5
👍7
የሳተርን ቀለበቶች ስንት አመታትን አስቆጥረዋል?

የሳተርን ቀለበቶች ለ100,100,000 ዓመታት ፕላኔቷን በማስዋብ እና ጊዜ የማይሽረው ውበት በማጎናትፀፍ ኖረዋል።

#SaturnsTimelessRings
#100MillionYearsofElegance
#EdMap
👍8👎4