EdMap Community
3.3K subscribers
910 photos
8 videos
40 files
596 links
EdMap, Powered by PiSpace Inc.
A one-stop destination platform for Ethiopian students.

For further information @contact_edmap

Our website:
🌐 www.edmap.et
Download Telegram
ራስዎን ለማስተማር ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸው 5 ምርጥ የ"ፓይተን/Python" ትምህርት የዩቲዩብ ቻናሎች እነሆ:

1) Corey Schafer
በዚህ ቻናል ውስጥ እንደ Django, Flask ሌሎች የWeb development ትምህርቶች ያገኛሉ።

2) Tech With Tim
ቴክ ዊዝ ቲም የዩቲዩብ ቻናል Data Science, Machine Learning, Game Development እና ሌሎችንም ጨምሮ በተለያዩ የፓይተን ዘርፎች ላይ ትምህቶችን ይሰጣል።

3) Sentdex
ይህ ቻናል ስለ Python, Data Science, Machine Learning እና Artificial Intelligence ዙሪያ ትምህርቶችን ይሰጣል።

4) CS Dojo
ስለ Python, Data Structures, Algorithms እና ሌሎችንም ጨምሮ በተለያዩ የኮምፒውተር ሳይንስ ዘርፎች ላይ አጋዥ ስልጠናዎችን የሚሰጥ የዩቲዩብ ቻናል ነው።

5) FreeCodeCamp.org
በአጠቃላይ ፕሮግራሚንግ ስልጠናዎች ማለትም በPython, Web Development እና Data Science ዙሪያ በሚሰጣቸው ሰፊ እውቀቶች የሚታወቅ የዩቲዩብ ቻናል ነው።


EdMap English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍6
በHubSpot አካዳሚ የሚሰጠውን ስልጠና በመውሰድ ራስዎን በማርኬቲንግ እና ሽያጭ ( Sales)  ብቁ ያድርጉ።

አዳዲስ ክህሎቶችና ዕውቀቶችን በራስ ላይ ለማዳበር እና ብቁ ለመሆን መሰል ስልጠናዎች እጅግ ጠቀሜታ አላቸው። በተጨማሪም፣ ኮርሶቹን አጠናቅቆ መጨረስ ሰርተፍኬት እንድታገኙ ይሄም ለተሻለ ስራ ዕድል ራሳችሁን እንድታወዳድሩ ይረዳል።

- Inbound Marketing
- Email Marketing
- Social Media Marketing
- Sales Enablement
- Content Marketing

ከላይ ከተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች አንዱን በመምረጥ እና በመማር ብሎም ሰርተፍኬት በማግኘት ራስዎን ተወዳዳሪና ብቁ ያድርጉ።

የመማሪያ አድራሻ ፡ https://academy.hubspot.com/


EdMap English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍9
የ"ሳይካትሪስት(የስነ-አዕምሮ ሀኪሞች)" እና "ሳይኮሎጂስት (የስነልቦና ባለሙያዎች)" ልዩነታቸው ምንድን ነው?

- ሳይካትሪስት ለታካሚዎቻቸው መድሀኒት የሚያዙ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ ሳይኮሎጂስቶች መድሃኒት ለታካሚዎቻቸው አያዙም።

- የስነ ልቦና ባለሙያዎች ሳይኮቴራፒን በመጠቀም ለታካሚዎች መድሃኒቶችን ማዘዝ ሳያስፈልጋቸው የህክምና አገልግሎት ይሰጣሉ።

በይበልጥ በኤድማፕ ድህረገፅ ላይ የሰፈረውን ፅሁፍ ማግኘት ይችላሉ።
በዚህ ያግኙት : http://www.edmap.et/programs
👍10
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የብርሃን ፍጥንት ምን ያክል ፈጣን ነው?

የብርሃን ጨረር ምድርን 7.5 Revolution Per Minute ያክል ይዞራል። ፈጣን ይመስላል አይደል!?
ነገር ግን በዚህ ፍጥነት በመሄዱ 1.255 Seconds ያክል ወደ ጨረቃ ለመጓዝ ይወስድበታል። ከመሬት ወደ ማርስ ደግሞ የብርሃን ጨረር 3 ደቂቃዎችን ያክል ይቆጥርበታል።

በአጠቃላይ የብርሃን ፍጥነት ከዩኒቨርስ ልኬት አንፃር ያን ያህል ፈጣን አይደለም።
👍11
የአዕምሮ ጤና ለተማሪዎች እጅግ አስፈላጊ እንደመሆኑ ለአካላዊ ጤንነትና ለአካዳሚክ ውጤቶች ትኩረት እንደምትሰጡት ሁሉ፣ የአዕምሮ ጤንነታችሁንም መከታተል አለባችሁ።

እንደ ድብርት፣ ጭንቀት እና የመሳሰሉት ከፍተኛ ጫና በተማሪዎች አዕምሮ ዘንድ ያሳድራሉ።

የትምህርት ተቋማትም እንደ የምክር፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና መሰል ዝግጅቶሽን በማዘጋጀት ለተማሪዎች አዕምሮ ጤና ዘብ መቆም አለባቸው።

አስታውሱ፤ ድብርት፣ ጭንቀትና ሌሎችም ባህሪያት ደጋግሞ ከጎበኛችሁ ብቻችሁን አይደላችሁም። ስለናንተ የሚጨነቁ፣ የሚያስቡ እና ሊረዳችሁ የሚፈልጉ ሰዎች አሉ። ለማማከር እና ለመወያየት አይፍሩ ፣ አይስጉ።

እኛ ከጎንዎ አለን!

EdMap English :
@EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍13
ከሰውነት ክፍላችን የህመም ስሜት የሚቀበሉ ህዋሶች ( Pain Receptors ) የሌለው ብቸኛ አካል አንጎላችን ነው። በዚህም ምክንያት የአንጎል ቀዶ ጥገና ህመምተኛው ማደንዘዣ ሳይሰጠው ሊደረግለት ይችላል።
👍3
እናስተዋውቅዎ!

ሊያ ከበደ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊት አለማቀፍ ሞዴል፣ ተዋናይትና ግብረሰናይ ሴት ነች።

በአዲስ አበባ መካከለኛ ገቢ ባለው ቤተሰብ የተወለደቺው ሊያ ከበደ የሞዴሊንግ ስራዋን በ1990ዎቹ መገባደጃ ላይ ጀመረች።

ከ Estée Lauder ጋር የተፈራረመች የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ሞዴል ስትሆን በኢንዱስትሪው ውስጥ በጣም ከሚፈለጉ ሞዴሎች መካከልም ትጠቀሳለች።

ከሞዴልነት ስራዋ ጎን ለጎን በአፍሪካ የእናቶችና ህፃናት ጤና ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ እያስጨበጠች የምትገኘው ሞዴልና ተዋናይት ሊያ ከበደ የአለም ጤና ድርጅት የበጎ ፍቃድ አምባሳደር ነች።

ይህ የሰበዓዊነት ስራዋም የአለም ኢኮኖሚክ ፎረም Crystal Award ሽልማትን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ስራዎችን እንድትጎናፀፍ አስችሏታል።

EdMap English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍19
"Becoming" በ 2018 በሚሼል ኦባማ የታተመ መፅሃፍ ነው። መፅሃፉ የሚሼልን ህይወት ከልጅነታቸው ጀምሮ በቺካጎ፣ በጠበቃነት እስከ ህይወታቸው ድረስ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳማዊት እመቤት እስከነበሩበት ጊዜ ድረስ ይተርካል።

በመጽሐፉ ውስጥ ሚሼል ስለ አስተዳደጓ፣ ከባራክ ኦባማ ጋር ስላላት ጋብቻ፣ እና እንደ እናት እና ቀዳማዊት እመቤት ያጋጠሟቸውን ግላዊ ታሪኮች እና ግንዛቤዎችን አካፍለዋል። በግል እና በሙያዊ ህይወቷ ውስጥም ዘረኝነትን እና ጾታዊነትን በመምራት ያጋጠሟትን ፈተናዎች ትናገራለች።

በመጽሐፉ ውስጥ ሚሼል የትምህርትን፣ ጠንክሮ መሥራት እና ጽናትን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰታለች፣ እና በሕይወቷ ሁሉ የተማረቻቸውን ትምህርቶች አካፍላለች። የልጅነት ውፍረትን ለመዋጋት ዓላማ ያላቸውን እንደ እንንቀሳቀስ! የመሳሰሉ ውጥኖችን በማስተዋወቅ ስራዋን እና የሴቶች ትምህርትን ‹Let Girls Learn› በመሳሰሉ መርሃ ግብሮች ላይ ያቀረበችውን ድጋፍ ተወያይታለች።

"Becoming" በዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ታዋቂ ከሆኑ ሴቶች መካከል የአንዷን ህይወት ፍንጭ የሚሰጥ ቅን እና አነቃቂ ማስታወሻ ነው።
👍8
የቤት ስራም ሆነ አሳይመንቶች ሲሰጥዎ ሊያግዝዎት የሚችሉ 4 ድህረገፆች:

1) BioInteractive : "ባዮሎጂ" እና በባይሎጂ ዙሪያ የሚያብራሩ ነፃ መረጃዎችና ቪዲዮዎች ያገኙበታል።

የድህረገፁ አድራሻ : www.biointeractive.org/

2) ChemCollective : "ኬሚስትሪ" እና በኬሚስትሪ ዙሪያ የሚያብራሩ ነፃ መረጃዎች፣ ጥያቄዎችና ቪዲዮዎች ያገኙበታል።

የድህረገፁ አድራሻ : https://chemcollective.org/

3) Physics Classroom : "ፊዚክስ" እና በፊዚክስ ትምህርት ዙሪያ የሚያብራሩ ነፃ መረጃዎች፣ ጥያቄና መልሶች ያገኙበታል።

የድህረገፁ አድራሻ : https://www.physicsclassroom.com/

4) Brilliant : በሂሳብ ፣ ፊዚክስ እና ኮምፒውተር ሳይንስ ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄና መልመጃዎች ያሳያል።

የድህረገፁ አድራሻ : https://brilliant.org/

EdMap English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍6
ተማሪ ስለሆኑ ብቻ በEdMap Marketplace ይከበራሉ።

እጅግ ታላቅ ቅናሽ:
- እጅ በሚያስቆረጥሙ ምግቦች ላይ
- በሴት/ወንድ የውበት ሳሎኖች ላይ
- ደስታን በሚሰጡ የመዝናኛ ስፍራዎች
- በትምህርት ቁሳቁሶች : እንደ ደብተሮች ፣ ስቴሽነሪ ምርቶች
- ላፕቶፖች ፣ ዘመናዊ ስልኮችና ሌሎችም ላይ ያገኛሉ።

የተማሪነት መንገድዎ የተስተካከለ እንዲሆን እንፈልጋለን።

እነዚህን ሁሉ ጥቅሞች ለማግኘት የኤድማፕ ESIC CARD መውሰድ አለብዎ።

በዚህ አድራሻ ተጠቅመው ESIC CARD ያውጡ : https://www.edmap.et/ESIC



@edmap_community
👍7
እናስታውስዎ!

The Fully Funded Shanghai Government Scholarship 2023-2024
የማመልከቻ የመጨረሻ ቀን: May15
እዚህ ያመልክቱ


UNESCO World Heritage Young Professionals Forum 2023 in Saudi Arabia
የማመልከቻ የመጨረሻ ቀን:June 04
እዚህ ያመልክቱ


EdMap English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍7
ፎቶ ኤዲቲንግ መማር እንዲሁም ችሎታችሁን ማዳበር ለምትፈልጉ በሙሉ ኤድማፕ እነዚህን የዩቲዩብ ገፆች እንድትጎበኙ ይጋብዛል።

1. Piximake
የዩቲዩብ አድራሻ: https://www.youtube.com/c/Piximake

2. PHLEARN
የዩቲዩብ አድራሻ: https://www.youtube.com/c/PhlearnLLC

3. Tutvid
የዩቲዩብ አድራሻ: https://www.youtube.com/c/tutvid

4. PiXimperfect
የዩቲዩብ አድራሻ: https://www.youtube.com/c/PiXimperfect

5. Spoon Graphics
የዩቲዩብ አድራሻ: https://www.youtube.com/c/SpoonGraphicsBlog

EdMap English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍9
ኤድማፕ፣ ለሚከተሉት ስራዎች ብቁ ከሆኑ እንዲያመለክቱ ይጋብዛል።

1. Advertising photo models

2. Graphics designer

3. Male Tutors

4. Social media host

5. Intern - Office Assistant
👍7
የኤድማፕ መተግበሪያ/አፕሊኬሽን በውስጡ ምን ይዟል?

ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች አመቺ ሆኖ የተፈበረከው የኤድማፕ መተግበሪያ እጅግ ልዩ ቅናሽ፣ የትርፍ ጊዜ የስራ እድሎች፣ እንዲሁም ለትምህርት የሚጠቅሙ መሳሪያዎችን የሚሸጡበትና የሚገዙበትን በሙሉ ይዟል።

🛒EdMap Marketplace : እጅግ ልዩ ቅናሽ ለተማሪዎች በሚያስፈልጉ የትምህርት ቁሳቁሶችን እንዲሁም እንደ ሲኒማ፣ ምግብ፣ መዝናኛ ስፍራዎች፣ የመዋቢያ ቦታዎችና ወዘተ ላይ እንድታገኙ ይረዳል።

🧑🏽‍💻EdMap TemariWork : ከቤትዎ ወይም ከዶርምዎ በመሆን የትርፍ ጊዜ ስራ በመስራት ገንዘብ እንድታገኙ ያግዛል።

📚EdShare : ተማሪዎች Worksheet እና መሰል ለትምህርት የሚጠቅሙ ነገሮችን የሚሸጡበትና የሚገዙበት የሚያስችል መድረክ ነው።

የኤድማፕ ድህረገፅ ላይ የESIC ካርድ በማውጣት እነዚህን አስገራሚ ግልጋሎቶች ማግኘት ይችላሉ።

በዚህ ይመዝገቡ : https://www.edmap.et/ESIC
👍6
አዲስ ቀን አዲስ ጅማሬ!
👍8
ሳይኮሎጂ የስነ-አዕምሮ እና ስነ-ባህሪን መሰረት አድርጎ የሚያጠና የትምህርት አይነት ነው። በዚህ ሙያ የሚሰሩ (ሳይኮሎጂስቶች) ሰዎች እንዴት እንደሚያስቡ፣ ምን እንደሚሰማቸውና እንዴት ስሜታቸውን እንደሚገልፁ ይሄም እንዴት ራሳቸው ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድሩ ይገመግማሉ።

በሳይኮሎጂ ስራ ውስጥ ለመሰማራት ጥሩ አድማጭ፣ የሰውን ችግር እንደራስ የማያት ልምድ፣ የንግግር ችሎታ፣ አስተዋይ እይታ፣ የመመርመር ብቃት፣ መልካም ስነምግባር ሊኖር ያስፈልጋል።

ሳይኮሎጂስቶች በሚከተሉት ተቋማት የመስራት አቅሙ አላቸው።

- ተማሪዎችን የሚደግፉ ትምህርት ቤቶች
- እውቀትን የሚያሰፉ የምርምር ተቋማት
- ማገገሚያ ማዕከላት

እና ሌሎችም የስራ መስኮች ላይ መሳተፍ ይችላሉ።

ይህ ትምህርትም የሰዎችን ባህርያት በመረዳት ችሎታን ለማጎልበት የተለያዩ እድሎችን ይከፍታል።

EdMap English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍5
የወደፊት የስራ እጣፈንታ በAI ዘመን

እንዲህ የAI ቴክኖሎጂ እየጎለበተና መሪነቱን እየተቆናጠጠ በመጣበት በዚህ ዘመን፣ የተለያዩ ሙያዎች እየተፈለጉ መምጣታቸው እሙን ነው። የሚከተሉት ስራዎች በሚቀጥሉት አስርት አመታት ተፈላጊ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

- AI and Machine Learning Specialists
  - Data Scientists
  - AI Ethics and Governance Experts
  - Robotics Engineers
  - Cybersecurity Specialists
  - AI Consultants and Strategists
  - Human-Machine Interaction Specialists
  - AI Trainers and Explainers

ታዲያ በነዚህ የስራ ዘርፎች ለመስራትና ተወዳዳሪ ለመሆን ሊረዷችሁ የሚችሉና ነፃ ትምህርት ከሰርተፍኬት ጋር የሚስውጡ ድህረገፆችን ኤድማፕ ሊያስተዋውቃችሁ ይወዳል።

1. Udacity
2. Kaggle
3. Google AI Education
4. IBM Developer Skills Network
5. DataCamp
6. MIT OpenCourseWare

ከዘመኑ ጋር እኩል መጓዝ!
👍18
ሴት ተማሪዎች ልዩ ቅናሽ ማግኘት አለባቸው!

🎁 ኤድማፕ ለሴት ተማሪዎች ቤተሰቦቹ ልዩ ቅናሽ አምጥቷል። ለሁሉም የኤድማፕ ቤተሰቦች በቅርቡ በምንለቀው አፕሊኬሽንም እጅግ ልዩ ቅናሾች እናመቻቻለን።

🎁 ኤድማፕ ከዳጊ Nail Studio 20% ልዩ የጥፍር ስራ ቅናሽ እንድታገኙ ይሄን እድል ይዞ መጥቷል። ስጦታውን የሚያገኙት ቀድመው የተመዘገቡ 10 ሴት የኤድማፕ ቤተሰቦች ሲሆኑ እድሉን ለማግኘትም ESIC ካርድ ከኤድማፕ ድህረገፅ ማውጣት አለባቸው።

በዚህ ይመዝገቡ: https://www.edmap.et/ESIC

መልካም እድል
👍14