EdMap Community
3.3K subscribers
910 photos
8 videos
40 files
596 links
EdMap, Powered by PiSpace Inc.
A one-stop destination platform for Ethiopian students.

For further information @contact_edmap

Our website:
🌐 www.edmap.et
Download Telegram
"...ፋሽን ዲዛይነር ለመሆን የፈለገች ሴት አሁን ላይ ማሽኑ አያስፈልጋትም። በቀላሉ እንዲህ ማድረግ ትችላለች..."

"...የፋሽን ዲዛይን በደንብ አዋጭ ነው። እኔ ብዙ ደንበኞቼ የሚመጡት በኦንላይን ነው። ትርፋማ የሆንኩት ደግሞ..."


ኤድማፕ ፣ በፋሽን ዲዛይን ስመጥር ከሆነቺው ዲዛይነር ሃፍሳ ሰለሞን /ሀፊ ትንሿ ዲዛይነር/ ጋር ያደረገው አጭርና ግልፅ ቃለምልልስ ፋሽን ዲዛይን ሙያ ውስጥ አሁን መጀመር ላሰቡ እና ትርፋማ ለመሆን ለሚፈልጉ በሙሉ ይጋብዛል።

ቃለምልልሱን በዚህ ያግኙት : https://www.edmap.et/how-to-be-a-fashion-designer/


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍9
በኢትዮጵያዊው ዲዛይነር እና አርክቴክት ናሆም ተክሉ የተዘጋጀ ኤግዚብሽን
Building Africa Exhibition, Addis Ababa

- መግቢያ: በነፃ
- ቀን : ሚያዚያ 21 - 22
- ቦታ ፡ አዲስ አበባ ሙዚዬም ፣ መስቀል አደባባይ


ለበለጠ መረጃ ይሄን ይጠቀሙ ፡ www.africanstatearchitecture.co.uk/post/building-africa-exhibition


@edmap_community | www.edmap.et
👍5
የጥፍር ስራ ሙያ መማር የምትፈልጉ በሙሉ ፤ ኤድማፕ እነዚህን የዩቲዩብ ገፆች እንድትጎበኙ ይጋብዛል።

1) Simply Nailogical
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/@simplynailogical

2) Cute Polish
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/@cutepolish

3) Nail Career Education
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/@NailCareerEducation

4) Nailbees
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/@Nailbees


እነዚህን በመመልከት በጥፍር ስራ ሙያ ዘርፍ ያላችሁን እውቀት አንድ እርምጃ ከፍ ማድረግ ትችላላችሁ።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍9
የስኮላርሺፕ መረጃዎች ላይ SAT የሚል ቃል አስተውላችሁ ይሆናል። ለመሆኑ ትርጉሙ ምንድን ነው?

SAT ሲተነተን Scholastic Assessment Test የሚል ትርጓሜ ሲኖረው በዩናይትድ ስቴትስ ለኮሌጆች መግቢያ የሚሰጥ የፈተና ስርዓት ነው። ይህ የፈተና ስርዓት በዋነኝነት ትኩረቱን በሂሳብ ክህሎት እና በእንግሊዝኛ ቁንቋ የሚያደርግም ነው።

ታዲያ SAT ፈተና ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት መውሰድ ይቻላል? ምን አይነት ጥያቄዎች ፈተናው ላይ ይኖራሉ እንዲሁም ሌሎች ጠቃሚ ሀሳቦች አርብ/ነገ ማታ 2 ሰዓት ላይ በዚሁ የቴሌግራም ገፃችን የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ይኖረናል።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍9
እናስተዋውቅዎ!

ሄኖክ አሰፋ፣ በአዲስአበባ መቀመጫውን ያደረገው "Precise Consult" የተሰኘ የማኔጅመንት አማካሪ ድርጅት መስራችና ኢትዮጵያዊ ስራ ፈጣሪ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ቢዝነሶች ተወዳዳሪነታቸውን እንዲያሻሽሉና ቀጣይነት ያለው እድገት እንዲያስመዘግቡ በማሰብ Precise Consult የተሰኘውን ድርጅት እ.ኤ.አ በ2007 ለመመስረት ችሏል።

Precise Consult በኢትዮጵያ ብሎም በምስራቅ አፍሪካ ላሉ ንግዶችና ድርጅቶች "የስትራቴጂ ዲቨሎፕመንት"፣ የ"ፋይናንስ" ፣ የግብይትና የሰው ሀይል አስተዳደርን ጨምሮ የተለያዩ የቢዝነስ አማካሪ አገልግሎቶችን ይሰጣል።

ድርጅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የአስተዳደር አማካሪ ድርጅቶች ግንባር ቀደሙ ከመሆኑ ባሻገር ከደንበኞች ጋር በቅርበት በመስራትና ዕድሎችን ለይቶ ተግዳሮቶችን የሚያሸንፍ የአማካሪ ድርጅት ለመሆን በቅቷል።


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍8
Steamunlocked በተሰኘው ድህረገፅ ለመዝናኛነት ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸውን የተለያዩ የኮምፒውተር ጨዋታዎች (ጌሞች) በስፋት ማግኘት ትችላላችሁ።

የድህረገፁ አድራሻ : Streamunlocked.net


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍4
ኤድማፕ፣ ለሚከተሉት ስራዎች ብቁ ከሆኑ እንዲያመለክቱ ይጋብዛል።

1. Advertising photo models

2. Graphics designer

3. Male Tutors

4. Social media host

5. Intern - Office Assistant
👍5
Live stream scheduled for
Live stream started
🔴 LIVE

ስለ SAT ፣ የ SAT ፈተና መውሰድ ለስኮላርሺፕ የሚያስገኘው ጥቅም ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ የፈተና ስርዓት እንዴት እንደሚወሰድ እና ሌሎች ጥያቄዎችን በተመለከተ ኤድማፕ ከቤተሰቦቹ ጋር በቀጥታ ውይይት እያደረገ ነው።

ውይይቱን Join በማድረግ ይከታተሉ።

@edmap_community
👍11
Live stream finished (35 minutes)
ነፃ የትምህርት እድል ከጎግል

የሚከተሉትን የትምህርት አይነቶች በነፃ በፈለጋችሁት ጊዜ እየተማራችሁ ከዛም ሰርተፍኬት በማግኘት ከነበርዎ ደረጃ አንድ ከፍ እንዲሉ ኤድማፕ ይጋብዛል።

-Digital Marketing
-Building AI
-Entrepreneurship
-Programming with JavaScript
-Python basics for Data Analysis and many more.

ከላይ የተገለፁትና ጎግል ያቀረባቸውን ትምህርቶች የምታገኙበትን አድራሻ የኤድማፕ ድህረገፅ ላይ ተለጥፏል።

በዚህ ያግኙት ፡ https://www.edmap.et/googles-free-online-courses/


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍8
SAT
EdMap Community
ስኮላርሺፕ ላይ ብዙ ጊዜ የሚታየው SAT ምንድን ነው? SAT ፈተና መውሰድ ለስኮላርሺፕ ዕድል ምን ይጠቅማል? ኢትዮጵያ ውስጥ ይሄን ፈተና እንዴት መውሰድ ይቻላል እንዲሁም ፈተናው በውስጡ ምን ያካትታል የሚሉና ሌሎች መረጃዎችን በተመለከተ የነበረንን ቆይታ በቀጥታ መከታተል ያልቻላችሁ ቤተሰቦቻችን የድምፅ ቅጂውን ማዳመጥ ይችላሉ።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍14
- የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ለተለያዩ የሞያ መስኮች የተፈጠሩ የስራ ዕድሎች በመኖራቸው ፍላጎት ያላቸው ዜጎች እንዲመዘገቡና የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቀረበ። በከፊልና በሙሉ የሚሰለጥኑት እነዚህ የሰው ሀይሎች ወደ የተለያዩ ሃገራት እንደሚላኩም ሚኒስትሩ ተናግሯል።
በዚህ ድህረገፅ መመዝገብ ይችላሉ : https://www.lmis.gov.et


- የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የብየዳ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ማዕከል የብየዳ ስልጠና እንዲሁም ስልጠናውን ላጠናቀቁ ዓለማቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ሰርተፍኬት እንደሚሰጥ አሳወቀ።

ዝርዝር መስፈርቶችን በማዕከሉ ድህረገፅ በመመልከት ከሚያዚያ 20/2015 ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት በሚከተለው ድህረገፅ እንድትመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።
የድህረገፅ አድራሻ : http://apply.ftveti.edu.et


#EdNews
www.edmap.et
👍9
ከላይ ካለው ሰንጠረዥ ውስጥ የተደበቁ ቃላትን ማግኘት ይችላሉ፧ 🤔 ራሳችሁን ፈትኑ እና ሁሉንም ለማግኘት ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድባችሁ ተመልከቱ፦

🕵️‍♀️ ውጤቶችዎን ከእኛ (@contact_edmap) ጋር ማጋራትዎን አይርሱ። ፦ 🙌 #የቃላት ፍለጋ #የእንቆቅልሽ ጨዋታ #እራስዎን ይፈትኑ
👍11
Supply Chain Management (SCM) : ይህ የትምህርት መስክ ድርጅቶች የሚያመርቱትን ዕቃዎች እንዲሁም የሚያቀርቡትን አገልግሎቶች ስለ መቆጣጠር፣ መምራትና ማስተዳደር የሚያተኩር ነው። ይሄም ሁሉንም ተግባራት፣ ግብዓቶች፣ እቅድ እና አስተዳደርን ያጠቃልላል።

በዚህ መስክ የተመረቁ ሰዎች:
- ትላልቅ ድርጅቶች ውስጥ
- የሎጅስቲክ አማካሪ ተቋማት
- የግዥ እና አቅርቦት አስተዳደር ቢሮ እና ወዘተ መቀጠር እና መስራት ይችላሉ።

ስለ ትምህርቱ ውጤት አያያዝ እና በዚህ ዘርፍ ተመርቀው ምን እንደሚሰሩ የኤድማፕ ድህረ-ገፅ ላይ ተቀምጧል።

በዚህ ያግኙት : www.edmap.et/logistics-and-supply-chain-management/


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍8
የፎቶ ሞዴል : ከቅርብ አመታት ወዲህ ተወዳጅነት ያተረፈ እና ጥሩ ገንዘብ የሚያስገኝ ስራ ሆኖ ተስተውሏል።

ጥራት ያለው ፎቶ ከመነሳት ውጪ የሰውነት አቋምና የውበት መስፈርት የማያስፈልገውን ይህ ስራ ከትምህርታችሁ ጎንለጎን በትርፍ ጊዜ አልያም በሙሉ ሰዓት መስራት የምትችሉትና ገንዘብ እንድታገኙ የሚረዳችሁም ነው።

ኤድማፕ፣ ይሄንን ስራ እንዴት መጀመር እንደምትችሉ በቀጣይ ያሳውቃችኋል።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍13
በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ከቤታቸው/ከዶርማቸው ሆነው ስራ መስራትና ገንዘብ ማግኘት ይችላሉ።

EdMap Temari Work ለዚህ መልስ አለው!

በቅርብ ቀን!

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍19
ሙሉ በሙሉ ወጪዎች የተሸፈኑለት የሻንጋይ ገቨርንመንት ስኮላርሺፕ

የትምህርት ደረጃ
- በዲግሪ ፕሮግራም
- በማስተርስ ፕሮግራም
- በ PhD ፕሮግራም

ሙሉ ወጪዎች ይሸፈናል!

ለማመልከት እና ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይሄን ይጠቀሙ ፡ https://www.edmap.et/ecnu-shanghai-government-scholarship-2023-fully-funded-study-in-china/

የማመልከቻው ማጠናቀቂያ ቀን ፡ May 15, 2023

ኤድማፕ ፣ ከዚህ በፊት ብቁና ፕሮፌሽናል የሆነ የስኮላርሺፕ የማመልከቻ ደብዳቤ እንዴት መፃፍ እንደሚችሉ በምሳሌ አስደግፎ በአማርኛ ያቀረበውን ፅሁፍ በዚህ ያግኙት : https://t.me/EdMap_Community/244


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍8
ይህ ግለሰብ 'አማር ባራቲ' ይባላል። ከ40 አመታት በላይ ቀኝ እጁን ወደላይ በመዘርጋት ህይወቱን የገፋ ሰው ነው።

በህንድ 'ኡታር ፕራዴሽ' በተሰኘች አንዲት መንደር ውስጥ የተወለደው አማር ባራቲ እ.ኤ.አ እስከ 1973 ህይወቱን እንደማንኛውም ሰው ይገፋ ነበር።

በ1973 ቀኝ እጁን ወደ ላይ በመዘርጋት ለደቂቃ ሳያወርድ መንፈሳዊ ጉዞ ለማድረግ ወሰነ። ይህን ማድረጉም ዓለማቀፋዊ ሰላም በህዝቦች ዘንድ እንደሚያመጣ እንዲሁም ብርሃንና መንፈሳዊ ንፅህናን እንዲያገኝ እንደሚረዳው በማመን ነበር። ምንም እንኳ ቀኝ እጁ አካላዊ ምቾት ቢያጥረው ፣ ቢጎሳቆልና ህመም ቢኖረውም ከአራት አስርት ዓመታት በላይ በዚህ ተግባሩ ቀጥሏል።

በብዙዎች ዘንድ እንደ መንፈሳዊ መሪ እንዲሁም የመንፈሳዊ ብርሃን ፈላጊ ተደርጎ የሚወሰደው አሚር ባራቲ የፅናትና የትጋት ምልክት ተደርጎም ይቆጠራል።

አሚር ባራቲ እጁን ያለማቋረጥ ከ40 አመታት በላይ ወደ ላይ በመዘርጋቱም በአለም ዙሪያ ያሉ ብዙ ሰዎች የራሳቸውን መንፈሳዊ ጉዞ በመከተል ለግል እድገትና እውቀት እንዲጥሩ አነሳስቷቸዋልም ይባላል።


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍6