EdMap Community
3.3K subscribers
910 photos
8 videos
40 files
596 links
EdMap, Powered by PiSpace Inc.
A one-stop destination platform for Ethiopian students.

For further information @contact_edmap

Our website:
🌐 www.edmap.et
Download Telegram
የማህበራዊ ሚዲያ አስተዳደር (Social Media Management) ከስሙ መመልከት እንደሚቻለው የተለያዩ ማህበራዊ መድረኮችን መቆጣጠር እና ማስተዳደር ነው።

በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ሰዎች የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመጠቀም የማህበራዊ ድህረገፆችን ከተጠቃሚዎች ጋር ማገናኘት እና ማሳደግ ይጠበቅባቸዋል።

ይሄንን ስራ በትርፍ ጊዜም ሆነ በሙሉ ሰዓት በመስራት ገቢ ማግኘት ይችላሉ።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍7
በ1986 ታትሞ የቀረበው የደራሲ James Carse "Finite and Infinite Games" መፅሀፍ በኤድማፕ ቡክ ሪቪው ልንዳስሰው ወደድን።

እዚህች ዓለም ላይ ጦርነትም ፣ ስፖርትም ፣ ህይወትም ፣ የፍቅር ግንኙነትም ፣ ቢዝነስም ፣ ፖለቲካም፣ ስራም ሆነ ማንኛውም ነገር በሁለት ጨዋታዎች ላይ የተመሰረተ ነው ይላል መፅሀፉ ።

አንደኛው "Finite games" ወይም "ማብቂያ ያለው ጨዋታ" ሲሆን ሰዎች፣ ቡድኖች ወይም ሃገራት ይሄንን ጨዋታ የሚጫወቱት ለማሸነፍ ነው። በዚህ ጨዋታ፣ ውድድር፣ ፍልሚያ ወይም ጦርነት ውስጥ የተገደበ የመጋጠሚያ ሜዳ እና የተወሰነ ግዜ አለ። ለምሳሌ የእግር ጓስ ጨዋታ ውስጥ አንዱ ቡድን 11 ሆኖ ሌላውን "X" የሚባል ቡድንን ይገጥማል። ጨዋታው የሚታወቁ ህጎች አሉት፣ ሸናፊውም መጨረሻ ላይ ይታወቃል።

በዚህ ጨዋታ ውስጥ ለምሳሌ ጦርነት ከሆነ ሁለቱ ተጋጣሚዎች በውስጠ ታዋቂነት የሚያከብሯቸው ህጎች ይኖሯቸዋል። ጦርነቱ ከየት ተጀምሮ የት እንደሚያልቅ ይታወቃል፣ ሁለቱም ተጋጣሚዎች የታወቀ ድንበር/ወሰን አላቸው።

ሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ "Infinite games" ወይም "ማለቂያ የሌለው ጨዋታ" ይባላል! በዚህ ጨዋታ ውስጥ ሁለቱም ቡድኖች ጦርነቱ/ጨዋታው እንዲያበቃ ወይም እንዲገደብ አይፈልጉም። ልክ ጨዋታው ወደ መገባደድ ሲደርስ ከሁለት አንዱ ግዜ ገዝቶ ጨዋታውን/ጦርነቱን ያራዝመዋል!

ይሄኛው ጨዋታ አሸናፊ እና ተሸናፊ የለውም፣ መቼ እንደሚያልቅ አይታወቅም፣ አንደኛው ተፋላሚ እንዳበቃለት ወይም ዋጋ እንደሌለው እየተረዳ በመጣ ቁጥር ጦርነቱን/ጨዋታውን ወጥሮ መጫወት ይጀምራል! የሱ ህልውና በጨዋታው መቀጠል ላይ የተመሰረተ ነውና!

ፀሃፊው ከህይወት፣ ስራ፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ሌሎች ጉዳዮች ጋር እያዛመደ የሚገልፅበት መንገድ መልካም ነው።
መልካም ንባብ!
👍9
Finite and Infinite Games - EdMap Book Review.pdf
7.6 MB
በጄምስ የተዘጋጀውን መፅሀፍ እነሆ!
👍6
ላለፉት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የኤድማፕ ይሸልማል ውድድር ዛሬ ከምሽቱ 12፡00 ላይ ፍፃሜውን ያገኛል።
ነገ አሸናፊዎችን እናሳውቃለን።

ሽልማቶቹም
1ኛ ለወጣ 2.2 ጂቢ ወርሃዊ የኢንተርኔት ፓኬጅ
2ኛ ለወጣ 1.1 ጂቢ ወርሃዊ የኢንተርኔት ፓኬጅ
3ኛ ለወጣ 500 ሜቢ ወርሃዊ የኢንተርኔት ፓኬጅ

ቀሪዎቹ ደረጃ ላይ ያሉትን ተያይዞ በሚሰጣቸው ቁጥር በእጣ በመለየት 1 ተወዳዳሪ 400Mb ሳምንታዊ የኢንተርኔት ፓኬጅ ሽልማት እንደሚሰጥ ማሳወቃችን አይረሳም።

ኤድማፕ ይሸልማል!
www.edmap.et | @edmap_community
👍5
ኤድማፕ፣ ለሚከተሉት ስራዎች ብቁ ከሆኑ እንዲያመለክቱ ይጋብዛል።

1.Social Media Strategist

2. Skilled Tailor

3.Designer

4.Graphics Designer

5.Female Tutor


@edmap_community
👍9
"...ፋሽን ዲዛይነር ለመሆን የፈለገች ሴት አሁን ላይ ማሽኑ አያስፈልጋትም። በቀላሉ እንዲህ ማድረግ ትችላለች..."

"...የፋሽን ዲዛይን በደንብ አዋጭ ነው። እኔ ብዙ ደንበኞቼ የሚመጡት በኦንላይን ነው። ትርፋማ የሆንኩት ደግሞ..."


ኤድማፕ ፣ በፋሽን ዲዛይን ስመጥር ከሆነቺው ዲዛይነር ሃፍሳ ሰለሞን /ሀፊ ትንሿ ዲዛይነር/ ጋር ያደረገው አጭርና ግልፅ ቃለምልልስ ፋሽን ዲዛይን ሙያ ውስጥ አሁን መጀመር ላሰቡ እና ትርፋማ ለመሆን ለሚፈልጉ በሙሉ ይጋብዛል።

ቃለምልልሱን በዚህ ያግኙት : https://www.edmap.et/how-to-be-a-fashion-designer/


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍9
በኢትዮጵያዊው ዲዛይነር እና አርክቴክት ናሆም ተክሉ የተዘጋጀ ኤግዚብሽን
Building Africa Exhibition, Addis Ababa

- መግቢያ: በነፃ
- ቀን : ሚያዚያ 21 - 22
- ቦታ ፡ አዲስ አበባ ሙዚዬም ፣ መስቀል አደባባይ


ለበለጠ መረጃ ይሄን ይጠቀሙ ፡ www.africanstatearchitecture.co.uk/post/building-africa-exhibition


@edmap_community | www.edmap.et
👍5
የጥፍር ስራ ሙያ መማር የምትፈልጉ በሙሉ ፤ ኤድማፕ እነዚህን የዩቲዩብ ገፆች እንድትጎበኙ ይጋብዛል።

1) Simply Nailogical
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/@simplynailogical

2) Cute Polish
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/@cutepolish

3) Nail Career Education
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/@NailCareerEducation

4) Nailbees
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/@Nailbees


እነዚህን በመመልከት በጥፍር ስራ ሙያ ዘርፍ ያላችሁን እውቀት አንድ እርምጃ ከፍ ማድረግ ትችላላችሁ።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍9
የስኮላርሺፕ መረጃዎች ላይ SAT የሚል ቃል አስተውላችሁ ይሆናል። ለመሆኑ ትርጉሙ ምንድን ነው?

SAT ሲተነተን Scholastic Assessment Test የሚል ትርጓሜ ሲኖረው በዩናይትድ ስቴትስ ለኮሌጆች መግቢያ የሚሰጥ የፈተና ስርዓት ነው። ይህ የፈተና ስርዓት በዋነኝነት ትኩረቱን በሂሳብ ክህሎት እና በእንግሊዝኛ ቁንቋ የሚያደርግም ነው።

ታዲያ SAT ፈተና ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት መውሰድ ይቻላል? ምን አይነት ጥያቄዎች ፈተናው ላይ ይኖራሉ እንዲሁም ሌሎች ጠቃሚ ሀሳቦች አርብ/ነገ ማታ 2 ሰዓት ላይ በዚሁ የቴሌግራም ገፃችን የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ይኖረናል።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍9
እናስተዋውቅዎ!

ሄኖክ አሰፋ፣ በአዲስአበባ መቀመጫውን ያደረገው "Precise Consult" የተሰኘ የማኔጅመንት አማካሪ ድርጅት መስራችና ኢትዮጵያዊ ስራ ፈጣሪ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ቢዝነሶች ተወዳዳሪነታቸውን እንዲያሻሽሉና ቀጣይነት ያለው እድገት እንዲያስመዘግቡ በማሰብ Precise Consult የተሰኘውን ድርጅት እ.ኤ.አ በ2007 ለመመስረት ችሏል።

Precise Consult በኢትዮጵያ ብሎም በምስራቅ አፍሪካ ላሉ ንግዶችና ድርጅቶች "የስትራቴጂ ዲቨሎፕመንት"፣ የ"ፋይናንስ" ፣ የግብይትና የሰው ሀይል አስተዳደርን ጨምሮ የተለያዩ የቢዝነስ አማካሪ አገልግሎቶችን ይሰጣል።

ድርጅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የአስተዳደር አማካሪ ድርጅቶች ግንባር ቀደሙ ከመሆኑ ባሻገር ከደንበኞች ጋር በቅርበት በመስራትና ዕድሎችን ለይቶ ተግዳሮቶችን የሚያሸንፍ የአማካሪ ድርጅት ለመሆን በቅቷል።


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍8
Steamunlocked በተሰኘው ድህረገፅ ለመዝናኛነት ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸውን የተለያዩ የኮምፒውተር ጨዋታዎች (ጌሞች) በስፋት ማግኘት ትችላላችሁ።

የድህረገፁ አድራሻ : Streamunlocked.net


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍4
ኤድማፕ፣ ለሚከተሉት ስራዎች ብቁ ከሆኑ እንዲያመለክቱ ይጋብዛል።

1. Advertising photo models

2. Graphics designer

3. Male Tutors

4. Social media host

5. Intern - Office Assistant
👍5
Live stream scheduled for
Live stream started
🔴 LIVE

ስለ SAT ፣ የ SAT ፈተና መውሰድ ለስኮላርሺፕ የሚያስገኘው ጥቅም ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ የፈተና ስርዓት እንዴት እንደሚወሰድ እና ሌሎች ጥያቄዎችን በተመለከተ ኤድማፕ ከቤተሰቦቹ ጋር በቀጥታ ውይይት እያደረገ ነው።

ውይይቱን Join በማድረግ ይከታተሉ።

@edmap_community
👍11
Live stream finished (35 minutes)
ነፃ የትምህርት እድል ከጎግል

የሚከተሉትን የትምህርት አይነቶች በነፃ በፈለጋችሁት ጊዜ እየተማራችሁ ከዛም ሰርተፍኬት በማግኘት ከነበርዎ ደረጃ አንድ ከፍ እንዲሉ ኤድማፕ ይጋብዛል።

-Digital Marketing
-Building AI
-Entrepreneurship
-Programming with JavaScript
-Python basics for Data Analysis and many more.

ከላይ የተገለፁትና ጎግል ያቀረባቸውን ትምህርቶች የምታገኙበትን አድራሻ የኤድማፕ ድህረገፅ ላይ ተለጥፏል።

በዚህ ያግኙት ፡ https://www.edmap.et/googles-free-online-courses/


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍8
SAT
EdMap Community
ስኮላርሺፕ ላይ ብዙ ጊዜ የሚታየው SAT ምንድን ነው? SAT ፈተና መውሰድ ለስኮላርሺፕ ዕድል ምን ይጠቅማል? ኢትዮጵያ ውስጥ ይሄን ፈተና እንዴት መውሰድ ይቻላል እንዲሁም ፈተናው በውስጡ ምን ያካትታል የሚሉና ሌሎች መረጃዎችን በተመለከተ የነበረንን ቆይታ በቀጥታ መከታተል ያልቻላችሁ ቤተሰቦቻችን የድምፅ ቅጂውን ማዳመጥ ይችላሉ።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍14
- የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ለተለያዩ የሞያ መስኮች የተፈጠሩ የስራ ዕድሎች በመኖራቸው ፍላጎት ያላቸው ዜጎች እንዲመዘገቡና የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቀረበ። በከፊልና በሙሉ የሚሰለጥኑት እነዚህ የሰው ሀይሎች ወደ የተለያዩ ሃገራት እንደሚላኩም ሚኒስትሩ ተናግሯል።
በዚህ ድህረገፅ መመዝገብ ይችላሉ : https://www.lmis.gov.et


- የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የብየዳ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ማዕከል የብየዳ ስልጠና እንዲሁም ስልጠናውን ላጠናቀቁ ዓለማቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ሰርተፍኬት እንደሚሰጥ አሳወቀ።

ዝርዝር መስፈርቶችን በማዕከሉ ድህረገፅ በመመልከት ከሚያዚያ 20/2015 ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት በሚከተለው ድህረገፅ እንድትመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።
የድህረገፅ አድራሻ : http://apply.ftveti.edu.et


#EdNews
www.edmap.et
👍9
ከላይ ካለው ሰንጠረዥ ውስጥ የተደበቁ ቃላትን ማግኘት ይችላሉ፧ 🤔 ራሳችሁን ፈትኑ እና ሁሉንም ለማግኘት ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድባችሁ ተመልከቱ፦

🕵️‍♀️ ውጤቶችዎን ከእኛ (@contact_edmap) ጋር ማጋራትዎን አይርሱ። ፦ 🙌 #የቃላት ፍለጋ #የእንቆቅልሽ ጨዋታ #እራስዎን ይፈትኑ
👍11