EdMap Community
3.3K subscribers
910 photos
8 videos
40 files
596 links
EdMap, Powered by PiSpace Inc.
A one-stop destination platform for Ethiopian students.

For further information @contact_edmap

Our website:
🌐 www.edmap.et
Download Telegram
ኬክ ጋጋሪ መሆን የምትፈልጉ በሙሉ ፤ ኤድማፕ እነዚህን የዩቲዩብ ገፆች እንድትጎበኙ ይጋብዛል።

1) Preppy Kitchen
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/c/PreppyKitchen/videos

2) Bigger Bolder Baking
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/c/BiggerBolderBaking/videos

3) Joy of Baking
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/user/joyofbaking1/videos


እነዚህን በመመልከት የኬክ የመጋገር እውቀታችሁን አንድ እርምጃ ከፍ ማድረግ ትችላላችሁ።
#ከየት_ልጀምር
EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍1
በጉጉት ስትጠብቁት የነበረውን ከማህሌት ጌታቸው ጋር ያደረግነውን ቆይታ እነሆ:

"እንዴት ኦንላይን ቢዝነስ መጀመር እንደሚቻል?"

"ምን ቢሸጥ ትርፋማ እንደሚያደርግ?"

እንዲሁም "የሚሸጡት እቃዎች የት እንደሚገኙ?"

ተናግራለች። ከኤድማፕ ጋር ያደረገቺውን አጭር እና ግልፅ ቃለምልልስ የኤድማፕ ድህረገፅ ላይ ተለጥፏል።

በዚህ ያግኙት : https://www.edmap.et/how-to-start-online-business/



EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍8
በ2019 የታተመው Anxious People ድርሰቱ የ"ፍሬድሪክ ባክማን" የሆነ ማራኪ ልቦለድ ነው። መፅሀፉ ስለ ባንክ ለመዝረፍ ስለሚካሄደው ታሪክ እና በዘረፋው ስለተሳተፉት ሰዎች ህይወት ይዳስሳል።

ታሪኩ የተካሄደው በአንዲት ትንሽ የስዊድን ከተማ ውስጥ ነው። ባንክ ዘራፊዎች አንድን ባንክ በመዝረፍ ላይ እያሉ ፖሊሶች ባንኩን ከበው ዘራፊዎቹ እጃቸውን እንዲሰጡ ይጠይቃሉ። ዘራፊዎቹም ውስጥ ሰው እንዳለ እና ፖሊሶች ወደ ውስጥ ለመግባት ቢሞክሩ ሰዎቹን እንደሚገሉ ያስጠነቅቃሉ።

መፅሀፉ ወደ ኋላ ይመልሰንና የእያንዳንዱ ገፀባህሪ ጭንቀታቸውንና ድብርታቸውን ያስቃኘናል። ሁላቸውም እርስ በርስ እንዴት እንደሚገናኙም ያሳያል።

በልዩ የአፃፃፍ ዘይቤ የተፃፈው ይህ መፅሀፍ፣ ደራሲው የሰዎችን ስሜት ውስብስብነት ፍንትው አድርጎ ያስቀምጣል።

በአጠቃላይ "Anxious People" ጭንቀትና ድብረትን እየጠቆመ የሰዎችን ተሞክሮ የሚዳስስ እጅግ ልብ አንጠልጣይ ልቦለድ ነው። ከአቅም በላይ የሆነ የመገለል ስሜት እንዲፈጠር በሚያደርግ አለም ስር የሰዎች የእርስበርስ ግኑኝነት እና የመተሳሰብ አስፈላጊነትን ፍንትው አድርጎ ያሳያል።


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍41
የ "ቴሲስ(Thesis)" ወይም የመመረቂያ ፅሁፍ ርዕስ አመረርጥ ላይ ግርታ ለተፈጠረባችሁ በመሉ:

ኤድማፕ የሚከተሉትን ጠቃሚ ነጥቦች በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከምሳሌ ጋር አሰናድቷል። ከታች ተያይዟል።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
በአጭር ጊዜ ውስጥ ለዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና (ማትሪክ) እንዴት መዘጋጀት እንችላለን?

1: ለማጥናት ከሚቀልዎት ወደሚከብድዎት የትምህርት መስክ ይሂዱ!
2: ከዚህ ቀደም የተጠየቁትን ጥያቄዎች ይመልከቱ፣ አስፈላጊ የሚሉትን ርዕስ ይለዩ!
3: ርዕሶችን መሰብሰብ
4: ለፈተናው የቀረውን ጊዜ ያስሉ
5: የአጠናን እቅድ ያዘጋጁ
6: ጥናትዎን ይጀምሩ

ኤድማፕ በምሳሌ በታገዘ እና በተብራራ መልኩ እንዴት በአጭር ጊዜ ለዩንቨርስቲ የመግቢያ ፈተና (ማትሪክ) እንደሚዘጋጁ እና ብቁ እንደሚሆኑ የሚያሳይ መረጃ እነሆ ሊያጋራችሁ ይወዳል። ከታች የተያያዘውን ፋይል ይመልከቱት።
👍7
ኤድማፕ ፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ ለናንተ በሚያቀርበው መተግበሪያ (Application) ውስጥ:

-ለተማሪዎች የሚጠቅሙ መረጃዎች
-የስኮላርሺፕ እድሎች
-ለወጣቶች የሚጠቅሙ መንገዶች
-በትርፍ ጊዜ የሚሰሩ ስራዎች
-ተማሪዎች ስለሆኑ ብቻ በጣም በቅናሽ የሚገበያዩበትን ቦታ

እንዲሁም ሌሎች እዚህ ያልተዘረዘሩ መልካም ግልጋሎቶችን አካቶ ይዟል።

በቅርብ ቀን!

www.edmap.et | @edmap_community
👍10
ይሄንን ያውቃሉ?

WolframAlpha የተሰኘው ድህረገፅ የተለያዩ ውስብስብ ስሌቶችን እንዲሁም ለምትሰሩት የምርምር (Research) ውጤቶች እንደ ማጣቀሻ ሊያገለግሏችሁ የሚችሉ ፅሁፎችን በውስጡ አካቶ ይዟል።

የድህረገፁ አድራሻ : www.wolframalpha.com



EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍4
እ.ኤ.አ በ2014 ኢስፋሃን፣ ኢራን ውስጥ በሴቶች ላይ ተከታታይ የአሲድ ጥቃቶች እንዳጋጠማቸው እና ይህም ድርጊት የብዙ ሴቶችን ህይወትን ማበላሸቱ ይነገራል። ከጥቃቱ በስተጀርባ ያለው ምክንያት ግልፅ አለመሆኑ ደግሞ ሌላው አለምን ያስገረመ ዜና ነበር።

የዚህ ዘግናኝ ጥቃት ሰለባ ከሆኑት ውስጥ "ማርዚዬ ኢብራሂም" አንዷ ነች። አሁን ላይ ማርዚዬ የደረሰባት አስከፊ ጉዳት ሳይበግራት በኢራን ውስጥ የአሲድ ጥቃትን የሚከላከል ህግ በማውጣትና ሰለባ ለሆኑትንም እርዳታ በማድረጓ እውቅናን አፍርታለች።

ኤድማፕ፣ በ"ከታሪክ" አምዱ ይሄንን መረጃ ለእናንተ ለማጋራት ወደደ።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍3
በዳንቴል ሙያ ራሳችሁን አሻሽላችሁ የተለያዩ ምርቶችን መስራት የምትፈልጉ በሙሉ ፤ ኤድማፕ እነዚህን የዩቲዩብ ገፆች እንድትጎበኙ ይጋብዛል።

1) The Crochet Crowd
የዩቲዩብ አድራሻ: www.youtube.com/user/mikeyssmail

2) KnittingHelpCom
የዩቲዩብ አድራሻ: www.youtube.com/user/knittinghelpcom

3) VeryPink Knits
የዩቲዩብ አድራሻ: www.youtube.com/user/verypinkknits


እነዚህን በመመልከት በዳንቴል ሙያ ዘርፍ ያላችሁን እውቀት አንድ እርምጃ ከፍ ማድረግ ትችላላችሁ።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍10
ይሄንን ያውቃሉ?

የኤድማፕ ድህረገፅ ላይ በሀገራችን ዩንቨርስቲዎች የሚሰጡ የትምህርት ፕሮግራሞችን እንዲሁም በነዚህም የትምህርት መስኮች የተማረ ግለሰብ የት ተቋማት ላይ መቀጠር እንደሚችል ይገልፃል።

በዚህ ያግኙት ፡ www.edmap.et/programs/


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍10
ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የኤድማፕ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።


www.edmap.et
👍14
5 በነፃ "ፕሮፌሽናል" የሆነ ሲቪ እንዲሰሩ የሚያግዝዎት ድህረገፆች።

1. Canva
2. Zety
3. Resume
4. Novoresume
5. VisualCV


EdMap In English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍10
ውድ የኤድማፕ ቤተሰቦች፣ ረቡዕ ማታ 2:00 ላይ IELTS ምን እንደሆነ እና IELTSን በኢትዮጵያ ስለ መውሰድ ሂደት እናወራለን።

ጥያቄዎችዎን @contact_edmap ላይ ያሳውቁን። በክፍለ-ጊዜው ላይም እናነሳቸዋለን።

#Live #IELTS #EdMap
👍5
"... ኦንላይን ቢዝነስ ላይ የትኛው ያዋጣል ለሚለው እንደከስተመሮቻችሁ ይወሰናል። ከስተመሮቼ ምን ይፈልጋሉ የሚለውን ለማወቅ ደግሞ ሁሉንም አይነት እቃ በማስተዋወቅ መሞከር ይቻላል..."

"...
ሁለት አይነት አማራጮች አሉ። የመጀመሪያውና እኔ የምመክረው እሷ ገንዘብ እንዳታወጣ ማለትም ያለመነሻ ገንዘብ እንድትሰራ ነው። ይሄ እንዴት ይሆናል ከተባለ Resell የሚባለውን ቴክኒክ በመጠቀም ነው..."


ኤድማፕ
፣ የኦንላይን ቢዝነስ ላይ ውጤታማ ከሆነቺው "ኮንተንት ክሬተር / ዲጂታል ማርኬተር" ማህሌት ጌታቸው ጋር ያደረገው አጭርና ግልፅ ቃለምልልስ በኦንላይን ቢዝነስ ላይ ለመጀመር እና ትርፋማ ለመሆን ለሚፈልጉ በሙሉ ይጋብዛል።

ቃለምልልሱን በዚህ ያግኙት ፡ https://www.edmap.et/how-to-start-online-business/



EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍5
#EdNews

Anyone Can Start Up

-ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ወጣት ኢንተርፕርነር እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መካከል አንዷ ከሆነቺው ቤተልሄም ደሴ ጋር ነፃ የውይይት መድረክ ለተማሪዎች እና ለወጣቶች ተዘጋጅቷል።

ሚያዚያ 11፣2015 ምሽት 12፡00 ላይ አዲስ አበባ፣ ቦሌ መድሀኒያለም፣ ሊንጎ ታወር፣ 12ኛ ፎቅ ለሚካሄደው ይህ መድረክ መሳተፍ የምትፈልጉ በሙሉ በሚከተለው አድራሻ https://forms.gle/LphWeGc11V3w2Dso7 መመዝገብ እና መሳተፍ እንደሚቻል አዘጋጆቹ ገልጸዋል።


Soul, Mind & Body Workshop

-በሥነ ምግባራዊ እና መንፈሳዊ ትምህርቶች ላይ የሚያተኩር ነፃ አውደጥናት በአዲስአበባ ፣ ታንቶስ ታወር፣ ሁለተኛ ፎቅ ላይ እንደተዘጋጀ ተሰምቷል።

ሚያዚያ 13፣2015 ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ የሚሰናደው ይህ መድረክ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ("ሊንክ") Limitlessyouthtc@gmail.com በመመዝገብ ማንኛውም ሰው መታደም እንደሚችል ተገልጿል።

EdMap In English : @EdMap_Eth
www.edmap.et | @EdMap_Community
👍6
የህግ ትምህርት (Law) : ይህ የትምህርት መስክ ስለ አጠቃላይ የህግ ስርዓት እና በህብረተሰብ ውስጥ ስላለው አተገባበር የሚያተኩር ነው። እንደ ሕገ መንግሥታዊ ሕግ፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ፣ የውል እና የንብረት ሕግ እና መሰል ትምህርቶች በዚህ መስክ ይሸፍናሉ። የሕግ ትምህርት ጠበቃ፣ ዳኛ ወይም ሌሎች የሕግ ባለሙያዎች መሆን ለሚፈልግ ግለሰብ የሚሆን አስፈላጊ ነው።

በህግ ትምህርት የተመረቁ ሰዎች
- የህግ መስሪያ ቤቶች ውስጥ
- የመንግስት ኤጀንሲዎች
- NGO እና አካዳሚዎች ወዘተ የመቀጠር እና የመስራት እድል አላቸው።

ስለ ትምህርቱ ውጤት አያያዝ እና በዚህ ዘርፍ ተመርቀው ምን እንደሚሰሩ በዝርዝር የ ኤድማፕ ድህረ-ገፅ ላይ ተቀምጧል።

በዚህ ያግኙትhttps://www.edmap.et/law/


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍6