EdMap Community
3.3K subscribers
910 photos
8 videos
40 files
596 links
EdMap, Powered by PiSpace Inc.
A one-stop destination platform for Ethiopian students.

For further information @contact_edmap

Our website:
🌐 www.edmap.et
Download Telegram
በጃፓን ውስጥ ምርምር ለማድረግ ለምትፈልጉ በሙሉ የቀረበ ልዩ እድል

Matsumae International Foundation Fellowship

ሙሉ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት የፌሎውሺፕ ፕሮግራም

የወርሃዊ ክፍያ፣ የመጠለያ እና የጉዞ ወጪዎች በሙሉ በአዘጋጆች ይሸፈናል!

በተፈጥሮ ሳይንስ ( Natural Science ) ፣ ምህንድስና ( Enginnering ) እና ህክምና ( Medicine ) የትምህርት መስኮች ላይ!

የፌሎውሺፕ ፕሮግራሙ : ከ3 እስከ 6 ወራት ይቆያል።

የማመልከቻው ጊዚያት : ከApril 1 እስከ June 30፣ 2023።

ፕሮግራሙም በApril 2024 ይጀምራል።

የማመልከቻ አድራሻ እና ሙሉ መስፈርቶች እዚህ ያግኙ : https://www.edmap.et/matsumae-international-foundation-fellowship-2024-in-japan-full-funded-mif-fellowship/


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍4
እ.ኤ.አ በ 1889 አንዳቸው የሌላውን ህይወት ስለታደጉት "መሀመድ እና ሰሚር" ስለተባሉት ጓደኛማቾች እናስተዋውቅዎ!

መሀመድ ዓይነ ስውር ቢሆንም በእምነቱ ደግሞ ጠንካራ ሙስሊም ነበር ፣ ሰሚር ደግሞ ሰውነቱ "ፓራላይዝ" የሆነ ሲሆን የክርስትና ሀይማኖትን ይከተላል።

በፎቶው ላይ እንደሚታዩት ህይወታቸውን ሲገፉ የነበሩት ሰሚር የመሐመድ አይን ፤ መሐመድ ደግሞ የሰሚር እግር በመሆን ነበር።

በህይወት ውስጥ እርስ በርስ ለመረዳዳት ሲሉ ሁኔታዎቻቸውንና እክሎቻቸውን አሸንፈዋል

ታሪካቸው የተለያዩ ባህሎች እና ሃይማኖቶች አንድ ላይ ሆነው እርስበርስ ሲረዳዱ ተአምር እንደሚፈጠር የሚያሳይ ድንቅ ምሳሌ ነው።

#ከታሪክ

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍18
እናስተዋውቅዎ!

ዳዊት አብርሃም ፣ በቴክ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ራሱን ያጎለበትና ወጣት የ "ጌም" ፈጣሪ ሲሆን የ "ኩኩሉ ጌምስ" መስራችም ነው።

በቪዲዮ ጌም ኢንዱስትሪ ውስጥ የአፍሪካ ባህልና ታሪኮች እየተወከሉ እንዳልሆነ ያወቀው ዳዊት፣ የ"ጌም"  ፈጠራ ስራ ውስጥ ጉዞውን ጀመረ።

ከአመታት ትጋትና ራስን ማስተማር በኋላ እ.ኤ.አ በ2016 የ "ኩኩሉ ጌምስ" መሰረተ። በ"ኩኩሉ ጌምስ" ስር ስኬታማ የሚባሉ "ጌሞችን" አስተዋውቋል። ከነዚህም ውስጥ ገበጣ አንዱ ነው።

ዳዊት፣ በ 2021 በፎርብስ ከ30 ዓመት በታች የአፍሪካ ዝርዝር ውስጥ በመካተት በስራው እውቅና አግኝቷል። የእሱ የጉዞና ውጣወረድ ታሪክ በቴክኖሎጂ ሙያ ለመቀጠል ለሚመኙ ወጣቶች በሙሉ እንደ ጥሩ መነሳሻ በመሆን ያገለግላል።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍9
እናስታውስዎ!

1) በጀርመን የሚካሄደው የአንስታይን ፌሎውሺፕ ፕሮግራም

የማመልከቻ ቀናት : April 15 - May 31,2023

እዚህ ያመልክቱ: https://www.edmap.et/einstein-fellowship-2024-in-germany-fully-funded/

2) በአሜሪካ፣ Uk፣ ጃፓን ፣ አውስትራሊያ ፣ ስዊድን፣ ታይላንድ እና ኡጋንዳ ውስጥ የሚሰጠው የRotary Peace Fellowship ፕሮግራም

የማመልከቻ የመጨረሻ ቀን : May 15, 2023

እዚህ ያመልክቱ : https://www.edmap.et/rotary-peace-fellowship-program-2024-25-fully-funded/

3) በጃፓን ሀገር የተዘጋጀው የMatsumae  International Foundation Fellowship ፕሮግራም

የማመልከቻ ጊዜያት : April 1 - June 30, 2023

እዚህ ያመልክቱ : https://www.edmap.et/matsumae-international-foundation-fellowship-2024-in-japan-full-funded-mif-fellowship/


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍7
ስለ ኤድማፕ የሚሰማዎትን፣ እንዲሻሻልና እንዲቀጥል የሚፈልጉትን ያሳውቁን!

ለሀሳብዎ ትልቅ ቦታ እንሰጣለን!

በዚህ ያሳውቁን : @Contact_edmap


www.edmap.et
👍9
"3-6-9" የኒኮላስ ቴስላ ማኒፌስቴሽን

ኒኮላስ ቴስላ
እንዲህ ይላል : የምንፈልጋቸውና እንዲሆኑልን የምናስባቸውን ነገሮች ማድረግ እንችላለን። እንዴት? ለሚሉ የ 3-6-9 መርህን በመተግበር ይላል።

ኤድማፕ ፣ ይሄን ሀሳብ በምሳሌ እንደሚከተለው ለማብራራት ይሞክራል።

እናንተ በህይወታችሁ እንዲሳካልችሁ የምትፈልጉት ነገሮች ይኖራሉ። ለአብነት ያክል፤ "ንብረት ማፍራት፣ በትምህርት ጥሩ ደረጃ መድረስ፣ ውጪ ሀገር ሄዶ መማር፣ ሰዎችን መርዳት... ወዘተ" ። ታዲያ እናንተ እጅግ የምትፈልጉትና እንዲሳካላችሁ የምትመኙትን ነገር ምረጡ ይላል የ 3-6-9 ማኒፌስቴሽን አለቃ የሚባለው ኒኮላስ ቴስላ!

የመረጣችሁት ነገር እንበልና "በትምህርት ጥሩ ደረጃ መድረስ ከሆነ" ጠዋት ከእንቅልፋችሁ እንደተነሳችሁ "በትምህርት ጥሩ ደረጃ መድረስ አለብኝ" ብላችሁ ማስታወሻ ደብተራችሁ ላይ 3 ጊዜ ደጋግማችሁ ፃፉት ። በመቀጠልም ከ8 ሰዓት በኋላ ቀን ላይ ድጋሚ ይሄንኑ ምኞታችሁን 6 ጊዜ ማስታወሻ ደብተራችሁ ጋር ፃፉ። በመጨረሻም በድጋሚ ከ8 ሰዓት በኋላ ከላይ የተጠቀሰውን ምኞታችሁን 9 ጊዜ እየደጋገማችሁ በመፃፍ ማስታወሻችሁ ጋር አስቀምጡ። ይሄንንም ድርጊት ለአንድ ሳምንት ያክል ደጋግሙት።

"ምኞታችሁ ይሳካል" ይላል ኒኮላስ ቴስላ ፣ እንዴት ተብሎም ሲጠየቅ "የሰው ልጅ ትኩረት የሚይዘውን ነገር ሲያገኝ ሙሉ ሀይሉን እዛጋ ያደርጋል ይሄም እንዲሳኩ ይሆናል" ብሏል።

ብዙዎች ይሄ መንገድ ምኞታችንን እንዲሳካልን አድርጓል ይላሉ፣ እናንተስ!? አሳውቁን!

Tiktok | Facebook | Telegram | Website
👍27👎2
ይሄንን ያውቃሉ?

ይህ ድህረገፅ የማንኛውንም የ "PDF" ፋይል እንድታስተካክሉ / "Edit" እንድታደርጉ ያስችላችኋል።

የድህረገፁ አድራሻ : www.sejda.com/pdf-editor


Tiktok | Facebook | Telegram | Website
👍4
Marketing Management :  ስልታዊ የሆኑ
- የግብይት ፕሮግራሞችን
- ሂደቶችን
- እንቅስቃሴዎችን
ከሰፊ የንግድ ዓላማዎች ጋር በማቀናጀት እንዲሁም የደንበኛ ግንዛቤዎችን በመጠቀም ስኬትን እንድናገኝ የሚያስችለን ዘርፍ ነው።

ስለ ትምህርቱ ውጤት አያያዝ እንዲሁም በዚህ መስክ የተማረ ሰው የት መቀጠር እንደሚችል እና የመሳሰሉትን በዝርዝር የ ኤድማፕ ድህረ-ገፅ ላይ ተቀምጧል።

በዚህ ያግኙት : https://www.edmap.et/marketing-management/

Facebook  |  Telegram  |  Tiktok  |  Website
👍9
ማህሌት ጌታቸው (Mahita Vlogs) ትባላለች።
የተሳካላት "ኮንተንት ክሬተር" እንዲሁም "ዲጂታል ማርኬተር" ነች።

Glossy Shopping ተባባሪ መስራች እንደመሆኗ በ"ኦንላይን ገበያ" ላይ ብዙ የካበተ ልምድ አላት።

ኤድማፕ ጋር ባደረገቺው ቃለ ምልልስም "ሴቶች ኦንላይን ገበያ እንዴት መጀመር እንደሚችሉ ? ትርፋማ ለመሆን ምን አይነት መንገዶች መጠቀም እንደሚገባ?" እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ነጥቦችን አንስታለች።

ሙሉውን መረጃ ነገ ከቀኑ 9:00 ያገኛሉ!
ይጠብቁን!

Telegram | Tiktok | Facebook | Website
👍16👎1
የተሻለ የResearch ልምድ እንድታገኙ ሙሉ በሙሉ ወጪዎች የተሸፈኑለት የጃፓን OIST Internship ፕሮግራም

በትምህርት ላይ ያሉ
ወይም በቅርቡ የተመረቁ ተማሪዎች ማመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የሚሸፈኑ ወጪዎች ፡ - ወርሃዊ አበልን ጨምሮ የትራንስፖርት /የጉዞ/ ወጪዎች እንዲሁም የመኖሪያ ቤትና ለኑሮ የሚያስፈልጉ ወጪዎች ይሸፈናሉ።

የማመልከቻ ማጠናቀቂያ ቀን ፡
April 15th, 2023

ለማመልከት እና ለበለጠ መረጃ : https://www.edmap.et/oist-internship-in-japan-2023/


Tiktok | Facebook | Telegram | Website
👍5
ይሄንን ያውቃሉ?

learn-anything-xyz
የተሰኘው ድህረገጽ መማር የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር በመፅሀፍ መልክ አልያም በቪዲዮ መልክ ትምህርቶችን ያቀርብላችኋል። ይሄም ለተማሪዎች መልካም ብስራት ነው።

የድህረ-ገፁ አድራሻ
: learn-anything.xyz



www.edmap.et | @edmap_community
ኬክ ጋጋሪ መሆን የምትፈልጉ በሙሉ ፤ ኤድማፕ እነዚህን የዩቲዩብ ገፆች እንድትጎበኙ ይጋብዛል።

1) Preppy Kitchen
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/c/PreppyKitchen/videos

2) Bigger Bolder Baking
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/c/BiggerBolderBaking/videos

3) Joy of Baking
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/user/joyofbaking1/videos


እነዚህን በመመልከት የኬክ የመጋገር እውቀታችሁን አንድ እርምጃ ከፍ ማድረግ ትችላላችሁ።
#ከየት_ልጀምር
EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍1
በጉጉት ስትጠብቁት የነበረውን ከማህሌት ጌታቸው ጋር ያደረግነውን ቆይታ እነሆ:

"እንዴት ኦንላይን ቢዝነስ መጀመር እንደሚቻል?"

"ምን ቢሸጥ ትርፋማ እንደሚያደርግ?"

እንዲሁም "የሚሸጡት እቃዎች የት እንደሚገኙ?"

ተናግራለች። ከኤድማፕ ጋር ያደረገቺውን አጭር እና ግልፅ ቃለምልልስ የኤድማፕ ድህረገፅ ላይ ተለጥፏል።

በዚህ ያግኙት : https://www.edmap.et/how-to-start-online-business/



EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍8
በ2019 የታተመው Anxious People ድርሰቱ የ"ፍሬድሪክ ባክማን" የሆነ ማራኪ ልቦለድ ነው። መፅሀፉ ስለ ባንክ ለመዝረፍ ስለሚካሄደው ታሪክ እና በዘረፋው ስለተሳተፉት ሰዎች ህይወት ይዳስሳል።

ታሪኩ የተካሄደው በአንዲት ትንሽ የስዊድን ከተማ ውስጥ ነው። ባንክ ዘራፊዎች አንድን ባንክ በመዝረፍ ላይ እያሉ ፖሊሶች ባንኩን ከበው ዘራፊዎቹ እጃቸውን እንዲሰጡ ይጠይቃሉ። ዘራፊዎቹም ውስጥ ሰው እንዳለ እና ፖሊሶች ወደ ውስጥ ለመግባት ቢሞክሩ ሰዎቹን እንደሚገሉ ያስጠነቅቃሉ።

መፅሀፉ ወደ ኋላ ይመልሰንና የእያንዳንዱ ገፀባህሪ ጭንቀታቸውንና ድብርታቸውን ያስቃኘናል። ሁላቸውም እርስ በርስ እንዴት እንደሚገናኙም ያሳያል።

በልዩ የአፃፃፍ ዘይቤ የተፃፈው ይህ መፅሀፍ፣ ደራሲው የሰዎችን ስሜት ውስብስብነት ፍንትው አድርጎ ያስቀምጣል።

በአጠቃላይ "Anxious People" ጭንቀትና ድብረትን እየጠቆመ የሰዎችን ተሞክሮ የሚዳስስ እጅግ ልብ አንጠልጣይ ልቦለድ ነው። ከአቅም በላይ የሆነ የመገለል ስሜት እንዲፈጠር በሚያደርግ አለም ስር የሰዎች የእርስበርስ ግኑኝነት እና የመተሳሰብ አስፈላጊነትን ፍንትው አድርጎ ያሳያል።


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍41
የ "ቴሲስ(Thesis)" ወይም የመመረቂያ ፅሁፍ ርዕስ አመረርጥ ላይ ግርታ ለተፈጠረባችሁ በመሉ:

ኤድማፕ የሚከተሉትን ጠቃሚ ነጥቦች በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከምሳሌ ጋር አሰናድቷል። ከታች ተያይዟል።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
በአጭር ጊዜ ውስጥ ለዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና (ማትሪክ) እንዴት መዘጋጀት እንችላለን?

1: ለማጥናት ከሚቀልዎት ወደሚከብድዎት የትምህርት መስክ ይሂዱ!
2: ከዚህ ቀደም የተጠየቁትን ጥያቄዎች ይመልከቱ፣ አስፈላጊ የሚሉትን ርዕስ ይለዩ!
3: ርዕሶችን መሰብሰብ
4: ለፈተናው የቀረውን ጊዜ ያስሉ
5: የአጠናን እቅድ ያዘጋጁ
6: ጥናትዎን ይጀምሩ

ኤድማፕ በምሳሌ በታገዘ እና በተብራራ መልኩ እንዴት በአጭር ጊዜ ለዩንቨርስቲ የመግቢያ ፈተና (ማትሪክ) እንደሚዘጋጁ እና ብቁ እንደሚሆኑ የሚያሳይ መረጃ እነሆ ሊያጋራችሁ ይወዳል። ከታች የተያያዘውን ፋይል ይመልከቱት።
👍7
ኤድማፕ ፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ ለናንተ በሚያቀርበው መተግበሪያ (Application) ውስጥ:

-ለተማሪዎች የሚጠቅሙ መረጃዎች
-የስኮላርሺፕ እድሎች
-ለወጣቶች የሚጠቅሙ መንገዶች
-በትርፍ ጊዜ የሚሰሩ ስራዎች
-ተማሪዎች ስለሆኑ ብቻ በጣም በቅናሽ የሚገበያዩበትን ቦታ

እንዲሁም ሌሎች እዚህ ያልተዘረዘሩ መልካም ግልጋሎቶችን አካቶ ይዟል።

በቅርብ ቀን!

www.edmap.et | @edmap_community
👍10