EdMap Community
3.3K subscribers
910 photos
8 videos
40 files
596 links
EdMap, Powered by PiSpace Inc.
A one-stop destination platform for Ethiopian students.

For further information @contact_edmap

Our website:
🌐 www.edmap.et
Download Telegram
የፎቶግራፍ እውቀታችሁን ማዳበር የምትፈልጉ በሙሉ፤ ኤድማፕ እነዚህን የዩቲዩብ ገፆች እንድትጎበኙ ይጋብዛል።

1) Peter Mckinnon
የዩቲዩብ አድራሻ : https://www.youtube.com/user/petermckinnon24

2) PHLEARN
የዩቲዩብ አድራሻ : https://www.youtube.com/user/PhlearnLLC

3) Tony & Chelsea Northrup
የዩቲዩብ አድራሻ : https://www.youtube.com/user/VistaClues

#ከየት_ልጀምር
EdMap In English :
@edmap_eth

www.edmap.et | @edmap_community
👍10
ውድ የኤድማፕ ቤተሰቦችስኮላርሺፕ ዕድሎች ስታመለክቱ ከኤድማፕ እርዳታ ማግኘት የሚፈልጉ ብዙዎች እንዳሉ አስተውለናል። ይሄን ታሳቢ በማድረግ አንድ የመወያያ መድረክ (Group) ለመፍጠር ወስነናል። በመወያያ መድረክ ውስጥ ግር ያላችሁን ጥያቄ እርስበርስ መጠያየቅ እና መረዳዳት እንድትችሉ እንዲሁም በማመልከቻ ሂደት ውስጥ የሚካሄዱ መንገዶችን እንድትመለከቱ ይረዳል። የምታነሱት ጥያቄ በቀጥታ ስርጭት (Live Stream) እና በጋራ እየተወያየን እንዲመለስ ይደረጋል።

ይቀላቀሉ: https://t.me/EdMapSupportGroup

- - -

Hello EdMap family ,We've noticed that many of you need help with Scholarship applications, so we're creating a group for everyone to join and ask questions. We'll have live sessions and group discussions to provide answers and support.

Join the Group : https://t.me/EdMapSupportGroup
👍13
#EdNews

- መሰረቱን ካሊፎርኒያ ላይ ያደረገው "BirdView" የተሰኘ የሶፍትዌር አልሚ ድርጅት AI ተኮር ትምህርትን ወደ ኢትዮጵያ እያመጣ ነው።

- ሳፋሪኮም 1 ሚሊዮን ደንበኞችን ለመሸለም እንደተዘጋጀ አሳወቀ።

- ላለፉት 7 አመታት የትራንስፖርት ግልጋሎት ሲያቀርብ የነበረውና መሰረቱን ኬንያ ያደረገው "ሊትል ሊሚትድ" ወደ ኢትዮጵያ አድማሱን በቅርቡ ሊያሰፋ እንደሆነ ገለፀ።

- የዕለት ተዕለት ጭንቀቶችን ለመቋቋም ስለሚረዱ ዘዴዎችና ክህሎቶች ለመወያየት ካዛንቺስ፤ ነጋ ሲቲ ሞል፣ ሁለተኛ ፎቅ ላይ መጋቢት 30 መድረክ ተዘጋጅቷል። መግቢያ ከቁርስ ጋር ነፃ እንደሆነም ተነግሯል።
በዚህ አድራሻ ቦታ ማስያዝ ይችላሉ : https://forms.gle/TjuNEbJCqg2PteA39


www.edmap.et
👍1
ይሄንን ያውቃሉ?

ይህ ድህረገፅ በምትሰሩት የ Thesis ርዕስ የተሰሩ ሌሎች የ Thesis ስራዎችን ያቀርብላችኋል። እንደማጣቀሻ በመጠቀም የተሻለ Thesis እንድትሰሩ ይረዳችኋል።

የድህረገፁ አድራሻ : paperbrain.study


EdMap In English : @edmap_eth

www.edmap.et | @edmap_community
👍11
በአሜሪካ ፣ UK ፣ ጃፓን ፣ አውስትራሊያ ፣ ስዊድን ፣ ታይላንድ እና ኡጋንዳ ውስጥ ይማሩ!

ሙሉ የገንዘብ ድጋፍ
የሚደረግለት ይህ የ Rotary Peace Fellowship ፕሮግራም በሰላምና ግጭት አፈታት መስክ የማስተርስ ዲግሪ ወይም የሙያ ማሻሻያ ሰርተፍኬት መውሰድ ለሚፈልጉ ትልቅ እድል ነው።

የሚሸፈኑ ወጪዎች
- የተለያዩ ክፍያዎች
- የክፍልና የጉዞ እንዲሁም የስራ ልምምድ ወጪዎች

የማመልከቻ ማጠናቀቂያ ቀን : May 15, 2023

የማመልከቻ አድራሻ እና ሙሉ መስፈርቶች እዚህ ያግኙ : https://www.edmap.et/rotary-peace-fellowship-program-2024-25-fully-funded/


EdMap In English :
@edmap_eth

www.edmap.et | @edmap_community
👍5
#EdNews

- በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል በተከሰተው ጦርነት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ስምንት ሺህ ያክል ገደማ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንደሚመለሱ የአፋር ክልል ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

- አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የቁጠባ ሒሳብ ላላቸው ደንበኞቻቸው ‘አሌኝታ’ የተሰኘ የዲጂታል ብድር አገልግሎት አስጀመረ።

- ጀነሲስ ማርኬት በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የተጠለፉ አካውንቶች የሚቀርቡበት ገበያ በኤፍቢአይ ቁጥጥር ስር ዋለ።

www.edmap.et | @edmap_community
ኮንተንት ክሬተር መሆን የምትፈልጉ በሙሉ፤ ኤድማፕ እነዚህን የዩቲዩብ ገፆች እንድትጎበኙ ይጋብዛል።

1) Peter McKinnon
የዩቲዩብ አድራሻ : https://www.youtube.com/user/petermckinnon24

2) Casey Neistat
የዩቲዩብ አድራሻ : https://www.youtube.com/user/caseyneistat

3) iJustine
የዩቲዩብ አድራሻ : https://www.youtube.com/user/ijustine

4) Jenna Marbles
የዩቲዩብ አድራሻ : https://www.youtube.com/user/JennaMarbles


እነዚህ "ኮንተንት ክሬተሮች" በዩቲዩብ አዝናኝና ሳቢ ቪዲዮዎችን በመስራት ብዙ ተከታዮች አፍርተዋል።

ቴክኒካቸውን በማጥናት እናንተም ሰዎች የሚፈልጓቸውን ስራዎች በመስራትና በማጋራት ብዙ ተከታዮችን ከማፍራት በተጨማሪ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ትችላላችሁ።

#ከየት_ልጀምር
EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍10👎1
ይሄንን ያውቃሉ?

Michael Nicholson የተባሉት እኚህ አሜሪካዊ ግለሰብ 2 ዲፕሎማዎች3 ዲግሪዎች እንዲሁም 1 የዶክትሬት ዲግሪ ከመጎናፀፋቸው በተጨማሪ 22 የማስተርስ ዲግሪ ባለቤት በመሆን አለምን ያስደመሙ ሰው ናቸው።

እ.ኤ.አ December 11,2016 በ79 አመታቸው ከዚህ አለም የተለዩት ግለሰቡ ለ55 አመታት ያክል በትምህርት ላይ ጊዜያቸውን እንዳዋሉ ይነገራል።


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍12👎2
ከታላላቅ ኩባንያዎች የተግባር ልምድ ለማግኘት እንዲሁም በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስ፣ በግብይት እና መሰል ጠቃሚ ክህሎቶች ራስን ለማዳበር የሚረዳ ነፃ ስልጠናPiSpace Innovations ቀርቧል።

SkillMatch ድህረገፅ ያግኙት : https://skillmatchjobs.com/courses/renewable-energy-fundamentals/


ራስዎን ብቁ ያድርጉ!
www.edmap.et | @edmap_community
👍4
በጃፓን ውስጥ ምርምር ለማድረግ ለምትፈልጉ በሙሉ የቀረበ ልዩ እድል

Matsumae International Foundation Fellowship

ሙሉ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት የፌሎውሺፕ ፕሮግራም

የወርሃዊ ክፍያ፣ የመጠለያ እና የጉዞ ወጪዎች በሙሉ በአዘጋጆች ይሸፈናል!

በተፈጥሮ ሳይንስ ( Natural Science ) ፣ ምህንድስና ( Enginnering ) እና ህክምና ( Medicine ) የትምህርት መስኮች ላይ!

የፌሎውሺፕ ፕሮግራሙ : ከ3 እስከ 6 ወራት ይቆያል።

የማመልከቻው ጊዚያት : ከApril 1 እስከ June 30፣ 2023።

ፕሮግራሙም በApril 2024 ይጀምራል።

የማመልከቻ አድራሻ እና ሙሉ መስፈርቶች እዚህ ያግኙ : https://www.edmap.et/matsumae-international-foundation-fellowship-2024-in-japan-full-funded-mif-fellowship/


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍4
እ.ኤ.አ በ 1889 አንዳቸው የሌላውን ህይወት ስለታደጉት "መሀመድ እና ሰሚር" ስለተባሉት ጓደኛማቾች እናስተዋውቅዎ!

መሀመድ ዓይነ ስውር ቢሆንም በእምነቱ ደግሞ ጠንካራ ሙስሊም ነበር ፣ ሰሚር ደግሞ ሰውነቱ "ፓራላይዝ" የሆነ ሲሆን የክርስትና ሀይማኖትን ይከተላል።

በፎቶው ላይ እንደሚታዩት ህይወታቸውን ሲገፉ የነበሩት ሰሚር የመሐመድ አይን ፤ መሐመድ ደግሞ የሰሚር እግር በመሆን ነበር።

በህይወት ውስጥ እርስ በርስ ለመረዳዳት ሲሉ ሁኔታዎቻቸውንና እክሎቻቸውን አሸንፈዋል

ታሪካቸው የተለያዩ ባህሎች እና ሃይማኖቶች አንድ ላይ ሆነው እርስበርስ ሲረዳዱ ተአምር እንደሚፈጠር የሚያሳይ ድንቅ ምሳሌ ነው።

#ከታሪክ

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍18
እናስተዋውቅዎ!

ዳዊት አብርሃም ፣ በቴክ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ራሱን ያጎለበትና ወጣት የ "ጌም" ፈጣሪ ሲሆን የ "ኩኩሉ ጌምስ" መስራችም ነው።

በቪዲዮ ጌም ኢንዱስትሪ ውስጥ የአፍሪካ ባህልና ታሪኮች እየተወከሉ እንዳልሆነ ያወቀው ዳዊት፣ የ"ጌም"  ፈጠራ ስራ ውስጥ ጉዞውን ጀመረ።

ከአመታት ትጋትና ራስን ማስተማር በኋላ እ.ኤ.አ በ2016 የ "ኩኩሉ ጌምስ" መሰረተ። በ"ኩኩሉ ጌምስ" ስር ስኬታማ የሚባሉ "ጌሞችን" አስተዋውቋል። ከነዚህም ውስጥ ገበጣ አንዱ ነው።

ዳዊት፣ በ 2021 በፎርብስ ከ30 ዓመት በታች የአፍሪካ ዝርዝር ውስጥ በመካተት በስራው እውቅና አግኝቷል። የእሱ የጉዞና ውጣወረድ ታሪክ በቴክኖሎጂ ሙያ ለመቀጠል ለሚመኙ ወጣቶች በሙሉ እንደ ጥሩ መነሳሻ በመሆን ያገለግላል።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍9
እናስታውስዎ!

1) በጀርመን የሚካሄደው የአንስታይን ፌሎውሺፕ ፕሮግራም

የማመልከቻ ቀናት : April 15 - May 31,2023

እዚህ ያመልክቱ: https://www.edmap.et/einstein-fellowship-2024-in-germany-fully-funded/

2) በአሜሪካ፣ Uk፣ ጃፓን ፣ አውስትራሊያ ፣ ስዊድን፣ ታይላንድ እና ኡጋንዳ ውስጥ የሚሰጠው የRotary Peace Fellowship ፕሮግራም

የማመልከቻ የመጨረሻ ቀን : May 15, 2023

እዚህ ያመልክቱ : https://www.edmap.et/rotary-peace-fellowship-program-2024-25-fully-funded/

3) በጃፓን ሀገር የተዘጋጀው የMatsumae  International Foundation Fellowship ፕሮግራም

የማመልከቻ ጊዜያት : April 1 - June 30, 2023

እዚህ ያመልክቱ : https://www.edmap.et/matsumae-international-foundation-fellowship-2024-in-japan-full-funded-mif-fellowship/


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍7
ስለ ኤድማፕ የሚሰማዎትን፣ እንዲሻሻልና እንዲቀጥል የሚፈልጉትን ያሳውቁን!

ለሀሳብዎ ትልቅ ቦታ እንሰጣለን!

በዚህ ያሳውቁን : @Contact_edmap


www.edmap.et
👍9
"3-6-9" የኒኮላስ ቴስላ ማኒፌስቴሽን

ኒኮላስ ቴስላ
እንዲህ ይላል : የምንፈልጋቸውና እንዲሆኑልን የምናስባቸውን ነገሮች ማድረግ እንችላለን። እንዴት? ለሚሉ የ 3-6-9 መርህን በመተግበር ይላል።

ኤድማፕ ፣ ይሄን ሀሳብ በምሳሌ እንደሚከተለው ለማብራራት ይሞክራል።

እናንተ በህይወታችሁ እንዲሳካልችሁ የምትፈልጉት ነገሮች ይኖራሉ። ለአብነት ያክል፤ "ንብረት ማፍራት፣ በትምህርት ጥሩ ደረጃ መድረስ፣ ውጪ ሀገር ሄዶ መማር፣ ሰዎችን መርዳት... ወዘተ" ። ታዲያ እናንተ እጅግ የምትፈልጉትና እንዲሳካላችሁ የምትመኙትን ነገር ምረጡ ይላል የ 3-6-9 ማኒፌስቴሽን አለቃ የሚባለው ኒኮላስ ቴስላ!

የመረጣችሁት ነገር እንበልና "በትምህርት ጥሩ ደረጃ መድረስ ከሆነ" ጠዋት ከእንቅልፋችሁ እንደተነሳችሁ "በትምህርት ጥሩ ደረጃ መድረስ አለብኝ" ብላችሁ ማስታወሻ ደብተራችሁ ላይ 3 ጊዜ ደጋግማችሁ ፃፉት ። በመቀጠልም ከ8 ሰዓት በኋላ ቀን ላይ ድጋሚ ይሄንኑ ምኞታችሁን 6 ጊዜ ማስታወሻ ደብተራችሁ ጋር ፃፉ። በመጨረሻም በድጋሚ ከ8 ሰዓት በኋላ ከላይ የተጠቀሰውን ምኞታችሁን 9 ጊዜ እየደጋገማችሁ በመፃፍ ማስታወሻችሁ ጋር አስቀምጡ። ይሄንንም ድርጊት ለአንድ ሳምንት ያክል ደጋግሙት።

"ምኞታችሁ ይሳካል" ይላል ኒኮላስ ቴስላ ፣ እንዴት ተብሎም ሲጠየቅ "የሰው ልጅ ትኩረት የሚይዘውን ነገር ሲያገኝ ሙሉ ሀይሉን እዛጋ ያደርጋል ይሄም እንዲሳኩ ይሆናል" ብሏል።

ብዙዎች ይሄ መንገድ ምኞታችንን እንዲሳካልን አድርጓል ይላሉ፣ እናንተስ!? አሳውቁን!

Tiktok | Facebook | Telegram | Website
👍27👎2
ይሄንን ያውቃሉ?

ይህ ድህረገፅ የማንኛውንም የ "PDF" ፋይል እንድታስተካክሉ / "Edit" እንድታደርጉ ያስችላችኋል።

የድህረገፁ አድራሻ : www.sejda.com/pdf-editor


Tiktok | Facebook | Telegram | Website
👍4
Marketing Management :  ስልታዊ የሆኑ
- የግብይት ፕሮግራሞችን
- ሂደቶችን
- እንቅስቃሴዎችን
ከሰፊ የንግድ ዓላማዎች ጋር በማቀናጀት እንዲሁም የደንበኛ ግንዛቤዎችን በመጠቀም ስኬትን እንድናገኝ የሚያስችለን ዘርፍ ነው።

ስለ ትምህርቱ ውጤት አያያዝ እንዲሁም በዚህ መስክ የተማረ ሰው የት መቀጠር እንደሚችል እና የመሳሰሉትን በዝርዝር የ ኤድማፕ ድህረ-ገፅ ላይ ተቀምጧል።

በዚህ ያግኙት : https://www.edmap.et/marketing-management/

Facebook  |  Telegram  |  Tiktok  |  Website
👍9
ማህሌት ጌታቸው (Mahita Vlogs) ትባላለች።
የተሳካላት "ኮንተንት ክሬተር" እንዲሁም "ዲጂታል ማርኬተር" ነች።

Glossy Shopping ተባባሪ መስራች እንደመሆኗ በ"ኦንላይን ገበያ" ላይ ብዙ የካበተ ልምድ አላት።

ኤድማፕ ጋር ባደረገቺው ቃለ ምልልስም "ሴቶች ኦንላይን ገበያ እንዴት መጀመር እንደሚችሉ ? ትርፋማ ለመሆን ምን አይነት መንገዶች መጠቀም እንደሚገባ?" እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ነጥቦችን አንስታለች።

ሙሉውን መረጃ ነገ ከቀኑ 9:00 ያገኛሉ!
ይጠብቁን!

Telegram | Tiktok | Facebook | Website
👍16👎1
የተሻለ የResearch ልምድ እንድታገኙ ሙሉ በሙሉ ወጪዎች የተሸፈኑለት የጃፓን OIST Internship ፕሮግራም

በትምህርት ላይ ያሉ
ወይም በቅርቡ የተመረቁ ተማሪዎች ማመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የሚሸፈኑ ወጪዎች ፡ - ወርሃዊ አበልን ጨምሮ የትራንስፖርት /የጉዞ/ ወጪዎች እንዲሁም የመኖሪያ ቤትና ለኑሮ የሚያስፈልጉ ወጪዎች ይሸፈናሉ።

የማመልከቻ ማጠናቀቂያ ቀን ፡
April 15th, 2023

ለማመልከት እና ለበለጠ መረጃ : https://www.edmap.et/oist-internship-in-japan-2023/


Tiktok | Facebook | Telegram | Website
👍5
ይሄንን ያውቃሉ?

learn-anything-xyz
የተሰኘው ድህረገጽ መማር የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር በመፅሀፍ መልክ አልያም በቪዲዮ መልክ ትምህርቶችን ያቀርብላችኋል። ይሄም ለተማሪዎች መልካም ብስራት ነው።

የድህረ-ገፁ አድራሻ
: learn-anything.xyz



www.edmap.et | @edmap_community
ኬክ ጋጋሪ መሆን የምትፈልጉ በሙሉ ፤ ኤድማፕ እነዚህን የዩቲዩብ ገፆች እንድትጎበኙ ይጋብዛል።

1) Preppy Kitchen
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/c/PreppyKitchen/videos

2) Bigger Bolder Baking
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/c/BiggerBolderBaking/videos

3) Joy of Baking
የዩቲዩብ አድራሻ ፡ https://www.youtube.com/user/joyofbaking1/videos


እነዚህን በመመልከት የኬክ የመጋገር እውቀታችሁን አንድ እርምጃ ከፍ ማድረግ ትችላላችሁ።
#ከየት_ልጀምር
EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍1