EdMap Community
3.3K subscribers
910 photos
8 videos
40 files
596 links
EdMap, Powered by PiSpace Inc.
A one-stop destination platform for Ethiopian students.

For further information @contact_edmap

Our website:
🌐 www.edmap.et
Download Telegram
ስቶክ ማርኬት ምንድን ነው?

- ስቶክ ማርኬት ፣ ሰዎች በኩባንያዎች ውስጥ ባለቤትነት የሚገዙበት እና የሚሸጡበት ቦታ ነው። በስቶክ ገበያ ላይ ኢንቨስት በማድረግ ኩባንያዎች እያደጉና እየተስፋፉ ሲሄዱ በረዥም ጊዜ ከፍተኛ ትርፍ የማግኘት ዕድል እንዲኖር የሚረዳ ስርዓት ነው። ይህም ሀብትን ለመገንባት እና የፋይናንስ ግቦችን ለማሳካት ይረዳል።

ኢትዮጵያም ለመጀመሪያ ጊዜ ስቶክ ማርኬት ልትከፍት ነው። ፤ እዚህ ስርዓት ላይ ብቁ ተሳታፊ ለመሆን የስቶክ ማርኬት እውቀትዎን ማሳደግ የግድ ይሆናል።

ጠቀሜታውን ምክንያት በማድረግ ፤ ትምህርቱን ለመስጠት ለትንሽ ቀናት ያክል በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ሲጠይቁ እየታየ ነው። ነገር ግን PiSpace Innovations PLC ከ ስኪልማች ጋር በመተባበር ነፃ የስቶክ ማርኬት ስልጠና ከሰርተፍኬት ጋር ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች እና ተማሪዎች እንዳመቻቸ ተሰምቷል።

በዚህ ያግኙት ፡ http://skillmatchjobs.com/skill+



www.edmap.et | @edmap_community
👍21
የጌጣጌጥ ስራ : ተማሪዎች ከትምህርታቸው ጎንለጎን ገንዘብ ከሚያስገኛቸው ስራ ይመደባል። ስራዎቹን እንደ ሰርግ፣ ልደት እና የምርቃት ላሉ ዝግጅቶች ለሽያጭ ማቅረብም ትችላላችሁ።

ኤድማፕ ፣ እነዚህን ስራዎች ለመስራትና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት ለምታስቡ በሙሉ ከታች የተዘረዘሩትን ገፆች እንድትመለከቱ እና እውቀታችሁን እንድታዳብሩ ይጋብዛል።

1) Beadaholique
የዩቲዩብ አድራሻ : https://www.youtube.com/@beadaholique

2) Jewelry tutorial hq
የዩቲዩብ አድራሻ : https://www.youtube.com/@JewelryTutorialHQ

3) Jewelry making journal
የድህረገፅ አድራሻ : https://jewelrymakingjournal.com/


EdMap in English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍11👎1
ላለፉት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ውድድር እነሆ ለ10 ደቂቃዎች በቆየው በ ኤድማፕ ይሸልማል ገፅ በቀጥታ (Live Stream) አሸናፊዎችን በመለየት ተጠናቋል።

ኤድማፕ ፣ አሸናፊዎችን "እንኳን ደስ አላችሁ" እያለ በ @Contact_edmap ላይ እየገባችሁ ሙሉ ስማችሁንና ስልክ ቁጥራችሁን በመላክ እስከ መጋቢት 26 ሽልማታችሁን እንድትወስዱ ለማሳወቅ ይወዳል።

እንደየደረጃቸው 4.4 ፣ 2.2 ፣ 1.1 ጂቢ ወርሃዊ የኢንተርኔት ጥቅልና ለቀሩት ሁለት ተወዳዳሪዎች ደግሞ 500Mb ወርሃዊ የኢንተርኔት ጥቅል ቤተሰቦቹን ለመሸለም ይሄንን ውድድር እንዳዘጋጀ ይታወሳል!

ኤድማፕ ይሸልማል!
በቅርቡ ይመለሳል!

EdMap In English : @edmap_eth

www.edmap.et | @edmap_community
👍11
✨ የወረደ በራስ መተማመን ያለው ግለሰብ ምን ባህሪያት አሉት?

- እዚህ ምድር ላይ ምንም ነገር ማሳካት የሚችል አይመስለውም።
- ሁልጊዜ በእሱ ላይ ክፉ/መጥፎ ነገር የሚደርስ ይመስለዋል።
- ሁልጊዜ ስለራሱ መጥፎ ነገር ነው የሚናገረው / መጥፎ ነገር በተፈጠረ ቁጥር ራሱን ይወቅሳል።
- ሰዎች ከእሱ የተሻሉ እንደሆነ ያስባል።
- ሰዎችን ለማስደሰት ብቻ ይሞክራል / ማድረግ የማይፈልገውን ለሰዎች ሲል ያደርጋል።

✨ በራስ መተማመንን እንዴት ማዳበር ይቻላል?

ለራስ የምንሰጣቸውን መጥፎ ግምቶች መቀየር : "ይህን ማድረግ አልችልም" የሚለውን ሀሳብ "እኔ ከማንም አላንስም፣ ልምምድ ካደረግኩ እና ከተማርኩት ይህን ማድረግ እችላለሁ" ወደ የሚል ሀሳብ መምጣት።

ግብ ማውጣት : ግቦችን ማውጣትና እነሱን ማሳካት በራስ የመተማመን ስሜትን ለመፍጠር ይረዳል። ከትናንሽና ሊደረስባቸው ከሚችሉ ግቦች ጀምሩ።

ጠንካራ ጎን ላይ ማተኮር : ከድክመቶች ይል ጥንካሬን በመዘርዘር እነሱ ላይ ማተኮር ፤ ጥሩ በሆናችሁበት ላይ ራሳችሁን አድንቁ።

ራስን መንከባከብ : በአካል እና በአእምሮ ራስን መንከባከብ በራስ የመተማመን ስሜትን ለመጨመር ይረዳል። በቂ እንቅልፍ ማግኘት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ተመራጭ ናቸው።

አስታውሱ : በራስ መተማመንን ለመገንባት ጊዜና ጥረት ይጠይቃል! በአንድ ጀምበር አይገኝም!

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍15
በጀርመን የሚካሄደው የአንስታይን ፌሎውሺፕ ፕሮግራም, 2024

ይህ ፕሮግራም ሙሉ በሙሉ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገበት ነው። በዓለም ዙሪያ ለተወጣጡ ወጣቶች በሙሉ የቀረበ ነው።

የሚሸፈኑ ወጪዎች
-ወርሃዊ ክፍያ
-የመጠለያና የጉዞ ክፍያዎች

አመልካቾች ከ35 ዓመት በታች መሆን አለባቸው።

ፕሮግራሙም September, 2024 ይጀመራል።

የማመልከቻ ቀናት : April 15 - May 31, 2023

የማመልከቻ አድራሻ እና ሙሉ መስፈርቶችን እዚህ ያግኙ : https://www.edmap.et/einstein-fellowship-2024-in-germany-fully-funded/


EdMap In English : @edmap_eth

www.edmap.et | @edmap_community
👍9
ኤድማፕ ፣ በትምህርት ላይ ላሉ ተማሪዎችም ሆነ ለምሩቃን ወጣቶች ተጨማሪ የገንዘብ ምንጭ ያስገኛሉ ብሎ ያሰባቸውን እነዚህን ስራዎች ላይ እንድታመለክቱ ለመጋበዝ ይወዳል።

1) Facilitator - Part time
2) Animator - Contractual
3) IT intern - Contractual
4) Translator - Freelance
5) Content Writer and Voice Over - Remote
6) Content owner - Permanent (Full-Time)

መሰል የስራ ቅጥሮች ላይ ብቁ እንድትሆኑና ዕድሉን እንድታገኙ ኤድማፕ የተለያዩ መንገዶች እየጠቆመ እንደሚገኝ ይታወቃል።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍16
#EdNews

- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር (MinT) እና የጃፓን ዓለማቀፍ ኮርፖሬሽን ኤጀንሲ (JICA) ለቴክኖሎጂ "Startups" ሙሉ ወጪን በመቻል ወደ GITEX Africa 2023 ጉዞ ተዘጋጅቷል።

- የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የአቢሲኒያ አዋርድ የዓመቱ የላቀ ተሸላሚ ሆኗል።

- አዋሽ ባንክ ዲጂታል ብድር ለመስጠት በኡጋንዳ ከሚገኘው የ "ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ" ድርጅት ጋር እየሰራ ነው።

- የስልጠኛ ቋንቋን በቀላል መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል የሞባይል መተግበሪያ መዝገበ ቃላት ተመርቋል።


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍3
ኢኮኖሚክስ : "ማክሮ እና ማይክሮ" ኢኮኖሚክስን ከ "ስታቲስቲክስ" ጋር ያጣምራል።

የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች : የኢኮኖሚ መረጃዎችን ይመረምራሉ፣ ጥናት ያካሂዳሉ፣ እና የኢኮኖሚ ክስተቶችን እና የገበያ አዝማሚያዎችን ለመተንበይ ስታቲስቲካዊ ሞዴሎችን ይጠቀማሉ።

በኢኮኖሚክስ የትምህርት ዘርፍ የተመረቁ የትኛው የስራ መስክ ላይ ሊሳተፉ ይችላሉ?

- ባንኮች
- መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (NGO)
- አማካሪ ድርጅቶች
- የኢንሹራንስ እና የሂሳብ ድርጅቶች
እንዲሁም ሌሎች በርካታ መስኮች ላይ ይሳተፋሉ።

ስለ ኢኮኖሚክስ አጠቃላይ መረጃ እንዲሁም ዩንቨርስቲ ላይ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ነጥብ አያያዝ ምን እንደሚመስል በተብራራ መልኩ የ ኤድማፕ ድህረገፅ ላይ ተቀምጧል።

በዚህ ያግኙት : https://www.edmap.et/economics/


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍9
የውድድር ዳይሬክተሮች "ካትሪን ስዊዘር" የተባለች ሴት በቦስተን ማራቶን እንዳትሳተፍ ለማድረግ ሲሞክሩ ፤ ውድድሩን ያጠናቀቀች ብቸኛ ሴት ከመሆን ግን አላገዷትም። (1967 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር)

#ከታሪክ

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍11
የፀጉር ማስያዣ ጌጦች ሾል  ( "Scrunchies" ) : ከቅርብ አመታት ወዲህ ተወዳጅነት ያተረፈ እና ጥሩ ገንዘብ የሚያስገኝ ሆኖ ተስተውሏል።

እነዚህን የማስያዣ ጌጦች ስራ ላይ የራሳችሁን ልዩ ፈጠራ ("Design") በመጠቀምና ለአይን ማራኪ በማድረግ ከትምህርታችሁ ጎንለጎን በትርፍ ጊዜ የሚሰሩና ገንዘብ የሚያስገኙ ስራዎች ናቸው።

EdMap In English : @edmap_eth

www.edmap.et | @edmap_community
👍8
#EdNews

- ኢትዮጵያን የወከሉ ስድስት ተማሪዎች የ Huawei Global Ict ውድድር የመጨረሻው ዙር ደረሱ።

- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ Accounting & Finance እና በ Management የሦሥተኛ ዲግሪ (PhD) ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው።

- ማይግሬሽን ፊልም ፌስቲቫል ለአንድ ሳምንት ያህል የአፍሪካ ዘጋቢ ፊልሞችና ሲኒማ አከባበር በተመለከተ ከመጋቢት 27 - ሚያዚያ 1 የሚቆይ ዝግጅት አሰናድቷል። ቦታው አዲስ አበባ - GOETHE-INSTITUT ፣ መግቢያውም በነፃ እንደሆነ ኤድማፕ ማረጋገጥ ችሏል።

EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍5
"Research Paper" እንዴት ይዘጋጃል?

ርዕስ መምረጥ
: የሚስብ እና ልታዘጋጁት ካሰባችሁት ጋር ተዛማጅነት ያለው ርዕስ መምረጥ።

ምርምር ማካሄድ : በርዕሳችሁ ላይ እንደ መፅሀፍት፣ የ"አካዳሚክ" መፅሄቶች እና የ"ኦንላይን" መድረኮችን በመጠቀም መረጃ ማሰባሰብ።

ረቂቅ መፍጠር : ለፅሁፋችሁ ግልፅ እና የተደራጀ ንድፍ ማዘጋጀት : የፅሁፉ መግቢያ ፣ ዋና ሀሳብና መደምደሚያ ምን እንደሚመስል ማሰብ/መረዳት።

ረቂቅ መፃፍ : የተሰበሰቡትን መረጃዎች በመጠቀም የመጀመሪያውን ፅሁፍ መፃፍ መጀመር። (ሁሉንም መረጃዎችና ምንጮች ማካተታችሁን አረጋግጡ።)

አርትኢ እና ክለሳ : የፃፋችሁትን በመገምገም መረጃ መጨመር / መቀነስ ፣ የፅሁፍ ስልቱን ማሻሻል ወዘተ አስፈላጊ ለውጦችን ማድረግ።

ማረም : ምንም የፊደል ወይም የሰዋሰው ስህተቶች አለመኖራቸውን ማረጋገጥ እንዲሁም ወረቀታችሁ በደንብ የተደረጀ እና ለማንበብ ቀላል መሆኑን ማስተዋል።

ወረቀቱን ማስገባት : በመጨረሻም የ"Research Paper"ዎን ለሚፈለገው አካል ማቅረብ።


EdMap In English : @edmap_eth

www.edmap.et | @edmap_community
👍12
የፎቶግራፍ እውቀታችሁን ማዳበር የምትፈልጉ በሙሉ፤ ኤድማፕ እነዚህን የዩቲዩብ ገፆች እንድትጎበኙ ይጋብዛል።

1) Peter Mckinnon
የዩቲዩብ አድራሻ : https://www.youtube.com/user/petermckinnon24

2) PHLEARN
የዩቲዩብ አድራሻ : https://www.youtube.com/user/PhlearnLLC

3) Tony & Chelsea Northrup
የዩቲዩብ አድራሻ : https://www.youtube.com/user/VistaClues

#ከየት_ልጀምር
EdMap In English :
@edmap_eth

www.edmap.et | @edmap_community
👍10
ውድ የኤድማፕ ቤተሰቦች፣ ስኮላርሺፕ ዕድሎች ስታመለክቱ ከኤድማፕ እርዳታ ማግኘት የሚፈልጉ ብዙዎች እንዳሉ አስተውለናል። ይሄን ታሳቢ በማድረግ አንድ የመወያያ መድረክ (Group) ለመፍጠር ወስነናል። በመወያያ መድረክ ውስጥ ግር ያላችሁን ጥያቄ እርስበርስ መጠያየቅ እና መረዳዳት እንድትችሉ እንዲሁም በማመልከቻ ሂደት ውስጥ የሚካሄዱ መንገዶችን እንድትመለከቱ ይረዳል። የምታነሱት ጥያቄ በቀጥታ ስርጭት (Live Stream) እና በጋራ እየተወያየን እንዲመለስ ይደረጋል።

ይቀላቀሉ: https://t.me/EdMapSupportGroup

- - -

Hello EdMap family ,We've noticed that many of you need help with Scholarship applications, so we're creating a group for everyone to join and ask questions. We'll have live sessions and group discussions to provide answers and support.

Join the Group : https://t.me/EdMapSupportGroup
👍13
#EdNews

- መሰረቱን ካሊፎርኒያ ላይ ያደረገው "BirdView" የተሰኘ የሶፍትዌር አልሚ ድርጅት AI ተኮር ትምህርትን ወደ ኢትዮጵያ እያመጣ ነው።

- ሳፋሪኮም 1 ሚሊዮን ደንበኞችን ለመሸለም እንደተዘጋጀ አሳወቀ።

- ላለፉት 7 አመታት የትራንስፖርት ግልጋሎት ሲያቀርብ የነበረውና መሰረቱን ኬንያ ያደረገው "ሊትል ሊሚትድ" ወደ ኢትዮጵያ አድማሱን በቅርቡ ሊያሰፋ እንደሆነ ገለፀ።

- የዕለት ተዕለት ጭንቀቶችን ለመቋቋም ስለሚረዱ ዘዴዎችና ክህሎቶች ለመወያየት ካዛንቺስ፤ ነጋ ሲቲ ሞል፣ ሁለተኛ ፎቅ ላይ መጋቢት 30 መድረክ ተዘጋጅቷል። መግቢያ ከቁርስ ጋር ነፃ እንደሆነም ተነግሯል።
በዚህ አድራሻ ቦታ ማስያዝ ይችላሉ : https://forms.gle/TjuNEbJCqg2PteA39


www.edmap.et
👍1
ይሄንን ያውቃሉ?

ይህ ድህረገፅ በምትሰሩት የ Thesis ርዕስ የተሰሩ ሌሎች የ Thesis ስራዎችን ያቀርብላችኋል። እንደማጣቀሻ በመጠቀም የተሻለ Thesis እንድትሰሩ ይረዳችኋል።

የድህረገፁ አድራሻ : paperbrain.study


EdMap In English : @edmap_eth

www.edmap.et | @edmap_community
👍11
በአሜሪካ ፣ UK ፣ ጃፓን ፣ አውስትራሊያ ፣ ስዊድን ፣ ታይላንድ እና ኡጋንዳ ውስጥ ይማሩ!

ሙሉ የገንዘብ ድጋፍ
የሚደረግለት ይህ የ Rotary Peace Fellowship ፕሮግራም በሰላምና ግጭት አፈታት መስክ የማስተርስ ዲግሪ ወይም የሙያ ማሻሻያ ሰርተፍኬት መውሰድ ለሚፈልጉ ትልቅ እድል ነው።

የሚሸፈኑ ወጪዎች
- የተለያዩ ክፍያዎች
- የክፍልና የጉዞ እንዲሁም የስራ ልምምድ ወጪዎች

የማመልከቻ ማጠናቀቂያ ቀን : May 15, 2023

የማመልከቻ አድራሻ እና ሙሉ መስፈርቶች እዚህ ያግኙ : https://www.edmap.et/rotary-peace-fellowship-program-2024-25-fully-funded/


EdMap In English :
@edmap_eth

www.edmap.et | @edmap_community
👍5
#EdNews

- በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል በተከሰተው ጦርነት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ስምንት ሺህ ያክል ገደማ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንደሚመለሱ የአፋር ክልል ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

- አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የቁጠባ ሒሳብ ላላቸው ደንበኞቻቸው ‘አሌኝታ’ የተሰኘ የዲጂታል ብድር አገልግሎት አስጀመረ።

- ጀነሲስ ማርኬት በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የተጠለፉ አካውንቶች የሚቀርቡበት ገበያ በኤፍቢአይ ቁጥጥር ስር ዋለ።

www.edmap.et | @edmap_community
ኮንተንት ክሬተር መሆን የምትፈልጉ በሙሉ፤ ኤድማፕ እነዚህን የዩቲዩብ ገፆች እንድትጎበኙ ይጋብዛል።

1) Peter McKinnon
የዩቲዩብ አድራሻ : https://www.youtube.com/user/petermckinnon24

2) Casey Neistat
የዩቲዩብ አድራሻ : https://www.youtube.com/user/caseyneistat

3) iJustine
የዩቲዩብ አድራሻ : https://www.youtube.com/user/ijustine

4) Jenna Marbles
የዩቲዩብ አድራሻ : https://www.youtube.com/user/JennaMarbles


እነዚህ "ኮንተንት ክሬተሮች" በዩቲዩብ አዝናኝና ሳቢ ቪዲዮዎችን በመስራት ብዙ ተከታዮች አፍርተዋል።

ቴክኒካቸውን በማጥናት እናንተም ሰዎች የሚፈልጓቸውን ስራዎች በመስራትና በማጋራት ብዙ ተከታዮችን ከማፍራት በተጨማሪ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ትችላላችሁ።

#ከየት_ልጀምር
EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍10👎1
ይሄንን ያውቃሉ?

Michael Nicholson የተባሉት እኚህ አሜሪካዊ ግለሰብ 2 ዲፕሎማዎች ፣ 3 ዲግሪዎች እንዲሁም 1 የዶክትሬት ዲግሪ ከመጎናፀፋቸው በተጨማሪ 22 የማስተርስ ዲግሪ ባለቤት በመሆን አለምን ያስደመሙ ሰው ናቸው።

እ.ኤ.አ December 11,2016 በ79 አመታቸው ከዚህ አለም የተለዩት ግለሰቡ ለ55 አመታት ያክል በትምህርት ላይ ጊዜያቸውን እንዳዋሉ ይነገራል።


EdMap In English : @edmap_eth
www.edmap.et | @edmap_community
👍12👎2
ከታላላቅ ኩባንያዎች የተግባር ልምድ ለማግኘት እንዲሁም በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስ፣ በግብይት እና መሰል ጠቃሚ ክህሎቶች ራስን ለማዳበር የሚረዳ ነፃ ስልጠና በ PiSpace Innovations ቀርቧል።

በ SkillMatch ድህረገፅ ያግኙት : https://skillmatchjobs.com/courses/renewable-energy-fundamentals/


ራስዎን ብቁ ያድርጉ!
www.edmap.et | @edmap_community
👍4